Kominikeeshinii Magaalaa Baatee/ባቲ ከተማ ኮሚኒኬሽን

  • Home
  • Ethiopia
  • Bati
  • Kominikeeshinii Magaalaa Baatee/ባቲ ከተማ ኮሚኒኬሽን

Kominikeeshinii Magaalaa Baatee/ባቲ ከተማ ኮሚኒኬሽን We aspire to see a society where citizens have access to accurate and timely information !!!!

Qaammee 1 Guyyaa Oomishtummaa
06/09/2026

Qaammee 1 Guyyaa Oomishtummaa

06/09/2026

በባቲ ከተማ የጷጉሜ 1 ቀን "እመርታ ለዘላቂ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል በደመቀ ሁኔታ ተከበረ።

Qaammee 1 : Guyyaa Oomishtummaa Ol-ka'iinsa Biyyaatiif!‎Magaalaa Baatee Ganda Saalmaneetti Kilaastera Misooma Qonnaa Mid...
06/09/2026

Qaammee 1 : Guyyaa Oomishtummaa Ol-ka'iinsa Biyyaatiif!

Magaalaa Baatee Ganda Saalmaneetti Kilaastera Misooma Qonnaa Midhaanii fi Fuduraalee Suuraan:-📷

Gaarummaan Olka'insa Biyyaaf!Waajjirri Geejjibaa fi Lojistikii Magaalaa Baatee Barattootaaf Deeggarsa Taasise.Bulchiinsa...
06/09/2026

Gaarummaan Olka'insa Biyyaaf!

Waajjirri Geejjibaa fi Lojistikii Magaalaa Baatee Barattootaaf Deeggarsa Taasise.

Bulchiinsa Magaalaa Baateettii Wajjirri Geejjibaa fi Lojistikii Mata-duree "Gaarummaan Olka'insa Biyyaaf!" jedhuun Barattoota Harka Qalleyyii Ta'aniif Deeggarsa adda addaa taasisee jira.

በባቲ ከተማ የጳጉሜ 1 ቀን "እመርታ ለዘላቂ ከፍታ" በደመቀ ሁኔታ ተከበረ።በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር በባቲ ከተማ ሳልመኔ ቀበሌ የእርሻ ልማት በክላስተር እየለማ የሚገኝ ሰብል...
06/09/2026

በባቲ ከተማ የጳጉሜ 1 ቀን "እመርታ ለዘላቂ ከፍታ" በደመቀ ሁኔታ ተከበረ።

በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር በባቲ ከተማ ሳልመኔ ቀበሌ የእርሻ ልማት በክላስተር እየለማ የሚገኝ ሰብልና ፍራፍሬ ምስል በከፊል።

የባቲ ከተማ አስተዳደር ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የ2018 የበጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 ዕቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄደ!*****በፕሮግራሙ ላይ የባቲ ከ...
03/09/2026

የባቲ ከተማ አስተዳደር ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የ2018 የበጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 ዕቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄደ!
*****
በፕሮግራሙ ላይ የባቲ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሀመድ ሷሊህ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የባቲ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሀመድ ሷሊህ ጽሕፈት ቤቱ በ2018 የበጀት ዓመት ባሳየው የላቀ አፈጻጸም በዞን ደረጃ 1ኛ ሆኖ በመጠናቀቁ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው፣ ለጽሕፈት ቤቱ አመራሮችና ባለሙዎች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

አቶ መሀመድ አክለውም የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም አተገባበር እና የአገልግሎት አሰጣጥ ሁኔታ በማጠናከር ማህበረሰቡን ማገልገል ይጠበቅብናል ብለዋል።

የባቲ ከተማ ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አብዱልቃድር ሲራጅ በበኩላቸው ያገኘነው ውጤት የጋራ ጥረት እንደሆነ ገልፀው ተቋሙ በቀጣይ የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት የሚሰሩ ተግባራቶችን በየጊዜው መገምገምና ጥንካሬዎችን በማስቀጠል የሚታዩ ድክመቶችን በማረም ይበልጥ መስራት አለብን ብለዋል።

በመጨረሻም በበጀት አመቱ በሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም አተገባበር እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት ሁኔታ የተሻለ አፈጻጸም ላመጡ የተቋሙ አመራሮች እና ባለሙያዎች የዋንጫ ሽልማት እና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።

የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ በክልል ደረጃ የእውቅና ምስክር ወረቀት ተበረከተለት!​የአማራ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ...
03/09/2026

የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ በክልል ደረጃ የእውቅና ምስክር ወረቀት ተበረከተለት!

​የአማራ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩም በ2018 በጀት ዓመት በክልሉ ባሉ ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች የተከናወኑ የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ስራዎች በእጥረትና በውጤታማነት የተገመገሙ ሲሆን፣ ደረጃ ወጥቶላቸው የዋንጫና የደረጃ ሽልማት የተሰጣቸው ሲሆን፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ደግሞ በተለየ ሁኔታ በጣም ከፍተኛ አፈጻጸም በማስመዝገቡ የመልካም አፈጻጸም የምስክር ወረቀትና የላቀ ምስጋና ተበርክቶለታል።

​ይህ የተገኘው የላቀ እውቅና በየደረጃው ያሉ አመራሮች፣ ባለሙያዎችና የመላው ህዝባችን የጋራ ጥረት ውጤት ነው!

​በ2019 በጀት ዓመትም የህዝብና የመንግስትን የመረጃ ተደራሽነት የበለጠ ለማሳደግና የኮሙኒኬሽን ስራችንን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ያለንን ቁርጠኝነት አጠናክረን እንቀጥላለን።

የባቲ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ጽሕፈት ቤት የ2018 የበጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 ዕቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄደ!****በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት...
02/09/2026

የባቲ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ጽሕፈት ቤት የ2018 የበጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 ዕቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄደ!
****
በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባቲ ከተማ አስተዳደር አፈ ጉባኤ አቶ ሀቢብ መሐመድ፣ ጽሕፈት ቤቱ በ2018 የበጀት ዓመት ባሳየው የላቀ አፈጻጸም በዞን ደረጃ 1ኛ ሆኖ በመጠናቀቁ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው፣ ለጽሕፈት ቤቱ አመራሮችና ባለሙዎች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

አፈ ጉባኤው አክለውም ባለፈው የበጀት ዓመት የተመዘገቡ መልካም አፈጻጸሞችን አጠናክሮ ማስቀጠልና የታዩ ክፍተቶችን ደግሞ በ2019 የበጀት ዓመት በቁርጠኝነት ማረም እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

የባቲ ከተማ ሥራና ክህሎት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሁሴን ሷሊህ በበኩላቸው፤ ጽሕፈት ቤቱ በበጀት ዓመቱ የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በርካታ አበረታች ሥራዎችን ማከናወኑን ጠቅሰው፣ ለተመዘገበው ውጤት የባለሙያዎችና የባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ጥረት ከፍተኛ ድርሻ እንደነበረው ገልጸዋል።

አቶ ሁሴን አክለውም በ2019 የበጀት ዓመት አዳዲስ አሠራሮችን በመከተልና አገልግሎቶችን በማዘመን፣ የሥራ ዕድል ፈጠራውንና የክህሎት ሥልጠናውን ጥራት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በትኩረት እንደሚሠራ አረጋግጠዋል።

በመጨረሻም በዕቅድ ዝግጅት ባለሙያው አቶ ስጦታ ጉቹ የቀረበውን የ2018 ዓ.ም አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸም እና የ2019 ዓ.ም ዕቅድ ሰነድ መነሻ በማድረግ ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊና ፍሬያማ ውይይት ተካሂዷል።

Kominikeeshinii Magaalaa Baatee/ባቲ ከተማ ኮሚኒኬሽን

ሪሀመር የቢዝነስና ስራ አመራር ኮሌጅ ተማሪዎቹን በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ!በባቲ ከተማ አስተዳደር የሚገኘው ሪሀመር የቢዝነስና ስራ አመራር የግል ኮሌጅ በደረጃ 4 በትምህርት ዘርፎች ያስተማራቸ...
29/08/2026

ሪሀመር የቢዝነስና ስራ አመራር ኮሌጅ ተማሪዎቹን በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ!

በባቲ ከተማ አስተዳደር የሚገኘው ሪሀመር የቢዝነስና ስራ አመራር የግል ኮሌጅ በደረጃ 4 በትምህርት ዘርፎች ያስተማራቸውን ተማሪዎች በባቲ ማዘጋጃ ቤት አዳራሽ በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመረቀ።

ኮሌጁ በአካውንቲንግ፣ በማናጅመንት እና በዳታቤዝ የትምህርት ዘርፎች ያስተማራቸውን ከ42 በላይ ተማሪዎች ያስመረቀው የተመራቂ ወላጆችና የተለያዩ የክብር እንግዶች በተገኙበት ነው።

በምረቃው ስነ-ስርዓት ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የባቲ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ እና የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ መሀመድ ሷሊህ፤ «የዛሬው ቀን የድካማችሁ ፍሬ ያፈራበትና የእውቀት ጉዟችሁ አዲስ ምዕራፍ የያዘበት ታሪካዊ ቀን በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ!» ካሉ በኋላ፣ የዛሬ ተመራቂዎች የነገዋ ሀገራችን የብልፅግና መሰረት መሆናቸውን ገልጸዋል።

በስነ-ስርዓቱ ላይ የሪሀመር ቢዝነስና ስራ አመራር ኮሌጅ ዲን አቶ በላይ አሰፋ፣ የባቲ ወረዳ አፈጉባኤ አቶ አብዱ ሰይድ፣ የባቲ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አህመድ አብዱ፣ የባቲ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ መሀመድ ሷሊህን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የተመራቂ ወላጆች ተገኝተዋል።

በመጨረሻም በትምህርት ቆይታቸው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የዋንጫና የሜዳሊያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

Gaarummaan Olka'insa Biyyaaf!Bulchiinsa Magaalaa Baateetti Hojiin Tola Ooltummaa Gannaa Deeggarsa Barattootaaf Taasifamu...
28/08/2026

Gaarummaan Olka'insa Biyyaaf!

Bulchiinsa Magaalaa Baateetti Hojiin Tola Ooltummaa Gannaa Deeggarsa Barattootaaf Taasifamu Itti Fufe jira.

Address

Bati

Telephone

+251335530865

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kominikeeshinii Magaalaa Baatee/ባቲ ከተማ ኮሚኒኬሽን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share