25/02/2025
ትግራይ ባልሻረ ቁስሏ ላይ ዳግም እሳት ሊጭሩባት ያልዳነ ቁስሏን ሊያመረቅዙባት የጭካኔ ጦራቸዉን መዘዋል::የህውሃት ሰዎች ቡችሎች ናቸዉ ላበላቸዉ የሚያጎበድዱ ፥ስጋ እየተከተሉ ገደል የሚገቡ ቡችሎች ናቸዉ ። በዚህ ሰዓት ጦርነት ለማወጅ ደፋ ቀና የሚሉ የገዛ ልጆቿ ዛሬም አልተኙላትም::ለጦርነት መዘጋጀት እና የገዛ ህዝባቸዉን ወደ ጦርነት ለመመለስ የህዉሃት ሰዎች የሚያደርጉት ሽርጉድ ፥
ከ 60 አመት በታች የሆነ ሁሉ ወደ ጦር ካምፕ ይግባ ብሎ አዋጅ ላስነገረዉ የሸዓቢያዉ መንግስት አዲስ የምስራች ቢሆን እንጂ ለትግራይ ህዝብ ምኑም አይደለም፡፡በጦርነት በርካታ እህትና ወንድሞችን ህፃናት እናት አባት ሳይል ወገኖቻቸውን አተዋል::የውጊያ አስቀያሚነትን እንደ ትግራይ ህዝብ ያየ የለም አሁንም በዚህ መሃል ፍዳዉን የሚበላዉ የፈረደበት ደሃዉ የትግራይ ህዝብ ነዉ፡፡