Worebabo Woreda Livestock Resource Development Office

Worebabo Woreda Livestock Resource Development Office የዚህ ገጽ ዋና አላማ በወረዳው ውስጥ የሚሰሩ የዘርፉን ስራዎች ለማስተዋወቅ እና ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን ለመለዋወጥ በመሆኑ እርስዎም ቤተሰብ ይሁኑ!!

በወረባቦ ወረዳ 04 ወዋ እየደለቡ ያሉ ፍየሎች (ሙክቶች)
19/08/2026

በወረባቦ ወረዳ 04 ወዋ እየደለቡ ያሉ ፍየሎች (ሙክቶች)

በወረባቦ ወረዳ የ«ወዋ» ጎጥ እናቶች በአመልድ ኢትዮጵያ ድጋፍ የኢኮኖሚ ባለቤት እየሆኑ ነው!​አመልድ ኢትዮጵያ (ORDA Ethiopia) የሕብረተሰቡን፣ በተለይም የሴቶችንና የእናቶችን የኑሮ...
18/08/2026

በወረባቦ ወረዳ የ«ወዋ» ጎጥ እናቶች በአመልድ ኢትዮጵያ ድጋፍ የኢኮኖሚ ባለቤት እየሆኑ ነው!

​አመልድ ኢትዮጵያ (ORDA Ethiopia) የሕብረተሰቡን፣ በተለይም የሴቶችንና የእናቶችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻልና በኢኮኖሚ ለማብቃት በሚያደርገው ጥረት በወረባቦ ወረዳ 04 ቀበሌ «ወዋ» ጎጥ ለሚገኙ እናቶች የፍየል እርባታ ድጋፍ በማድረግ ዘላቂ የገቢ ማስገኛ እድል ፈጥሮላቸዋል።

​በተደረገላቸው የፍየል ድጋፍ ተጠቃሚ የሆኑት እናቶች አሁን ላይ ውጤታማ መሆናቸውንና ቁጥራቸውንም ማራባት መቻላቸውን ገልጸዋል፡-

​የወ/ሮ አሚናት ከበዴ እንዳሉት በፕሮጀክቱ ከተሰጣት 3 ፍየሎች በመነሳት በጥሩ እንክብካቤ አሁን ላይ ቁጥራቸውን ወደ 7 ማድረስ ችላለች።

​የወ/ሮ ጀማነሽ ረታ በተመሳሳይ ከተሰጣት የ3 ፍየሎች ድጋፍ ተነስታ ቁጥራቸውን ወደ 6 አድርሳለች።

​ፕሮጀክቱ እናቶች በራሳቸው እግር እንዲቆሙና የቤተሰቦቻቸውን የኑሮ ደረጃ እንዲያሻሽሉ ትልቅ ዕድል የፈጠረላቸው ሲሆን፣ ተጠቃሚ እናቶቹ ለአመልድ ኢትዮጵያ ላደረገላቸው ያልተቋረጠ ድጋፍ የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

​ #አመልድኢትዮጵያ #የሴቶችማብቃት #የእናቶችስኬት #ወረባቦ #የፍየልእርባታ #ልማት

ወቅቱን የጠበቀ እንክብካቤ እና ጤናማ ህብረ-ንብ ለተሻለ የማር ምርታማነት እድገት! ‎‎የንብ ሀብት ልማት ምርታማነት የሚወሰነው ካለው የህብረ-ንብ ቁጥር ባለፈ የአየር ሁኔታ፣ የንብ መኖ ተክ...
17/08/2026

ወቅቱን የጠበቀ እንክብካቤ እና ጤናማ ህብረ-ንብ ለተሻለ የማር ምርታማነት እድገት!

‎የንብ ሀብት ልማት ምርታማነት የሚወሰነው ካለው የህብረ-ንብ ቁጥር ባለፈ የአየር ሁኔታ፣ የንብ መኖ ተክሎች የሚያብቡበት ጊዜ እና ወቅታዊ የንብ እንክብካቤ ስራዎችን በትክክል በመለየት መተግበር ላይ የተመሰረተ ነው።

‎ለዚህም ንብ አናቢዎች በአካባቢያቸው ያሉ የንብ መኖ ተክሎችን አይነትና የአበባ ጊዜያቸውን በማወቅ ሥራቸውን ከወቅቱ ጋር አጣጥመው መስራት ይገባቸዋል።

‎በተለይም ከነሐሴ አጋማሽ እስከ መስከረም አጋማሽ ባለው ጊዜ ለቀጣዩ የማር ምርት ወቅት ጠንካራ መሠረት የሚጣልበት በመሆኑ የንብ መኖ ተክሎችን መትከልና መንከባከብ፣ የንብ ማነቢያ ቦታንና ቀፎዎችን ማጽዳት፣ የተበላሹ ቀፎዎችን መጠገንና የቀፎ ማስቀመጫዎችን ማጠናከር ያስፈልጋል።

‎የንብ ጤናን መጠበቅ አንዱ ተግባር በመሆኑ በሽታና ተባይ በወቅቱ መከታተል እና በቅንጅታዊ አሰራር የፀረ-ተባይና የፀረ-አረም መድኃኒቶች አጠቃቀም ንቦችን በማይጎዳ መልኩ እንዲከናወን ማድረግ ተገቢ ነው፡፡

‎የህብረ-ንብ ጥንካሬን ለመጨመር በቂ ምግብ መስጠት፣ የንግሥት ንብ ማባዛትን ማበረታታትና ለቀጣዩ የማር ወቅት ዝግጁ ማድረግ ያስፈልጋል።

‎የተፈጥሮ ፖለን ምንጭ (የአበባ ብናኝ) በሚጎድልበት ጊዜ ይህን የሚተካ ተገቢ የሆነ ተጨማሪ ምግብ በመስጠት ህብረ-ንቦችን ለማባዛት፣ ለማዛወርና የማር ምርትን ለማጠናከር ያስችላል።

‎የግብዓት እና ቴክኖሎጂ አቅርቦትና ስርጭት ለምርታማነት ቁልፍ ጉዳይ በመሆኑ የተሻሻሉ የፍሬምና የሽግግር ቀፎዎችን ማዘጋጀት፣ ነባር ቀፎዎችን ማጽዳት፣ ያረጁ የሰም እንጀራዎችን በአዲስ መተካት እና የሰም እንጀራ ማዘጋጀት የወቅቱ ዋነኛ ስራዎች ናቸው።

‎ከባህላዊ ቀፎ ወደ ተሻሻለ ቀፎ የሚዛወሩ ጤናማ ህብረ-ንቦችን በመምረጥ በቂ የማዛወሪያ ቦታና ቁሳቁስ ከወዲሁ መዘጋጀት ይገባል።

‎በምርት ወቅት የማር ምርትን በጥራት ለመሰብሰብ እንዲቻል የማር ማውጫ፣ ማጣሪያ፣ ንጹህ ማጠራቀሚያና ማሸጊያ ቁሳቁሶችን አስቀድሞ ማሟላት ያስፈልጋል። ያልደረሰ ማር አለመሰብሰብ፣ የምርት ንጽህናን መጠበቅና ተገቢውን የማር አያያዝ ሂደት መከተል ለምርት ጥራትና ለገበያ ተወዳዳሪነት መሠረታዊ ስራዎች ናቸው።

‎በንብ ማነብ ሥራ ወቅት የአየር ሁኔታንና የአበባ ጊዜን መከታተል፣ ቀፎ ሲከፈት ተገቢውን የመከላከያ ልብስ፣ ጓንትና የዓይን መከላከያ መጠቀም እና ንቦችን ለማረጋጋት ጥቅም ላይ የሚውለው ጭስ ንቦችን የማይጎዳ መሆኑን ማረጋገጥ ወሳኝ ነው።

‎ይህንን ሁሉ ለማሳካት ንብ አናቢዎች ወቅታዊ አጫጭር የመስክ ስልጠናዎችን እና የልምድ ልውውጦችን ማድረግ እንዲሁም ስለ ገበያ ትስስርና የምርት ጥራት ደረጃዎች በቂ ግንዛቤ ማግኘት ይገባቸዋል።

‎የመረጃ አያያዝን በማጠናከር የህብረ-ንብ ብዛት፣ የቀፎ ሽፋን፣ የበሽታና የተባይ ሁኔታ እንዲሁም የግብዓት አጠቃቀም በየደረጃው በትክክል እየመዘገቡ ለቀጣይ ስራ እንደ ግብዓት መጠቀም ያስፈልጋል፡፡

በወረባቦ ወረዳ 01 ሀራ የአየር ንብረት ለውጥ ተስማሚ የሆነ የማያ ፕሮግራም የንብ ማነብ የአቻ ለአቻ ስልጠና ተሰጠ
17/08/2026

በወረባቦ ወረዳ 01 ሀራ የአየር ንብረት ለውጥ ተስማሚ የሆነ የማያ ፕሮግራም የንብ ማነብ የአቻ ለአቻ ስልጠና ተሰጠ

09/08/2026
በወረባቦ ወረዳ የእንስሳት መኖ ችግኝ እና የሳር ቁርጥራጭ ተከላ ስራ እንደቀጠለ ነው
09/08/2026

በወረባቦ ወረዳ የእንስሳት መኖ ችግኝ እና የሳር ቁርጥራጭ ተከላ ስራ እንደቀጠለ ነው

በወረባቦ ወረዳ ቢስቲማ ከተማ እየረቡና እየደለቡ ያሉ ፍየሎች
09/08/2026

በወረባቦ ወረዳ ቢስቲማ ከተማ እየረቡና እየደለቡ ያሉ ፍየሎች

በወረባቦ ወረዳ 04 ቀበሌ «ወዋ» ጎጥ የሚገኙ እናቶች በአመልድ ኢትዮጵያ (ORDA Ethiopia) ፕሮጀክት አማካይነት በተደረገላቸው የፍየል እርባታ ድጋፍ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገለጹ። ​አመል...
07/08/2026

በወረባቦ ወረዳ 04 ቀበሌ «ወዋ» ጎጥ የሚገኙ እናቶች በአመልድ ኢትዮጵያ (ORDA Ethiopia) ፕሮጀክት አማካይነት በተደረገላቸው የፍየል እርባታ ድጋፍ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገለጹ።

​አመልድ ኢትዮጵያ የሕብረተሰቡን፣ በተለይም የሴቶችንና የእናቶችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻልና በኢኮኖሚ ለማብቃት በሚያደርገው ጥረት ለወዋ ጎጥ እናቶች ፍየሎችን ገዝቶ በማስረከብ የገቢ ማስገኛ እድል ፈጥሮላቸዋል።

​ተጠቃሚ እናቶቹ ለአመልድ ኢትዮጵያ ላደረገላቸው ድጋፍ የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

06/08/2026
በወረባቦ ወረዳ እንስሳትና አሳ ሀበት ልማት ጽ/ቤት አስተባባሪነት እየተተከለ ያለ እንስሳት መኖ ችግኝ ተከላ በምስል (ሀምሌ27/2018)
03/08/2026

በወረባቦ ወረዳ እንስሳትና አሳ ሀበት ልማት ጽ/ቤት አስተባባሪነት እየተተከለ ያለ እንስሳት መኖ ችግኝ ተከላ በምስል (ሀምሌ27/2018)

Address

Ready
Bistima
2021

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Worebabo Woreda Livestock Resource Development Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share