Media times

Media times Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Media times, Public & Government Service, Wolaiyta, Boditi.

24/12/2024
 #እንኳን ወደ 50 ነገስታት ምድር ወደ ውቢቷ ወላይታ ሶዶ ከተማ ከበደና መጡ  #ጊፋታን 2017  #የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ ጊፋታ በዓላ ደረሰ
01/09/2024

#እንኳን ወደ 50 ነገስታት ምድር ወደ ውቢቷ ወላይታ ሶዶ ከተማ ከበደና መጡ #ጊፋታን 2017
#የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ ጊፋታ በዓላ ደረሰ

25/08/2024
የወላይታ ዞን የብልፅግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ከዞን ጀምሮ እስከ መሠረታዊ ድርጅት ድረስ የሚገኙ የኮሚሽን አመራሮች በተገኙበት የ2016 በጀት ዓመት የዕቅድ...
15/08/2024

የወላይታ ዞን የብልፅግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ከዞን ጀምሮ እስከ መሠረታዊ ድርጅት ድረስ የሚገኙ የኮሚሽን አመራሮች በተገኙበት የ2016 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ እና የ2017 የዕቅድ ኦረንቴሽን መድረክ ተካሄደ።

ነሐሴ 09/2016 ዓ.ም የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት የ2016 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ እና የ2017 የዕቅድ ኦረንቴሽን መድረክ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተካሄደ።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የወላይታ ዞን ዋና አፈ-ጉባዔና የብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ ወይንሸት ሞላ የፓርቲው የፖለቲካ ጤንነት እንዲጠበቅ ኮሚሽኑ ዘርፈ-ብዙ ተግባራት እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸው በበጀት ዓመቱ በጥንካሬ የተመዘገቡ ውጤቶችን አጠናክሮ በማስቀጠል ጠንካራ ፓርቲ ለመገንባት በትኩረት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

የፓርቲውን የፖለቲካ ጥራት ማረጋገጥ የተከናወኑ ተግባራት በጥንካሬ የሚወሰድ እንደሆነ ያመላከቱት ክብርት ወ/ሮ ወይንሸት በቀጣይ በጀት ዓመት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ፣ የጠንካራ ፓርቲ ግንባት እውን ለማድረግ መረባረብ ያስፈልጋል ብለዋልም፡፡

የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወንድማገኝ አበራ በኮሚሽኑ ቁልፍና ዐበይት ተግባራት እየተመዘገቡ ያሉ ውጤቶች የኮሚሽኑን መጠናከር የሚያሳዩ በመሆኑ ኮሚሽኑ ለፓርቲው ጥንካሬ የበኩሉን አስተዋፅዖ ማበርከት ስላለበት በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ የተሰጡ የኮሚሽኑ ተግባርና ኃላፊነቶች፤ እንዲሁም በፓርቲው አሥር ዓመት ስትራቴጂካዊ ዕቅድ የተመላከቱ ጉዳዮች ውጤታማ በሆነ አግባብ መፈፀም እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡ በፓርቲ በኩል የተመዘገቡ ስኬቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የኮሚሽኑ ሚና እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ ለዘርፉ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራቱን ጠቁመው፣ የኮሚሽኑ የአሰራርና የአደረጃጀት መመሪያው ተግባራዊ እንዲሆን የሱፐርቪዥንና ኢንስፔክሽን ሥራ መጠናከር እንዳለበት አመላክተዋል።

በ2016 በጀት ዓመት በኮሚሽኑ ቁልፍና ዐበይት ተግባራት የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የኮሚሽኑ አደረጃጀቶች የእውቅና ሰርተፊኬት እንዲሁም ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለወጡ የዋንጫ ሽልማት ተበርክቷል፡፡

በዚህም መሠረት በበጀት ዓመቱ ሶዶ ከተማ፣ አረካ ከተማ እና ጠበላ ከተማ አስተዳደር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤቶች ከከተማ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤቶች መካከል የላቀ አፈፃፀም በማስመዝገብ የእውቅና ሰርተፊኬት የተሰጣቸው ሲሆን ሁምቦ፣ ቦ/ቦምቤ እና ኦፋ ደግሞ የላቀ አፈፃፀም በማስመዝገብ የእውቅና ሰርተፊኬት የተሰጣቸው የወረዳ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤቶች ናቸው፡፡

በአጠቃላይ አፈፃፀም ከ23ቱ ወረዳና ከተማ አስተዳደር የኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤቶች ውስጥ ሶዶ ከተማ፣ አረካ ከተማ እና ሁምቦ ወረዳ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ በመውጣት የዋንጫ ሽልማት ተሰጥቷቸዋል፡፡

ከዞን ማዕከል ፐብሊክ ሰርቫንት መሠረታዊ ድርጅት ኮሚሽኖች ውስጥ ማህበራዊ ቁጥር አንድ፣ አስተዳደራዊ ቁጥር ሁለት እና ኢኮኖሚያዊ ቁጥር ሁለት ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ በመውጣት የእውቅና ሰርተፊኬት የተበረከተላቸው ግንባርቀደም የኮሚሽን መሠረታዊ ድርጅቶች ናቸው፡፡

በመድረኩ የወላይታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ሰብሳሳቢ ክብርት ወ/ሮ ወይንሸት ሞላ፣ የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወንድማገኝ አበራ፣ የቅ/ጽ/ቤቱ ም/ኃላፊ አቶ መቱሳል ቦሻ፣ የዞኑ ኮሚሽንና የመዋቅሮች ኮሚሽኖች ተገኝተዋል

የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የ2016 በጀት ዓመት የ10 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛልግንቦት 21/2016 የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የ2...
29/05/2024

የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የ2016 በጀት ዓመት የ10 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል

ግንቦት 21/2016 የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የ2016 በጀት ዓመት የ10 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ እየመከረ ይገኛል።

የአፈጻጸም ግምገማ መድረኩ ባለፋት አስራ ወራት በፓርቲ መሪነት የተሰሩ ዋና ዋና ተግባራት አፈፃፀም እና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ትኩረት እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡

ባለፋት አስር ወራት የተከናወኑ የፓርቲና የመንግስት ተግባራትን በመገምገምና ጥንካሬዎችን በማጽናትና በማስፋት እንዲሁም ጉድለቶችን በመለየት ቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ ወይይት ተደርጎ አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በመድረኩ የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተመስገን አለማየሁ የፓርቲ ስራ አመራር እና የወረዳና ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊዎችና ዘርፉ አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

 #እንኳን ደስ አላችሁ ከበዙ ጨዋታ በኋላ ወደ አሸናፊነት ተመልሰናል 💪💪💪
20/04/2024

#እንኳን ደስ አላችሁ ከበዙ ጨዋታ በኋላ ወደ አሸናፊነት ተመልሰናል 💪💪💪

ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የተገራ የሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ስራ እጅግ አስፈላጊ መሆኑ ተገለጸ ወላይታ ሶዶ፤መጋቢት 7/2016 በወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የህዝብ ግ...
15/04/2024

ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የተገራ የሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ስራ እጅግ አስፈላጊ መሆኑ ተገለጸ

ወላይታ ሶዶ፤መጋቢት 7/2016 በወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነትና ማህበራዊ ሚዲያ ዘርፍ የ2016 ዓ.ም የዘጠኝ ወር አፈጻጸም ግምገማና ቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ተወያይቷል።

በመድረኩ የተገኙ የወላይታ ዞን የደሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደግፌ ኤርሚያስ ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ስራ እጅግ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

አመራሩና አባሉ የነቃ የማህበራዊ ሚዲያ ተሳትፎ በማድረግ የተቀነባበሩ እና ሀሰተኛ መረጃዎች የመመከት ስራ በመስራት ህብረተሰቡ ትክክለኛውን መረጃ እንዲያገኝ መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል።

የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነትና ማህበራዊ ሚዲያ ዘርፍ አቶ ጀምበሩ ኦርጩ ፓርቲያችን አንግቦ የተነሳውን ራዕይን ወደ ዳር ለማድረግ ሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ስራ በተደራጀና በተቀናጀ ሁኔታ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

ባለፉት በዘጠኝ ወራት በፓርቲ መሪነት የተከናወኑ የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለህብረተሰቡ ተደራሽ የማድረግ ስራ መሰራቱንም ገልጸዋል።

በመድረኩ የወረዳና ከተማ አስተዳደር የደሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊዎች፣ የህዝብ ግንኙነትና ማህበራዊ ሚዲያ ዘርፍ ኃላፊዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

"አንድ መጽሐፍ ለአንድ ተማሪ" ዘመቻ ሁሉም ወጣቶች የበኩላቸውን አሻራ እንዲያሳርፍ ጥሪ ቀረበሚያዝያ፦ 07/2016 ዓ.ም( ወ/ዞ/መ/ኮ/ጉ/መምሪያ )"አንድ መጽሐፍ ለአንድ ተማሪ" ዘመቻ ሁሉ...
15/04/2024

"አንድ መጽሐፍ ለአንድ ተማሪ" ዘመቻ ሁሉም ወጣቶች የበኩላቸውን አሻራ እንዲያሳርፍ ጥሪ ቀረበ

ሚያዝያ፦ 07/2016 ዓ.ም( ወ/ዞ/መ/ኮ/ጉ/መምሪያ )"አንድ መጽሐፍ ለአንድ ተማሪ" ዘመቻ ሁሉም ወጣቶች የበኩላቸውን አሻራ እንዲያሳርፍ ጥሪ ቀርቧል።

በወላይታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ወጣቶች ሊግ "አንድ መጽሐፍ ለአንድ ተማሪ" በሚል መሪ ቃል የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል።

ዘመቻው ለአንድ ወር የሚቆይ ሲሆን "አንድ መጽሐፍ ለልጄ፣ ለእህቴ፣ ለወንድሜ!" የሚል ሲሆን መጽሐፍ የማሰባሰብ እና የመለገስ ዘመቻ በመሆኑ ሁሉም ወጣቶች በንቃት መሳተፍ እንደሚገባ ተጠቁሟል።

በመድረኩም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት ኃላፉ ፣ የወላይታ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፍ የዞኑ ወጣቶች ሊግ ኃላፉዎች እና ከወረዳ/ከተማ የወጣቶች ሊግ አመራሮችም ተገኝቷል።

በበልግ እርሻ አርሶአደሩን ተጠቃሚ ለማድረግ አስፈላጊውን የድጋፍና ክትትል ስራ እየተደረገ ይገኛል፦ አቶ አሳምነው አይዛወላይታ ሶዶ፤ መጋቢት 4/2016 የወላይታ ዞን ከፍተኛ አመራሮች ዳሞት ...
13/03/2024

በበልግ እርሻ አርሶአደሩን ተጠቃሚ ለማድረግ አስፈላጊውን የድጋፍና ክትትል ስራ እየተደረገ ይገኛል፦ አቶ አሳምነው አይዛ

ወላይታ ሶዶ፤ መጋቢት 4/2016 የወላይታ ዞን ከፍተኛ አመራሮች ዳሞት ፑላሳ ወረዳ በመገኘት የበልግ እርሻ ልማት እንቅስቃሴን መስክ ምልከታ በማድረግና ድጋፍም አድርገዋል።

በመስክ ምልከታው የተገኙ የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሳምነው አይዛ በወረዳው እጅግ ተስፋ የሚሰጥ የበልግ እርሻ ልማት ስራዎችን መመልከቱን ገልጸዋል።

የበልግ እርሻ ሥራዎች የአርሶአደሩን ተጠቃሚነትን በዘላቂነት ከማረጋገጥ ባሻገር የኑሮ ውድነትን እና ገበያን ለማረጋጋት የላቀ አሰተዋጽኦ እንደሚያበረክት ጠቅሰዋል።

ህዝባችንን ወደ ብልጽግና ህይወት ለማሸጋገር በየአካባቢው ያሉ ፀጋዎችን መጠቀምና በግብርናው ዘርፍ ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥተው መስራት እንደሚገባም አመላክተዋል።

በወረዳው አርሶአደሩ በቡድን እና ወጣቶች መንግስት ባመቻቸው ስራ ዕድልን በመጠቀም በማህበር ተደራጅተው በግብርናው ዘርፍ እየሰሩ ያሉ ስራዎች ሌሎች አከባቢዎች ተሞክሮ የሚሆን ነው ብለዋል።

የወላይታ ዞን ም/አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ዳዊት በበልግ እርሻ በንቅናቄ መስራት አርሶአደሩን ተጠቃሚ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር መግባባት በመፍጠር ወደ ስራ መግባቱን ገልጸዋል።

አሁን በማሳው ላይ ያለው ቁመና እጅግ አበረታችና ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት አውንታዊ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም ጠቅሰዋል።

ከ129 ሺህ በላይ ሄክታር ማሳ ለመሸፈን የታቀደ ሲሆን አሁን 75 ሺህ ሄክታር ማሳ የተሸፈነው መሆኑን የገለጹት አቶ መስፍን በአጠቃላይ በበልግ እርሻ ከ19.8 ሚሊዮን በላይ ምርት ለማግኘት ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

የዳሞት ፑላሳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደመቀ ኩኬ በበኩላቸው በዘንድሮው በልግ እርሻ በወረዳው ከ9 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ በዘር ለመሸፈን ዕቅድ ተይዞ ወደ ሥራ የተገባ ሲሆን እስካሁን 7 ሺህ 384 ሄክታር በላይ ማሳ በተለያዩ ሰብል ዓይነቶች መሸፈኑን አብራርተዋል።

በወረዳው ድንች፣ጎዴረ፣ስኳር ድንች፣ በቆሎ፣ ጤፍ፣ ቦሎቄ፣ገብስና ማሽላ የመሳሰሉ የሰብል ዓይነቶች በበልግ እርሻ በስፋት የሚመረቱ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በወረዳው በወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራና በአርሶአደሮች እየለማ ከሚገኘው 25 ሄክታር ማሳ ድንች ከ8 ሺህ በላይ ኩንታል ምርት ይጠበቃልም ነው ያሉት።

በመስክ ምልከታው የፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተመስገን አለማየሁን ጨምሮ የወረዳው አስተባባሪ አካላት ተሳትፈዋል።

Address

Wolaiyta
Boditi

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Media times posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share