Southwest Ethiopia Police Commission

Southwest Ethiopia Police Commission “በጀግንነት መጠበቅ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል!!”
(2)

የቅጥር ማስታወቂያየኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በ2019 በጀት ዓመት የተቋሙን የሰው ኃይል ለማጠናከር በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚገኙ ብሔር ብሔረሰብና ሕዝቦች፣ የጾታ ተ...
30/08/2026

የቅጥር ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በ2019 በጀት ዓመት የተቋሙን የሰው ኃይል ለማጠናከር በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚገኙ ብሔር ብሔረሰብና ሕዝቦች፣ የጾታ ተዋፅዖን ከግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ ተመልምለው በተቋሙ ባሉት ልዩ ልዩ የሥራ ዘርፎች ተመድበው ማገልገል የሚፈልጉ ዕጩ ፖሊሶችን አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል።

ዕጩ ተመልማዮቹ ምልመላው ተጠናቆ ወደ ኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሥልጠና ማዕከል ገብተው ሥልጠና ከመጀመራቸው በፊት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 720/2004 እና ደንብ ቁጥር 268/2005 በሚያዘው መሠረት የ7 ዓመት የሥራ ውል ግዴታ በመግባት በማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ አማካይነት የሚሰጣቸውን ሥልጠና በሚገባ በመከታተል ማጠናቀቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡

በሥልጠና ቆይታ ጊዜያቶችም በማሠልጠኛ ትምህርት ቤቱ በኩል የምግብ፣ የመኝታ፣ የሕክምና እና ለሥልጠናው የሚያስፈልጉ የአልባሳት፣ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችና የኪስ ገንዘብ ይሰጣል።

ሥልጠናው ሲጠናቀቅም እያንዳንዱ ተመራቂ በተቋሙ የደመወዝ ስኬል መሰረት ወርሃዊ ደመወዝና የቀለብ ሂሳብ የሚከፈለው ሆኖ በተቋሙ ልዩ ልዩ የስራ አልባሳት፣ ነፃ የሕክምና አገልግሎት፣ በካምፕ የጋራ መኖሪያ ቤት እንዲሁም የትራንስፖርት አገልግሎት ያገኛሉ።

ተመርቀው ፖሊሳዊ የሙያ አገልግሎት በሚያበረክቱባቸው ጊዜያትም በተቋሙ ውስጥ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ማቋቋሚያ አዋጅ፣ ደንብ እና የስልጠና መመሪያዎች መሠረት በሚወጡ መመዘኛዎች አማካኝነት በልዩ ልዩ የትምህርትና ሥልጠና ፕሮግራሞች በመወዳደር ተጠቃሚ የመሆን ሠፊ ዕድል የሚጠብቃቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በደስታ ይገለፃል።

የምልመላ መስፈርት (መመዘኛ)

1. ዜግነት ኢትዮጵያዊ የሆነ/የሆነች፣

2. ለሕገ-መንግስንቱና ለሀገሪቱ ሕጎች ተገዥና ታማኝ የሆነ/የሆነች፣

3. ከማናቸውም ደባል ሱሶች የፀዳ/የፀዳች እና መልካም ስነ-ምግባር ያለው/ያላት፣

4. በሚመለመልበት አካባቢ ነዋሪ ስለመሆኑ የቀበሌ መታወቂያ ወይም የፋይዳ መታወቂያ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፣

5. ከሚኖርበት ቀበሌ አስተዳደር፣ ከአካባቢው ፖሊስ እና ከተማረበት ትምህርት ቤት የተዘጋጁ ቅፆችን በማስሞላት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፤

6. በብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እንዲሁም በሃይማኖት እኩልነት የሚያምን/የምታምን፣

7. ለፖሊስነት የሚያበቃ ሙሉ ጤናማ መሆኑን/መሆኗን በህክምና የተረጋገጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፣

8. ዕድሜው/ዋ ከ18 እስከ 25 ዓመት ያላነሰና ያልበለጠ/ያልበለጠች፣

9. የማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆነ/ያልሆነች፣

10. የትምህርት ደረጃ 10ኛ ክፍል እና በላይ የሆነ/የሆነች እንዲሁም ትምህርት ያጠናቀቀበት ካርድ ዋናውንና የማይመለስ አንድ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፣

11. ብዝሃነትንና አካታችነትን ለማረጋገጥ ሲባል ያልተካተቱና አነስተኛ ቁጥር ባለባቸው ብሔሮች አካባቢ ለሚመለመሉ ወጣቶች ቢያንስ 6ኛ ክፍል እና በላይ የሆነ/የሆነች፣

12. ቁመት ለወንድ 1.65 ሜትር በላይ የሆነ፣ ለሴት 1.60 ሜትር በላይ የሆነች፣

13. የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 720/2004 እና ደንብ ቁጥር 268/2005 በተደነገገው መሠረት የ7 ዓመት የሥራ ውል ግዴታ በመግባት ሥልጠናው ሲጠናቀቅ በየትኛውም የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ተቋም የሥራ አከባቢ ተመድቦ/ተመድባ ለመሥራት ፈቃደኛ የሆነ/የሆነች፣

14. ከአሁን በፊት በወንጀል ተከሶ ያልተቀጣ/ያልተቀጣች ወይም የወንጀል ሪከርድ የሌለበት/የሌለባት የአሻራ ምርመራ ለማድረግ ፍቃደኛ የሆነ/የሆነች፣

15. ከአሁን በፊት በማንኛውም የፖሊስ እና የመከላከያ ሰራዊት ተቋም ሥልጠና ያልተሳተፈ/ያልተሳተፈች ወይም በአባልነት ተቀጥሮ ያልሰራ/ያልሰራች፤

16. ያላገባ እና ያልወለደ ወይም ያላገባች እና ያልወለደች፣

ማሳሰቢያ፡- ማንኛውም ዕጩ ተመልማይ በምዝገባ ወቅት ከላይ የተገለፁት መመዘኛዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ይዞ በመቅረብ መመዝገብ ይኖርበታል፡፡

1) የትምህርት ማስረጃ ዋናውንና የማይመለስ 1 ፎቶ ኮፒ፣

2) ከ2 ዓመት በላይ ነዋሪነትን የሚያመለክት የቀበሌ ነዋሪነት መታወቂያ ወይም የፋይዳ መታወቂያ ይዞ መቅረብና መመዝገብ ይጠበቅበታል፣

3) የተመልማዩን ማንነት አጠቃላይ ሁኔታ ለመገንዘብ እንዲያስችል ታስቦ በሥልጠና ማዕከሉ አማካይነት የተዘጋጀውን ፎርም ከምዝገባ ጣቢያውን በመቀበል የመጨረሻ አመት ካጠናቀቀበት ወይም ካጠናቀቀችበት ትምህርት ቤት፣ ከመኖሪያ ቀበሌና ከአከባቢው የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ጽ/ቤት ቀርቦ ወይም ቀርባ የማስሞላትና በተጠቀሰው የቀን ገደብ መሰረት ለምልመላ ጣቢያው አስቀድሞ ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

4) ሴት ተወዳዳሪዎች ይበረታታሉ።
ማንኛውም ምልምል ከ500 ብር በላይ፣ ወርቅ፣ የተለያዩ ስለታማ ነገሮችን፣ ምግብ ነክ ነገሮች እና ከሁለት ቅያሪ ልብስ በላይ ይዞ ወደ ማሰልጠኛው ማዕከል መግባት የተከለከለ ነው፡፡

የምዝገባ ጊዜው ከጳጉሜን 3 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚካሄድ ሲሆን፣ መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች በየክልሉ በሚገኙ ዞኖች፣ ወረዳዎች እና በምልመላ ጣቢያዎች በአካል በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

10ኛው የፍትሕ ሚኒስቴር እና የክልል ፍትሕ ቢሮዎች የጋራ ጉባዔ ተጠናቀቀበአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የፍትሕ ሚኒስቴር እና የክልል ፍትሕ ቢሮዎች የጋራ ጉባኤ የተ...
28/08/2026

10ኛው የፍትሕ ሚኒስቴር እና የክልል ፍትሕ ቢሮዎች የጋራ ጉባዔ ተጠናቀቀ

በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የፍትሕ ሚኒስቴር እና የክልል ፍትሕ ቢሮዎች የጋራ ጉባኤ የተለያዩ የስራ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥና የቀጣዩን ጉባዔ አዘጋጅ በመምረጥ ተጠናቋል።

በጉባዔው የሚነሱ አጀንዳዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደጉና እየተሻሻሉ የመጡ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን የወንጀል ፍትሕ አስተዳደሩን በማጠናከር ቀልጣፋና ውጤታማ በሆነ መልኩ የፍትሕን ተደራሽነት ማረጋገጥ እንደሚገባም ተገልፆል።

በመሆኑም እስካሁን የተገኙ ስኬቶችን በማስቀጠል በቀጣይ በቅንጅትና በትብብር መስራት ዋነኛው ተግባር ሊሆን እንደሚገባ አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን በተጨማሪም በምርመራ ስራዎች፣ በፍልሰት ጉዳዮች፣ በሀብት ማስመለስ፣ በጋራ ፍትሕ መለኪያዎች፣ በዲጂታላይዜሽን፣ ያለንን ውስን ሀብት አቀናጅቶ በመጠቀም፣ በሕዝብ ግንኙነት ሥራዎች፣ በማሕበረሰብ ፍትሕ፣ ማረም ማነፅ፣ በሽግግር ፍትሕ፣ ተአማኒ እና የተሟላ ሪፓርት በማቅረብ፣ ትብብርና ቅንጅትን በማጠናከርና በሌሎች መሠል ጉዳዬች ላይ ለቀጣይ ተጠናክሮ መስራት እንደሚገባ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

በመጨረሻም የ11ኛውን የፍትሕ ሚኒስቴርና የክልሎች የጋራ ጉባኤ የፍትሕ ሚኒስቴር እንዲያዘጋጅ የተመረጠ ሲሆን ጉባዔው በተሳካ መልኩ እንዲካሄድ ከፍተኛ ሚና ላበረከቱ አካላት እዉቅና ተሰቶ የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮራ የአንድ ማዕከል የመሶብ አገልግሎት ጉብኝት ተካሂዶ ጉባዔው ተጠናቋል መረጃዉ የፍትሕ ሚኒስቴርን ነዉ።

የፀጥታ መዋቅሩ ከህዝቡ ጋር ተቀናጅቶ በመስራቱ የውስጥ ባንዳዎች እና የውጭ ባዳዎችን ሴራ አክሽፏል - ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤልየፀጥታ መዋቅሩ ከህዝቡ ጋር ተቀናጅቶ በመስራቱ የው...
27/08/2026

የፀጥታ መዋቅሩ ከህዝቡ ጋር ተቀናጅቶ በመስራቱ የውስጥ ባንዳዎች እና የውጭ ባዳዎችን ሴራ አክሽፏል - ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል

የፀጥታ መዋቅሩ ከህዝቡ ጋር ተቀናጅቶ በመስራቱ የውስጥ ባንዳዎች እና የውጭ ባዳዎችን ሴራ ማክሸፍ መቻሉን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ገለጹ።

የኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽነሮችና የሰላምና ፀጥታ ኃላፊዎች ሀገራዊ የጋራ የፀጥታ መድረክ እየተካሄደ ነው።

ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የፀጥታ መዋቅሩ ከህዝቡ ጋር በጋራ ተቀናጅቶ በመስራቱ ሰላምን የሚያጸኑ ውጤቶች ተገኝተዋል።

ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም እንዲከናወን፣ በየደረጃው ያለው የፖሊስ ሰራዊት፣ የፀጥታና አስተዳደር ኃላፊዎች፣ ሚሊሻዎች፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት በጋራ በማቀድ መስራታቸውን አመልክተው፤ በዚህም በሀገርም ሆነ በዓለም በአርአያነት የሚጠቀስ ምርጫ በሰላማዊ መንገድ መካሄድ መቻሉን ተናግረዋል።

ሁል ጊዜ ኢትዮጵያ በችግር እንድትቆይ ሰላሟን ለማናጋት የሚሹ የውስጥ እና የውጭ ጠላቶች በመገናኘት በርካታ ሴራዎችን እንደሚያቅዱ ያወሱት ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ፤ እነዚያን ሴራዎች በየደረጃው ህይወታቸውን ጭምር በመክፈል እና ሴራውን በማምከን፣ የሀገርን ሰላምና ደህንነት በማስጠበቅ ዛሬ ለተደረሰበት ደረጃ መሰራቱን ተናግረዋል።

መድረኩ በቀጣይም የኢትዮጵያ ጠላቶች ሰላምና ደህንነት ለማናጋት ከውስጥ ባንዳዎች እና ከውጭ ባዳዎች ጋር ተገናኝተው የሚሰሩትን ሴራ ሁሉ ለማክሸፍ፣ ሰራዊቱ አሁንም ዝግጁ መሆኑን የሚያረጋግጥበት እና ለቀጣይ ተልዕኮዎች ራሱን የሚያዘጋጅበት ነው ሲሉም ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የቱሪስቶች መዳረሻ ከመሆን ባለፈ ትላልቅ የአህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ኹነቶች የሚካሄድባት ተመራጭ ሀገር መሆኗን አንስተዋል።

የእነዚህ ኹነቶች በሰላም እና ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከናወኑ የፖሊስ ሰራዊቱ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በጋራ ከፍተኛ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን አክለዋል።

በቀጣይም ለሚካሄዱ ትላልቅ ሀገራዊ ኹነቶች በጋራ መወያየት፣ በጋራ ማቀድ እና በመዘጋጀት የጠላትን ሴራ እያከሸፍን በሰላም እንዲካሄዱ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

የዛሬው መድረክም ​በዋናነት የተከናወኑትን ሥራዎች እና በእዚያ ውስጥ የተገኙ ጥሩ ተሞክሮዎች እና ያጋጠሙን ክፍተቶች በመለየት በቀጣይ ደግሞ ለሚኖር ተልዕኮ ከወዲሁ ለመዘጋጀት ያለመ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ጠላቶችን ሴራ በማክሸፍና የሀገሪቱን ብልጽግና እውን ለማድረግ የሚከናወኑ ተግባራት ውጤታማ እንዲሆኑ የጋራ ስራችንን ልናጠናክር ይገባል ብለዋል።ኢዜአ

ባለሀብቱ የ80 ሺህ ብር ፕሪንተር ገዝተው ለጌሻ ወረዳ ፖሊስ ድጋፍ አደረጉ። በወረዳው ኢንቨትመንት ስራዎች የተሰማሩት ነብዩ ደስታ ቡና ተክል ልማት ባለቤት አቶ ነብዩ ደስታ ፖሊስ በሚያደርገ...
27/08/2026

ባለሀብቱ የ80 ሺህ ብር ፕሪንተር ገዝተው ለጌሻ ወረዳ ፖሊስ ድጋፍ አደረጉ።

በወረዳው ኢንቨትመንት ስራዎች የተሰማሩት ነብዩ ደስታ ቡና ተክል ልማት ባለቤት አቶ ነብዩ ደስታ ፖሊስ በሚያደርገው የወንጀል መከላከል ስራ ውጤታማ እንዲሆን በማሰብ ፖሊስ በቢሮ ያለበትን የቁሳቁስ ችግር ግምት ውስጥ በማስገባት ሰማኒያ ሺህ ብር ወጪ በማድረግ Hp የፕሪንተር በመግዛት ለጌሻ ወረዳ ፖሊስ አስረክበዋል፡፡

አቶ ነብዩ ደስታ በርክክብ ወቅት እንደገለፁት ፖሊስ በአከባቢው ወንጀልን እየተከላከለ ሰላምና ፀጥታን ለልማታቸው አስተዋፅኦ ማድረጉን ጠቅሰው በቀጣይም ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡

ድጋፉን የተረከቡት የጌሻ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ረ/ኢንስፔክተር ሀብታሙ አለማየሁ በበኩላቸው ነብዩ ደስታ ቡና ተክል ልማት ባለቤት ላደረጉት ድጋፍ በሳቸውን በተቋማቸው ስም አመስግነው የፖሊስ ተቋም ስራ ጫና የሚያቃልል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የአምስት አመቷን ታዳጊ 10 ሜትር የውሃ ጉድጓድ ውስጥ ጣለች ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሏን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ታዳጊዋ ከሁለት ሰዓት በኃላ በህይወት መገኘቷን ፖሊስ አመልክቷል፡፡የዋቻ ከተማ አ...
27/08/2026

የአምስት አመቷን ታዳጊ 10 ሜትር የውሃ ጉድጓድ ውስጥ ጣለች ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሏን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ታዳጊዋ ከሁለት ሰዓት በኃላ በህይወት መገኘቷን ፖሊስ አመልክቷል፡፡

የዋቻ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር ደነቀ ዳኜ ለኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን እንደገለፁት በካፋ ዞን ዋቻ ከተማ 02 ቀበሌ ልዩ ስፍራው ሆስፒታል ሰፈር ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ተጥላ ከምሽቱ 2:30 ሰዓት የ5 ዓመት ታዳጊ በውሃ ጉድጓድ ውስጥ ተጥላ በህይወት መገኘቷን ተናግረዋል፡፡

እንደ ፖሊስ አዛዡ ገለፃ በዕለቱ ታዳጊዋ ከግለሰቧ ልጆች ጋር እየተጫወተች ከወላጆቿ ጋር በነበራት ጥል ከልጆቿ ነጥላ በመውሰድ 10 ሜትር ጉድጓድ ውስጥ ጥላት ቤት መግቧታን እንዲሁም የታዳጊዋ ወላጆች እና የአከባቢው ሰዎች ፍለጋ ሲያደርጉ ታዳጊዋ ከጉድጓድ ውስጥ ባሰማችሁ ለቅሶ መገኘቷን አስረድተዋል፡፡

ፖሊስ እና የአከባቢው ነዋሪዎችን በማስተባበር ታዳጊዋን ከ10 ሜትር ጉድጓድ አውጥተው ወደ ዋቻ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በመላክ ህክምና ተደግጓላት ቤተሰቧን መቀላቀሏን ያመለከቱት አዛዡ ግለሰቧ በቁጥጥር ስር ውላ ምርመራ እየተጣራባት መሆኑን እና ወላጆች ልጆቻቸውን በቅርበት ክትትል ማድረግ እንደሚገባቸው ተናግረዋል ሲል የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

✍️ በኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ

ተጨማሪ መረጃዎችን Southwest Ethiopia Police Commission በቴሌግራም ገፃችን ይመልከቱ https://t.me/swpolice

በኮንታ ዞን በተደጋጋሚ የትራፊክ አደጋ በሚከሰትበት አከባቢ የመንገድ ዳር ምልክት እና ማመልከቻ ተተከለ።የኮንታ ዞን ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ አደጋ የሚበዛባቸው ቦታ ከኮይሻ ሳሊኒ ፕሮጀክት ጋ...
27/08/2026

በኮንታ ዞን በተደጋጋሚ የትራፊክ አደጋ በሚከሰትበት አከባቢ
የመንገድ ዳር ምልክት እና ማመልከቻ ተተከለ።

የኮንታ ዞን ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ አደጋ የሚበዛባቸው ቦታ ከኮይሻ ሳሊኒ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በመካና ፤በግርሾሌ፤አጅኮሌ እና ቀይ አፈር ቦታዎች ምልክት ተተከሏል።

የነዳጅ አጠቃቀም ጥንቃቄ ይጠይቃል ሲል የአርባምንጭ ፖሊስ ጽ/ቤት መልዕክቱን አስተላልፏል።በአርባምንጭ ከተማ ሲቀላ ክፍለ ከተማ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ፍትለፍት ቤንዚል በባጃጅ ጀርባ ተጭኖ በሚጓ...
26/08/2026

የነዳጅ አጠቃቀም ጥንቃቄ ይጠይቃል ሲል የአርባምንጭ ፖሊስ ጽ/ቤት መልዕክቱን አስተላልፏል።
በአርባምንጭ ከተማ ሲቀላ ክፍለ ከተማ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ፍትለፍት ቤንዚል በባጃጅ ጀርባ ተጭኖ በሚጓጓዝበት ወቅት ባጃጁ ተቀጣጥሎ የመንደድ አደጋ መድረሱ አሳዛኝ ክስተት ነው።

ይህ አደጋ ለሁላችንም ትምህርት ሊሆን ይገባል። ስለሆነም የባጃጅ ባለንብረቶች፣ አሽከርካሪዎች እና ከባጃጅ ጀርባ ቤንዚል ይዘው የሚንቀሳቀሱ ማንኛውም ባጃጅ አሽከርካሪ በህግ እንደሚጠየቅ አውቆ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የአርባምንጭ ፖሊስ ጽ/ቤት ያሳስባል።

ቤንዚን በፕላስቲክ ውኃ «ሃይላንድ» ወይም በጀርካን መያዝ ፣መሸጥና ማስቀመጥ እጅግ አደገኛ እና በሕግ የተከለከለ ነው ።

ከፍተኛ የእሳት አደጋ፡ የፕላስቲክ ጠርሙሶችና ጀርካኖች በቀላሉ ሊበሱ፣ ሊቀልጡ ወይም እሳትን ሊስቡ ይችላሉ ኤሌክትሪክ ጋር ሊያያዝም ይችላል።

ሕገወጥ ንግድ፡ ዕገዳው ቢኖርም በአንዳንድ አካባቢዎች በድብቅ በችርቻሮ ሲሸጥ ይስተዋላል። ይህን ሕገወጥ ተግባር ማጋለጥ እና ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።

በአደጋው ለተጎዳው የባጃጅ ባለንብረትና ቤተሰቦቹ የአርባምንጭ ፖሊስ ጽ/ቤት ሀዘኑን እየገለጸ፣ ለሁሉም የአካባቢው ነዋሪዎችም ደህንነትን በቅድሚያ እንዲያስቀምጡ ጥሪ ያቀርባል።

ነዳጅ በጥንቃቄ ይጠቀሙ ፤ ህግን ያክብር፤ ህይወትን ይጠብቅ!

ሞተር የጠፋበት ቀርቦ ይዉሰድ ሲል ፖሊስ ጥሪዉን አቀረበ።ባለቤትነቱ ያልታወቀ ባለ ሁለት እግር ተሽከርካሪ ሞተር ሳይክል ቦንጋ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ በህብረተሰብ ጥቆማ ባደረገው ክትትል ከሌ...
26/08/2026

ሞተር የጠፋበት ቀርቦ ይዉሰድ ሲል ፖሊስ ጥሪዉን አቀረበ።

ባለቤትነቱ ያልታወቀ ባለ ሁለት እግር ተሽከርካሪ ሞተር ሳይክል ቦንጋ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ በህብረተሰብ ጥቆማ ባደረገው ክትትል ከሌባ ያስጣለው የሞተር ዓይነት boxer ፣ የጉልበት መጠን150 CC ፣ ታርጋ ቁጥር የለለው ሞተር ሳይክ ይገኛል።

ስለዚህ ይህ ከላይ የተጠቀሰው ባለ ሁለት እግር ተሽከርካሪ ሞተር ባለቤት ነኝ የሚል ህጋዊ ሰነድ ይዞ በመቅረብ መዉሰድ ይችላል ሲል‎ የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት ጠቅሶ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ዘግቧል።

በአመያ ዙሪያ ወረዳ ኮዳ ማጅ  ከተማ የደረሰ አደጋ ነዉ።ሁሌም ጥንቃቄ አይለየን መልዕክታችን ነዉ።
25/08/2026

በአመያ ዙሪያ ወረዳ ኮዳ ማጅ ከተማ የደረሰ አደጋ ነዉ።ሁሌም ጥንቃቄ አይለየን መልዕክታችን ነዉ።

የትራፊክ አደጋ በሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት አደረሰ።‎‎በዳውሮ ዞን ታርጫ ዙሪያ ወረዳ መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ በደረሰበት መገልበጥ አደጋ መሆኑ ተገልጿል።በዳውሮ ዞን ...
25/08/2026

የትራፊክ አደጋ በሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት አደረሰ።

‎በዳውሮ ዞን ታርጫ ዙሪያ ወረዳ መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ በደረሰበት መገልበጥ አደጋ መሆኑ ተገልጿል።

በዳውሮ ዞን ታርጫ ዙሪያ ወረዳ ጎዞ ሻሾ ቀበሌ ልዩ ስም ውቂ ቁልቁለት ተብሎ በሚጠራበት አከባቢ ከምሽቱ 1:30 ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ በአስራ ሰባት ሰዎች ከባድና ቀላል ጉዳት እንደደረሰባቸዉ የዞኑ ፖሊስ በመረጃዉ አመልክቷል።

እንደ ዳውሮ ዞን ፖሊስ መምሪያ መረጃ በአደጋዉ ስድስት ከባድ እና አስራ አንድ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸው ተጎጂዎቹ ታርጫ ጠቅላላ ሆስፒታል ለህክምና ተወስደዋል።

በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት የተመዘገበ ሲሆን ‎የአደጋው መንስኤውን የታርጫ ዙሪያ ወረዳ ትራፊክ ፖሊስ በማጣራት ላይ እንደሚገኝ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።


‎ የትራፊክ አደጋን በጋራ እንከላከል!!!

Address

ሸታ
Bonga

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Southwest Ethiopia Police Commission posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category