02/09/2026
በጌሻ ወረዳ የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲና የመንግሥት የሥራ አፈጻጸም ግምገማና የአመራር ምዘና መድረክ መካሄድ ተጀመረ።
ጌሻ፦ ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም (የጌሻ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት) በካፋ ዞን በጌሻ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የብልፅግና ፓርቲ የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲና የመንግስት ተግባራት አፈፃፀም ግምገማና የአመራር ምዘና መድረክ በጌሻ ወረዳ እየተካሄደ ይገኛል።
የምዘና መድረክን የመሩት የካፋ ዞን ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ ኃላፍ አቶ አብረሃም አባቴ እንደተናገሩት የመድረኩ ዋና ዓላማ በአመራሩ መካከል የአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን በማጠናከር ጉድለቶችን በማረም ለቀጣይ ተልዕኮዎች አመራሩን ይበልጥ ለማዘጋጀት እንደሆነ ነው ብለዋል።
አያይዘውም አቶ አብረሃም በ2018 በጀት ዓመት የተከናወኑ የፓርቲና የመንግሥት ተግባራት አፈጻጸም በጥልቀት በመገምገም አመራሩ ጥንካሬዎቹን አጠናክሮ እንዲቀጥልና የታዩ ክፍተቶችን በዝርዝር በመፈተሽ ቀጣይ ለላቀ ስኬት እንዲዘጋጅ ለማድረግ ያለመ መሆኑንም ነው የገለፁት።
የካፋ ዞን የግብርና መምሪያ ም/ኃላፍና የቡና ሻይና ቅመማቅመም ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሞገስ ተክሌ በበኩላቸው ምዘናው በአመራሩ መካከል የተግባር እና የአስተሳሰብ አንድነት ወጥነት በማጠናከር የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ለማስቀጠል ትልቅ አቅም እንደሚኖረው ትልቅ ተስፋ ሰጭ መድረክ ነው ብለዋል።
ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው የምዘና መድረክ ላይ የወረዳው የመንግሥት ረዳት ተጠሪና አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አጥናፉ አሰፋ አማካኝነት የፓርቲና የመንግሥት የሥራዎች አፈጻጸም ሪፖርት ሰነድ እየቀረበ ይገኛል።
የካፋ ዞን ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ ኃላፍ አቶ አብረሃም አባቴ፣ የካፋ ዞን የግብርና መምሪያ ም/ኃላፍና የቡና ሻይና ቅመማቅመም ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሞገስ ተክሌ መድረኩን እየመሩ ስሆን በመድረኩም የወረዳው አስተባባሪ አካላት እና አጠቃላይ አመራር አካላት እየተሳተፉ ይገኛል።
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇
📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100064824279218
📌በቲክቶክ https://tiktok.com/
📌በቴሌግራም https://t.me/GW_communicationlink2025
📌በዋትስአፕ https://chat.whatsapp.com/FzBtziS1ViPKt6bnnEZ3lp
🙏ዘውትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን🙏
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ዘገባው:-የጌሻ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ነው።