02/09/2026
ባለፉት ለውጥ ዓመታት በኢኮኖሚ ፣ በማህበራዊ ፣ በአስተዳደር እንዲሁም በፖለቲካ ዘርፍ የሚጨበጥ እና የሚታይ ዘርፈ ብዙ አዳዲስ ነገሮች ተመዝግቧል።አቶ ጋዎ አባመጫ
ቦንጋ፦ነሐሴ ፣27/2018 ዓ.ም (የቦንጋ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ /ቤት)
የቦንጋ ከተማ አስተዳደር የ2018 ዓ.ም ማጠቃለያ ግምገማ እና የአመራር ምዘና መድረክ መካሄድ ጀምሯል።
የማጠቃለያ ግምገማ መድረኩን የመሩት የካፋ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጋዎ አባመጫ ባለፈው በጀት ዓመት የታዩ ጉድለቶችን በማረም ህዝብ የሰጣቸውን አደራዎች ውጤታማ ተግባር በመፈፀም ኃላፊነትን በአግባቡ መወጣት ያስፈልጋል ብለዋል።
የ2018 ዓ.ም አፈፃፀም ችግሮችን ለይተው መፍትሔ በመስጠት ጥንካሬዎችን በማስቀጠል መሻገር እና ማሻገር የሚችል አመራር መገንባት የመድረኩ ዋና ዓላማ መሆኑን አስረድተዋል።
ባለፉት ለውጥ ዓመታት በኢኮኖሚ ፣ በማህበራዊ ፣ በአስተዳደር ዘርፍ እንዲሁም በፖለቲካ የሚጨበጥ እና የሚታይ ዘርፈ ብዙ አዳዲስ ነገሮች አዳዲስ ነገሮች የታዩበት እና የተመዘገቡ መሆናቸውን ነው የተናገሩት አቶ ጋዎ አባመጫ ።
ሁለት የምርጫ መንትያ ግቦችን በማሳካት ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫን ዴሞክራሲያዊ እና በህዝብ ተዓማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በማድረግ ስኬታማ መሆን ተችሏል ብለዋል።
የግምገማ እና የምዘና መድረኩ በተዋረድ ከክልል ጀምሮ እየተካሄደ መምጣቱን ያስታወሱት አቶ ጋዎ አመራር በተግባር እና በአመለካከት አንድ ሆነው በመንግሥት እና በፓርቲ የሚሰጡ ተልዕኮዎችን ስኬታማ እንዲሆን የአመራር ማጥራትና ለተግባር ማዘጋጀት ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል።
የምዘና እና ግምገማ መድረኩን የካፋ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጋዎ አባመጫ እና የዞኑ ፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ አቶ መቅደስ ማሞ እየመሩት ይገኛሉ።
ቦንጋ ከተማን በጋራ እናልማ ❗️
✍ተጨማሪ መረጃዎቸን ✍
በቴሌግራም 👉 t.me/BongatownGCAO
በፌስቡክ ?Bonga Town Government Communication Affairs OfficeCA
በቲውተር 👉 https://twitter.com/BongaTown?t=1Hfq-1TmjDHkrNlWUiPA7g&s=09 ተወዳጅተው ይከታተሉን፡፡
በቲክቶክ 👉 https://www.tiktok.com/?_t=ZM-8uW0x6Jb0CL&_r=1
🙏ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን🙏