03/09/2026
የቆዳና ሌጦ ምርት ብክነትን ለመቀነስ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የቢጣ ወረዳ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ጽህፈት ቤት አስታወቀ
የጽ/ቤቱ ምክትል ኃላፊ አቶ ነፃነት ወንድሙ እንደገለፁት በወረዳው ከዚህ ቀደም በዘርፉ የተሰማራ ነጋዴ ባለመኖሩ ምክንያት የቆዳና ሌጦ ምርት በየቦታው ሲባክንና የአካባቢን ንፅህና ሲበክል መቆየቱን አስታውሰዋል።
ይህንን ዘላቂ በሆነ መንገድ ለመፍታት የወረዳው ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ጽህፈት ቤት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ነው ኃላፊው የጠቀሱት።
አቶ ነፃነት እንዳመለከቱት፣ ከዚህ ቀደም ያጋጥም የነበረውን የምርት ብክነትና የአካባቢ ብክለት የሚያስቀር አዲስ እድል በመፈጠሩ በዘርፉ ለመሰማራት ፈቃደኛ ለሆነ ነጋዴ ምርቱን በማቅረብ ህብረተሰቡ ተጨማሪ ገቢ ከማግኘት ባሻገር የአካባቢውን ንፅህና እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል።
በወረዳው በቆዳና ሌጦ ንግድ ዘርፍ የተሰማሩት ባለሀብትና ነጋዴ አቶ ቆጭቶ ወልደጊዮርጊስ እንደገለጹት፣ አሁን ላይ ምርቱን በስፋት ለመረከብና ለገበያ ለማቅረብ ዝግጁ መሆናቸውን በመግለጽ፣ ህብረተሰቡ የሚያመርተውን የቆዳና ሌጦ ምርት ያለስጋት እንዲያቀርብ ጥሪ አቅርበዋል።
በተጨማሪም የቆዳና ሌጦ ምርት ጥራቱን ጠብቆ እንዲቆይና እንዳይበላሽ ለማድረግ የጨው አቅርቦት ወሳኝ በመሆኑ፣ የሚመለከተው አካል አስፈላጊውን የጨው አቅርቦት እንዲያመቻችላቸው ባለሀብቱ ጥሪ አቅርበዋል።
በባለሀብቱ በኩል የተጠየቀውን የጨው አቅርቦት ከሚመለከታቸው ጋር በመነጋገር የመፍትሔ እርምጃ እንደሚወሰድ ጽ/ቤቱ አመላክቷል።
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
ለተጨማሪ መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/Bittaworeda
በቲክ-ቶክ ገፃችን woreda.commu
ላይ በመቀላቀል ይከታተሉን
የቢጣ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን