Goba woreda government communication affairs office

Goba woreda government communication affairs office ይህ የጎባ ወረዳ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ይፋዊ የማኅበራዊ ሚዲያ(የፌስቡክ) ገጽ ነው።

04/09/2026
 #የማሽቃሮ" በዓል ታሪካዊ ዳራ!የካፈቾ ዘመን መለወጫ በዓል "ማሽቃሮ" ታሪካዊ መሠረቱን ስንመለከት በጣም ረጅም ዘመን ያስቆጠረና ማህበረሰቡ ባህላዊ የአኗኗር ሥርዓት መስርቶ መኖር ከጀመረበ...
04/09/2026

#የማሽቃሮ" በዓል ታሪካዊ ዳራ!

የካፈቾ ዘመን መለወጫ በዓል "ማሽቃሮ" ታሪካዊ መሠረቱን ስንመለከት በጣም ረጅም ዘመን ያስቆጠረና ማህበረሰቡ ባህላዊ የአኗኗር ሥርዓት መስርቶ መኖር ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ እንደሆነ ይነገራል፡፡

ለዚህም ማሳያ የተለያዩ ባህላዊና ትውፊታዊ ክዋኔዎች የታጀበ መሆኑ ነው፡፡

በተለይ የግብርና ሥራን በወቅቶች ከፋፍሎ ለመስራት የወጣውን የጊዜ ቀመር መሠረት ያደረገ መሆኑም ይነገራል፡፡ማሽቃሮ በንጉሱ መሪነት መከበር ከመጀመሩ በፊት እያንዳንዱ የካፋ ማህበረሰብ በተለይ አርሶ አደሩ አዝመራውን ቆጥሮ አሮጌው ዓመት መበአዲስ ዓመት መተካቱን ለማብሰር በተለያዩ ባህላዊ ዝግጅቶች ሲያከብር የኖረበት መሆኑን የታሪክ አዋቂዎች ያስታውሳሉ፡፡

በዓሉ ከመንደር ጀምሮ አስከ ታላቁ ንጉሡ ቤተ መንግስት ቦንጌ ሻምበቶ አደባባይ ድረስ ይከበራል፡፡

በዓሉ ጥንት ካፈቾ የራሱ የሆነ የአስተዳደር ሥርዓት የነበረበት በዓል እንደመሆኑ መጠን ምንም ዓይነት ኃይማኖታዊም ሆነ የዘርና የጎሳ ልዩነት ሳይኖረው በሁሉም የካፋ አካባቢዎች በደማቅ ሁኔታ በአንድነት ፣ በመከባበርና በመደጋገፍ የሚከበር በዓል ነው፡፡

የበዓሉ ቅድመ ዝግጅት ከወራት አስቀድሞ የሚጀመር ሆኖ በተለይ በቤተ መንግስት የሚደረገው ዝግጅት እጅግ ሰፋ ያለና ታሪካዊ ነው፡፡

ወራፎዎቹ የየራሳቸውን አካባቢና ገፅታ በሚገልፅ መልኩ በዘፈንና በቀረርቶ አዲሱን ዓመት ከንጉሳቸው ጋር ማሳለፋቸውን በደስታ ስለሚገልፁ ለዚህም በርካታ ህዝብ ይዞ ይታደማሉ፡፡

ዝግጅቱም በዋናነት ዓመታዊ ሥራ አፈጻጸም፣ የተፈጥሮ ሀብት አጠባበቅና አጠቃቀም እንዲሁም ህዝቡ በሠላምና ያለጸጥታ ችግር ዓመቱን ማሳለፉ ትኩረት ተሰጥቶበት ይገመገማል፡፡

ያለፈውን ዓመት የመሩ መሪዎች ሥራቸው ታይቶ ከነበሩበት በሹመት ያደጉ፣በቦታቸው የቀጠሉና ከሹመታቸው የተነሱ ወራፎዎች፣ምክረቾዎችና ሌሎች ሹማምንቶች ካሉ ለሕዝቡ በይፋ የሚገለጽበት በዓል ነው፡፡

ተግባራት እንደተጠናቀቁ የተመረጡ ሰዎች 100 ነጭ ፣ 100 ጥቁር እና 100 ቀይ ፈረሶች በማዘጋጀት ሀረሸራሻ በሚባሉት መሪነት ፈረሶቹ ባንደራ በአንገታቸው ታስሮ የነገስታት መካነ መቃብር ወደ ምገኝበት "ሾሻ ሞጎ" ጉዟቸውን ይቀጥላሉ ።

ፈረሰኞቹ ቅኝታቸውን ጨርሰው ቤተ-መንግስት እንደደረሱ በሀረሸራሻ አማካኝነት አካባቢውና መካነ መቃብሩ በሰላም እየተጠበቀ መሆኑ ለንጉሱ መልዕክት ይደርሳል፡፡

ንጉሱም ሀገር ሰላም መሆኑ ስለተረጋገጠ ለተሰበሰበው ሕዝብ ወጥቶ በመታየት ባንዲራውን በመሰቀል ክብረበዓሉን ያስጀምራሉ።በዓሉ ስለመጀመሩ ነጋሪት ይጎሰምና ቦንጌ ሻምበቶ ሆኮ ሲመታ በ4ቱ አቅጣጫ ኬላዎች ሆኮ ይመታና በሁሉም አቅጣጫዎችና በመላው ግዛት የሆኮ ድምጽ በማሰማት የበዓሉ መጀመር በይፋ ይበሰራል፡፡

በመቀጠል ንጉሱ የተሰበሰበውን ሕዝብ በበገና በክረምት የማይደርቅ ሐረግ(ሐውቶ ቆመቦ) የሚባለውን በመያዝና በአራቱም አቅጣጫዎች አምላኩን ተማጽኖ ይመርቅና ጮንጎ ይበላል ።

ደኑ ጫካው እንዲሁም ሀገሩ ህዝቡና መላው ዓለም ሰላም እንዲሆን በህብረት ፀሎት ይደረጋል ።

እንኳን ለካፈቾ ብሔረብ ዘመን መለወጫ "ማሽቃሮ" በሠላም አደረሳችሁ አደረሰን።

መረጃው፦ የካፋ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው ።

‎ህብረ ብሔራዊ አንድነት በሚንፀባረቅባት "ትንሿ ኢትዮጵያ" ጎባ ወረዳ የ2019 ዓ.ም የ"ማሽቃሮ" በዓልን በድምቀት ለማክበር ሰፊ ዝግጅት እየተደረገ ነው‎‎ብዝሃነትና ህብረ ብሔራዊ አንድነት...
04/09/2026

‎ህብረ ብሔራዊ አንድነት በሚንፀባረቅባት "ትንሿ ኢትዮጵያ" ጎባ ወረዳ የ2019 ዓ.ም የ"ማሽቃሮ" በዓልን በድምቀት ለማክበር ሰፊ ዝግጅት እየተደረገ ነው

‎ብዝሃነትና ህብረ ብሔራዊ አንድነት ደምቆ በሚታይባት፣ እንዲሁም በ"ትንሿ ኢትዮጵያ"፤ በካፋ ዞን ጎባ ወረዳ የ2019 ዓ.ም የ"ማሽቃሮ" በዓልን በልዩ ድምቀት ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በከፍተኛ መነቃቃት እየተከናወኑ ይገኛሉ።

‎በዚሁ ደማቅ ባህላዊ በዓል ላይ ዝግጅቱን ይበልጥ አድምቀው ለማቅረብ፤ የካፋ፣ የናይ፣ የጻራ እንዲሁም በወረዳው የሚገኙ የሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ታዳጊዎችና ወጣቶች በጋራ በመሆን የባህል ልምምዶችንና ልዩ ልዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በማድረግ ላይ ናቸው።

‎የ"ማሽቃሮ" በዓል ከባህላዊ እሴቱ ባሻገር በአካባቢው ለሚኖሩ ልዩ ልዩ ማህበረሰቦች የአብሮነት፣ የፍቅር እና የህብረ ብሔራዊ አንድነት መገለጫ ሆኖ የቆየና የሚቀጥል ነው።

‎በዚህ ዝግጅት ላይ ታዳጊ ወጣቶች በስፋት መሳተፋቸው ደግሞ፣ የየራሳቸውን ብሔር ባህላዊ ትውፊቶች በማስተዋወቅና ውብ የሆነውን የአካባቢውን ባህል ለቀጣዩ ትውልድ ለማሸጋገር ትልቅ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል።

‎ልዩ ልዩ ባህሎች፣ ቋንቋዎችና ትውፊቶች በአንድነት ተሰባጥረው ውበት በሚፈጥሩባት በዚች ወረዳ፣ ዘንድሮ የሚከበረው የ"ማሽቃሮ" በዓል ከተለመደው በተለየ ድምቀትና የህዝብ ተሳትፎ እንደሚከበርም ከወዲሁ እየተደረጉ ያሉ ዝግጅቶች ያመለክታሉ።

እንኳን አደረሳችሁ/አደረሰን!

‎‎የደረጃ "ለ" ግብር ከፋዮች የግብር ግዴታቸውን በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ በማጠናቀቅ ከቅጣት እንዲጠበቁ የጎባ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት አሳሰበ‎‎የጎባ ወረዳ ገቢዎች ጽህፈት ቤት የደረጃ "ለ" ...
03/09/2026

‎‎የደረጃ "ለ" ግብር ከፋዮች የግብር ግዴታቸውን በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ በማጠናቀቅ ከቅጣት እንዲጠበቁ የጎባ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት አሳሰበ

‎የጎባ ወረዳ ገቢዎች ጽህፈት ቤት የደረጃ "ለ" ግብር ከፋዮች ቀሪውን አጭር ጊዜ በመጠቀም የግብር ግዴታቸውን እንዲወጡና ራሳቸውን ከተጨማሪ ቅጣት እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርቧል።

‎የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ አሰግድ ኃይሌ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ግብር ለአንድ ሀገር የኢኮኖሚ እድገትና ለልማት ስራዎች መፋጠን ያለው ሚና እጅግ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

‎በመሆኑም ግብር ከፋዮች የግብር ግዴታቸውን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ማለትም እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ አጠናቀው እንዲከፍሉ አቶ አሰግድ በጥብቅ አሳስበዋል።

‎የተያዘው የግብር መክፈያ ጊዜ ሊጠናቀቅ የቀረው ሁለት ቀናት ብቻ መሆኑን ያስታወሱት ኃላፊው፤ የደረጃ "ለ" ግብር ከፋዩ ማህበረሰብ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ጽህፈት ቤቱ በመቅረብ ክፍያቸውን ፈጽመው ህጋዊ ግዴታቸውን እንዲወጡና ከማንኛውም አስተዳደራዊ ቅጣት ነፃ እንዲሆኑ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

‎ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የጎባ ወረዳ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የግምገማና ምዘና መድረክ ተጠናቀቀ‎‎በካፋ ዞን ጎባ ወረዳ የ2018 ዓ.ም የመንግስትና የፓርቲ ተግባራት አፈፃፀምን መ...
03/09/2026

‎ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የጎባ ወረዳ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የግምገማና ምዘና መድረክ ተጠናቀቀ

‎በካፋ ዞን ጎባ ወረዳ የ2018 ዓ.ም የመንግስትና የፓርቲ ተግባራት አፈፃፀምን መነሻ በማድረግ ለተከታታይ ሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የጎባ ወረዳ አጠቃላይ የአመራር ግምገማና የምዘና መድረክ በስኬት ተጠናቋል።

‎በትናንትናው ዕለት ጅምሩን ያደረገው ይህ የአመራር ግምገማ መድረክ፤ በመጀመሪያ በቡድን ደረጃ ጥልቅ በሆነ የሂስና ግለ-ሂስ አሰራር ሲካሄድ ቆይቷል።

‎ቀጥሎ አመሻሹ ላይ በጋራ የኃይል መድረክ የማጠቃለያ ሀሳቦችና አስተያየቶች ቀርበው፣ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በጋራ በማስቀመጥ መቋጫውን አግኝቷል።

‎የግምገማ መድረኩ ዋነኛ ዓላማ የአመራሩን የተግባርና የአመለካከት አንድነት ይበልጥ በማጠናከር፣ የሚመራውን ተቋም ውጤታማነት በተጨባጭ ማረጋገጥና ማሻሻል በሚያስችል አግባብ መካሄዱ ተገልጿል።

‎የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታረቀኝ ታደሰ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ግምገማው ከተለመደው አካሄድ የወጣና ተጨባጭ ማነቆዎችን የፈተሸ ነበር ብለዋል።

‎አክለውም፣ ይህ መድረክ አመራሩ በ2018 ዓ.ም የነበሩበትን ክፍተቶች በድፍረት በመለየት፣ ለቀጣይ የልማት ተልዕኮዎች ከወዲሁ ራሱን እንዲያዘጋጅ የሚያስችል አቅም መፍጠሩን ተናግረዋል።

‎የህዝቡን የልማት፣ የሰላምና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በተገቢው መንገድ ለመመለስና የተጀመሩ የብልጽግና ጉዞዎችን ከግብ ለማድረስ ሁላችንም በአዲስ መንፈስና ቁርጠኝነት እንድንነሳ አድርጎናል በማለት ሀሳባቸውን ገልጸዋል።

‎መድረኩን የመሩት የዞኑ ስራና ክህሎት መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ መብራቱ መሸሻ ባስተላለፉት መልዕክት፣ በአመራር ደረጃ በተካሄደው በዚህ መድረክ ላይ የታዩ ስኬቶች ይበልጥ ሊጎለብቱ እንደሚገባ አስምረውበታል።

‎አክለውም ምክትል ኃለፊው፥ በግምገማው የተነሱ ጉድለቶችን በተቋም ደረጃ ከሁሉም ፈፃሚ ባለሙያዎች ጋር በጥልቀት በመወያየት ለቀጣይ የዕቅድ አካል ማድረግና ማረም እንደሚገባ አሳስበዋል።

‎ወረዳው እጅግ ተስፋ ሰጪና ሰፊ እምቅ ፀጋ ያለው ነው ያሉት አቶ መብራቱ፤ አመራሩ ይህን ፀጋ በአግባቡ በመጠቀም፣ በቅንጅትና በቁርጠኝነት በመስራት ወረዳውን በማልማት የህዝቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንዳለበት አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

‎በተመሳሳይ መድረኩን በጋራ የመሩት የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ አጦ ወዳጆ በበኩላቸው፤ ግምገማው በትኩረት መታየት ያለባቸውን ጉዳዮች በጥልቀት ያሳየ መድረክ መሆኑን ገልጸዋል።

‎በመጨረሻም በቀጣይ ስኬቶቻችንን አጠናክረን በማስቀጠል፣ የተነሱትን ጉድለቶች ደግሞ በፍጥነት በማረም በተግባር ለማሳየት ከፍተኛ መነሳሳትና የጋራ ርብርብ ያስፈልጋል ሲሉ አቶ አጦ ወዳጆ አጽንኦት ሰጥተዋል።

‎የጎባ ወረዳ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ነው
‎ለተሻለች ጎባ በጋራ እንሥራ!

ኢንዱስትሪው የቡና ምርት ከወረዳው ተቀሽሮ፣ ታጥቦና ጥራቱን ጠብቆ ወደ ማዕከላዊ ገበያ እንዲላክ በማድረግ ረገድ የጎላ ሚና እንደሚኖረው ተገለጸ ‎‎በጎባ ወረዳ ኡያ ታዳጊ ማዘጋጃ ከተማ የወረ...
03/09/2026

ኢንዱስትሪው የቡና ምርት ከወረዳው ተቀሽሮ፣ ታጥቦና ጥራቱን ጠብቆ ወደ ማዕከላዊ ገበያ እንዲላክ በማድረግ ረገድ የጎላ ሚና እንደሚኖረው ተገለጸ

‎በጎባ ወረዳ ኡያ ታዳጊ ማዘጋጃ ከተማ የወረዳው መንግሥት ከማዘጋጃ ቤቱ ጋር በመተባበር ለቡና መቀሸሪያና ማጠቢያ ኢንዱስትሪ ግንባታ የሚውል ቦታን ለባለሀብቶች አስረከበ።

‎በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታረቀኝ ታደሰ፣ የዞኑ ስራና ክህሎት መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ መብራቱ መሸሻ፣ የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ አጦ ወዳጆን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የወረዳው አመራሮችና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

‎የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታረቀኝ ታደሰ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ በቅርብ ጊዜያት ውስጥ በወረዳው በተለያዩ አካባቢዎች ተመሳሳይ ኢንዱስትሪዎችን ለመገንባት የመሠረት-ድንጋይ ማስቀመጥ የተቻለ ሲሆን፣ አሁን የተረከበው የቡና ኢንዱስትሪም ለወረዳው አምስተኛው ነው።

‎አክለውም፣ ኢንዱስትሪው ለበርካታ ዓመታት ከወረዳው ባልተገባ መንገድ ሲወጣ የነበረውን የቡና ምርት በማስቀረት፤ ተቀሽሮ፣ ታጥቦና ጥራቱን ጠብቆ ወደ ማዕከላዊ ገበያ እንዲላክ በማድረግ ረገድ የጎላ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።

‎"ከወረዳው እምቅ አቅም አንጻር ይህ ገና ጅማሮ ነው" ያሉት ዋና አስተዳዳሪው፤ ፕሮጀክቱ ለአካባቢው ማህበረሰብና ለወረዳው ሰፊ የስራ ዕድል እንደሚፈጥር በመጠቆም፣ ባለሀብቶቹ በአፋጣኝ ወደ ስራ እንዲገቡ አሳስበዋል።

‎የዞኑ ስራና ክህሎት መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ መብራቱ መሸሻ በበኩላቸው፤ በአካባቢው ያለውን እምቅ የቡና ምርት አቅም በአግባቡ ለመጠቀም፣ እንዲሁም ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።

‎ለዚህም እንዲህ ዓይነት ዘመናዊ የቡና መቀሸሪያና ማጠቢያ ኢንዱስትሪዎች ግንባር ቀደም ሚና እንዳላቸው አስረድተዋል።

‎የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ አጦ ወዳጆም፤ የካፋ ማህበረሰብ አኗኗር ከቡና ጋር በጥብቅ የተቆራኘ መሆኑን ጠቅሰው፣ ይህ ኢንዱስትሪ ማህበረሰቡን ይበልጥ ተጠቃሚ እንደሚያደርገው ተናግረዋል።

‎የወረዳው መንግሥት ከህዝብና ከአልሚዎች ለሚነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ እየሰጠ መሆኑንም አድንቀው፤ ባለሀብቶችም የተመቻቸላቸውን ሁኔታ በመጠቀም ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

‎የኡያ ታዳጊ ማዘጋጃ ከተማ ስራ አስኪያጅ አቶ አትርሴ አሰፋው፤ ኢንዱስትሪው ለአካባቢው ማህበረሰብ ትልቅ ጥቅም እንደሚያስገኝ ገልጸው፣ ቦታውን ከማንኛውም የሶስተኛ ወገን ይገባኛል ጥያቄ ሙሉ በሙሉ ነፃ በማድረግ ለኢንዱስትሪው ምቹ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

‎ኢንዱስትሪውን በጋራ የሚገነቡት የአካባቢው ባለሀብቶች አቶ ቆጭቶ ማሞ እና አቶ ታደለ በቀለ ላቀረቡት ጥያቄ ፈጣን ምላሽ የሰጠውን የወረዳውን መንግሥት በማመስገን፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ ፕሮጀክቱን ወደ ስራ እንደሚያስገቡ አረጋግጠዋል።

‎የጎባ ወረዳ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ነው
‎ለተሻለች ጎባ በጋራ እንሥራ!

በካፋ ዞን ጎባ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም ማጠቃለያ ግምገማ እና የአመራር ምዘና መድረክን እያካሄደ ይገኛል‎‎በካፋ ዞን የጎባ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ...
02/09/2026

በካፋ ዞን ጎባ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም ማጠቃለያ ግምገማ እና የአመራር ምዘና መድረክን እያካሄደ ይገኛል

‎በካፋ ዞን የጎባ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት፤ "ከድል ማግስት ጠንካራ መንግሥት" በሚል መሪ ቃል የ2018 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ማጠቃለያ ግምገማ እና የአመራር ምዘና መድረክን ማካሄድ ቀጥሏል።

‎በዚህ መድረክ ላይ የዞኑ ስራ ክህሎት መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ መብራቱ መሸሻ እና የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኢኒስፔክሽንና ስነ-ምግባር ምክትል ኃላፊ አቶ አጦ ወዳጆ ተገኝተው መድረኩን እየመሩ ይገኛሉ።

‎በወረዳው የሚገኙ ከፍተኛ የፓርቲ እና የመንግሥት አመራሮች እየተሳተፉ ሲሆን፣ የ2018 የበጀት ዓመት የመንግሥትና የፓርቲ ቁልፍ የልማት፣ የመልካም አስተዳደር እንዲሁም የፖለቲካ ተግባራት አፈጻጸም ሪፖርት ሰነድ በወረዳው አስተባባሪዎች ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይት ተካሂዶበታል።

‎የቀረበው የአፈጻጸም ሪፖርት በዋናነት በበጀት ዓመቱ የተመዘገቡ ስኬቶችን፣ በሂደት ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን እና ክፍተቶችን በሚገባ የዳሰሰ ነው።

‎በተለይም ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልማትን ከማፋጠን አኳያ የተሰሩ ስራዎች በዝርዝር የቀረቡ ሲሆን፣ ተሳታፊዎችም በሰነዱ ላይ ጥልቅ እና ግልጽ ውይይት አድርገዋል።

‎የቀረበውን ሪፖርት መነሻ በማድረግ የወረዳው አመራሮች በሰጡት አስተያየት እና በግምገማው ሂደት፤ ባለፈው ዓመት የተከናወኑ አበረታች ስራዎችን ይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።

‎ከዚሁ ጎን ለጎን በህዝብ ዘንድ ለሚነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ፈጣንና ተገቢውን ምላሽ መስጠት የአመራሩ ቀዳሚ ተግባር ሊሆን እንደሚገባ ተመላክቷል።

‎መድረኩ "ከድል ማግስት ጠንካራ መንግሥት" በሚል መሪ ቃል መካሄዱ፤ የተገኙ አገራዊ፣ ክልላዊ እና ዞናዊ እንዲሁም ወረዳዊ ድሎችን በማስጠበቅ የተቋማትን አሰራር ይበልጥ ማዘመንና የህዝብን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን የሚያመላክት ነው ተብሏል።

‎በምዘናው ሂደትም አመራሩ ለቀጣይ ተልዕኮ ራሱን በቁርጠኝነት እንዲያዘጋጅ እና የተሰጠውን ህዝባዊ አደራ በታማኝነት እንዲወጣ አቅጣጫ ተቀምጧል።

‎በመቀጠልም ይህ የማጠቃለያ ግምገማ እና የአመራር ምዘና መድረክ በቀጣዩ የ2019 ዓ.ም የሥራ ዘመን የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ፣ ውስጣዊ አንድነትን ለማጠናከር እና ጠንካራ የፓርቲና የመንግሥት መዋቅርን በወረዳው ለመገንባት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ተጠቁሟል።

‎ውይይቱና ምዘናው በቀጣይ ቀናትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎች‎‎ጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”‎‎ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”‎‎ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”‎‎ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”‎‎ጳጉሜን 5 – “የ...
02/09/2026

የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎች

‎ጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”

‎ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”

‎ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”

‎ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”

‎ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”

በካፋ ዞን ጎባ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የ2018 ዓ/ም ማጠቃለያ ግምገማ እና የፑል አመራር ምዘና መድረክ በመካሄድ ላይ ነው ‎‎በዚህ መድረክ ላይ የዞኑ ስራ ክህሎት መም...
02/09/2026

በካፋ ዞን ጎባ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የ2018 ዓ/ም ማጠቃለያ ግምገማ እና የፑል አመራር ምዘና መድረክ በመካሄድ ላይ ነው

‎በዚህ መድረክ ላይ የዞኑ ስራ ክህሎት መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ መብራቱ መሸሻ እና የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኢኒስፔክሽንና ስነ-ምግባር ምክትል ኃላፊ አቶ አጦ ወዳጆ ተገኝተዋል።

‎የወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታረቀኝ ታደሰ በመክፈቻው ንግግራቸው እንዳሉት፤ በ2018 በጀት ዓመት ያጋጠሙንን ልዩ ልዩ ፈተናዎች በአመራሩ እና በህዝባችን የተቀናጀ ጥረት ተሻግረን ተስፋ ሰጪ የልማት፣ የሰላምና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ማከናወን ችለናል።

‎ከዚህ ግምገማ በኃላ ያስመዘገብናቸውን ድሎች አጠናክረን በማስቀጠል ለህዝባችን የላቀ አገልግሎት የሚሰጥ ጠንካራ ተቋማዊ አቅም እና አመራር መገንባት ይኖርብናል ብለዋል።

‎ይህ የማጠቃለያ ግምገማ እና የአመራር ምዘና መድረክም በዓመቱ የታዩ ጥንካሬዎቻችንን የምናጎለብትበት፣ እንዲሁም ያጋጠሙንን የአፈጻጸም ክፍተቶች ነቅሰን በማውጣት በቀጣይ ማስተካከያ የምናደርግበት ወሳኝ ምዕራፍ ነው ሲሉ አስተዳዳሪው ተናግረዋል።

‎አቶ ታረቀኝ አክለውም እያንዳንዱ አመራር በመድረክ ቆይታው በግልጽነት፣ ከግለሰባዊ እይታና ከመጠቃቃት በመውጣት በኃላፊነት ስሜት እና በመርህ ላይ ተመስርቶ የፓርቲያችንን ዲስፕሊን በጠበቀ መልኩ ራሱንና አቻውን በተግባር ሚዛናዊነት ሊገመግም ይገባል በማለት አሳስበዋል።

‎በ2018 ዓ/ም የተከናወኑ የመንግስትና የፓርቲ ተግባራት አፈጻጸማችንን ስንገመግም፣ አመራሩ የፓርቲያችንን ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ወደ መሬት በማውረድ የህዝቡን የልማት፣ የሰላምና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ ያደረገውን ርብርብ በጥልቀት የምንፈትሽበት ይሆናል ያሉት የዞኑ ስራ ክህሎት መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ መብራቱ መሸሻ ናቸው።

‎ምክትል ኃላፊው በመድረኩ እንዳሉት 'ከድል ማግስት ጠንካራ መንግስት' መገንባት የሚቻለው የመንግስትን ተቋማዊ አቅም የሚያጎለብትና የፓርቲውን ዲስፕሊን አጥብቆ የያዘ ብቁ አመራር ሲኖር ብቻ መሆኑን ተናግረዋል።

‎በዚህ መድረክ መድረክም ፤ እያንዳንዱ አመራር የተሰጠውን ተልዕኮ ምን ያህል በብቃት እንደተወጣ፣ የፓርቲውን ፖለቲካዊ መስመር ተከትሎ በህዝብ አገልጋይነት መንፈስ መስራት አለመስራቱን እና የገጠሙንን ተግዳሮቶች የተሻገርንበትን አቅም በግልጽነትና በሃላፊነት ስሜት የምንመዝንበት ነው ብለዋል።

‎ስለዚህም ግምገማው ጥፋትን መፈለጊያ ወይም መተቻቻት ሳይሆን፤ በፓርቲያችን መርህ መሰረት እርስ በርስ መተራረምን፣ የተመዘገቡ ጠንካራ አፈጻጸሞችን አውቆ ማስቀጠልን እና ለቀጣዩ የስራ ዘመን ለህዝባችን የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ቁመና ላይ እንድንገኝ አቅም የምንፈጥርበት ወሳኝ መድረክ ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

‎በመድረኩም የ2018 ዓ/ም የመንግሥትና የፓርቲ የተግባራት አፈጻጸም ሪፖርትና የአመራር ምዘና ሰነድ በወረዳ አስተባባሪዎች እየቀረበ ሲሆን፣ የወረዳ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በንቃት እየተከታተሉ ይገኛሉ።

"ከድል ማግስት ጠንካራ መንግስት" በሚል መሪ ቃል በካፋ ዞን ጎባ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የ2018 ዓ/ም ማጠቃለያ ግምገማ እና የፑል አመራር ምዘና መድረክ ተጀምሯልበዚህ...
02/09/2026

"ከድል ማግስት ጠንካራ መንግስት" በሚል መሪ ቃል በካፋ ዞን ጎባ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የ2018 ዓ/ም ማጠቃለያ ግምገማ እና የፑል አመራር ምዘና መድረክ ተጀምሯል

በዚህ መድረክ ላይ የዞኑ ስራ ክህሎት መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ መብራቱ መሸሻ እና የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኢኒስፔክሽንና ስነ-ምግባር ምክትል ኃላፊ አቶ አጦ ወዳጆ ተገኝተዋል።

ተከታተሉን.....!

Address

Goba Wereda
Bonga
1988

Telephone

+251924416207

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Goba woreda government communication affairs office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share