Kechi Woreda Communication

Kechi Woreda Communication ዉድ የገጻችን ተከታዮቻችን ዘዉትር ተዓማንነት ያለውን የወረዳችን፣ አጎራባች ወረዳዊ፣ ዞናዊ፣ ክልላዊ፣ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ መረጃዎችን Share, Comment Like እያደረጋችሁ ስለምታበረክቱ፣ ስላበረከታችሁ አስተዋጽኦ ከልብ እናመሰግናችኋለን።

01/06/2026
ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!በኢሰራ ቶጫ ምርጫ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ዕጩ አቶ መላኩ ተረፈ ዋራ ማዘጋጃ 02 ምርጫ ጣቢያ ቀርበው ድምፃቸውን ሰጥተዋል።በለላ በኩል የዳውሮ ዞን መንግስት ምክትል...
01/06/2026

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!

በኢሰራ ቶጫ ምርጫ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ዕጩ አቶ መላኩ ተረፈ ዋራ ማዘጋጃ 02 ምርጫ ጣቢያ ቀርበው ድምፃቸውን ሰጥተዋል።

በለላ በኩል የዳውሮ ዞን መንግስት ምክትል ተጠሪ አቶ ተስፋዬ ታደሰ በዳውሮ ዞን ማረቃ-ገና ምርጫ ክልል በታርጫ ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ ምርጫ ጣቢያ ላይ ቀርቦው ድምፃቸውን ሰጥተዋል።

በዳውሮ ዞን ኢሰራ-ቶጫ ምርጫ ክልል የ7ኛው አጠቃላይ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት በሰላማዊ መንገድ እየተከናወነ ይገኛልበ7ኛው አጠቃላይ ምርጫ በዳውሮ ዞን የኢሰራ-ቶጫ ምርጫ ክልል የክልል ም...
01/06/2026

በዳውሮ ዞን ኢሰራ-ቶጫ ምርጫ ክልል የ7ኛው አጠቃላይ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት በሰላማዊ መንገድ እየተከናወነ ይገኛል

በ7ኛው አጠቃላይ ምርጫ በዳውሮ ዞን የኢሰራ-ቶጫ ምርጫ ክልል የክልል ምክር ቤት ዕጩዎችና መራጮች ድምፅ የሰጡ ሲሆን፣ ሂደቱም ሙሉ በሙሉ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ መካሄዱን ጠቁመዋል።

ክልል ምክር ቤት የብልጽግና ፓርቲ ዕጩና የዳውሮ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አስፋው ደሳለኝ እንዲሁም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የመሠረተ ልማትና የኢኮኖሚ ዘርፍ አማካሪ አቶ ታምራት ቦጋለ በኢሰራ-ቶጫ ምርጫ ክልል ከጪ ከተማ ተገኝተው ድምፅ ሰጥተዋል።

ምርጫው የዲሞክራሲ ሥርዓት ልምምድ የታየበት መሆኑን በመጠቆም ኅብረተሰቡ የሚፈልገውን የፖለቲካ ፓርቲ በነፃነት ለመምረጥና የሀገሪቱን ሁለንተናዊ ዕድገት ለማረጋገጥ ያሳየው ዲሞክራሲያዊ ተሳትፎ ትልቅ ትምህርት የሚቀሰምበት መሆኑን አስታውቀዋል።

ክልል ምክር ቤት የብልጽግና ፓርቲ ዕጩ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ባንጉ ኢትዮጵያውያን የፖለቲካ ሥልጣንን በምርጫ ካርድ ብቻ ያለምንም ግርግር ግጭትና ደም መፋሰስ መያዝ እንደሚቻል በተግባር ያሳዩበት ታሪካዊ ወቅት መሆኑንም ገልጸዋል።

በተመሳሳይ በምርጫ ክልሉ በቶጫ ከተማ ድምፅ የሰጡት የክልል ምክር ቤት ዕጩ አቶ ፍቃዱ ወ/ሩፋኤል ምርጫው እጅግ ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እየተካሄደ መሆኑን አረጋግጠዋል።

# SWMN!

አትችልም ሲባል አድርጎ ሚያሳይ ታላቅ ህዝብ አለን-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) #ኢትዮጵያ  #ኢትዮጵያእየመረጠችነው  #በምርጫብቻ  #ፋናዲጂታል
01/06/2026

አትችልም ሲባል አድርጎ ሚያሳይ ታላቅ ህዝብ አለን-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
#ኢትዮጵያ #ኢትዮጵያእየመረጠችነው #በምርጫብቻ #ፋናዲጂታል

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው።በከጪ ወረዳ በሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች ሕዝቡ ከማለዳው ጀምሮ ለ7ተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በነቂስ ወጥተው እየመረጠ ይገኛል።የተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች የመራጭ ተሳትፎ...
01/06/2026

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው።

በከጪ ወረዳ በሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች ሕዝቡ ከማለዳው ጀምሮ ለ7ተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በነቂስ ወጥተው እየመረጠ ይገኛል።

የተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች የመራጭ ተሳትፎ በምስል!

01/06/2026

Address

ዳውሮ
Bonga

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kechi Woreda Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Kechi Woreda Communication:

Share