10/09/2025
ለመላው የክልላችን ህዝቦችና ኢትዮጵያዊያን በሙሉ እንኳን ለ2018 ዓ/ም የዘመን መለወጫ በዓል በሠላም እና በጤና አደረሳችሁ !!!
የ2018 ዓ/ም የዘመን መለወጫ ስናከብር የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ተመርቆ አገልግሎት በሰጠበት ማግስትና ኢትዮጵያችን ማንሰራራት የጀመረችበት በመሆኑ ደስታችን እጥፍ ድርብ ያደርገዋል።
ውድ የክልላችን ህዝቦች አዲሱ ዓመት የሠላም ፣የፍቅር ፣ የጤና ፣የብልጽግና እና ያቀድነውን ሁሉ የምናሳካበት ዓመት እንዲሆንልን መልካም ምኞቴን በራሴና በደ/ምዕ/ ኢት/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ ስም እገልጻለው።
በጤናው ዘርፍ ማህበራዊ ብልፅግናን ለማስፈን የጤና አገልግሎት ተደራሽነት፣ ፍትሃዊነት እና ጥራትን በማረጋገጥ የእናቶችንና የህጻናትን ሞት መቀነስ፣ ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ዘርፈ ብዙ ተግባራት ትኩረት ተሰጥተው እየተሰራ ሲሆን ተግባሩም ተጠናክሮ ይቀጥላል።
ፍትሐዊ የጤና አገልግሎትን ለማዳረስ የጤና መድህን አገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋት ሰፊ ርብርብ እየተደረገ ሲሆን የመድኃኒት አቅርቦትን ለማሻሻል ከወትሮ በተለየ ስልት በ2018 ይሰራል።
በተለይም በክልላችን በወረርሽኝ መልክ የተከሰተውን የወባ በሽታ በአመራሩ ዘንድ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲመራ በማድረግ ውጤት እየተመዘገበ ሲሆን የክረምት ወቅት መውጣትን ተከትሎ የወባ በሽታ ሊጨምር ስለሚችል በየደረጃው የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ህዝባችን በማሳተፍ የመከ/መቆ/ ተግባር ተጠናክሮ ይሰራል።
ህዝባችን በበዓል ወቅት ጤናችን የሚያውኩ ከባዕድ ነገር ጋር የተቀላቀሉ የምግብ እና የምግብ ነክ ምርቶች ራሱን መጠበቅ እና በግብይት ወቅት በምርቶች ላይ ከወትሮ የተለየ ጥርጣሬ ሲኖር ለሚመለከተው አካል ጥቆማ እንዲያደርግ አሳስባለሁ።
በዓዲሱ ዓመት የአገሪቱን ከፍታ ለማረጋገጥ በትብብር፣በቅንጅት፣ በውጤታማነት፣በይቅርታና በምህረት የምንሰራበት ዓመት እንዲሆን መልካም ምኞቴን እገልፃለው።
በድጋሚ ለመላው ኢትዮጵያውያን፣ የጤና አመራሮቻችን፣ የጤና ባለሙያዎቻችን፣ የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞቻችንና የጤናው ሴክተር ቤተሰቦች እንኳን አደረሳችሁ መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልን!!!
አቶ ኢብራሂም ተማም
የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ ኃላፊ