Kafa Zone Revenue Department

Kafa Zone Revenue Department ይህ የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ ህጋዊ የፌስቡክ ገፅ ነው።

30/05/2026

#ማስታወቂያ

ግንቦት 22/2018 (የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ)

 #ማስታወቂያለካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ ለደረጃ "ለ" እና ለደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች በሙሉግንቦት 21/2018 (የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ)በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ 49/2018 በተሸጋ...
29/05/2026

#ማስታወቂያ
ለካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ ለደረጃ "ለ" እና ለደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች በሙሉ

ግንቦት 21/2018 (የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ)

በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ 49/2018 በተሸጋሸገው አንቀፅ 82 ንዑስ አንቀፅ 2 እና 4 መሰረት የደረጃ 'ለ' እና 'ሀ' ግብር ከፋዮች አመታዊ ግብራቸው 1/4ኛ ወይም 25% ቅድመ ግብር በየሩብ ዓመቱ መክፈል እንዳለባቸው ተደንግጓል፡፡

በዚህም መሰረት የግንቦት ወር ማለትም ከግንቦት 01_30/2018ዓ.ም በተሻሻለው የክልሉ ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 49/2018 መሠረት የደረጃ 'ለ' ግብር ከፋዮች 3ተኛ ዙር እንዲሁም የደረጃ 'ሀ' ግብር ከፋዮች 2ተኛ ዙር 1/4ኛ ወይም (25%) ቅድመ ግብር የሚከፈልበት ጊዜ በመሆኑ ግብር ከፋዮቻችንም በወቅቱ የሚጠበቅባቸውን 1/4ኛ ቅድመ ግብር በመክፈል ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ያሳስባል።

ለክልላችን ልማት ግብርን በታማኝነት!
የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ

ለመላው  የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛ የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ። የተከበሩ አቶ ደመላሽ ንጉሴ; የካፋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የገቢዎች መምሪያ ...
27/05/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛ የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ። የተከበሩ አቶ ደመላሽ ንጉሴ; የካፋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የገቢዎች መምሪያ ሀላፊ

ዒዱ የመተሳሰብ፣ የመረዳዳት እና ዛሬም እንደ ትላንቱ የአብሮነት እንዲሆን ምኞታቸውን በመግለፅ የሙስሊሙ ማህበረሰብ በተሰማራንበት መስክ በዞናችን የተጀመሩ ሰፋፊ የልማት ስራዎች፣ የመሰረተ ልማትና የማህበራዊ አገልግሎት ግንባታዎች ዳር እንዲደርሱ አስተማማኝ አቅም ለሆነው የገቢ ዕድገት የበኩላችንን ድርሻ በመወጣት ሊሆን ይገባል፡፡

በመሆኑም፤ ‎የንግዱ ማህበረሰብ በበዓል ወቅት የሚኖረውን ከፍተኛ የገበያ እንቅስቃሴ ተከትሎ የሚያካሂዳቸውን ግብይቶች በህጋዊ ደረሰኝ በማድረግ ግዴታና ኃላፊነትን በታማኝነት የመወጣት ልምዱን አጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል፡፡

‎ሸማቹ ማህበረሰብም ማንኛውንም ግብይት ሲፈጽም ደረሰኝ የመጠየቅና የመቀበል ልምድን በማሳደግ፣ የዞኑ ልማት የሚውለው ገቢ በትክክል ወደ መንግስት ካዝና መግባቱን በማረጋገጥ የዜግነት ድርሻውን ሊወጣ ይገባል፡፡

የዞናችን የልማትና የብልጽግና ጉዞ ሊሳካ የሚችለው የገቢ ተቋማት፣ ባለድርሻ አካላት፣ የንግዱ ማህበረሰብና ሸማቹ የህብረተሰብ ክፍል የድርሻውን ሲወጣ በመሆኑ ሁላችንም የዜግነት ግዴታና ሀላፊነታችንን በተገቢው እንድንወጣ ከአደራ ጭምር እያሳሰብን፤

‎በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የመተጋገዝ እንዲሆን እመኛለሁ፡፡

ዒድ ሙባረክ!

አቶ ደመላሽ ንጉሴ

የካፋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የገቢዎች መምሪያ ሀላፊ

የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ የ10 ወራት አፈፃፀም ግምገማ አካሂዷል።ግንቦት 15/2018 (የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ)የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ በአራት ክላስተር የተደራጀውን የታችኛው መዋቅር ...
23/05/2026

የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ የ10 ወራት አፈፃፀም ግምገማ አካሂዷል።

ግንቦት 15/2018 (የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ)

የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ በአራት ክላስተር የተደራጀውን የታችኛው መዋቅር የ10 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሂዷል።

ባለፉት 10 ወራት የተከናወኑ ዋና ዋና የሥራ ተግባራትን፣ የተመዘገቡ ስኬቶችን እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን የሚዳስስ እንዲሁም የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የገቢ ዕቅድ ለማሳካት የተከናወኑ ተግባራት ላይ ያተኮረ የግምገማ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በተያዘው በጀት ዓመት ባለፉት ወራት የታየውን ጉድለት በቀሪዎቹ ሁለት ወራት ውስጥ በማስተካከል የበጀት ዓመቱን ዕቅድ 100% ለማሳካት ቀሪ ስራዎችን በማከናወን የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ የተሻለ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚገባ ተገልጿል።

በግምገማው ወቅት በተለያዩ የገቢ አሰባሰብ እና የአገልግሎት አሰጣጥ ዘርፎች በ10 ወራት ውስጥ የተከናወኑ ሥራዎች በዝርዝር ተገምግመዋል።

በቀሪ ወራት የገቢ አሰባሰብን ለማሳደግ፣ የታክስ ከፋዮችን አገልግሎት ለማሻሻልና የተቋሙን የሥራ ቅንጅት ለማጠናከር በጋራ እንዲሰራ አቅጣጫ መቀመጡ ተገልጿል።

የሰው ሀይል እጥረት፣ የቴክኖሎጂ ውስንነት፣ የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ አቅርቦት መዘግየት፣ መብራት እና ኔትዎርክ መቆራረጥ ለገቢ አሰባሰብ ትልቅ ተግዳሮት እንደሆኑ ተገልጾ ምላሽ ልሰጠው እንደሚገባም አሳስበዋል።

በግምገማው ወቅት በአራቱም ክላስተር የመምሪያው የማኔጅመንት አባላት እና ከፍተኛ ባለሙያ፣ የገቢ ፅ/ቤቶች/ዩኒቶች ሀላፊዎች እና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ በደካ ክላስተር የ10 ወራት የገቢ እቅድ አፈጻጸም የግምገማ መድረክ በደካ ከተማ ተካሂዷል ።ግንቦት 14/2018 (የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ)‎የካፋ ዞን ገቢዎች መ...
22/05/2026

የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ በደካ ክላስተር የ10 ወራት የገቢ እቅድ አፈጻጸም የግምገማ መድረክ በደካ ከተማ ተካሂዷል ።

ግንቦት 14/2018 (የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ)

የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ በደካ ከተማ ክላስተር ከጌሻ ወረዳ፣ ከቆንዳ ወረዳና ከደካ ከተማ ከተውጣጡ የገቢዎች ባለሙያዎች ጋር የግምገማ መድረክ አካሂዷል ።

በዞኑ ገቢዎች መምሪያ በሶስቱም መዋቅር ባለፉት 10 ወራት የተከናወኑ ዋና ዋና የሥራ ተግባራትን፣ የተመዘገቡ ስኬቶችን እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን የሚዳስስ እንዲሁም የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የገቢ ዕቅድ ለማሳካት የተከናወኑ ተግባራት ላይ ያተኮረ የግምገማ ሰነድ ቀርቧል ።

በመጨረሻም በ10 ወራት የታየውን ጉድለት በቀሪዎቹ ሁለት ወራት ውስጥ በማስተካከል የበጀት ዓመቱን ዕቅድ 100% ለማሳካት ቀሪ ስራዎችን በማከናወን የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ የተሻለ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚገባ የጋራ አቅጣጫ ተቀምጦ መድረኩ ተጠናቋል ።

በመድረኩ የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ የልማት ዕቅድ አስተባባሪ አቶ መለሠ መሸሻ፣ የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ የደንበኞች አገልግሎት ባለሙያ አቶ አክልሉ ኃይለ፣የጌሻ ወረዳ፣ ገዋታ ወረዳና ከደካ ከተማ የተውጣጡ የማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል ።

ዘገባው የደካ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው

በካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት በሺሺንዳ ማዕከል የ3 ወረዳና የ2 ከተማ አስተዳደር ገቢ ጽ/ቤት የ10 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ተደርጓል።ግንቦት 14/2018 (የካፋ ዞን ገቢዎች...
22/05/2026

በካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት በሺሺንዳ ማዕከል የ3 ወረዳና የ2 ከተማ አስተዳደር ገቢ ጽ/ቤት የ10 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ተደርጓል።

ግንቦት 14/2018 (የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ)

‎የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ ግብር ህግ ማስከበር ዳይሬክቶረት አስተባባሪ አቶ መስፍን ተክሌ የ2018 በጀት ዓመት የገቢ ጽ/ቤቶች የ10 ወር ዕቅድ አፈፃፀም አቀርበዋል።

‎፩ የሰው ኃይልውጤታማነትን ለማሻሻል 100 ታቅዶ 91 ተከናውኗል።
‎፪ የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽን 57 ታቅዶ 7 ተከናውኗል።
‎፫ በ2018 በጀት ዓመት የግብር ከፋይ የተሰሩ አሰስሜንንት 4,133 ታቅዶ 853 ተከናውኗል።
‎፬ ቤት ለቤት ድጋፋዊ ክትትል 297 ታቅዶ 25 ተከናውኗል።
‎፭ የሦስተኛ ወገን መረጃ ለመስጠት 61 ታቅዶ 21 ተከናውኗል።

‎የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ የታክስ ትም/ት ኮሚንከሽንና ታክስ ቅሬታ አጣሪ ዳይሬክቶረት አስተባባሪ አቶ ክፍሌ ሰበቡ የ2018 በጀት ዓመት የገቢ ጽ/ቤቶች የ10 ወር ዕቅድ አፈፃፀም አቀርበው በቀረበው ሰነድ ዙሪያ ከቤቱ ጥያቄና አስተያዬት ቀርቦ ሰፋ ያለ ምላሽ ተሰጥቶአል።

‎አስተያዬት ከሰጡት መካከል አቶ ተረፈ ዓለሙና አቶ አሸናፍ ኃይሉ እንደተናገሩት ገቢን በአግባቡ በመሰብሰብ ሀገርን ለመገንባትና በወረዳው የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ወሣኝ ነው ብለዋል።


ዘገባው ‎የሺሾ እንዴ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ነው

የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ በአደራ ለማስቀመጥ መሟላት ያለበት ቅድመ ሁኔታግንቦት 10/2018 (የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ)ግብር ከፋዮች የንግድ ድርጅታቸዉ በልማት ምክንያት ሲፈርስ የቤት ኪራ...
18/05/2026

የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ በአደራ ለማስቀመጥ መሟላት ያለበት ቅድመ ሁኔታ

ግንቦት 10/2018 (የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ)

ግብር ከፋዮች የንግድ ድርጅታቸዉ በልማት ምክንያት ሲፈርስ የቤት ኪራይ ዉል ሲቋረጥ ወይም ድርጅታቸዉን በመዝጋት ሂደት ላይ በሚሆኑበት ጊዜ ማሽኑ በአደራ አገልግሎት ማዕከል የሚቀመጥ ሲሆን ይህንን አገልግሎት ለማግኘት ግብር ከፋዮች ከዚህ የሚከተሉትን ሟሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

1. በልማት ምክንያት የንግድ ቤት ሲፈርስ
የንግድ ድርጅት በልማት ምክንያት የፈረሰ ከሆነ የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያዉ በሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ አቅራቢ የአገልግሎት ማዕከል ዉስጥ ለ3 ወራት ድርጅቱ ተለዋጭ የንግድ አድራሻ እስከሚያገኝ ድረስ በአደራ የሚቀመጥ ይሆናል ፡፡ በመሆኑም ማሽኑ በአደራ እንዲቀመጥ ከዚህ በታች የሚዘረዘሩትን መሟላት ይኖርበታል ፡፡

•የንግድ ድርጅቱ በልማት የፈረሰ መሆኑን ከሚመለከታቸዉ አካል ደብዳቤ ማቅረብ
•ለአቅራቢዉ ማሽኑ በአደራ እንዲቀመጥ ከግብር ከፋዩ የግብር ማዕከል የተጻፈ ደብዳቤ መዉሰድ
•የተሰጠዉ ጊዜ ከማለቁ በፊት ተለዋጭ የንግድ አድራሻ ማግኘት ካልተቻለ የተሰጠዉ ጊዜ ከማለቁ በፊት ለግብር ማዕከሉ ማሳወቅ አለበት ፡፡

2.የቤት ኪራይ ዉል ሲቋረጥ
•የንግድ ድርጅቱ በዉል መቋረጥ ምክንያት ዉሉ ከፈረሰ ከዉልና ማስረጃ ደብዳቤ ማቅረብ
•ለአቅራቢዉ ማሽኑ በአደራ እንዲቀመጥ ከግብር ከፋዩ የግብር ማዕከል የተጻፈ ደብዳቤ መዉሰድ
•የተሰጠዉ ጊዜ ከማለቁ በፊት ተለዋጭ የንግድ አድራሻ በማስተካከል የአድራሻ ለዉጡን ለግብር ማዕከሉ ማሳወቅ
•ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ተለዋጭ የንግድ አድራሻ ማግኘት ካልተቻለ የተሰጠዉ ጊዜ ከማለቁ በፊት ለዋናዉ መ/ቤት ቀርበዉ ያለዉን ችግር ማመልከት እና ዉሳኔ እንዲያገኝ ማድረግ አለበት ፡፡

3የንግድ ደርጅትን ለመዝጋት በኦዲት ላይ ሲሆን የንግድ ድርጅቱን ለመዝጋት ያመለከተ ድርጅት ሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ በአደራ አገልግሎት ማዕከል የሚቀመጥ ሲሆን መሟላት ካለበት ቅድመ ሁኔታ ዉስጥ
•የንግድ ፍቃድ አዉጥቶ ሲሰራበት የነበረዉን የንግድ ድርጅት ለማዘጋት በግብር ማዕከሉ ላለ ለሚመለከተዉ አካል ጥያቄ ማቅረብ
•የንግድ ድርጅቱን ለመዝጋት ያመለከተ መሆኑን የሚገልፅና ከደንበኞች አገልግሎት የተፃፈ ደብዳቤ በግብር ማዕከሉ ላለ ለሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ቡድን ማቅረብ
•የንግድ ድርጅቱን ለመዝጋ አዲት ላይ መሆኑን ተገልጾ ሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያዉ በአደራ እንዲቀመጥ በግብር ማዕከሉ ካለ ሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ቡድን ደብዳቤ ለአቅራቢዉ መጻፍ ፡፡
ማሳሰቢያ:- በአደራ የተቀመጡ ማሽኖች በየዓመቱ መታደስ ይኖርባቸዋል።

እስካሁኑ  ከ70 ሚልዮን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል፦ የጎባ ወረዳ ገቢዎች ጽህፈት ቤትግንቦት 09/2018 ዓ.ም (የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ) በተያዘው በጀት አመት በእስካሁኑ አፈጻጸም ከ70...
18/05/2026

እስካሁኑ ከ70 ሚልዮን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል፦ የጎባ ወረዳ ገቢዎች ጽህፈት ቤት

ግንቦት 09/2018 ዓ.ም (የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ)

በተያዘው በጀት አመት በእስካሁኑ አፈጻጸም ከ70 ሚልዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን በካፋ ዞን የጎባ ወረዳ ገቢዎች ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ አሰግድ ኃይሌ በበጀት አመቱ 1መቶ ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን ተናግረዋል፡፡

ባለፉት 9 ወራት ደግሞ 75 ሚለዮን ብር ገቢ ለመሰባሰብ ከታቀደው በእስካሁኑ አፈጻጸም 79 ሚልዮን ብር በመሰብሰብ ከዕቅድ በላይ ማሳካት ተችሏል ብለዋል፡፡

በአድሱ የግብር አከፋፈል ስርዓት መሰረት ግብር ከፋዮች ግብራቸውን በወቅቱ መክፈላቸው ለአፈጻጸሙ ዕድገት አስተዋጺኦ ማበርከቱን የተናገሩት ኃላፊው የህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን ለመከታተል ግብረ ኃይል በማቋቋም የክትትልና ቁጥጥር ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ከወረዳው ግብር ከፋዮች መካከል አቶ ታደለ በቀለ እና አቶ መስፊን ማሩ በሰጡት አስተያየት ግብር ለአካባቢያቸው ዕድገት መሰረት መሆኑን በመገንዘብ በወቅቱ ግበራቸውነ እየከፈሉ መሆናቸውነ ተናግረዋል፡፡

መንግስት ግብር ከፋዮችን በማይጎዳ መልኩ የዓመቱን ግብር በ3 ዙር ከፍለው እንድጨርሱ ማመቻቸቱ እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል።

ዘገባው ቦንጋ ኤፍ ኤም 97.4 ነው

16/05/2026

የሃዘን መግለጫ!

ግንቦት 08/2018 ዓ. ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

በገቢዎች ሚኒስቴር ጅማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ በመሆን ሀገራቸውን ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ደሜ ከበደ ገጀአ ባጋጠማቸው የጤና እክል ምክንያት በሀገር ውስጥ እና ከአገር ውጭ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም ሕይወታቸው በማለፉ የገቢዎች ሚኒስቴር አመራር እና ሰራተኞች የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እንመኛለን!

አቶ ደሜ ከበደ በገቢው ዘርፍ ያላቸውን እውቀት እና የአመራር ክህሎት በመጠቀም ውጤታማ ስራ ከሰሩ አመራሮች መካከል ተጠቃሽ ነበሩ።

የአቶ ደሜ ከበደ የቀብር ስነ-ስርዓት እሁድ ግንቦት 9 ቀን 2018 ዓ.ም በጅማ ከተማ ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት የሚፈጸም ይሆናል፡፡

የወንድማችን ነፍስ በሰላም ትረፍ!

የገቢዎች ሚኒስቴር

ባለፉት 10 ወራት ከ አንድ መቶ ሰማኒያ ስድስት ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉን የጠሎ ወረዳ ገቢዎች ፅ/ቤት አስታወቀ።ግንቦት 07/2018 (የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ)የወረዳው ገቢዎች ...
15/05/2026

ባለፉት 10 ወራት ከ አንድ መቶ ሰማኒያ ስድስት ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉን የጠሎ ወረዳ ገቢዎች ፅ/ቤት አስታወቀ።

ግንቦት 07/2018 (የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ)

የወረዳው ገቢዎች ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ተሻለ ሽፈራው እንደገለፁት ባለፉት አስር ወራት ውስጥ ከ አንድ መቶ ሰማኒያ ስድስት ሚሊዮንን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉን ገልፀዋል።

ከመደበኛ ገቢ ከ171 ሚሊዮን ብር በላይ እና ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ ከ14 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል። በድምሩም ከመደበኛ እና ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ ከ186 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉን ገልፀዋል።

በወረዳው የሚገኙትን የገቢ ኮሪደሮች በመለየት የነጋዴውን ግንዛቤ በማሳደግ የገጠር መሬት መጠቀሚያ፣ የኢንቨስትመንት ገቢ፣ የስራ ግብር፣ ደራሽ ገቢ እና የበረት ገቢን በዋናነት አፅንኦት በመስጠት ባለፉት አስር ወራት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር እየተሰበሰበ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

አቶ ተሻለ አክለውም ከየትኛውም የግብር ዘመን በዘንድሮው ከፍተኛ ገቢ እንደተሰበሰበ ገልፀው የዞኑ ገቢዎች መምሪያ ሀላፊ፣ ማኔጅመንቱ እና ባለሙያዎች ያላለሰለሰ ድጋፍ እና ክትትል እንዳደረጉ በመግለፅ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በተጨማሪም የወረዳው አስተዳዳሪ፣ አስተባባሪዎች፣ ባለድርሻ አካላት እና የፖሊስ ድጋፍ የጎላ ሚና እንደነበራቸው ገልፀዋል።

እየተሰበሰቡ የቀሩ የገቢ ምንጮች እንደተለዩ በመግለፅ ከመቼውም ግዜ በላይ ርብርብ እንደሚደረግና የትኩረት አቅጣጫ እንደሆነም ተናግረዋል።

በመጨረሻም ወቅቱ ለደረጃ "ሀ" ሁለተኛ ለደረጃ "ለ" ደግሞ ሦስተኛ የግብር ወቅት እንደመሆኑ መጠን ግዜው ሳይጠናቀቅ መጥተው ግብራቸውን አሳውቀው እንዲከፍሉ እና በመጨረሻ ከሚኖር መጉላላትና አላስፈላጊ ቅጣት እና ወጪ እንዳይገቡ አሳስበዋል።

Address

BONGA, KAFA, SOUTHWEST ETHIOPIA REGION
Bonga

Opening Hours

Monday 02:30 - 17:30
Tuesday 02:30 - 17:30
Wednesday 02:30 - 17:30
Thursday 02:30 - 17:30
Friday 02:30 - 05:30
Saturday 02:30 - 17:30

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kafa Zone Revenue Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share