Kaffa Zone Revenue Department

Kaffa Zone Revenue Department ይህ የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ ህጋዊ የፌስቡክ ገፅ ነው።

ለታክስ ከፋይነት መመዝገብ ያለባቸው እነማን ናቸው?ማንኛውም ሰው ማንኛውንም የንግድ ሥራ ከመጀመሩ በፊት ቀደም ብሎ በታክስ ከፋይነት መመዝገብ ይኖርበታል። ለዚህም አስቀድሞ የተመዘገበ ካልሆነ...
27/08/2026

ለታክስ ከፋይነት መመዝገብ ያለባቸው እነማን ናቸው?

ማንኛውም ሰው ማንኛውንም የንግድ ሥራ ከመጀመሩ በፊት ቀደም ብሎ በታክስ ከፋይነት መመዝገብ ይኖርበታል። ለዚህም አስቀድሞ የተመዘገበ ካልሆነ በስተቀር በታክስ ሕግ መሠረት ታክስ የመክፈል ኃላፊነት ያለበት ሰው በባለሥልጣኑ ዘንድ ለመመዝገብ ማመልከት አለበት፡፡

• ለታክስ ከፋይነት መመዝገብ ያለባቸው …
👉 በንግድ ወይም በሙያ ሥራ (መቀጠርን ሳይጨምር) የተሰማራ ግለሰብ፣
👉 ቤት በማከራየት ገቢ የሚያገኝ ግለሰብ፣
👉 ተቀጣሪ፣
👉 የመንግሥት የልማት ድርጅት፣
👉 የመንግሥት ባለበጀት መሥሪያ ቤት፣
👉 መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣
👉 የሃይማኖት ተቋማት፣
👉 የንግድ ማህበር፣
👉 በኢትዮጵያ ነዋሪ ባልሆነ ኩባንያ በቋሚነት የሚሠራ ድርጅት፣
👉 የወጪ መጋራት ተጠቃሚዎች፣
👉 በጋራ ሃብትነት ያልተመዘገበ ሃብት ያላቸው ሰዎች፣
👉 ባለ ልዩ መብት፣
👉 በመንግሥታት መካከል የሚደረግ ስምምነት በጽሕፈት ቤት ማቋቋሚያ ስምምነት የሚቋቋም ድርጅት እንዲሁም
👉 የኩባንያ አክሲዮን ባለድርሻ ናቸው።

27/08/2026

ለታክስ ከፋይነት መመዝገብ ያለባቸው እነማን ናቸው?

ማንኛውም ሰው ማንኛውንም የንግድ ሥራ ከመጀመሩ በፊት ቀደም ብሎ በታክስ ከፋይነት መመዝገብ ይኖርበታል። ለዚህም አስቀድሞ የተመዘገበ ካልሆነ በስተቀር በታክስ ሕግ መሠረት ታክስ የመክፈል ኃላፊነት ያለበት ሰው በባለሥልጣኑ ዘንድ ለመመዝገብ ማመልከት አለበት፡፡

• ለታክስ ከፋይነት መመዝገብ ያለባቸው …

👉 በንግድ ወይም በሙያ ሥራ (መቀጠርን ሳይጨምር) የተሰማራ ግለሰብ፣
👉 ቤት በማከራየት ገቢ የሚያገኝ ግለሰብ፣
👉 ተቀጣሪ፣
👉 የመንግሥት የልማት ድርጅት፣
👉 የመንግሥት ባለበጀት መሥሪያ ቤት፣
👉 መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣
👉 የሃይማኖት ተቋማት፣
👉 የንግድ ማህበር፣
👉 በኢትዮጵያ ነዋሪ ባልሆነ ኩባንያ በቋሚነት የሚሠራ ድርጅት፣
👉 የወጪ መጋራት ተጠቃሚዎች፣
👉 በጋራ ሃብትነት ያልተመዘገበ ሃብት ያላቸው ሰዎች፣
👉 ባለ ልዩ መብት፣
👉 በመንግሥታት መካከል የሚደረግ ስምምነት በጽሕፈት ቤት ማቋቋሚያ ስምምነት የሚቋቋም ድርጅት እንዲሁም
👉 የኩባንያ አክሲዮን ባለድርሻ ናቸው።

የአውራዳ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ዩኒት የደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች የዕለት ገቢ ግመታ አፈጻጸምን ገመገመ።ነሐሴ 21/2018 (የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ) የደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች የዕለ...
27/08/2026

የአውራዳ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ዩኒት የደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች የዕለት ገቢ ግመታ አፈጻጸምን ገመገመ።

ነሐሴ 21/2018 (የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ)

የደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች የዕለት ገቢ ግመታ አፈጻጸም እንዲሁም አጠቃላይ የገቢ አፈጻጸም በዝርዝር ከአስተባባሪ አካላት ጋር ተገምግሟል።

በግምገማው ወቅት እስካሁን በተከናወኑ የገቢ ሥራዎች የተመዘገቡ ጠንካራ ጎኖችን በማጠናከር፣ በአፈጻጸም ላይ የታዩ ድክመቶችንና ተግዳሮቶችን በመለየት እና ለቀጣይ ጊዜ ተጨባጭ የሆነ የሥራ አቅጣጫ ለመያዝ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።

በተለይም የዕለት ግመታ ሥራዎች በተያዘላቸው ጊዜና መስፈርት መሠረት እንዲከናወኑ፣ የገቢ አሰባሰብ አፈጻጸም እንዲሻሻል እና የታዩ ክፍተቶች በቀጣይ ሥራዎች እንዲስተካከሉ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከአስተባባሪዎች ጋር የጋራ ውይይትና የሥራ አቅጣጫ ተወስዷል።

የግብር ከፋዮችን በተገቢው መልኩ በማገልገል፣ የገቢ አፈጻጸምን በማሻሻልና የተቋሙን የገቢ አሰባሰብ አቅም በማጠናከር የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በትኩረት እንደሚሰራ በውይይቱ ላይ ተገልጿል።

የተሻሻለው አዋጅ ስለታክስ ማጭበርበር ምን ይላል?ነሐሴ 20/2018 ዓ.ም (የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ) በተሻሻለው የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1434/2018 መሰረት “የታክስ ማ...
26/08/2026

የተሻሻለው አዋጅ ስለታክስ ማጭበርበር ምን ይላል?

ነሐሴ 20/2018 ዓ.ም (የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ)

በተሻሻለው የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1434/2018 መሰረት “የታክስ ማጭበርበር” ማለት ታክስን ለመሰወር ወይም ህጋዊ ያልሆነ የታክስ ጥቅም ለማግኘት ሲባል የሚከተሉትን ድርጊቶች መፈጸም ነው፤
👉 ሐሰተኛ የሂሳብ መዝገቦችን፣ ሰነዶችን፣ ደረሰኞችን ወይም ሌሎች ሰነዶችን ማቅረብ፣
👉 ገቢን፣ ግብይትን ወይም ታክስ የሚከፈልበትን እንቅስቃሴ መደበቅ፣
👉 ሐሰተኛ ደረሰኞችን ማዘጋጀት ወይም መጠቀም፣
👉 ሐሰተኛ የታክስ ማስታወቂያ ማቅረብ
👉 ሰነዶችን ማጥፋት፣ መቀየር፣ መደበቅ፣
👉 ከአንድ በላይ ወይም ትይዩ የሂሳብ መዛግብትን ወይም ሰነዶችን ማዘጋጀትና መያዝ፣ እንዲሁም ለታክስ ባለስልጣኑና ለሌሎች አካላት ማቅረብ፤
👉ሐሰተኛ የተቀናሽ ወጪዎችን፣ የግብር ወይም የታክስ ነፃ መብት፣ የተመላሽን ወይም የማካካሻ ጥያቄን ማቅረብ፤
👉 ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ የታክስ ግዴታን ለመቀነስ ማናቸውንም ሌሎች ድርጊቶች መፈጸም ወይም ሕግ እንዲፈፅሙ የሚያስገድዳቸውን አለመፈጸም፡፡

በአዋጁ የተሻሻሉ የታክስ ስሌቶች እና የይርጋ ጊዜ ገደብን በተመለከተ ሲገልጽ የታክስ ባለስልጣኑ የማጭበርበር ድርጊት የተፈጸመ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ያገኘ እንደሆነ የራስ ታክስ ስሌት ማስታወቂያውን ካቀረበበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 10 (አስር) ዓመት ውስጥ ሊያሻሽል ይችላል ይላል፡፡

ይሁን እንጂ በአዋጁ ንዑስ አንቀጽ 5 ላይ የታክስ ማጭበርበር ድርጊት መፈጸሙ በማስረጃ የተረጋገጠ በሚሆንበት ጊዜ የታክሱ ባለስልጣን የ10 (አስር) ዓመቱን የይርጋ ጊዜ ገደብ ሳያልፍ በማናቸውም ጊዜ የታክስ ውሳኔ ማሻሻያን ሊያደርግ እንደሚችል ይገልጻል፡፡

በገቢዎች ሚኒስቴር የተዘጋጀ

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1 ሺህ 501ኛው የነብዩ መሀመድ ልደት (መውሊድ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ! የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ!
24/08/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1 ሺህ 501ኛው የነብዩ መሀመድ ልደት (መውሊድ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ!

ለውድ የማህበራዊ ሚዲያ ተከታታዮቻችን ፡-   በማኅበራዊ_ሚዲያ፡-🌐 WhatsApp:  https://whatsapp.com/channel/0029Vb8qwRX7z4keqXuVec2s🌐 Facebook:  ...
24/08/2026

ለውድ የማህበራዊ ሚዲያ ተከታታዮቻችን

፡-
በማኅበራዊ_ሚዲያ፡-
🌐 WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029Vb8qwRX7z4keqXuVec2s
🌐 Facebook: https://www.facebook.com/kafrev
🌐 Telegram: https://t.me/kafrevn
🌐 YouTube: https://www.youtube.com/
🌐 E-MAIL: [email protected]" rel="ugc" target="_blank">[email protected]

☎️ 047 331 1141 ላይ በመደወል መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡

'ለክልላችን ልማት ገቢን በታማኝነት

24/08/2026
ተቋሙ የግብር ህግ ማስከበር ስራዎችን ውጤታማነት ለማጠናከር ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ቅንጅት በማላቅ ይሰራል - ወ/ሮ ትዕግስት በላይ ነሐሴ 16/2018 (የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ)የ...
22/08/2026

ተቋሙ የግብር ህግ ማስከበር ስራዎችን ውጤታማነት ለማጠናከር ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ቅንጅት በማላቅ ይሰራል - ወ/ሮ ትዕግስት በላይ

ነሐሴ 16/2018 (የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ)

የደምኢህክመ ገቢዎች ቢሮ የግብር ህግ ማስከበር ዘርፍ ከተቋሙ ባለድርሻ አካል ከሆኑት ከፍትህ እና ከፖሊስ ተቋማት ጋር በጋራ በሚሰሩ የግብር ህግ ማስከበር ስራዎች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

በከተሞች ላይ በተለይ የሚደረገው የታክስ ማጭበርበር ተግባራትን በመከላከል ለህብረተሰቡ የልማት መከወኛ የሚሆን ገቢ እንዳይሰበሰብ ሆን ብለው በማድረግ በየደረጃው ያሉ የገቢ ተቋማት ተግባራትን የሚያደናቅፉ አካላትን በተለዬ ትኩረት ክትትል በማድረግ ከእኩይ ተግባራቸውን ለማረም እንደሚሰራ በውይይቱ ተመላክቷል።

የቢሮው ምክትል ኃላፊና የግብር ህግ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ትዕግስት በላይ በመድረኩ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ከግብር ከፋዮች ጋር መልካም ግንኙነት እንዳለው ገልፀው ነገር ግን ሆን ብለው የታክስ ደረሰኝ በማይሰጡና የህዝብ ልማት መከወኛ የሚሆነውን ግብርና ታክስ በመሰወር እንዲሁም በአገልግሎትና ሸቀጥ ሸመታ ወቅት ሆን ብለው የታክስ ደረሠኝ በማሰጡና የህዝብ ልማት መከወኛ የሆነውን ገቢ በራሳቸው ጥገኛ ጥቅም የሚያውሉ ግለሰቦች ላይ መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ በማድረግ የግብር ህግ የበላይነት የማስከበር ስራ ይሰራል ብለዋል።

አጠቃላይ ማህበረሰቡ የግብር ህግ ተገዥነት እንዲከበር ከገቢ ተቋም ጎን እንዲቆም ጥሪ ያቀረቡት ወ/ሮ ትዕግስት በላይ ለህዝብ ሁለንተናዊ ጥቅም ሲባል ህገ-ወጥ ተግባር በሚያጋጥምበት ጊዜ ለሚመለከተው አካል ጥቆማ በመስጠት ትብብር እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

የታክስ ስሌቶች እና የይርጋ ጊዜ ገደብን በተመለከተነሐሴ 15/2018 ዓ.ም (የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ) በተሻሻለው የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1434/2018 መሰረት የተሻሻሉ ...
21/08/2026

የታክስ ስሌቶች እና የይርጋ ጊዜ ገደብን በተመለከተ

ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም (የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ)

በተሻሻለው የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1434/2018 መሰረት የተሻሻሉ የታክስ ስሌቶች እና የይርጋ ጊዜ ገደብን በተመለከተ የሚከተለውን ይላል
አግባብነት ባለው የታክስ ህግ ባለሥልጣኑ ማንኛውንም የታክስ ስሌት፡-

ሀ) የታክስ ባለስልጣኑ የማጭበርበር ድርጊት የተፈፀመ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ያገኘ እንደሆነ የራስ ታክስ ስሌት ማስታወቂያውን ካቀረበበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 10 (አስር) ዓመት ውስጥ፤ ወይም

ለ) በሌላ በማናቸውም ሁኔታ በሚከተለው የይርጋ ጊዜ ውስጥ ታክስ ከፋዩ በራሱ የሚያሰላው የታክስ ስሌት ሲሆን ታክስ ከፋዩ የራስ ታክስ ስሌት ማስታወቂያውን ካቀረበበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 5 (አምስት) ዓመት ውስጥ፣ ለሌላ ማንኛውም የታክስ ስሌት ባለሥልጣኑ ለታክስ ከፋዩ የታክስ ስሌት ማስታወቂያ ከሰጠበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 5 (አምስት) ዓመት ውስጥ ሊያሻሽል ይችላል፡፡

በገቢዎች ሚኒስቴር በታክስ ጉዳዮች ትምህርት ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ

የገቢ ስራ ልዩ ትኩረት እና የሁሉንም ድጋፍ የሚሻ በመሆኑ ሁሉም አካላት በቅንጅት ሊሠሩ እንደሚገባ ተገለጸ።ነሐሴ 14/2018 (የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ)የቦንጋ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት ኃላፊ...
20/08/2026

የገቢ ስራ ልዩ ትኩረት እና የሁሉንም ድጋፍ የሚሻ በመሆኑ ሁሉም አካላት በቅንጅት ሊሠሩ እንደሚገባ ተገለጸ።

ነሐሴ 14/2018 (የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ)

የቦንጋ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደመቀ ሀብቴ የ2019 በጀት ዓመት የገቢ ግብር ግምት አፈጻጸም እና የዕቅድ አቅጣጫዎችን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።

ኃላፊው በመግለጫቸው፣ የመንግሥት የተሻሻሉ አሰራሮችን በመጠቀም በበጀት ዓመቱ የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ትኩረት ተሰጥተው እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም መሠረት ግብር ከፋዮች የሥራ እንቅስቃሴያቸውን መሠረት ያደረገ ግምት እንዲኖራቸውና የጽሕፈት ቤቱ ማኔጅመንትም ሂደቱን በአግባቡ በመገምገም አስፈላጊውን ማስተካከያ እንዲያደርግ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መከናወናቸውን ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል በግመታ ሂደቱ ወቅት ከቴክኖሎጂና ከሲስተም አጠቃቀም ጋር ተያይዞ በውሳኔዎች ላይ መዘግየቶች መከሰታቸውን አቶ ደመቀ አመልክተዋል።

የጽ/ቤቱ ማኔጅመንት እነዚህን ችግሮች በመለየትና ክፍተቶቹን ለማስተካከል ተከታታይነት ያለ ተግባር እየተሰራ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።

በአጠቃላይ በበጀት ዓመቱ ከደረጃ "ለ" ግብር ከፋዮች ብቻ ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ ታቅዶ የነበረ ሲሆን አዳዲስ አሰራሮችን በመጠቀም የተሻለ ውጤት ለማምጣት ተግባራት ተጠናክሮ መቀጠሉን አብራርቷል።

የገቢ ሥራዎች ልዩ ትኩረትና የሎጂስቲክስ ድጋፍ የሚሹ በመሆናቸው ሁሉም አካላት በቅንጅት ሊሠሩ እንደሚገባ የገለጹት ኃላፊው፣ የገቢ ዕቅድ መሳካት የከተማው ማህበረሰብና አስተዳደሩ የሚያነሷቸውን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስና ሀብት ለመሰብሰብ ትልቅ ድርሻ እንዳለው አስገንዝበዋል።

በዚህም መሠረት በበጀት ዓመቱ በጽሕፈት ቤቱ መደበኛ ገቢ አማካይነት የጤና የትምህርትና የሌሎች ዘርፎችን ያካተተ 1 ቢሊዮን 111 ሚሊዮን 872 ሺህ 770 ብር ለመሰብሰብ ታቅዷል።

በተጨማሪም ከማዘጋጃ ቤት በኩል 295 ሚሊዮን 17 ሺህ 521 ብር ለመሰብሰብ እንደታቀደና በአጠቃላይ በዋናው መዋቅር 1 ቢሊዮን 406 ሚሊዮን 889 ሺህ 998 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሠራ ይገኛል።

ይህንንም ዕቅድ በተሳካ ሁኔታ ለማጠናቀቅ ባለድርሻ አካላት በባለቤትነት ስሜትና በተቀናጀ መንገድ እንዲንቀሳቀሱ አቶ ደመቀ ጥሪ አቅርበዋል።

Address

BONGA, KAFA, SOUTHWEST ETHIOPIA REGION
Bonga

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kaffa Zone Revenue Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share