Central Ethiopia Region Urban Development and Construction Bureau

Central Ethiopia Region Urban Development and Construction Bureau This is the Official page of Centra Ethiopia Region Urban Development and Construction Bureau.

በከተሞች የሚታየውን የሥራ አጥነት ቁጥር ለመቀነስና ሰፊ የሥራ ዕድል ለመፍጠር፣ የኢንቨስትመንት አቅምን ለማጎለበት፣ በከተሞች ልማትን ለማፋጠንና መልካም አስተዳደርን ለመገንባት፣ የንግድ ሥርዓቱን ዘመናዊ ለማድረግ ከመስከረም 2003 ዓ.ም ጀምሮ የንግድ ኢንዱስትሪ ከተማ ልማት ሴክተር ተብሎ በመጠራትና መዋቅራዊ አደረጃጀቱን እስከታችኛው መዋቅር ድረስ በማድረስ ለ5 ዓመታት ያህል በከተሞች የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን አከናውኗል፡፡
በመሆኑም ሴክተሩ በመጀመሪያው ዙር የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን የተጣሉ ግቦችን ለማሳካት ሰፊ ርብርብ በማድረግ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ ችሏል፡፡
ይሁንና በሴክተሩና በስሩ በሚገኙ

ተቋማት ላይ የሚታዩ የአደረጃጀት ክፍተቶችን በመፈተሽ በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዘመን ከመጀመሪያው ምዕራፍ ጀምሮ አዲስ አደረጃጀት በአዋጅ እንዲፈጠር ተደርጓል፡፡
በዚህም መሠረት በቀድሞ ስሙ ን/ኢ/ከ/ል/ቢሮ ተብሎ የሚጠራው አደረጃጀት የከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ ፣የንግድና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ፣ እና የኢንቨስትመንት ኮሚሽን በሚል የአደረጃጀትና የመዋቅር ለውጥ ተደርጓል፡፡
ስለሆነም ይህ ጽሁፍ በዋናነት የሚዳስሰው ከጥቅምት 16/2008 ዓ.ም ጀምሮ በአዋጅ ቁጥር 161/2008 ፀድቆ ወደ ተግባር በገባው በከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ ላይ ትኩረት በማድረግ መረጃውን ለአንባቢው እንዲደርስ ያደርጋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በተገኙበት በምስራቅ ጉራጌ ዞን በምስራቅ መስቃን ወረዳ፣ በእንሴኖ ከተማ አስተዳደር እና በማረቆ ልዩ ወረዳ ሲካሄድ የቆየውን የሰላም እና ልማት ውይ...
07/09/2026

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በተገኙበት በምስራቅ ጉራጌ ዞን በምስራቅ መስቃን ወረዳ፣ በእንሴኖ ከተማ አስተዳደር እና በማረቆ ልዩ ወረዳ ሲካሄድ የቆየውን የሰላም እና ልማት ውይይቶች ግምገማ፣ቀጣይ አቅጣጫ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በቡታጅራ ከተማ እየተካሄደ ነው

ቡታጅራ፣ ጳጉሜ 2/2018

መድረኩ በሁለቱ ህዝቦች መካከል ዘላቂ ሰላም በማረጋገጥ የወንድማማችነት እና የእህታማማችነት እሴቶች ይበልጥ እንዲጎለብት በማድረግ ረገድ የጎላ አበርክቶ እንዳለውም ተመላክቷል።

በመድረኩ የክልል፣የምስራቅ ጉራጌ ዞን፣የማረቆ ልዩ ወረዳ፣የሀገር ሸማግሌዎች ፣የሀይማኖት አባቶች እና ከየመዋቅሩ ጥሪ የተደረገላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል ሲል የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ዘግቧል።

"የኢትዮጵያ ማንሰራራት""የእምርታ ቀን"በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዱራሜ ክላስተር "እምርታ ለዘላቂ ከፍታ" በሚል መሪ ሀሳብ በግብርናው ዘርፍ እምርታዎች የመስክ ምልከታ እየተከበረ ነው።  "...
06/09/2026

"የኢትዮጵያ ማንሰራራት"

"የእምርታ ቀን"

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዱራሜ ክላስተር "እምርታ ለዘላቂ ከፍታ" በሚል መሪ ሀሳብ በግብርናው ዘርፍ እምርታዎች የመስክ ምልከታ እየተከበረ ነው።

"ያለፉት የለውጥ አመታት የማይቻሉ የሚመስሉ ስኬቶች የተመዘገቡባቸው ናቸው!"

"ይህ የእምርታ ቀን ያገኘነውን ስኬት የምናሰፋበት፣ የጎደለውን የምንሞላበት ልዩ አጋጣሚ ነው!"

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዱራሜ ክላስተር የክላስተሩ፣የከምባታ ዞንና የዱራሜ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች እና የህብረተሰብ ተወካዮች በተገኙበት "እምርታ ለዘላቂ ከፍታ" በሚል መሪ ሀሳብ "የእምርታ ቀን" በግብርናው ዘርፍ እምርታዎች የመስክ ምልከታ እየተከበረ ነው።

ዛሬ በኢትዮጵያዊያን የጊዜ አቆጣጠር ጳጉሜን 1/2018 ላይ እንገኛለን። መላው ኢትዮጵያዊ ያን ደግሞ "በእምርታ ቀን" ባለፉት አመታት በጥረት፣ በራስ አቅም በየዘርፉ ያገኟቸውን አስደናቂ እምርታዎች በልዩ ሁኔታ እየዘከሩ ይገኛሉ።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዱራሜ ክላስተርም ይሄው ሀገራዊ የእምርታ ቀን በግብርናው መስክ በተገኙ መልካም ተሞክሮዎች የመስክ ምልከታ ቀኑ እየተከበረ ይገኛል።

በክልሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የግብርናና ገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ሃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር በዚሁ ወቅት እንዳሉት ያለፉት 8 የለውጥ አመታት እንደ ሀገት የማይቻሉ የሚመስሉ ስኬቶች የተመዘገቡባቸው ናቸው ብለዋል።

"ይህ የእምርታ ቀን ያገኘነውን ስኬት የምናሰፋበት፣ የጎደለውን የምንሞላበት ልዩ አጋጣሚ ነው ሲሉም አስታውቀዋል ። ለዚህ ሀገራዊ እምርታ ትልቁ ማሳያ የግብርናው ዘርፍ ስኬቶች መሆናቸውን የገለጹት አቶ ኡስማን የበጋ ስንዴ ልማትና የሌማት ትሩፋት ስራዎች ለስኬቱ ትልቅ ማሳያዎች እንደሆኑ ገልጸዋል ።

የጉራጌ ዞን ህገ ወጥ የመሬት ወረራና ህገወጥ ግንባታን ለመከላከል የተቋቋመው አብይ ኮሚቴ በእስካሁን ስራዎች አፈፃፀም ላይ በወልቂጤ ከተማ ውይይት አካሂዷል።ቡታጅራ፣ ነሀሴ 28/2018"ውስን...
03/09/2026

የጉራጌ ዞን ህገ ወጥ የመሬት ወረራና ህገወጥ ግንባታን ለመከላከል የተቋቋመው አብይ ኮሚቴ በእስካሁን ስራዎች አፈፃፀም ላይ በወልቂጤ ከተማ ውይይት አካሂዷል።

ቡታጅራ፣ ነሀሴ 28/2018

"ውስን የሆነውን የመሬት ሀብታችንን ከህገ-ወጥ ወረራና ምዝበራ በመከላከል፣ ፍትሐዊ የከተሞች ዕድገትን እናረጋግጣለን" በሚል መሪ ቃል ህገ ወጥ መሬቶችን የመለየትና እርምጃ የመውሰድ ስራ እየተካሄደ እንደሚገኝ ይታወቃል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ጨምር ሀይሌ እንዳሉት ህገ ወጥ የመሬት ወረራ ግብረ ሀይል ተቃቁሞ መሠራቱ መሬቶች በአግባቡ እንዲተዳደሩና ከተሞች በፕላን መሰረት እንዲመሩ ያስችላል ብለዋል።

በአጭር ጊዜ ውስጥ በዞኑ ህገ ወጥ መሬት ለማስመለስ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አበረታች መሆናቸውና ውጤት እያመጡ መሆኑ ተናግረዋል።

አቶ ጨምር አክለውም በከተሞች ያሉ የግሪነሪ አካባቢዎች ከህገ ወጥ ወረራ ነጻ መሆናቸው በጥብቅ መከታተል ይገባል።

አያይዘውም በዞኑ ከህገ ወጥ መሬት ወረራ ነጻ የሆኑ ከተሞች ድጋሚ መረጃ በማጥራት ምርጥ ተሞክሮ መስራት እንሚገባ መክረዋል።

የጉራጌ ዞን የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ናስር ሀሰን እንደገለፁት በጉራጌ ዞን ያሉ ከተሞች ከህገ ወጥ የመሬት ወረራ ነጻ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

ህገ ወጥ የመሬት ወረራ የመልካም አስተዳደር ችግር የሚፈጥርና የከተሞች እድገት የሚያጨናግፍ በመሆኑ በልዩ ትኩረት እየተሰራበት ይገኛል።

በዞኑ እስካሁን 19 ከተሞች ከህገ ወጥ የመሬት ወረራ ነጻ መሆናቸው ገልጸው ይህ ደግሞ የዞኑ ማህበረሰብ ህገ ወጥነትን አጥብቆ የሚጠላ ህዝብ መሆኑ ማሳያ ነው ሲሉ አስገንዝበዋል።

ከተሞች በፕላን እንዲመሩ በማድረግ እድገታቸው እንዲፋጠን ህገ ወጥነትን መከላከል ቀዳሚ ተግባር አድርጎ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

አቶ ናስር አክለውም ከህብረተሰቡ ውይይይት ተደርጎ ተግባቦት በመፈጠሩ በስራው ትልቅ ስኬት እንዲገኝ አስችሏል ሲሉ ገልፀዋል።

የጉራጌ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ትብለጥ እስጢፋኖስ እስካሁን 6 ሄክታር መሬት እርምጃ መውሰድ ተችሏል ብለዋል።

1መቶ 38 አጥር እና 1መቶ 57 ቤቶች የተለዩ ሲሆን 93 አጥሮች እንዲሁም 30 ቤቶች ፈርሰዋል ብለዋል።

በማህበር መሬት ወስደው ያላለሙ 61 ማህበራት የተለዩ ሲሆን ለ45ቱ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል ነው ያሉት ኃላፊዋ።

በውላቸው መሰረት ያላለሙ 28 የኢንቨስትመንት መሬቶች ሲለዩ 2 ኢንቨስትመንቶች ወደ መሬት ባንክ ተመልሰዋል።

በትርፍነት ያጠሩት 7ሺ 900 ካሬ ሜትር ደግሞ ወደ መሬት ባንክ ገብቷል ሲሉ ወ/ሮ ትብለጥ አስታውቀዋል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ በአቶ ጨምር ሃይሌ የተመራ ቡድን በአረቅጥ ከተማ እየተካሄደ ያለውን የኮሪደር ልማት ስራ ጎበኙ፡፡ቡድኑ በጉብኝቱ ወቅ...
03/09/2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ በአቶ ጨምር ሃይሌ የተመራ ቡድን በአረቅጥ ከተማ እየተካሄደ ያለውን የኮሪደር ልማት ስራ ጎበኙ፡፡

ቡድኑ በጉብኝቱ ወቅት በከተማዋ እየተከናወነ ያለው የመንገድ፣የእግረኛ መንገድ፣ የመብራት፣ የአረንጓዴ ልማት፣ የውሃ ማፋሰሻ እና ሌሎች ከከተማ ውበትና ዘመናዊነት ጋር ተያያዥ የሆኑ የልማት ስራዎችን በቦታው ተገኝተው ተመልክቷል፡፡

የኮሪደር ልማቱ የከተማዋን ገጽታ በመቀየር፣ የተሽከርካሪና የእግረኞችን እንቅስቃሴ ምቹ በማድረግ፣የአካባቢ ጽዳትና ውበትን በማሻሻል እንዲሁም ለነዋሪዎች የተሻለና ምቹ የከተማ አካባቢ ለመፍጠር ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን ተገልጿል፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ጨምር ሃይሌ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት፣የኮሪደር ልማት ከተሞችን ዘመናዊ፣ ምቹና ተወዳዳሪ ለማድረግ ከሚያግዙ የልማት ስራዎች አንዱ ነው፡፡

በመሆኑም በአረቅጥ ከተማ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ስራ ጥራታቸውን፣ፍጥነታቸውንና የተያዘላቸውን መርሃ ግብር ጠብቀው መጠናቀቃቸው ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ከተማዋ የኮሪደር ልማቱን በማስፋፋት ንጹህ፣ ውብና ለመኖር ምቹ የሆነች ከተማ ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አቶ መንግስቱ ሹሜ ገልፀዋል፡፡

በተለይም በልማቱ ላይ የሚሳተፉ አካላት በቅንጅት በመስራት የተጀመሩ ስራዎች በጥራትና በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ ርብርብ እንደሚያደርጉም ጠቁመዋል፡፡

በመጨረሻም የጉብኝት ቡድኑ በስራው ሂደት የተገኙ ጠንካራ አፈጻጸሞችን በማድነቅ፣ ሊሻሻሉ የሚገባቸውን ጉዳዮች በመለየት ለቀጣይ ስራ አቅጣጫ ሰጥቷል፡፡

ቡድኑ በተጨማሪም በከተማው ከህገወጥ የመሬት ወረራ ነፃ የተደረጉና የአንድ ከተማ አንድ ማዕከል አገልግሎት አካል የሆነው የአንድ ማዕከል ቢሮ ግንባታ ጎብኝተዋል።

በከተማው ህገወጥ መሬት ወረራ ነፃ ለማድረግ በተሰራው ስራ 0.55 ሄክታር መሬት ወደ መሬት ባንክ ተመላሽ እንደተደረገ የከተማው ማዘገጃ ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ አበራ ለማ ተናግረዋል ሲል የአረቅጥ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽፈትቤት መረጃ ያመላክታል ።

‎‎ ‎የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ እና የዞኑ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ሱፐርቪዥን ቡድን በጉንችሬ ከተማ የኮሪደር ልማት ስራ ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ...
03/09/2026


‎ ‎የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ እና የዞኑ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ሱፐርቪዥን ቡድን በጉንችሬ ከተማ የኮሪደር ልማት ስራ ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ እና ህገ ወጥ የመሬት ወረራ ለመከላከል እየተሰራ ያለው ተግባር ተዟዙረው ምልከታ አደረጉ።

‎ ቡታጅራ፣ ነሐሴ 28/2018

‎ቡድኑ የኮሪደር ልማቱ በተቀመጠው ዲዛይን መሰረት በማከናወን በጥራት በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ አግልግሎት እንዲሰጥ በትኩረት መሰራት እንዳለበት ገልጿል።

‎የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ጨምር ሀይሌ እንደገለፁት ከተማዋን ለነዋሪዎች ምቹ እና ውብ ለማድረግ የኮሪደር ልማቱ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል ።

‎የጉራጌ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ትብለጥ እስጢፋኖስ እንደገለፁት የከተማው የኮሪደር ልማት ስራው በአጭር ቀናት ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆን በአጽንኦት ይሰራል ብለዋል።

‎የጉንችሬ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አ/ቋድር ሂጅራ እንደተናገሩት ከተማውን ለማሳደግ የተለያዩ መሰረተ ልማትና ግንባታዎች በማከናወን ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸው የኮሪደር ልማቱ በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

‎ሱፐርቪዥን ቡድኑ በጉንችሬ ከተማ እየታዩ ያሉ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉና የከተማውን እድገትና ውበት የሚያጎናጽፉ ስራዎች እየተሰሩ በመሆናቸው ገልጸው ፤ህብረተሰቡን በማሳተፍ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባና የኮሪደር ልማቱ በጥራትና በወቅቱ መጠናቀቅ እንዳለበት ተናግረዋል።

‎የከተማው ፕላን ለሌሎች ከተሞች ጭምር ተምሳሌት የሚሆን እንደሆነና ህገወጥ የመሬት ወረራ ለመከላከል የሚደረገው ተግባር ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው ነጻ የተደረጉ መሬቶች በተቀመጠው ፕላን መሰረት ለልማት መዋል እንዳለባቸው ገልጸዋል።

‎ቡድኑ በእለቱም በከተማው የኮሪደር ልማት አካል የሆነው የአረንጓዴ ልማት ላይ አሻራውን አሳርፏል ሲል ዘገባው የከተማው መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ነው

የከተሜነት ምጣኔ መጨመር እና የከተሞችን እድገት ማሻሻል ላይ በትኩረት መስራት ይገባል:- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) (ቡታጅራ፣ነሐሴ 28/2018)በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በ...
03/09/2026

የከተሜነት ምጣኔ መጨመር እና የከተሞችን እድገት ማሻሻል ላይ በትኩረት መስራት ይገባል:- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

(ቡታጅራ፣ነሐሴ 28/2018)በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በቀጣይ አምስት ዓመታት የከተሞችን እድገት ማሻሻል በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት በክልሉ የከተሞች እድገት በቀጣይ ዓመታት እየተሻሻለ መምጣት እንዳለበት በሀገር አቀፍ ደረጃ የጋራ ተግባቦት መፈጠሩን ተናግረዋል።

የከተሜነት ምጣኔ መጨመር እና የከተሞችን እድገት ማሻሻል ተገቢ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል።

ከተሞች ለኑሮ፣ለንግድ እና ለኢንቬስትመንት ተመራጭ በማድረግ ሂደት ያልተሟሉ ጉዳዮች መኖራቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።

ባለፉት ዓመታት ከተሞችን ለማሻሻል የተጀመሩ ስራዎች መኖራቸውን የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ ነገር ግን በሚፈለገው ደረጃ የተሟላ አለመሆኑን ጠቅሰዋል።

በክልሉ በቀጣዩ አምስት ዓመታት ሰባት ዋና ዋና ከተሞች ሊተገበሩ በታቀዱ ስራዎች ላይ የጋራ ተግባቦት መፍጠር አስፈላጊ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።

በሚቀጥሉት ዓምስት አመታት በከተሞች እድገት ላይ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት አስቀድሞ ማቀድ አስፈላጊ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ አጽንኦት ሰጥተዋል።

በመድረኩ የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች የአምስት ዓመታት ስትራቴጂክ እቅድ አቅርበው ምክክር እንደሚካሄድበት ይጠበቃል ሲል የክልሉ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ዘግቧል ።

በከተሞች የሚከሰተውን ሕገወጥ የመሬት ወረራ ለመከላከል የተቀናጀ ክትትልና ቁጥጥር ሥርዓት እንደሚጠናከር ተጠቆመ​ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም​በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የከተማ ልማትና ኮንስትራክ...
02/09/2026

በከተሞች የሚከሰተውን ሕገወጥ የመሬት ወረራ ለመከላከል የተቀናጀ ክትትልና ቁጥጥር ሥርዓት እንደሚጠናከር ተጠቆመ

​ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም​በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊና የቤቶች ልማት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ንጉሴ አቢሶ፣ ከክልሉ ከፍተኛ ባለሙያዎች፣ ከማረቆ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጀማል አማሮ፣ ከእስትሪም ኮሚቴዎችና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በከተሞች የሚከሰተውን የከተማ መሬት ወረራ ለመከላከልና የቁጥጥር ሥራውን ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

​በውይይቱ የተሳተፉት የክልሉ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም የልዩ ወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጀማል አማሮ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ የከተማ መሬት ለከተሞች ዕድገትና ለተለያዩ የልማት ሥራዎች ወሳኝ ሀብት በመሆኑ ከወረራና ከሕገወጥ ይዞታ መጠበቅ የሁሉም የጋራ ኃላፊነት ነው።

​የመሬት ወረራ ከተከሰተ በኋላ ችግሩን ከመፍታት ይልቅ፣ ወረራው ከመከሰቱ በፊት በመከላከል ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ ተመልክቷል። ለዚህም የከተማ መሬት ወሰኖችን በግልጽ መለየት፣ በአግባቡ መከለልና የመሬት አጠቃቀምን በቀጣይነት መከታተል እንደሚገባ ተጠቁሟል።

​በተለይም የመሬት ወረራ ምልክት በተገኘ ጊዜ ችግሩ ከመስፋፋቱ በፊት ፈጣን ምላሽ በመስጠትና በሕግ መሠረት ተገቢውን ርምጃ በመውሰድ የከተማ መሬትን መጠበቅ እንደሚገባ አሳስበዋል።
​የመሬት ወረራን መከላከል በአንድ ተቋም ብቻ ሊሳካ የሚችል ሥራ እንዳልሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ የክልሉ ተቋማት፣ የልዩ ወረዳው አመራሮች፣ እስትሪም ኮሚቴዎችና ሌሎች ባለድርሻዎች በቅንጅት በመሥራት የቁጥጥር ሥራውን ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባቸው ተመልክቷል።

​የመሬት ጉዳይ በትክክለኛና በወቅቱ በሚዘመን መረጃ የተደገፈ አሠራር እንዲኖረው በማሳሰብ፤ የመሬት ሁኔታን በየጊዜው በመፈተሽ፣ ለውጦችን በመለየትና ሕገወጥ ድርጊቶችን በወቅቱ በመቆጣጠር የከተማ መሬትን ከወረራ መጠበቅ እንደሚቻል ተመልክቷል።

​በውይይቱ የተሳተፉ የእስትሪም ኮሚቴዎችና ባለሙያዎች በበኩላቸው፣ የከተማ መሬትን በአግባቡ ለማስተዳደር ትክክለኛ የመሬት መረጃና ግልጽ የመሬት ወሰን መኖሩ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። በሕገወጥ መንገድ በሚያዙ የከተማ መሬቶች ላይ በሕግ መሠረት ርምጃ መውሰድና የቁጥጥር አሠራሩን ማጠናከር የመሬት ወረራን ለመግታት ወሳኝ መሆኑንም አመልክተዋል።

​በመጨረሻም በከተሞች የሚከሰቱ የመሬት ወረራ ሙከራዎችን በወቅቱ ለመለየት፣ ፈጣን ምላሽ ለመስጠትና ሕገወጥ ይዞታዎችን ለመቆጣጠር በክልልና በወረዳ ደረጃ የተቀናጀ ክትትልና ቁጥጥር ሥራ እንዲጠናከር አቅጣጫ ተያስዟል።

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በክልሉ በመንገድ ትስስር  ጥናት ላይ በጽ/ቤታቸው እየመከሩ ነው (ቡታጅራ፣ነሐሴ 27/2018)የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ...
02/09/2026

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በክልሉ በመንገድ ትስስር ጥናት ላይ በጽ/ቤታቸው እየመከሩ ነው

(ቡታጅራ፣ነሐሴ 27/2018)የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)በክልሉ የመንገድ ተደራሽነትን ለማሳደግ በተደረገ ጥናት ላይ በጽ/ቤታቸው እየመከሩ ነው

በክልሉ እያደገ የመጣ የመንገድ መሰረተ ልማት ፍላጎት ቢኖርም በሁሉም አካባቢዎች ተደራሽ በማድረግ ረገድ ያለውን ውስንነት እና ወደፊት በዘርፉ ለሚካሄድ የልማት ስራ ስኬታማነት ጥናቱ የሚኖረው ድርሻ የላቀ መሆኑም ተመላክቷል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት በክልሉ በዞኖች እና በልዩ ወረዳዎች በመንገድ መሰረተ ልማት ላይ የተካሄደው ሳይንሳዊ ጥናት የክልሉ መንግስት በዘርፉ ተግባራዊ ለሚያደርገው ስራ ምክረ ሀሳብ በማቅረብ ረገድ የጎላ አበርክቶ እንዳለው ተናግረዋል።

በክልሉ የመንገድ መሰረተ ልማት አሁን ያለበትን ደረጃ እና የመንገድ ሽፋን አመላካች መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።

ጥናቱ የክልሉ መንግስት በዘርፉ ለሚያከናውነው ሁሉን አቀፍ ልማት የእቅድ አካል ማድረግ የሚያስችል ስለመሆኑም ጠቅሰዋል።

የመንገድ ኔትወርክ ትስስር ለማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ እድገት መረጋገጥ መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑም ተጠቁሟል ሲል የክልሉ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ መረጃ ያመላክታል ።

በሀላባ ዞን ህገወጥ የመሬት ወረራንና ህገወጥ ግንባታን ለመከላከል የተቋቋመው አብይ ኮሚቴ እስካሁን በተሰሩ ስራዎችና በቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ተወያየ!!!በሀላባ ዞን ህገወጥ የመሬት ወረራንና...
01/09/2026

በሀላባ ዞን ህገወጥ የመሬት ወረራንና ህገወጥ ግንባታን ለመከላከል የተቋቋመው አብይ ኮሚቴ እስካሁን በተሰሩ ስራዎችና በቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ተወያየ!!!

በሀላባ ዞን ህገወጥ የመሬት ወረራንና ህገወጥ ግንባታን ለመከላከል የተቋቋመው አብይ ኮሚቴ በዞኑ ደረጃ እስካሁን በተሰሩ ስራዎች አፈፃፀም እና እንዲሁም በቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ያተኮረ የውይይት መድረክ በዛሬው ዕለት የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ም/ኃላፊና የካዳስተር ኤጀንሲ ዳይሬክተር አቶ ፍሬው ተዘራን ጨምሮ ከክልሉ ምደባ የተሰጣቸው አመራሮችም በተገኙበት አካሂዷል።

በመድረኩ ላይ እስካሁን ህገወጥ የመሬት ወረራንና ህገወጥ ግንባታን ከመከላከል አንፃር በእስካሁኑ ሂደት የተሰሩ ስራዎች ሪፖርት በዝርዝር የቀረበ ሲሆን በመከላከል ሂደቱ ዙሪያ ቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮችም ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።

የውይይት መድረኩን የሀላባ ዞን ም/አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሃጂ ኑርዬ እንደተናገሩት የመሬት ወረራንና ህገወጥ ግንባታ ከመከላከልና እርምጃ ከመውሰድ አንፃር እስካሁን ባለው ሂደት እየተደረጉ የሚገኙ እንቅስቃሴዎች አበረታች መሆናቸውን በመግለጽ በሁሉም መዋቅሮች ደረጃ ሂደቱን ይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

በዚህ ርብርብ ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላትና ተቋማት ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ ጠንካራ ቅንጅትን በመፍጠር አስተማሪ እና ህጋዊ ተጠያቂነት የተሞላበት እርምጃ መውሰድ እንደሚገባም አያይዘው ተናግረዋል።

የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ም/ኃላፊና የካዳስተር ኤጀንሲ ዳይሬክተር አቶ ፍሬው ተዘራ በበኩላቸው በከተማው የመሬት ወረራንም ሆነ ህገወጥ ግንባታ ለማካሄድ ጥረት በሚያደርጉ አካላት ላይ ተገቢውን እርምጃ እየወሰዱ ማረም እንደሚገባ በመግለፅ በዚህ ሂደት ላይ የክልሉ መንግሥትና ባለድርሻዎች ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ከዚህ አንፃር የተጀመሩ ንቅናቄዎችን ከግብ ለማድረስ አስፈላጊው ጥረት እንደሚደረግ ተናግረዋል።

በመድረኩ ላይ በእስካሁኑ የአፈፃፀም ሂደት ላይ ባጋጠሙ ችግሮች፣ በተወሰዱ የመፍትሔ እርምጃዎችና በቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ከአብይ ኮሚቴውና ከግብረ-ሃይል አባላት በርካታ ሀሳቦችና አስተያየቶችም የተነሱ ሲሆን ሰፊ ምክክርም የተካሄደባቸው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

ህገወጥ የመሬት ወረራን ከመከላከልና ማስቆም አኳያ እየተሰራ ያለውን ሥራ የሀዲያ ዞን አብይ ኮሚቴ ገመገመ።ቡታጅራ፣ ነሐሴ 26/2018 ዓ/ም ህገወጥ የመሬት ወረራን ለመከላከልና ለማስቆም ትኩ...
01/09/2026

ህገወጥ የመሬት ወረራን ከመከላከልና ማስቆም አኳያ እየተሰራ ያለውን ሥራ የሀዲያ ዞን አብይ ኮሚቴ ገመገመ።

ቡታጅራ፣ ነሐሴ 26/2018 ዓ/ም

ህገወጥ የመሬት ወረራን ለመከላከልና ለማስቆም ትኩረት ተሰጥቶት ወደ ሥራ መገባቱን አስመልክቶ የተቋቋመው አብይ ኮሚቴ የተሰሩ ሥራዎችን ገምግሟል።

በግምገማ መድረኩ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተወጣጡ የድጋፍና ክትትል ቡድን አባላት የተሳተፉ ሲሆን በሀዲያ ዞን ህገወጥ የመሬት ወረራን ለመከላከል የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት በዞኑ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ኃላፊ በአቶ ተሾመ አናሞ በኩል ቀርቧል።

የሀዲያ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊና ዋና የመንግስት ተጠሪ እንዲሁም የአብይ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ታምራት ግዛው እንደገለፁት ህገወጥ የመሬት ወረራን ለማስቆም የተቋቋመው ኮሚቴው ተጠናክሮ ሊሰራ እንደሚገባ ገልጸዋል።

የመሬት ወረራን ለማስቆም ከህዝብ ጋር ውይይት ተደርጎ ወደ ሥራ ከተገባ ወዲህ በርካታ ስራዎች በመሰራቱ የተመዘበሩ መሬቶችን የማስመለስ እና ህገወጥ የመሬት ወረራ እንቅስቃሴን መቀነስ እንደተቻለ ተናግረዋል።

በሀዲያ ዞን 59 ከተሞች መኖራቸውን የተናገሩት አቶ ታምራት በሁሉም ቦታ ተመሳሳይ ክትትልና ቁጥጥር መደረግ እንዳለበት እና በህገወጥ መንገድ የተያዙ መሬቶችን ወደ ባንክ በማስገባት በአግባቡ ለልማት ማዋል ይገባል ሲሉም ጠቁመዋል።

ህገወጥነትን ለማስቆም ያለምንም ልዩነት ፍትሐዊ አሰራር ተጠናክሮ መቀጠል እንዲሁም ጥቆማ በተሰጠባቸው አከባቢዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ ማጥራት እንደሚያስፈልግ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

በሆሳዕና ከተማ በተደረገው ህገወጥ የመሬት ቁጥጥር 455 ህገወጥ ቤቶች መፍረሳቸውን ከከተማው አስተዳደር በሪፖርት የቀረበ ሲሆን በቀጣይም ህገ-ወጥ የመሬት ወረራን የማስቆም ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

ከኢንቨስትመንት አኳያ ምንም ሥራ ሳይሰራባቸው ለበርካታ አመታት የቆዩ መሬቶች መኖራቸውን አንስተው በትኩረት ሊታይ እንደሚገባም ተገልጿል።

በተመሳሳይ ለተለያዩ ማህበራት የተሰጡ መሬቶች ላይም የማልማት ሥራ ያልተሰራባቸው ቦታዎች ከመመሪያው አኳያ ሊታይ እንደሚገባ ተነስቷል።

በመጨረሻም አንደ ሀዲያ ዞን 89ሄር መሬት ከህገወጥነት መመለሱንም በሪፖርቱ የተገለፀ ሲሆን ከህገ ወጥነት የነፃች ዞን ለመመስረት ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራ እንደሚገባም ተነስቷል ሲል የሀድያ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ዘግቧል።

Address

Butajira

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Central Ethiopia Region Urban Development and Construction Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share