የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ

  • Home
  • Ethiopia
  • Butajira
  • የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ, Government Organization, Butajira/Capital of East gurage zone/, Butajira.

07/09/2026
በያዝነው በጀት አመት ለአምራች ኢንደስትሪው ዘርፍ የመሬት ዝግጅትና ማስተላለፍ ተግባራትን በማጠናከር ዘርፉ የተሻለ አፈጻጸም እንዲያስመዘግብ በትኩረት ይሰራል ሲል የክልሉ የኢንቨስትመንትና ኢ...
04/09/2026

በያዝነው በጀት አመት ለአምራች ኢንደስትሪው ዘርፍ የመሬት ዝግጅትና ማስተላለፍ ተግባራትን በማጠናከር ዘርፉ የተሻለ አፈጻጸም እንዲያስመዘግብ በትኩረት ይሰራል ሲል የክልሉ የኢንቨስትመንትና ኢንደስትሪ ቢሮ አስታወቀ።

(ሆሳዕና፣ነሃሴ 28/2018)፣ በያዝነው የ2019 በጀት አመት ለአምራች ኢንደስትሪው ዘርፍ የመሬት ዝግጅትና ማስተላለፍ ተግባራትን በማጠናከር ዘርፉ የተሻለ አፈጻጸም እንዲያስመዘግብ በልዩ ትኩረት ይሰራል ሲል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የኢንቨስትመንትና ኢንደስትሪ ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው በአምራች ኢንደስትሪው ዘርፍና በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ዙሪያ ከዘርፉ መዋቅሮች ፣ ከከተማና ኮንስትራክሽን ሴክተር ተጠሪዎች፣በክልሉ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከዘርፉ ቋሚ ኮሚቴና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በወልቂጤ ውይይት አካሂዷል።

የቢሮው ሃላፊ አባስ መሀመድ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት አምራች ኢንደስትሪው የክልሉ ቁልፍ የትኩረት መስክ በመሆኑ ሴክተሩ በተቀናጀ መንገድ በመንቀሳቀስ አበረታች ውጤት እንዲያስመዘግብ ማስቻል ይጠበቅበታል። ለዚህ ዘርፍ ስኬት ትልቁ ጉዳይ የመሬት አቅርቦት በመሆኑ በትክክል ማልማት የሚችሉ ፕሮጀክቶችን በአግባቡ በመለየት ከሶስተኛ ወገን ነጻ የሆኑ መሬቶችን ለማቅረብ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

ይህም ብቻ ሳይሆን የዘርፉን ህገ ወጥ ተግባራት መቅረፍ ላይ ትኩረት እንደሚደረግ ገልጸው በየአካባቢው ኢንቨስትመንትን ለመሳብ የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎችን እንፈጥራለን ሲሉም ተናግረዋል ።

እንደ መዋቅር አሰራር መዘመን እንዳለበት የተናገሩት ዶ/ር አባስ ይህ ሲሆን አላስፈላጊ ቢሮክራሲንና ብልሹ አሰራርን ማስቀረት ይቻላል ሲሉም አክለዋል።

በክልሉ በየአካባቢው ልዩ የኢንደስትሪ ዞኖችን የማስፋፋት፣ድጋፍና ማበረታቻዎችን የማጠናከር ተግባራት ትኩረት የሚሹ እንደሆኑ አስታውቀዋል ።

ሴክተሩ ከከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን በተለይም ከከንቲባና ማዘጋጃ ጋር ጠንካራ ቅንጅት የመፍጠር ፣የክልሉን የላይዘን ኦፊስ በመጠቀም የኢንቨስትመንት አማራጮችን የማስተዋወቅና ተሞክሮዎችን የማስፋት ተግባራት ትኩረት አድርጎ ይሰራል ነው ያሉት የቢሮ ሃላፊው።

በክልሉ አዋጭ በሆኑ የግብርና ኢንቨስትመንቶች የሚሰጠው ትኩረት እንዳለ ሆኖ ቅድሚያ ለታላላቅ አምራች ኢንደስትሪዎች ይሰጣል ሲሉም አክለዋል።

የቢሮው ምክትልና የኢንዱስትሪ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ደምሰው ባቾሬ በበኩላቸው ዘርፉ በ2019 በጀት አመት የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘግብ ዘንድ የመሬት አቅርቦትን ማጠናከር ይገባል ብለዋል። በክልሉ ሼዶችን ወደ ምርት የማስገባት ስራ እንደሚጠናከር ገልጸው ለዚህም የሃይልና የፋይናንስ አቅርቦት ተደራሽነትና ላይ በቅንጅት እንደሚሰራ አብራርተዋል ።

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን የማስፋትና ማጎልበት ተግባራት የዘርፉ ተቀዳሚ ግብ እንደሚሆንም አስታውቀዋል ።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ለዘርፉ ስኬት የሃይልና ፋይናንስ አቅርቦት፣ የዘርፉን ማነቆዎች መፍታት፣የፕሮጀክቶች ክትትል፣ የፕሮሞሽን ስራዎች ፣የማሽነሪ አቅርቦት፣ የኢንደስትሪ ዞኖች ማቋቋም፣በማያለሙ ባለሀብቶች ላይ ጠንካራ እርምጃ የመውሰድ እና ዘርፉ አመርቂ የስራ እድል እንዲፈጥር ማስቻል ላይ ትኩረት መደረግ እንዳለበት አንስተዋል።

በውይይት መድረኩ የወልቂጤ፣ወራቤና ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲዎች ተወካዮች ተገኝተዋል ።

በዳውድ አብደላ

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር ) ከቻይናዉ ሁዋዬ ማዕድን ማዉጣትና ፕሮሴሲንግ ካምፓኒ ጋር በጋራ መስራት በሚቻልባቸዉ ሁኔታዎች ላይ ምክክር አደረጉሆሳዕና ፣ ነሐሴ 28 ፣ 2018 ...
03/09/2026

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር ) ከቻይናዉ ሁዋዬ ማዕድን ማዉጣትና ፕሮሴሲንግ ካምፓኒ ጋር በጋራ መስራት በሚቻልባቸዉ ሁኔታዎች ላይ ምክክር አደረጉ

ሆሳዕና ፣ ነሐሴ 28 ፣ 2018 ፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር ) ከቻይናዉ ሁዋዬ ማዕድን ማዉጣትና ፕሮሴሲንግ ካምፓኒ ጋር በጋራ መስራት በሚቻልባቸዉ ሁኔታዎች ላይ ዛሬ በጽህፈት ቤታቸዉ ምክክር አድርገዋል።

ካምፓኒዉ በተለይም በሴራሚክስ ማምረት ስራ ያካበተዉን ልምድ መነሻ በማድረግ በክልሉ ለሴራሚክስ ኢንዳስትሪ በሚሆኑ ግበዓቶች ዙሪያ የካምፓኒው ባለቤትና ስራ አስኪያጅ ሚስተር ሊ ሺሚንግ ከክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ ጋር በዝርዝር ተወያይተዋል።

ካምፓኒዉ በክልሉ የዉጭ ቀጥተኛ ኢንቬስትመንትን ለማበረታታትና ለመሳብ በተቋቋመዉ የላይዘን መስሪያ ቤት አማካኝነት ቀደም ሲል በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች ተንቀሳቅሶ የመስክ ምልከታ በማድረግ ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸዉን ማረጋገጡ ተመልክቷል።

በክልሉ ምቹ የሆነ የአምራች ኢንደስትሪ ስነ ምህዳር በመፍጠር ዘርፉን ለማጎልበት በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን የኢንቨስትመንትና ኢንደስትሪ ቢሮ ገለጸ። (ሆሳዕና፣ነሃሴ 28/2018)፣ በክል...
03/09/2026

በክልሉ ምቹ የሆነ የአምራች ኢንደስትሪ ስነ ምህዳር በመፍጠር ዘርፉን ለማጎልበት በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን የኢንቨስትመንትና ኢንደስትሪ ቢሮ ገለጸ።

(ሆሳዕና፣ነሃሴ 28/2018)፣ በክልሉ የተለያዩ ከተሞች የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን በተጠናከረ ሁኔታ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም አስታውቋል ።

በክልሉ ምቹ የሆነ የአምራች ኢንደስትሪ ስነ ምህዳር በመፍጠር ዘርፉን ለማጎልበት በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የኢንቨስትመንትና ኢንደስትሪ ቢሮ ገልጿል።

ቢሮው በአምራች ኢንደስትሪ ልማት ዙሪያ ከሴክተሩ መዋቅሮችና ባለድርሻ አካላት ጋር በወልቂጤ ውይይት እያካሄደ ነው።

የቢሮው ሃላፊ አባስ መሀመድ (ዶ/ር) የክልሉ መንግሥት ዘርፉን ለማሳደግ ፖሊሲና ስትራቴጂ ነድፎ በልዩ ሁኔታ ከሚንቀሳቀስባቸው ዘርፎች ውስጥ የአምራች ኢንደስትሪው ግንባር ቀደም መሆኑን ጠቁመዋል ።

ለዚሁ ስኬት ሰፊ መዋለ ንዋይ በመመደብ፣ለግል ባለሀብቱ ምቹ ስነ ምህዳር በመፍጠር ፣የብድርና ግብኣት አቅርቦትን በማመቻቸት ረገድ የተለያዩ ተግባራት በመከናወን ላይ ናቸው ብለዋል።

የዘርፉን የሰው ሃይል አቅም በመገንባትና አሰራሩ በቴክኖሎጂ እንዲደገፍ በማድረግ በኩልም ሰፊ ጥረት መደረጉን የቡሮ ሃላፊው አስታውቀዋል ።

ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ምቹ ሁኔታን ከመፍጠር ባለፈ የመሬት አቅርቦትን ማጠናከር እንደሚገባ ጠቁመው በክልሉ ተጨባጭ ሁኔታ ለዘላቂ ልማት ቁልፉ መሳሪያ አምራች ኢንደስትሪ በመሆኑ ለዘርፉ ልዩ ትኩረት መሰጠቱን ተናግረዋል ።

የኢንደስትሪ እውቀትን ማጎልበት ይገባል ያሉት ዶ/ር አባስ ለዚህ ስኬት የዩኒቨርሲቲዎች ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል።

ለዘርፉ እድገት የመሬትና የሃይል አቅርቦትን ማሳደግ፣አገልግሎትን ማዘመን፣የሰው ሃይል፣መሰረተ ልማት ና ፋይናንስን አቅርቦትን ማጎልበት እንደሚገባም ገልጸዋል ።

የቢሮው ምክትልና የኢንዱስትሪ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ደምሰው ባቾሬ በበኩላቸው
እንደ ክልል 620 ለሚሆኑ የኢንደስትሪ ባለቤቶች የኢንደስትሪ መሬት መተላለፉን ገልጸው ከእነዚህ ውስጥ 154 የሚሆኑት ወደ ምርት ሂደት ገብተዋል ብለዋል።

164 የሚሆኑ ኢንደስትሪዎች ደግሞ በግንባታ ሂደት ላይ ሲሆኑ 78 የሚሆኑት ደግሞ የሼድ ግንባታ ማጠናቀቃቸውን ተናግረዋል ። እነዚህ ኢንደስትሪዎች ወደ ተሟላ የማምረት ሂደት እንዲሸጋገሩ የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።

በቀጣይም በክልሉ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የኢንደስትሪ መሬት አቅርቦትን ለማስፋት በትኩረት እየተሰራ ሲሆን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በዘርፉ ቴክኖሎጂ ሽግግር ና ፈጠራ ሚናቸውን እንዲወጡ በትኩረት እንደሚሰራ አስታውቀዋል ።

በክልሉ በዚህ አመት በተለያዩ ከተሞች የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን በባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ና ትብብር በተጠናከረ ሁኔታ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም አስታውቀዋል ።

በዚሁ መሰረት በክልሉ በ2019 በጀት አመት በሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በልዩ ትኩረት በየደረጃው እንደሚካሄድ አስታውቀዋል ።

በዳውድ አብደላ

ነሀሴ 28/2018 አ.ም ወልቂጤየክልሉ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ "በእውነት  የሚመራ ፣በምርምር የሚያድግ ፣በፈጠራ የሚወዳደር አምራች ኢንዱስትሪ እንፈጥራለን ።"በሚል መሪ ቃል ...
03/09/2026

ነሀሴ 28/2018 አ.ም ወልቂጤ
የክልሉ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ "በእውነት የሚመራ ፣በምርምር የሚያድግ ፣በፈጠራ የሚወዳደር አምራች ኢንዱስትሪ እንፈጥራለን ።"በሚል መሪ ቃል የሚመለከታቸው የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ባሳተፈ መልኩ በወልቂጤ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው። የስልጠናና የውይይት መድረኩ አስከ ነገ ነሀሴ 29/2018 አ .ም የሚቆይ ይሆናል።

28/08/2026

መስተዳድር ምክር ቤቱ ዛሬ በካሄደዉ ስብሰባ በተለያዩ አጃንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል፣

ሆሳዕና ፣ ነሐሴ 22፣ 2018 ፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት፣ መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ በካሄደዉ መደበኛ ስብሰባ፦ በቀረቡለት የኢንቨስትመንት ልማት ፕሮጀክቶች ጥያቄዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፤ በገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ደንብ ላይም ተወያይቶ ደንቡን አፅድቋል።

መስተዳድሩ ምክር ቤቱ በቀረቡለት አስራ ሦስት የኢንቬስትመንት ልማት ፕሮጀክቶች ጥያቄዎች ላይ በዝርዝር በመወያየት እና በፕሮጀክቶቹ አስፈላጊነት ላይ መግባባት በመፍጠር ፕሮጀክቶቹ ወደ ልማት እንቅስቃሴ እንዲሸጋገሩ ወስኗል።

ከቀረቡት አስራ ሶስት የኢንቬስትመንት ልማት ፕሮጀክቶች ጥያቄዎች መካከል ዘጠኙ በኢንዱስትሪ ፣ ሁለቱ በግብርና የተቀሩት ሁለቱ ደግሞ በአገልግሎት ዘርፎች ለመሠማራት የተዘጋጁ መሆናቸዉ ተጠቁሟል።

ከኢንቬስትመንት ልማት ፕሮጀክቶቹ መካከል ሶስቱ የዉጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንቶች መሆናቸዉም ተጠቅሷል ።

መስተዳድር ምክር ቤቱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 32/2016 ማስፈፀሚያ ደንብ ላይም ተወያይቷል፤ ደንቡ ቀደም ሲል የወጣዉን የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 32/2016 ለማስፈጸም አስፈላጊ መሆኑ ተብራርቷል።

መስተዳድር ምክር ቤቱ በደንቡ ላይ በዝርዝር ከተወያየ በኋላ አፅድቋል።

24/08/2026

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )ለታላቁ ለነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) 1501ኛ የልደት በዓል / መውሊድ
የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

የመልዕክቱ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል

ለታላቁ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) 1501ኛ የልደት በዓል / መውሊድ በዓል እንኳን አደረሳችሁ!

ለእስልምና እምነት ተከታዮች ! እንኳን ለነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) 1501ኛ የልደት በዓል / መውሊድ በዓል አደረሳችሁ! እያልኩ መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ ።

ኢትዮጵያዉያን ሀገራዊ የምከክር ጉባኤያቸዉን በተሳካ ሁኔታ ባጠናቀቁበት እና ሀገራችን ኢትዮጵያም አብሮነትን፣አንድነትን እና ብሔራዊ መግባባትን ወደሚያፀና፣ አዲስ ምዕራፍ እየተሸጋገረች በምትገኝበት በአሁኑ ወቅት እየተከበረ የሚገኘው የዘንድሮዉ የነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) የልደት በዓል / የመውሊድ በዓል የወንድማማችነት /የእህትማማችነት እሴቶችን ከፍ ለማድረግ መልካም አጋጣሚ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ።

መልካም የመዉሊድ በዓል!

እንኳን ደስ አላችሁ!!የክልሉ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በ2018 በጀት አመት ከመካከለኛ ክልሎች በዕቅድ አፈጻጸም፣ በአሰራር ስርአት እና በኢትዮጵያ ታምርት የተሻለ ውጤት በማስመ...
24/08/2026

እንኳን ደስ አላችሁ!!
የክልሉ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በ2018 በጀት አመት ከመካከለኛ ክልሎች በዕቅድ አፈጻጸም፣ በአሰራር ስርአት እና በኢትዮጵያ ታምርት የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ ሶስተኛ ደረጃ በመውጣት ከፌደራል ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የዕውቅና ምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል፡፡
እንኳን ደስ አለን! እንኳን ደስ አላችሁ!!

ባለፉት ሦስት ዓመታት በክልሉ ለኢንቨስትመንት ልማት በተሰጠው ልዩ ትኩረት አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተመሠረተበት ነሐሴ/2015 ዓሠተ ምህረት ጀምሮ በክልሉ...
23/08/2026

ባለፉት ሦስት ዓመታት በክልሉ ለኢንቨስትመንት ልማት በተሰጠው ልዩ ትኩረት አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተመሠረተበት ነሐሴ/2015 ዓሠተ ምህረት ጀምሮ በክልሉ ኢንቨስትመንትን በማስፋፋት በዘርፉ የዜጎች ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በትኩረት በመሠራቱ አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡

በክልሉ የሚገኙ እምቅ ሀብቶችን፣ የኢንቨስትመንት አማራጮችንና ዕድሎችን፣ እና በህግ አግባብ የተፈቀዱ የቀረጥ ነጻ፣ የገቢ ግብር እፎይታ እና ልዩ ልዩ ማበረታቻዎች አሰጣጥ ያካተተ የኢንቨስትመንት ፖቴንሺያል ጋይድ ቡክሌት ክልሉ በተመሠረተ በአጭር ጊዜ ጥቅምት ወር 2016 ዓ/ም መዘጋጀቱ ለዘርፉ መነቃቃት አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡

የክልሉን እምቅ የኢንቨስትመንት አቅምና ዕድሎችን ይበልጥ ለማስተዋወቅና በዘርፉ የሚሰጠውን አገልግሎት ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ የውጭ ኢንቨስትመንት ማስተባበሪያ ቢሮ በአዲስ አበባ ተከፍቶ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ሌላው ለክልሉ ኢንቨስትመንት ዕድገት የተወሰደ ጉልህ እርምጃ ነው፡፡

ክልሉ በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በማዕድን፣ በአገልግሎትና በመሳሰሉ ዘርፎች ያለውን ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢ ከማስተዋወቅ በሻገር በክልሉ ለዘመናት የተገነባውን የሕዝቦች አንድነትና አብሮነት እሴትን በመጠቀም ዘላቂና አስተማማኝ ሠላም ግንባታን የክልሉ ቀዳሚ አጀንዳ ተደርጎ በመሠራቱ የመጣው ውጤትም ለኢንቨስትመንትና ቢዝነስ ሥራ እንዲሁም ለቱሪዝም ኢንዱስትሪ መነቃቃት የላቀ ሚና አበርክቷል፡፡

በየትኛውም የኢንቨስትመንት ዘርፍ ተቀጥረው መሥራት የሚችሉ ከፍተኛና መካከለኛ ሙያ ያላቸውን ሥራ ወዳድና ታታሪ ዜጎችን በማያቋርጥ ሁኔታ የሚያፈራ ክልል መሆኑ እንዲሁም ክልሉ ለማዕከላዊ ገበያ ያለው ቅርበት የግል ባለሀብቶች በክልሉ በስፋት ኢንቨስት እንዲያደርጉ ምክንያት ሆኗል፡፡

በኢንቨስትመንት ዘርፍ ይስተዋሉ የነበሩ የመልካም አስተዳደርና የቢሮክራሲ ችግሮችን ለመፍታት ትኩረት በመሰጠቱ እንዲሁም በክልሉ ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜ በፍጥነትና በጥራት አጠናቅቆ ለአገልግሎት ማብቃት አዲስ ባህል መገንበቱ ሌላው ለኢንቨስትመንት የተፈጠረ ምቹ ሁኔታ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

በዚህም ክልሉ ከተመሰረት በኋላ ማለትም ከ2016 እስከ 2018 በጀት ዓመት ባሉት ጊዜያት ውስጥ ወደ ክልሉ ከገቡት 326 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ውስጥ 271 ያህል ፕሮጀክቶች ከሦስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት ነፃ ሆነው መሬት ተረክበዋል፡፡

በ2018 በጀት ዓመት ብቻ በግብርና፣ በኢንዱስትሪና በአገልግሎት ዘርፎች 291 አዳዲስ ፈቃዶች የተሰጡ ሲሆን 257 ፈቃዶች ታድሰዋል። በተጨማሪም 39 የፈቃድ ለውጥ እና 2 የማስፋፊያ ፈቃድ ሥራዎች ተከናውነዋል። በተሰጡት ፈቃዶች 21.1 ቢሊየን ብር ካፒታል የተመዘገበ ሲሆን እነዚህ ፕሮጀክቶች ሲተገበሩ ለ43,283 ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል ይፈጥራሉ።

በክልሉ ከ5.1 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገበውን ብሉ ኤሌፋንት ፋይበር ቦርድ ማኑፋክቸሪንግ ፕሮጀክትን ጨምሮ በሆቴል፣ በግብርና ማምረትና ማቀናበር፣ በጨርቃ ጨርቅና በመሳሰሉት ዘርፎች ግዙፍ ኢንቨስትመንቶች በፍጥነት ወደሥራ በመግባት በዘርፋ ብዙ ፋይዳቸው የክልሉን እድገት እያፋጣኑ ይገኛል፡፡

በቀጣይ የውጭ ኢንቨስትመንት በተለይም በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ በስፋት እንዲገቡ ማድረግ እንዲሁም ታሪካዊና ባህላዊ ቅርሶችን ወደ ኢንቨስትመንት ሀብትነት ለመቀየር በትኩረት እየተሠራ እንደሆነ ከክልሉ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡

23/08/2026

Address

Butajira/Capital Of East Gurage Zone/
Butajira

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ:

Shortcuts

Share