Haqa Beekuu

Haqa Beekuu Gov

01/01/2026

"ዘመናዊ ወጣት" ነህ ወይስ “ዘመናዊ ለማኝ”⁉️
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
(በፈላስፋው ጭሰኛ)

iPhone 15 ይዘህ የቤት ኪራይህን እናትህ የምትከፍል ከሆነ… እራስህን አታምታታ! ኪስህ ባዶ፣ ስልክህ ግን የ100 ሺህ ብር? ይሄ ዘመናዊነት ሳይሆን “የኢኮኖሚ እብደት” ነው።

👇 ከዚህ “የይስሙላ ኑሮ” (Fake Life) ለመውጣት እነዚህን 4 መራራ እውነቶች ዋጥ አድርጋቸው፦

1. ስልክህ “ስማርት” ሆኖ፣ አንተ “ፋራ” አትሁን!
ወርሃዊ ገቢህ 5,000 ብር ሆኖ የ50,000 ብር ስልክ ከያዝክ፣ አንተ የኢኮኖሚ ወንጀለኛ ነህ። ስልክህ የመግባቢያ መሳሪያ እንጂ የወንድነት መለኪያ አይደለም።

2. እቃ (Liability) አትሰብስብ፣ ንብረት (Asset) ገንባ!
ስልክህ፣ ጫማህና ልብስህ ዛሬ ገዝተህ ነገ ዋጋቸው ይቀንሳል። ወንድ ልጅ መጀመሪያ መሬት፣ ወርቅ፣ ወይም ንግድ (“Asset”) ይገነባል፤ ከዚያ በትርፍ ገንዘቡ ይዘንጣል። ገና ሳትቆም አትሩጥ!

3. ሰዎችን ለማስደመም አትኑር!
ለማያውቁህ እና ለራስህ ችግር ደንታ ለሌላቸው ሰዎች ብለህ ውድ ጫማ አትግዛ። “ሰው ምን ይለኛል” ብለህ የምትከፍለው ዋጋ፣ የድህነት ዋጋ ነው። ለራስህ ኑር!

4. ዛሬን በልተህ፣ ነገን አትጹም!
“ወጣትነት አንድ ጊዜ ነው፣ ልዝናናበት” የሚለው የሰነፎች መፈክር ነው። ዛሬ ተቀማጥለህ ነገ ልጆችህ ድሃ እንዲሆኑ እየፈረምክ ነው። ጀግና ወንድ ዛሬን መስዋዕት አድርጎ ነገን በነጻነት ይኖራል።

⚠️ የጭሰኛው ማስጠንቀቂያ…

ወንድሜ… ከውጭ ያማረ፣ ከውስጥ ባዶ የሆነ ትውልድ ሀገር አይረከብም! የስልክ ኩባንያዎችን ከማክበር፣ ራስህን አክብር።

🗣 ለራሱ ቃል የሚገባ ጀግና ብቻ ኮሜንት ላይ ይጻፍ…

🔥 አንተ የትኛው ነህ?

ከዚህ “የይስሙላ ኑሮ” ወጥተህ እውነተኛ ሀብት ለመገንባት ከወሰንክ፣ ዝም ብለህ አትለፈው!
1. Like በማድረግ የስምምነት ድምፅህን አሰማ። 👍

2. Comment ላይ “እቃ አልሰበስብም፣ ንብረት እገነባለሁ!” ብለህ ለራስህ ቃል ግባ። 💬

3. Share በማድረግ ይሄንን እሳት ለተኛው ወዳጅህ አቀብለው! ይንቃበት! 🔗

ጭሱ ከኔ፣ እሳቱ ከአንተ! 🔥

©️ ጦማሪው ፈላስፋው ጭሰኛ ኦሪጅናል ሀሳቦች✍️

🚫 ምንጭ ሳይጠቅሱ መውሰድ የተከለከለ ነው።

#ኢትዮጵያ #ሐበሻ #ፍልስፍና #ገንዘብ #ድህነት #ወጣት

31/12/2025

7ቱ የመሪነት ጥበብ (Leadership Skills)

1⃣ ስትራቴጅካዊ አስተሳሰብ (Strategic Thinking) - የመሪ ትልቁ ጥበብና ልዩነት ዛሬ ላይ ቆሞ ነገን ማየት አለበት ። አምስት አስርትና ረዥም አመታትን ማየት !

2⃣ ውጤት ተኮርነት (Result Oriented) - የሚሰራውን ሥራ ሁሉ መሬት በማውረድ በውጤት መለካት ጥበብ ።

3⃣ ለውጥን መምራት ( Change Management) - ዓለም ቴክኖሎጂ በየቀን በየቅዝበት እየተቀየረ ይገኛል፣ በዚህ ልክ ለውጥን መምራት ። አንድ አንዱ ለውጥ የማይፈልግ አለ፣ መሪው ግን በጥበብ መምራት አለበት።

4⃣ መፍትሄ አመንጪነት (Problem Solving ) - ችግርና ምክንያት ከመደርደር መፍትሄ በማፍለቅ የተቆለለ የማህበረሰብ ችግሮችን መፍታት።

5⃣ አሳታፊነትና ውክልና መስጠት (Empowerment & Delegation) - ሁሉንም ሥራ መሪ ብቻ አይሰራም ፣ በሥሩ ያሉ ሰዎችን መወከል በጋራ መትጋት የተሻለ ውጤት ያመጣል። Delegation inspiration decentralization...

6⃣ ስሜታዊ ብልህነት ( Emotional intelligence) - ራስን ማወቅ የሌሎችን ስሜት መረዳት በመረዳዳት መምራት።

7⃣ ተከታታይ ትምህርት ( Continuous Learning) - ሁሉንም አውቃለሁ ከማለት ይልቅ በየቀኑ ከዓለም ባህል ፣ ከትናንት ስህተት ፣ ከአከባቢ ከሁኔታው በመማር በስልጠና ራስን በማብቃት ማህበረሰብን በእውቀት ለማገልገል መዘጋጀት ይጠበቃል ። ትህትና ፣ ፍቅር ፣ አብሮነት፣ እኔ ሳይሆን እኛ የኔ ሳይሆን የእኛ ማለት ከመሪ ይጠበቃል ። Don't say I instead say We !

በአጠቃላይ በየመስኩ ያለን ሁላችንም የተሰጠንን ኃላፊነት በአመራር ጥበብ፣ በአደራ መንፈስ፣ መልካም አሻራ ጥለን ለማለፍ ዘወትር የበኩላችንን ድርሻ መወጣት ያስፈልጋል ።

20/07/2023

Ani qooda koo ba'eera isin hoo?

12/05/2022

Maal wayyaa laata?

Koronaan nu fixuuf
01/06/2020

Koronaan nu fixuuf

27/09/2019
14/06/2019
NAMA DHIBA
19/11/2018

NAMA DHIBA

Namatu qabeenyaa Kenya irraa buuqqanaan .....
25/09/2018

Namatu qabeenyaa Kenya irraa buuqqanaan .....

Address

Oromia
Dambi
KELEM WOLLEGA

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Haqa Beekuu posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category