Dangila Ketema Communication

Dangila Ketema Communication This page states that to address day to day activities of dangila town

ሁሉም በየአካባቢው ያለውን ትንኮሳ በአስቸኳይ በማስቆም ወደ ሰላማዊ ውይይትና  ምክክር እንዲመለስ ርእሰ  መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ጥሪ አቀረቡ።ባሕር ዳር: ሐምሌ 26/2015 ዓ.ም...
02/08/2023

ሁሉም በየአካባቢው ያለውን ትንኮሳ በአስቸኳይ በማስቆም ወደ ሰላማዊ ውይይትና ምክክር እንዲመለስ ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ጥሪ አቀረቡ።

ባሕር ዳር: ሐምሌ 26/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) በመግለጫቸው ስለሰላም አማራጭ ያነሷቸው ነጥቦች፦

👉የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥ ያለውን ችግር በሰላምና በውይይት ለመፍታት አሁን መረባረብ ይገባል፡፡

👉 የክልሉ የፀጥታ ችግር መንስኤ የኾኑትን በውይይት መፍታት አለብን።

👉የሰላም ጉዳይ በክልሉ ምክር ቤትም አቋም ተወስዶ ተመራጮች በአካባቢያቸው ውይይት እያደረጉ መኾናቸውንም ገልጸዋል፡፡

👉ማንኛውም ችግር በውይይት እና በሰላማዊ መንገድ ቢፈታ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ሰብዓዊ ኪሳራን ማስቀረት ይቻላል ነው ያሉት፡፡

👉 የሰላም ዋጋው ከፍተኛ ስለኾነ ሁሉም ጥያቄ አለኝ የሚል ወገን ሁሉ ያለምንም ገደብ በየደረጃው እየተወያየ ችግሩን ለመፍታት መረባረብ ይገባል፡፡

👉ከውይይት ውጭ ያለው ሂደት ክልላዊ ኪሳራ ከማምጣት ውጭ መፍትሔ እንደማያመጣም ተናግረዋል፡፡

👉ሁሉም ልዩነት ያለው አካል ነፍጡን አስቀምጦ ወደ ሰላማዊ ውይይት በመመለስ፣ በየደረጃው ወደ ተቋቋመው፣ የሀገር ሽማግሌ፣ የሃይማኖት አባት፣ የሕዝብ ተወካዮች፣ ወጣቶችና ሌሎች አካላት ጋር ውይይት እያደረገ ችግሩ የሚፈታበትን አቅጣጫ ነድፎ መረባረብ ይገባዋልም፡፡

👉ለሰላም ዘብ በመቆም ልዩነታችንን አቻችለን፣ የሕግ የበላይነትን አስከብረን ችግሮቻችንን መፍታት ይገባናል፡፡

👉ሊመጣ የሚችለውን ክልላዊ ጉዳት አስቀድሞ በማሰብ አሁኑኑ ለሰላም መረባረብ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

👉አሁን ላይ በአንዳንድ አካባቢ ያለው ትንኮሳ እያደረ ሲሄድ ክልላዊ አለመረጋጋትና ሥርዐት አልበኝነት እንደሚፈጥርም ገልጸዋል፡፡

👉ክልሉን ለበለጠ አደጋ የሚጥል በመኾኑ ችግሩን የክልሉ ሕዝብ እንዲገነዘበውም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

👉 ከችግር መውጣት አዳጋችና ከባድ መኾኑን ከሌሎች መማር እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

👉እርስ በእርስ መገዳደል ለውጥ አላመጣልንም ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ ሰላማዊ አማራጭን በመከተል ችግሩ እንዲፈታም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

👉ለሰላም ሁሉም እንደሚያገባው የተናገሩት ርእሰ መሥተዳድሩ በየአካባቢው ያለውን ትንኮሳ በአስቸኳይ በማቆም ወደ ሰላማዊ ውይይት፣ ምክክር እንዲመለስ እና ክልሉ የተረጋጋ ኾኖ እንዲቀጥል ጥሪዬን አስተላልፋለሁ ብለዋል፡፡ ዘገባው የአሚኮ ነው።

የዳንግላ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት  "ትምህርት ለትውልድ"በሚል መሪ መልዕክት የንቅናቄ መድረክ አካሄዷል።ዳንግላ፡ ሀምሌ 25/2015ዓ.ም (ዳንግላ ከተማ ኮሙኒኬሽን) የዳንግላ ከተማ...
01/08/2023

የዳንግላ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት "ትምህርት ለትውልድ"በሚል መሪ መልዕክት የንቅናቄ መድረክ አካሄዷል።

ዳንግላ፡ ሀምሌ 25/2015ዓ.ም (ዳንግላ ከተማ ኮሙኒኬሽን) የዳንግላ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የ2015ዓ.ም የትምህርት ዘመን በትምህርት ዘርፉ ጥራት አስተዋፅኦ ላበረከቱ "ትምህርት ለትውልድ" በሚል መሪ መልዕክት የእውቅና እና የምስገና እንዲሁም የንቅናቄ መድረክ አካሄዷል።

በንቅናቄ መድረኩ የዞንና የከተማ አመራሮች፣ባለድርሻ አካላት እንዲሁም አጋር አካላት ተገኘተዋል።

የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አለልኝ በላይ የጽ/ቤቱን ሪፓርት በማቅረብ የመድረኩ አላማ በትምህርተ አመቱ ለትምህርት ጥራት መሻሻል አስተዎፅኦ ግለሰቦች፣ ተቋማት እና ከየትምህርት ቤቱ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ዕውቅና በመስጠት በቀጣይም ከዚህ በላይ እንዲሰሩ ኃላፊነት ለመስጠትም ጭምር መሆኑን ጠቁመዋል።

የዳንግላ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይርጋለም ዳኘው ትምህርት ሁለንተናዊ ለውጥ የምናመጣበት ቁልፍ ተግባር በመሆኑ ለትምህርት ጥራት ትኩረት መስጠት ይጠይቃል ሲሉ ተናግረዋል።

በመድረኩም በከተማዋ የሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች፣ ለትምህረት ቤቱ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ መምህራንና ርዕሳነ መምህራን፣ ሱፐር ቫይዘሮች፣የግል ተቋማት፣ የዕውቅናና የምስክር ወረቀት ተበረክቶላቸዋል።

በዳንግላ ከተማ አሥተዳደር ከ78 ሚሊዮን ብር በላይ  ወጪ የተደረገባቸው መሠረተ ልማቶች ግንባታቸው ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት ኾኑ።እንጅባራ: ሐምሌ 23/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በዳንግላ ከ...
30/07/2023

በዳንግላ ከተማ አሥተዳደር ከ78 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው መሠረተ ልማቶች ግንባታቸው ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት ኾኑ።

እንጅባራ: ሐምሌ 23/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በዳንግላ ከተማ አሥተዳደር በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ78 ሚሊዮን ብር በላይ በኾነ ወጪ ግንባታቸው የተጠናቀቁ 31የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ኾነዋል።

የጌጠኛ ድንጋይ ንጣፍ ፣የጎርፍ ማፋሰሻ ዲች ፣ የወጣቶች የሥራ እድል መፍጠሪያ ሸዶች፣የጠጠር መንገድ ግንባታ፣ የቢሮ ግንባታና መለስተኛ የንጹህ መጠጥ ውሃ ጥልቅ ጉድጓዶች ግንባታቸው ተጠናቀው ለአገልግሎት ከበቁ መሠረተ ልማቶች መካከል ይገኙበታል።

ለፕሮጀክቶቹ ማስፈጸሚያ ከዓለም ባንክ፣ከክልሉ መንግሥት ድጋፍና ከኀብረተሰቡ ተሳትፎ የተገኘ ከ78 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበታል ተብሏል።

የዳንግላ ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ሙሉቀን በዙ የተጠናቀቀው በበጀት ዓመት የመንግሥት፣የልማት አጋር ድርጅቶችንና የኀብረተሰቡን አቅም አቀናጅቶ በመጠቀም የነዋሪዎችን የመሠረተ ልማት ጥያቄ ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት የተደረገበት እንደነበር ገልጸዋል።

የተገነቡ መሠረተ ልማቶች የከተማዋን እድገት የሚያፋጥኑና የኢንቨስትመንት ፍሰትን የሚጨምሩ መኾናቸውንም ምክትል ከንቲባው ተናግረዋል።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አሥተዳዳሪ አቶ እንግዳ ዳኛው ግንባታቸው ተጠናቀው የተመረቁ መሠረተ ልማቶች በችግሮች ሳንወሰን የኀብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የማንታክት መኾናችንን ማሳያ ናቸው ብለዋል።

የከተሞችን ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ ለልማት ማነቆ የኾኑ የመልካም አሥተዳደር ችግሮችን እና ሥርዓት አልበኝነትን መታገል ወቅቱ የሚጠይቀው ጉዳይ ነው ያሉት ዋና አሥተዳዳሪው ኀብረተሰቡ ለሠላም ዘብ ሊቆም እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የዳንግላ ከተማ ነዋሪዎችም የተገነቡ መሠረተ ልማቶች የነዋሪዎችን ዘርፈ ብዙ ችግሮች የሚያቃልሉ መኾናቸውን ተናግረዋል።

ለመሠረተ ልማቶች ግንባታ አቅማቸው የፈቀደውን ሁሉ ሲደግፉ መቆየታቸውን የገለጹት ነዋሪዎቹ ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ እንክብካቤ እንደሚያደርጉላቸውም ተናግረዋል።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ማጠቃለያም በመሠረተ ልማት ግንባታ ወቅት አስተዋጽዖ ለነበራቸው ግለሰቦችና ተቋማት ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል። ዘገባው የአሚኮ ነው።

በዳንግላ ከተማ አስተዳደር በ2015ዓ.ም የተሰሩ መሰረት ልማቶቾ የምረቃ ስነ-ስርአት  እየተካሄደ ነው።
30/07/2023

በዳንግላ ከተማ አስተዳደር በ2015ዓ.ም የተሰሩ መሰረት ልማቶቾ የምረቃ ስነ-ስርአት እየተካሄደ ነው።

ፍኖተ ብርሃን ኮሌጅ ለ3ተኛ ዙር በተለያየ የትምህርት ዘረፍ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመርቋል።ዳንግላ: ሀምሌ 22/2015ዓ.ም (ዳንግላ ከተማ ኮሙኒኬሽን) በዳንግላ ከተማ አስተዳደር ፍኖተ ...
29/07/2023

ፍኖተ ብርሃን ኮሌጅ ለ3ተኛ ዙር በተለያየ የትምህርት ዘረፍ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመርቋል።

ዳንግላ: ሀምሌ 22/2015ዓ.ም (ዳንግላ ከተማ ኮሙኒኬሽን) በዳንግላ ከተማ አስተዳደር ፍኖተ ብርሃን ኮሌጅ በዛሬው ዕለት በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ከ2012ዓ.ም ጀምሮ በዲግሪና በዲፕሎማ ያሰለጠናቸውን 206 (ሁለት መቶ ስድስት) ተማሪዎችን አስመርቋል።

የኮሌጁ ፕሬዝዳንት አቶ ተመስገን ይመኑ ኮሌጃችን ከ2012ዓ.ም ከትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ባገኘው የእውቅና ፈቃድ በዲግሪ ፕሮግራም በሦስት የትምህርት ክፍልና በዳፕሎማ ፕሮግራም በአንድ የትምህርት ከፍል ሰልጣኞችን ተቀቦሎ ሲያሰለጥን ቆይቷል ብለዋል። በ2015ዓ.ም በዲግሪ በቀንና በማታ ፕሮግራም በ5 የትምህርት ክፍሎች በዲፕሎማ ፕሮግራም በቀንና በማታ በ8 የትምህርት ክፍል በአጠቃላይ በ13 የትምህርት ክፍሎች በማስተማር ላይ ይገኛል ያሉት አቶ ተመስገን ኮሌጃችን አድማሱን በማስፍት በሞጣ ከተማ ቁጥር 2 ካፓስ ከፍቶ ተማሪዎችን እያሰለጠ ይገኛል ብለዋል። በመጨረሻም በኮሌጅ ከፍተኛ ውጤት አምጥተው ለተመረቁ ሶስት ተማሪዎች በኮሌጁ ወጭ ነፃ የማስተርስ (Ms)ዲግሪ የትምህርት እድል የሚሰጥ መሆኑንና በኮሌጅ በመምህርነት እንዲያገለግሉ የስራ ዕድል ያመቻቸ መሆኑን ገልፀዋል። በመጨረሻም አቶ ተመስገን ውድ እጩ ተመራቂ ተማሪዎቻችን እንኳን ለዛሬዋ የተቀደሰች የምርቃት ቀናችሁ አደረሳችሁ አደረሰን በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የዳንግላ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ በምረቃት ስነ-ስርዓቱ ተገኝተው ትምህርት ለአንድ ሀገር እድገትና ብልፅግና አስተዋፅኦው ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል። ም/ከንቲባው ተመራቂዎች ስራ ፈላጊዎች ሳይሆን ስራ ፈጣሪዎች በመሆን ለሀገራችሁ ኢኮኖሚ የበኩላችሁን አስተዋፅኦ እንድታደርጉ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በምረቃ ስነ-ስርዓቱም ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ሽልማት አበርክቶ ፕሮግራሙ በሰላም ተጠናቋል።

ፍኖተ ብርሃን ኮሌጅ በዳንግላ ከተማ በዛሬው ዕለት  ለ3ተኛ ዙር በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያስለጠናቸውን ተማሪዎች የምርቃ ስነ-ስርዓት እያካሄደ ነው ።
29/07/2023

ፍኖተ ብርሃን ኮሌጅ በዳንግላ ከተማ በዛሬው ዕለት ለ3ተኛ ዙር በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያስለጠናቸውን ተማሪዎች የምርቃ ስነ-ስርዓት እያካሄደ ነው ።

በወቅታዊ የከተማዋ የፀጥታ ጉዳይ ላይ የከተማ አስተዳደሩ  የታክሲ/ባጃጅ አሽከርካሪዎች ጋር ጥልቅ ውይይት አካሄዷል።ዳንግላ፡ ሀምሌ 21/2015ዓ.ም(ዳንግላ ከተማ ኮሙኒኬሽን) የዳንግላ ከተማ...
28/07/2023

በወቅታዊ የከተማዋ የፀጥታ ጉዳይ ላይ የከተማ አስተዳደሩ የታክሲ/ባጃጅ አሽከርካሪዎች ጋር ጥልቅ ውይይት አካሄዷል።

ዳንግላ፡ ሀምሌ 21/2015ዓ.ም(ዳንግላ ከተማ ኮሙኒኬሽን) የዳንግላ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባና የፀጥታ አካላት በወቅታዊ የከተማዋ የፀጥታ ጉዳይ ላይ ከባጃጅ አሽከርካሪዎች ጋር ጥልቅ ውይይት አካሄደዋል።

በውይይቱ ተጠርጣሪዎች ምርመራው ሳይጠናቀቅ መለቀቅ፣የተሰረቁ ያሉ ባጃጆች የሚሸጡበት ከተማ እየታወቀ ወደ መፍትሔው አለመገባቱ፣ የምርመራ ሂደቱ ትክክል አይደለም፣የባጃጅ ማህበሩ ችግሩን በቶሎ አለማሳወቁና ወደ መፍትሔ አለመግባቱ፣የህግ አስከባሪዎች ህግን በአግባቡ አለማስከበር፣የስዓት ገደብ አለመከበሩ፣የፀጥታ ሀይሉ የተሟላ የመንግስት መገለጫ ዩኒፎርሙን ሳያሟላ ትጥቅ በመያዝ መንቀሳቀስ፣አንዳድ ባጃጆች የባጃጅ ማህበሩ አባል አለመሆናቸው፣የሀሳብ /ጥቆማ መስጫ ሳጥን አለመዘጋጀቱ እና የኬላ ፍተሻና ጥበቃ የተቀናጀ አለመሆኑ የሚሉና ሌሎችም ጥያቄዎች ከባጃጅ አሽከርካሪዎች ተነስተዋል።

የከተማ አስተዳደሩ የህዝብ ሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ምህረት አያሌውጰ በተፈፀመው ዘረፍና ግድያ በእጅጉ አዝነናል ነገር ግን ይህን ለማስቆም ሁላችንም የየድርሻችን መወጣት ይኖርብናል የባጃጅ አሽከርካሪ ወንጀለኞችን ጥቆማ መስጠት፣የወንጀሉ ተባባሪ አካላትን ለይቶ ማውጣት፣ የባጃጅ አሽከርካሪዎች ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በመቀናጀት ጠንካራ የመረጃ መለዋወጫ መዘርጋት፣ጫት ቤቶችና አልጋ ቤቶች ላይ የተቀናጀ ስራ መስራት ይጠበቅብናል፣ፀጉረ ልውጦችን ስንይዝ እርምጃ ከምንወስድ ይልቅ ለህግ ማቅረብ ይኖርብናል ሲሉ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ጠቁመዋል። አቶ ምህረት በከተማች የሚታየውን ዘረፊና ግድያ ለማስቆም ህብረተሰቡ ከፀጥታ ኃይላችን ጋር አንድ በመሆን መስራት ይኖርብናል ሲሉ አሳስበዋል።

የዳንግላ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይርጋለም ዳኛው በከተማች አሁን ላይ እየተባባሰ የመጣው የባጃጅ ስርቶትና ግድያ አሰፈሪ አስደንጋጭ ነው ተራ ስርቶትም አይደለም የተራጀ ዝርፊያና አሰቃቂ ግድያ ነው ሚሞትም የሚገድልም የእኛው ሰው ነው ብለዋል። አቶ ይርጋለም ይህን ለማስቆም አመራሩ መውሰድና ማስተካከል ያለበትን ወስዶ ያስተካክላል የከተማዋ የፀጥታ ኃይል፣አመራሩ፣ማህበረሰቡና አሽከርካሪው በመተባባር ወንጀሉን ማስቆም ይኖረብናልሲሉ ጠቁመዋል።በስሜት የሚወሰዱ እርምጃዎች መረጃን ከማጥፋት ባሻገር ለከተማዋ ገፅታም ቢሆን ጥሩ አይደለም ሲሉ መደገም እንደሌለበት አሳስበዋል።

የከተማ አስተዳሩ ም/ከንቲባ ሙሉቀን በዙ በደረሰው ጉዳት አዝነናል ከሰሞኑን የተፈጠረው ነገር አንዴ ተፈጥሯል መደገም የለበትም ትክክልም አይደለም ሲሉ አሳስበዋል። አስገዳጅ ነገር ካልሆነ በቀር 2:00 ሰዓት ውጭ ሲያሽከረክር የተገኘ እርምጃ ይወሰድበታል፣ የፀጥታ ኃይሉ የተዥጎርጎረ/ስርዓቱ ያልጠበቀ አለባበስ የለበሰ የፀጥታ አካል እንዳይኖር አቅጣጫ አስቀምጠናል፣ በማንኛውም ሰዓት መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፣ ሌባና ወንበዴ የምታንቀሳቆሱ የባጃጅ አሽከርካሪዎችን መለየት ይኖርብናል፣ለይስሙና የምትንቀሳቀሱ የባጃጅ አሽከርካሪዎች ልትስተካከሉ ይገባል፣ ሁሉም የባጃጅ አሽከርካሪዎች የባጃጅ ማህበሩ አባል በመሆን ወንጀሉን ማስቆምና በጊዜ መድረስ ይኖርብናል ሲሉ ተናግረዋል። መስራት፣ መለወጥ እና ውጤታማ ለመሆን ከውሸትና ከወሬ መቆጠብ ይኖርባችኋል ሁላችሁም ባትሆኑም ከታሪፍ ዎጭ ማስከፈል፣ታርጋን በማንሳት የምታሽከረክሩ ፣ያለመንጃ ፈቃድ የምታሽከረክሩና፣ ከመርሀ ግብር ውጭ የምትሰሩ ከዚህ ድርጊታችሁ ሊትቆጠቡ ይገባል ያሉት ም/ከንቲባው በመጨረሻም የጉዳዮን አሳሳቢነት በመረዳት ከዛሬ ጀምሮ የተቋቋመ የፀጥታ ግብረ ሀይል አለ ሁላችሁም መረጃን አጠናክራችሁ በመስጠትና ከጎናችን በመሆን የገጠመንን አስፈሪ ችግር መፍታት ማስቆምና ከምንጩ ማድረቅ ይኖርብናል ሲሉ ም/ከንቲባው አሳስበዋል።

ለጤና ባለሙያዎች የኮሌራ ወረርሽኝ የግንዛቤ ፈጠራ  እየተሰጠ መሆኑ ተገለፀ።ዳንግላ፡  ሀምሌ19/2015ዓ.ም(ዳንግላ ከተማ ኮሙኒኬሽን)  የዳንግላ ከተማ አስተዳደር ጤና አጠባበቅ ጣበቢያ ለጤ...
26/07/2023

ለጤና ባለሙያዎች የኮሌራ ወረርሽኝ የግንዛቤ ፈጠራ እየተሰጠ መሆኑ ተገለፀ።

ዳንግላ፡ ሀምሌ19/2015ዓ.ም(ዳንግላ ከተማ ኮሙኒኬሽን) የዳንግላ ከተማ አስተዳደር ጤና አጠባበቅ ጣበቢያ ለጤና ባለሙያዎች የኮሌራ ወረርሽኝ የግንዛቤ ፈጠራ እየተሰጠ ነው።

የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ጤና መምሪያ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ምላሽ ሰጭ ባለሙያ አቶ የኔው አላምረው የኮሌራ ወረርሽኝ በጊዜ ከተደረሰበት መግታት የሚቻል ሲሆን ይህ ካልሆነ ግን በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ መሆኑን ተናግረዋል። አቶ የኔው የበሽታው ምልክቶች ራስ ምታት፣ማስመለስ/ማቅለሽለሽ፣የሚያጣድፍ ተቅማጥ፣የሰውነት መዛልና የቆዳ መሸብሸብ ናቸው ሲሉ ጠቁመዋል። አቶ የኔው አያይዘውም ወረርሽኙ የሚተላለፍባቸው መንገዶች፦የተበከለ ውሃና ምግብ ፣ የአካባቢን ንፅህና አለመጠበቅ እና በወረርሽኙ የተያዘን ሰው ጋር ንክኪ የሚተላለፍ ሲሆን የመከላከያ መንገዱም ንፅህናው የተጠበቀ ምግብና ውሃ መጠቀም ፣በበሽታው የተያዘ ሰው ጋር ንክኪ አለማድረግ፣የአካባቢን ንፅህና መጠበቅ እና በቀብር ጊዜ ጥንቃቄ ማድረግ መሆኑን አቶ የኔው አስረድተዋል።

የዚህን ወረርሽኝ እንዳይስፋፋ ለማድረግ ለማህበረሰቡ የራሱንና የአካባቢዉን ንፅህና እንዴት መጠበቅ እንዳለበት ሰፊ ግንዛቤ መፍጠር እና ሁሉም ተቋማማት በመቀናጀት በጋራ መስራት ይኖርበታል ሲሉ ተናግረዋል።

ወድ የፔጃችን ተከታታዮቾ ሀምሌ 15/11/2015ዓ.ም በለቀቅነው መረጃ መሰረት ማክሰኞ ማለትም በ18/11/2015ዓ.ም በከተማ አስተዳደሩ የተሰሩ መሰረተ ልማቶች እንደሚመረቁ የገለፅን ቢሆንም...
26/07/2023

ወድ የፔጃችን ተከታታዮቾ ሀምሌ 15/11/2015ዓ.ም በለቀቅነው መረጃ መሰረት ማክሰኞ ማለትም በ18/11/2015ዓ.ም በከተማ አስተዳደሩ የተሰሩ መሰረተ ልማቶች እንደሚመረቁ የገለፅን ቢሆንም በስራ መደራረብ ምክንያት ወደ ሀምሌ 23/11/2015ዓ.ም የተሸጋገረ መሆኑን የዳንግላ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሠረተ ልማት ጽ/ቤት አሰታውቋል።

የዳንግላ ከተማ አስተዳደር  ትምህርት ጽ/ቤት የ2015ዓ.ም  የ12ተኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎችን  ወደ መፈተኛ ዩኒቨርስቲ ሽኝት አደረገ።ዳንግላ፡ ሀምሌ 17/2015ዓ.ም (...
24/07/2023

የዳንግላ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የ2015ዓ.ም የ12ተኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎችን ወደ መፈተኛ ዩኒቨርስቲ ሽኝት አደረገ።

ዳንግላ፡ ሀምሌ 17/2015ዓ.ም (ዳንግላ ከተማ ኮሙኒኬሽን) የዳንግላ ከተማ አስተዳደር 2015ዓ.ም የ12ተኛ ክፍል ሀገራቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ዩኒቨርስቲ በዛሬው ዕለት ሽኝት ማድረጉን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ጽ/ቤት አስታውቋል።

የከተማ አስተዳደሩ ትምህት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለልኝ በላይ ከፊታችን ረቡዕ ሀምሌ 19/2015ዓ.ም ጀምሮ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ግሽ አባይ ካፓስ የመጀመሪያ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ወንድ=393 ሴት=409 በድምሩ=8መቶ ሁለት ተማሪዎች የ2015ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተናውን እንደሚወስዱ ተናግረዋል። ፈተናውም ከሀምሌ19-21/2015ዓ.ም እንደሚቆይና በቀጣይ ዙር ከሀምሌ 25-28/2015ዓ.ም የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች እንደሚፈተኑ ገልፀዋል። ኃላፊው ተማሪዎች በሰላም መሸኘታቸውን ገልፀው ለዳንግላ ከተማ አስተዳደር፣ትራንስፓርት ተጠሪ ጽ/ቤት፣ሰላምና ደህንነት እንዲሁም ለፓሊስ ጽ/ቤት ላደረጉት ትብብር ምስጋናቸውን አቅርበዋል። አቶ አለልኝ ለተፈታኝ ለተማሪዎች መልካም የፈተና ጊዜ እንዲሆንላቸው ምኞታቸውን ተገልፀዋል።

የዳንግላ ከተማ አስተዳደር ትራንስፓርት ተጠሪ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይርጋለም ጥላሁን እንደተናገሩት ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ዩኒቨርሲቲ ለማድረስ በቂ ተሽከረካሪ ስምሪት የተሰጠ መሆኑንና ተማሪዎች በሰላም ደርሰው እንዲመለሱ ጽ/ቤቱ በአሽከርካሪና ተሽከርካሪዎች ላይ ተገቢውን ቁጥጥር ያደረገ ሲሆን የተማሪ ወላጆችም ከስጋት ነፃ እንዲሆኑ አቶ ይርጋለም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው።ባሕር ዳር: ሐምሌ 16/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በዛሬው እለት  ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የተመደቡ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲ...
23/07/2023

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው።

ባሕር ዳር: ሐምሌ 16/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በዛሬው እለት ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የተመደቡ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው በመግባት ላይ መሆናቸውን ከዩኒቨርሲቲው የተገኘው መረጃ ያመላክታል። ዘገባው የአሚኮ ነው

የ2015በጀት አመት መሠረተ ልማቶች በወቅቱ መጠናቀቃቸውን የዳንግላ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሠረት ልማት ጽ/ቤት ገለፀ።ዳንግላ፡15/2015ዓ.ም (ዳንግላ ከተማ ኮሙኒኬሽን)የ2015 በጀት ...
22/07/2023

የ2015በጀት አመት መሠረተ ልማቶች በወቅቱ መጠናቀቃቸውን የዳንግላ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሠረት ልማት ጽ/ቤት ገለፀ።

ዳንግላ፡15/2015ዓ.ም (ዳንግላ ከተማ ኮሙኒኬሽን)የ2015 በጀት አመት መሠረተ ልማቶች በወቅቱ መጠናቀቃቸውን የዳንግላ ከተማ አስተዳደር ከተማ መሠረት ልማት ጽ/ቤት ገልጿል።

የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አበበ መንግስቱ በዚህ በጀት አመት 6 የማፋሰሻ ቦይ ግንባታ፣3 የጌጠኛ መንገድ፣2 መለስተኛ ጥልቅ የውሃ ጉድጓድና 5 የእጅ ውሃ ጉድጎድ፣13 ነባር የገጠር መንገድ ጥገና፣ አንድ ብሎክ ባለ16 ክፍል የቢሮ ግንባታና አንድ ብሎክ ባለ9 ክፍል የሼድ ግንባታና፣ 3 አዲስ የጠጠር መንገድ እና ሌሎችንም ጨምሮ በዚህ አመት የተከናወኑ ተግባራት መሆናቸውን ኃላፊው ተናግረዋል።

ኃላፊው እንዳሉት ይህ ተግባር ሲከናወን ከአለም ባንክ፣ ከክልል ድጓማና ከከተማ ገቢ በአጠቃላይ 78,014,990.28(ሰባ ስምንት ሚሊዮን አስራ አራት ሺ ዘጠኝ መቶ ዘጠና)ብር በጀት በመያዝ ተግባሩ የተከናወነ ሲሆን ካለፈው አመት በተሻለ ጥራትና በወቅቱ ማጠናቀቅ መቻሉን ገልፀዋል።

አቶ አበበ በመጨረሻም እነዚህ መሠረተ ልማቶች በመጭው ማክሰኞ ሀምሌ 18/2015ዓ.ም ከተለያየ ቦታ የሚመጡ ተጋባዥ እንግዶች፣ የከተማና የቀበሌ አመራሮች እንዲሁም የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት የሚመረቅና ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ተናግረዋል። ህብረተሰቡም የተሰሩ መሠረት ልማቶችን በእኔነት ስሜት እንዲጠብቅና እንዲንከባከብ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

Address

Bahir Dar
Dangila
0660

Telephone

+251960532295

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dangila Ketema Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Dangila Ketema Communication:

Share