Janamora Communications

Janamora  Communications የጃናሞራ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የወረዳውን ህብረተሰብ የመረጃ ተጠቃሚ ማድረግ ነው።

‎በሂውማን ካፒታል ኦፕሬሽን ( ) በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በህፃናት ዕድገት ክትትልና ማበልፀግ ዙሪያ ለጤና ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው።‎‎ነሃሴ 27/2018 ዓ.ም‎‎የጃናሞራ ወረዳ ጤና...
02/09/2026

‎በሂውማን ካፒታል ኦፕሬሽን ( ) በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በህፃናት ዕድገት ክትትልና ማበልፀግ ዙሪያ ለጤና ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው።

‎ነሃሴ 27/2018 ዓ.ም

‎የጃናሞራ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት በሂውማን ካፒታል ኦፕሬሽን ዓለም ባንክ (HCO) ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ እድሜያቸው ከሁለት አመት በታች ለሆኑ ህፃናት እድገት፣ ክተትል እና ማበልፀግ (Growth Monitoring &Revitalatio / አስመልክቶ ስልጠና እየሰጠ መሆኑን አስታውቋል።

‎በስልጠናው የቀበሌ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችና የጤና ጣቢያዎች የስርአተ ምግብ ተጠሪዎች ተሳትፈዋል።

‎ስልጠናው ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ እነደሆነም ከጽ/ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

‎የጃናሞራ ወረዳ ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም የእቅድ አፈጻጸም እና የ2019 ዓ.ም እቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄደ።‎‎ነሃሴ 26/2018 ዓ.ም‎‎የሁሉም ቀበሌዎች ...
01/09/2026

‎የጃናሞራ ወረዳ ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም የእቅድ አፈጻጸም እና የ2019 ዓ.ም እቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄደ።

‎ነሃሴ 26/2018 ዓ.ም

‎የሁሉም ቀበሌዎች ስራ አስኪያጅ ባለሙያዎችና የሴቶች ጉዳይ ሃላፊዎች በተገኙበት የ2018 ዓ.ም የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።

‎ባለፈው በጀት አመት የነበሩ ጠንካራ ውስንነቶች ላይ ከሪፖርቱ በመነሳት ተሳታፊዎች ሃሳብ አስተያየት አንስተዋል።

‎የተቋሙ ተግር እጅክ ሰፊና የብዙ ባለድርሻ አካላት ቅንጅትና ትብብር የሚፈልግ በመሆኑ ተሳታፊዎች ወደ ቀበሌው ወርደው በጋራ መስራት እንደሚገባቸው የጽ/ቤቱ ሃላፊ ወ/ሮ ዘነብ ወረት ተናግረዋል።

‎የባለፈውን አመት የአፈጻጸም ሪፖርት መነሻ በማድረግ በቀጣይ መሰራት ያለባቸውን ያሏቸውን ነጥቦች የገለጹት ሃላፊዋ ትኩረት ለሚሹ የማህበረሰብ ክፍሎች የሚሰጠውን አካታች አገልግሎት አሰጣጥና እኩልነት ከማስከበር አኳያ የሚስተዋሉ ቅሬታዎችን መፍታትና በየቀበሌው ያሉ አደረጃጀቶችን ማጠናከርና የልጅነት ጋብቻን ለማስቀረት ባለድርሻ አካላት በእቀድ ይዘው መሰራት እንዳለባቸው አስቀምጠዋል።

‎በመድረኩ ላይ የተገኙት የወረዳው ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አዲሴ ነጋሽ በበኩላቸው ባለፈው በጀት አመት የነበሩ ጥንካሬዎችን ማስቀጠልና ድክመቶችን በማረም ለቀጣይ ውጤታማ ስራ ለመስራት የጋራ መግባባት መፈጠር እንደሚገባ ገልጸዋል።

‎በሂውማን ካፒታል ኦፕሬሽን / / በተገኘ የበጀት ድጋፍ በጎጂ ልማዳዊ ድርጊትና የሴቶች ልማት ህብረት ዙሪያ ለሚመለከታቸው አካላት ስልጠና እየተሰጠ ነው።‎‎ነሃሴ 25/2018 ዓ.ም‎‎የወረዳ...
31/08/2026

‎በሂውማን ካፒታል ኦፕሬሽን / / በተገኘ የበጀት ድጋፍ በጎጂ ልማዳዊ ድርጊትና የሴቶች ልማት ህብረት ዙሪያ ለሚመለከታቸው አካላት ስልጠና እየተሰጠ ነው።

‎ነሃሴ 25/2018 ዓ.ም

‎የወረዳው ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ከ በተገኘ የበጀት ድጋፍ ለሁሉም የቀበሌ ስራ አስኪያጅ ባለሙያዎች፣ የቀበሌ ሴቶች ጉዳይ ሃላፊዎችና የጽ/ቤቱ ሰራተኞች በማህበረሰቡ ዘንድ የሚፈጸሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለማስቆም ያለመ የአቅም ማሳደጊ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

‎ስልጠናው በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ምሳነው አማረ በማህበረሰቡ እየተፈጸሙ ያሉ ጎጂ ልምዶችን ለማስቆም በቅድሚያ ስለ አስከፊነታቸውና ለሚያስዳሩት ችግር ግንዛቤ መፈጠሩን አመስግነው በስልጠናው የሚሳተፉ አካላት ከተወከሉበት ቀበሌ ሄደው በየደረጃው ካሉ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት ማድረግና ችግሩን መቀነስ እንደሚገባ መልእክት አስተላልፈዋል።

‎በጎጂ ልማዳዊ ድርጊት ማስወገድ ዙሪያ በተዘጋጀው ሰነድ ለሁለት ቀናት ስልጠና የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል።

‎የክረምት የታዳጊዎች የውስጥ ለውስጥ የእግር ኳስ ውድድር ተጠናቀቀ።‎‎ነሃሴ 25/2018 ዓ.ም‎በወረዳው ባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው የክረምት የታዳጊዎች የእግ...
31/08/2026

‎የክረምት የታዳጊዎች የውስጥ ለውስጥ የእግር ኳስ ውድድር ተጠናቀቀ።

‎ነሃሴ 25/2018 ዓ.ም
‎በወረዳው ባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው የክረምት የታዳጊዎች የእግር ኳስ ውድድር ተጠናቋል።

‎ከ13 አመት በታች በተካሄደው ውድድር የሀይስኩል ቡድንና ከ17 አመት በታች ደግሞ የካፌው ቡድን ዋንጫውን ወስደዋል።

‎በመዝጊያ መርሃ ግብሩ የወረዳው ተወካይ አስተዳዳሪ እና የትምህርት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሀብታሙ ሀይሉና ሌሎች አመራሮች እና የስፖርት ቤተሰቡ ተገኝተዋል።

‎በመጨረሻም በሁለቱም የእድሜ ክልል ከ1-3 ለወጡ ቡድኖች የማበረታቻ ሽልማት፣ ለ2 ዳኞች የስፖርት ትጥቅ፣ በውድድሩ ለተመረጡ ኮከብ ተጫዋች ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪዎችና አጋር አካላት የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቷል።

‎በሁለቱም የእድሜ ክልሎች የተወጣጡ 10 ቡድኖችን ያካተተ የምድብ ውድድር እየተካሄደ ሲሆን በዘርፉ ተተኪ ወጣት ስፖርተኞችን ለማፍራት፣ ወጣቶች በክረምቱ የእረፍት ጊዜያቸውን በስፖርት ማዘወትሪያ ቦታዎች እንዲያሳልፉ የስፖርት የውድድሩ መጀመር ፋይዳው የጎላ መሆኑን ከወረዳው ባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

‎የመካነ ብርሃን ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ለ4ኛ ጊዜ ተማሪዎችን አስመረቀ።‎‎ነሃሴ 24/2018 ዓ.ም‎‎ኮሌጁ በተለያዬ የሙያ ዘርፍ ተማሪዎችን ሲያሰለጥን ቆይቶ በዛሬው እለት አስመርቋል።‎‎በደረ...
30/08/2026

‎የመካነ ብርሃን ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ለ4ኛ ጊዜ ተማሪዎችን አስመረቀ።

‎ነሃሴ 24/2018 ዓ.ም

‎ኮሌጁ በተለያዬ የሙያ ዘርፍ ተማሪዎችን ሲያሰለጥን ቆይቶ በዛሬው እለት አስመርቋል።

‎በደረጃ አራት በልዩ ልዩ የሙያ መስክ ሲማሩ የነበሩ 41 ተማሪዎችን በእለቱ በደማቅ መርሃ ግብር አስመርቋል።

‎በምርቃት ስነ ስርዓቱ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ተወካይ እና የትምህርት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሀብታሙ ሃይሉ ጨምሮ የወረዳው ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አዲሴ ነጋሽ እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።

‎በትምህርት ቆይታቸው የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ተመራቂ ተማሪዎች እና አጋር ተቋማት የምስክር ወረቀት ተሰቷቸዋል።

‎በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና 532 ነጥብ በወረዳው ከፍተኛ ውጤት መሆኑ ተገለፀ።‎**********‎ተማሪ  #ታድሎ ጌታሁን ከመካነ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ...
28/08/2026

‎በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና 532 ነጥብ በወረዳው ከፍተኛ ውጤት መሆኑ ተገለፀ።
‎**********
‎ተማሪ #ታድሎ ጌታሁን ከመካነ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ትምህርት በተፈጥሮ ሣይንስ 532 ነጥብ በማምጣት በወረዳው የዚህ አመት ከፍተኛ ውጤት ሲሆን በተመሳሳይ ተማሪ #ዋኘው አበጀ ይግዛው ከዋሰል 2ኛ ደረጃ ት/ት 529 ነጥብ በማምጣት 2ኛው መሆን ችሏል።

‎በአጠቃላይ በ2018 ዓ.ም ፈተና ከወሰዱት ተማሪዎች መካከል 60 ተማሪዎች ከግማሽ በላይ ውጤት ያመጡ መሆኑንና ከአምናው ጋር ሲነጻጸር የተወሰነ መሻሻል እንዳለ ከወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

‎በወረዳው በህገ ወጥ መንገድ የተወረሩ የወል መሬትና የተፈጥሮ ደን ማስመለስ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።‎********‎‎ነሃሴ 20/2018 ዓ.ም‎‎በወረዳው ያለውን ህገ ወጥ የመሬት ወረራ ለመከ...
26/08/2026

‎በወረዳው በህገ ወጥ መንገድ የተወረሩ የወል መሬትና የተፈጥሮ ደን ማስመለስ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
‎********

‎ነሃሴ 20/2018 ዓ.ም

‎በወረዳው ያለውን ህገ ወጥ የመሬት ወረራ ለመከላከል የተቋቋመው የደን አስከባሪ ግብረ ሃይል በየአመቱ በርካታ ህገ ወጥ የመሬት ወረራዎችን የደን መጨፍጨፍን ለመከላከል ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።

‎በዚህ የክረምት ወቅትም የችግሩን አሳሳቢነት የተረዳው ግብረ ሃይሉ በአሁኑ ወቅት በሁለት ቀበሌዎች በደረስጌና በጋሻጃግሬ ቀበሌ በህገ ወጥ መንገድ የተያዙ የወልና የደን መሬቶችን የመከለልና ለማህበረሰቡ የማስከረብ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

‎በዚህም ግብረ ሃይሉ በደረስጌ ቀበሌ ህዝቡን እያስመረሩ የነበሩ የወል መሬት ወረራ አስመልክቶ 5.5 ሄ/ር እና የተፈጥሮ ደን መንጥሮ የግል ጥቅሙ ያዋለ ግለሰብ ሰብል የመሻር ስራ ተሰርቷል።

‎በቀጣይም የማህበረሰቡን ጥያቄ መሰረት በማድረግ በሁሉም ቀበሌዎች በህገ ወጥ የተያዙ መሬቶችን የማስመለስ ተግባር እስከ ነሃሴ 30 በዘመቻ መልክ የሚቀጥል መሆኑን ከወረዳው አካባቢና ደን ጥበቃ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።



"የደባርቅን የመልማት ፀጋ ወደ ተጨባጭ አቅም ለመቀየር ከተማዋን በመሰረተ ልማት ማበልጸግ ይገባል" -ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደየደባርቅን የመልማት ፀጋ ወደ ተጨባጭ አቅም ለመቀየር ከተማዋ...
24/08/2026

"የደባርቅን የመልማት ፀጋ ወደ ተጨባጭ አቅም ለመቀየር ከተማዋን በመሰረተ ልማት ማበልጸግ ይገባል" -ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

የደባርቅን የመልማት ፀጋ ወደ ተጨባጭ አቅም ለመቀየር ከተማዋን በመሰረተ ልማት ማበልጸግ እንደሚገባ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ።

የደባርቅን ከተማ ለማልማት የተዘጋጀ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር "ደባርቅን እናሳምር ከተማችንን እናድምቅ" በሚል መሪ ሀሳብ በሂልተን ሆቴል እየተካሄደ ይገኛል።

በመርሃ ግብሩ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እና ባለሀብቶች ተገኝተዋል።

በገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብሩ "ኑ ተፈጥሮ የገለጠችውን ድንቅ የቱሪስት መስህብ የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ መግቢያ በር የሆነችውን ደባርቅ ከተማ በጋራ እናልማ" የሚል ጥሪ ቀርቧል።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ደባርቅ የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ መግቢያ ከተማ ናት።

ይሁን እንጂ ደባርቅ የታሪክ ባለቤትነቷን፣ የቱሪዝም መተላለፊያነቷን የሚመጥን ልማት አልታደለችም ብለዋል።

የደባርቅን የመልማት ፀጋ ወደ ተጨባጭ አቅም መለወጥ የሚያስችል እንቅስቃሴ መጀመሩንም ጨምረው ገልጸዋል።

በመሆኑም ከተማዋን በማልማት የተፈጥሮ ውበቷን ለመግለጥ ሁሉም በጋራ ትብብር ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።

የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲባ ጌትነት ፀጋየ በበኩላቸው፤ ደባርቅ የቀድሞ የሰሜን አውራጃ ከተማ፣ በዓለም ቅርስነት የተመዘገበው የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ መገኛ የቱሪዝም ቀዬ መሆኗን ገልጸዋል።

ደባርቅ በተፈጥሮ ሀብቶች የበለጸገች የቱሪዝም ማዕከል ብትሆንም የሚገባትን ያህል መልማት ባለመቻሏ የቱሪስቶችን የቆይታ ጊዜ ማራዘም አልቻለችም ነው ያሉት።

ስለሆነም መንግሥት ያመጣው የኮሪደር ልማት ተቋዳሽ እንድትሆን ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

"የዓለም ዐይን ለሰሜን ተራራዎች እንዲገለጥ ደባርቅ ከተማን ማልማት ይገባል" ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የደባርቅ ከተማ አሥተዳደር ከተማዋን ለማልማት የገቢ ማሠባሠቢያ መርሐግብር በአዲስ አበ...
24/08/2026

"የዓለም ዐይን ለሰሜን ተራራዎች እንዲገለጥ ደባርቅ ከተማን ማልማት ይገባል" ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ

የደባርቅ ከተማ አሥተዳደር ከተማዋን ለማልማት የገቢ ማሠባሠቢያ መርሐግብር በአዲስ አበባ እያካሄደ ይገኛል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የደባርቅ ከተማ ለሰሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፖርክ መግቢያ በር በመኾኗ የደባርቅን ከተማ ማልማት የሰሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክን ፀጋ በአግባቡ ለመጠቀም መሠረት ነው ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ በሥራ ምክንያት በተለያዩ ዓለማት ሲጓዙ ስለ ሰሜን ተራራዎች በሌላው ዓለም የተለየ ምልከታ እንዳለ መታዘባቸውን ተናግረዋል። በመኾኑም በሌሎች ዓለማት እንቁ የኾነውን የተፈጥሮ ፀጋ ማልማት የዜጎች ግዴታ ስለመኾኑ አንስተዋል።

የበርካታ ዕጽዋት፣ እንስሳት እና ሰንሰለታማ ተራራዎች መገኛ የኾነውን ብሔራዊ ፓርክ ለማልማት በጋራ መሥራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

ዕድሜ ጠገብ የኾነውን የደባርቅ ከተማን ማልማት ደግሞ በርካቶች ዓለማትን አቋርጠው ለመጎብኘት የሚጓጉለትን ውብ የተፈጥሮ እና የሰው ሠራሽ ፀጋን በአግባቡ ለማስተዋወቅ መሠረት መኾኑን ተናግረዋል።

የሰሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ መግቢያ በር የኾነችውን ደባርቅን ማልማት ዓለም ስለ ሰሜን ተራራዎች የበለጠ እንዲያውቅ በር መክፈት ነው ሲሉም ፕሬዝዳንቱ አንስተዋል።

‎"በጎነት ለአብሮነት"!  በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለ104 በችግር ለተጋለጡ ወገኖች የምግብ እህል ድጋፍ ተደረገ።‎*******‎‎ነሃሴ 15/2018 ዓ/ም‎በክረምት የበጎ ፈቃድ አገል...
21/08/2026

‎"በጎነት ለአብሮነት"! በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለ104 በችግር ለተጋለጡ ወገኖች የምግብ እህል ድጋፍ ተደረገ።
‎*******

‎ነሃሴ 15/2018 ዓ/ም
‎በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴ ከማህበረሰቡ ሀብት በማሰባሰብ በመካነ ብርሃን ከተማ ለሚገኙ አቅመ ደካማ ዜጎች ድጋፍ ተደርጓል።

‎ኮሚቴው ከከተማው ማህበረሰብ፣ ነጋዴው ፣ከመንግስት ሰራተኛው በአይነት ሀብት ያሰባሰበ ሲሆን በአጠቃላይ ከ105 ሺህ ብር በላይ የሚገመት 15 ኩንታል የምግብ እህል ለ104 ሰዎች ለእያንዳዳቸው 15 ኪሎ ግራም ማከፋፈል ተችሏል።

Address

Writer
Debark'

Telephone

+251927564796

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Janamora Communications posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share