ደብረ ማርቆስ ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ

ደብረ ማርቆስ ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ይህ የደ/ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የከተማና መሠረተ ልማት ይፋዊ የፌስቡክ ገጽ ነው።

16/08/2026
ክረምቱን ተከትሎ የሚከሰቱ የመሰረተልማት ስርቆትን እና ተያያዥ ችግሮች ለመከላከል የሚያስችል ውይይት ከባለድርሻ አካላት ጋር ተካሄደ ።የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ እና የመ...
17/07/2026

ክረምቱን ተከትሎ የሚከሰቱ የመሰረተልማት ስርቆትን እና ተያያዥ ችግሮች ለመከላከል የሚያስችል ውይይት ከባለድርሻ አካላት ጋር ተካሄደ ።

የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ እና የመሰረተ ልማት መምሪያ በጋራ ባዘጋጁት የውይይት መድረክ ክረምቱን ተከትሎ የሚከሰቱ የመሰረተልማት ስርቆትን እና ተያያዥ ችግሮች ለመከላከል የሚያስችል ውይይት ከባለድርሻ ጋር ተካሄዷል ።

በውይይት መረኩ ላይ የተገኙት የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ስራ አስኪያጅ አቶ አስምሮም ሞስነህ እንደተናገሩት በመሰረተልማት ላይ የሚፈፀሙ ስርቆቶች እና ተያያዥ ችግሮች ጉዳት የሚያስከትሉት በማህበረሰቡ ላይ ከመሆኑም በላይ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚገዙ በመሆኑ እና ችግሩ ከደረሰም በኋላ ለጥገና እና ለእቃ ግዢ ከፍተኛ ወጪን የሚያስከትል ስለሆነ ባለድርሻ አካላትም ሆኑ ህዝቡ ተገቢውን ጥበቃ ሊያደርጉ እንደሚገባ ገልጸዋል።

በተለይ የተቋማት መሪዎች የጥበቃሰራተኞችን ፣የተለያዩ የቴክኒክ ባለሙያዎችን ስነምግባር ማረቅ እና ችግር በሚፈጥሩ አካላት ላይ ተከታትሎ ርምጃ መውሰድ እንደሚገባ ተናግረዋል ፡፡

መሰረተ ልማት የሚገነባው ከህዝብ በሚሰበሰብ ግብር በመሆኑ ህብረተሰቡ ወንጀሉንም ከመከላከል አኳያ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር መስራት እንደሚገባ አስረድተዋል ፡፡

ሌላው በመድረኩ ላይ የተገኙት የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከል ምክትል መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ይልማ ስራብዙ እንደተናገሩት የመሰረተልማት ስርቆትን መቀነስ ወይም መከላከል የሚቻለው ተቋማት፣ህዝቡ ፣ባለድርሻ አካላት ከፀጥታ ሀይሉ ጋር በቅንጅት ሲሰሩ መሆኑ ተናገረዋል ፡፡

በተለይ ያገለገሉ ንብረቶችን የሚገዙ ቆራሊዮ ቤቶች ከድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባ አስረድተዋል ፡፡

ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ በመሰረተልማት ስርቆት የተጠረጠሩ ግለሰቦች በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ የተደረገበት እና ሌሎችም ጉዳያቸው በፍርድ ሂደት ላይ እንደሚገኝ ገልጸው ይህ አሰራር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

በውይይቱ የቆራሊዮ ነጋዴዎች፣የመብራት ሀይል አመራሮች፣የኢትዮ ቴሌ አመራሮች፣የውሃ እና ኢነርጂ አመራሮች፣ መሰረተልማት፣የሚሊሻ እና የፖሊስ መምሪያ አመራሮች ተሳትፈዋል።

በክልላችን የመጀመሪያ የሆነው የዲጂታል አድራሻ ስርዓት (Digital Addressing System) በደብረ ብርሃን ከተማ መተግበሩን አስመልክቶ፡ የአብክመ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሞ...
07/07/2026

በክልላችን የመጀመሪያ የሆነው የዲጂታል አድራሻ ስርዓት (Digital Addressing System) በደብረ ብርሃን ከተማ መተግበሩን አስመልክቶ፡ የአብክመ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሞላ መልካሙ (ዶ/ር) ያስተላለፉት መልዕክት፦

ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነው! የከተሞቻችንን ዕድገትና የአገልግሎት አሰጣጥ ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግረው የዲጂታል አድራሻ ሥርዓት (Digital Addressing System - DAS) በክልላችን ለመጀመሪያ ጊዜ በዛሬው ዕለት በደብረ ብርሃን ከተማ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሁኖል።

ደብረ ብርሃን ከተማ የኢንዱስትሪ፣ የኢንቨስትመንት እና የፈጣን የከተማ መስፋፋት ማዕከል ናት። ይህንን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ በዘመናዊ የመሠረተ ልማት መረጃ መደገፍ የግድ ይላል። የDAS መተግበር ለከተማዋ በርካታ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎችን ይዞ መጥቷል፤ የሎጂስቲክስና የማጓጓዣ ሥርዓትን በማቃለል የንግድ እንቅስቃሴን ያፋጥናል። የድንገተኛ አደጋ፣ የጸጥታና የጤና አገልግሎቶች ያለ ምንም መዘግየት በትክክለኛው ቦታና ሰዓት እንዲደርሱ ያደርጋል። የገቢ አሰባሰብንና የሀብት አስተዳደርን በቴክኖሎጂ በመደገፍ የከተማዋን ኢኮኖሚያዊ አቅም ያሳድጋል።

የዲጂታል አድራሻ ስርአት ስራ በክልላችን ከተሞች እየገነባነው ላለው የስሉጥ ከተማ (Smart city) ትልቅ ማሳያ እና መሰረት ነው። ይህን ስርዓት በክልላችን በመጀመሪያው ዙር በ9 ከተሞቻችን እውን ለማድረግ እየሰራን እንገኛለን። በደብረ ብርሃን ከተማ ዛሬ እንደተጀመረ ሁሉ፣ ይሀው ስርአት በተመሳሳይ መልኩ በጎንደር ከተማም በቅርቡ ለአገልግሎት ክፍት ይደረጋል። ይህ ተሞክሮ በሌሎች ከተሞችም በፍጥነት ተጠናክሮ ይቀጥላል።

በመጨረሻም ይህ ስራ እንዲሳካ በተለይም ዘመናዊ የሳተላይት መረጃዎችን በመጠቀም መዋቅራዊ ፕላን በማዘጋጀት ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላደረገው እና በሌሎችም 8 ከተሞቻችን በተመሳሳይ ሁኔታ ድጋፍ እያደረገ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩትን እያመሰገንኩ ድጋፋችሁ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መልዕክቴን ማስተላለፍ እፈልጋለሁ!

07/07/2026
በከተሞቻችን የጭቃ ቤት ቅነሳ ኢኒሼቲቭ እንዳለ ያውቃሉ?የጭቃ ቤት ቅነሳ ኢኒሼቲቭ ማለት በከተሞቻችን ውስጥ የአገልግሎት ዘመናቸው ያለፈባቸውና የከተማን ውበት የማይመጥኑ የጭቃ እና የእንጨት ...
11/06/2026

በከተሞቻችን የጭቃ ቤት ቅነሳ ኢኒሼቲቭ እንዳለ ያውቃሉ?

የጭቃ ቤት ቅነሳ ኢኒሼቲቭ ማለት በከተሞቻችን ውስጥ የአገልግሎት ዘመናቸው ያለፈባቸውና የከተማን ውበት የማይመጥኑ የጭቃ እና የእንጨት ቤቶች አዲስ ግንባታ እንዳይኖር ማድረግ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ነባር የጭቃ ቤቶችን ደረጃ በደረጃ እያሻሻሉ ወደ ዘመናዊ ግንባታ የመቀየር ስልት ነው።

ይህ ኢኒሼቲቭ ከተሞቻችንን ካረጀ አሰራር አውጥቶ ለነዋሪዎች ምቹ፣ ማራኪ እና ተወዳዳሪ የማድረግ ግብ ይዟል።

አላማው ከተሜነትን ማዘመንና የህዝባችንን የኑሮ ደረጃ ማሻሻል ቢሆንም፣ ከጀርባው ግን የአካባቢ ጥበቃ ፋይዳ አለው። ባህላዊው የእንጨትና የጭቃ ግንባታ በየዓመቱ ለከፍተኛ የደን ጭፍጨፋ እና ለተፈጥሮ ሀብት መመናመን ምክንያት በመሆኑ፣ ይህንን ጎጂ የግንባታ ልማድ ማስቀረት ያስፈልጋል።

ከተሞቻችን የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋሙ፣ አረንጓዴ እና ዘላቂ ልማትን ያረጋገጡ እንዲሆኑ የቆየውን የእንጨትና ጭቃ የቤት ግንባታ ባህል በአዲስ አሰራር መተካት ግድ ይላል።

በመሆኑም ከእንግዲህ በኋላ በከተሞቻችን ውስጥ ለማንኛውም አዲስ የጭቃ ቤት ግንባታ ፈቃድ አይሰጥም! በምትኩ ማንኛውም ግንባታ በብሎኬት፣ በጡብ እና ሀገር በቀል የቴክኖሎጂ ማቴሪያሎች ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ይደረጋል።

የአብክመ ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ

16/05/2026
14/05/2026

የዜጎችን መሠረታዊ የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ለመፍታት እየሰራ መሆኑን የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ገለጸ።

አሚኮ ደብረ ማርቆስ(ግንቦት 6/2018 ዓ.ም) በ2018 ዓ.ም እውቅና ያገኙ 94 የመኖሪያ ቤት ማህበራት ቦታ እንዲያገኙ ዝግጅት መጠናቀቁን ከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል።

የከተማውን ውስን መሬት በፍትሃዊነትና በቁጠባ ለመጠቀም ዜጎች በተለያዩ አማራጮች የቤት ባለቤት እንዲሆኑ እየተሰራ መሆኑን የከተማና መሠረተ ልማት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አስመሮም ሞስነህ ገልጸዋል።

በተለይም የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመቅረፍ በህብረት ስራ ማህበራት የሚደራጁ ዜጎችን በጋራ መኖሪያ ቤቶች (አፓርትመንቶች) እና በሌሎች የቤት አማራጮች ተጠቃሚ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው።

ከተቀመጡት አማራጮች መካከል በጋራ መኖሪያ ቤት ተደራጅተው ለሚመጡ ማህበራት ልዩ ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ተገልጿል።

ማህበራቱ 20 በመቶ ቁጠባ ማሟላት ከቻሉ የፋይናንስ ሥርዓቱ ተመቻችቶላቸው በአጭር ጊዜ የቤት ባለቤት መሆን እንደሚችሉም ተጠቁሟል።

በቪላና በሌሎች አማራጮች ተደራጅተው ለሚቀርቡ ዜጎችም እንደየፍላጎታቸው በጊዜ ሒደት ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑን ከተማ አስተዳደሩ ገልጿል።

ከዚህ በፊት በተለያየ መንገድ ሲቆጥቡ የነበሩ የቤት ማህበራትም በተቀመጡ አማራጮች መሠረት ወደ ከተማ አስተዳደሩ የህብረት ሥራ ማህበራት ተጠሪ ጽሕፈት ቤት በመቅረብ አስፈላጊ መስፈርቶችን በማሟላት እውቅና ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል።

አስተዳደሩ የመኖሪያ ቤት አሰጣጡ የዜጎችን ፍላጎት መሠረት ያደረገ ቢሆንም ቅድሚያ የሚሰጠው በጋራ መኖሪያ ቤቶች ለሚደራጁ መሆኑን አስገንዝቧል።

የሚገነቡት የጋራ መኖሪያ ቤቶችም ባለ አንድ፣ ባለ ሁለት እና ባለ ሶስት የመኝታ ቤት አማራጮችን የያዙ ሲሆን የዜጎችን የተለያዩ ፍላጎቶች ያማከሉ መሆናቸው ተጠቁሟል።

የደብረ ማርቆስ ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ የ2018 ዓ.ም የ3ኛው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ በድምቀት ተካሄደየደብረ ማርቆስ ከተማን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥና ነዋሪዎችን ተ...
21/04/2026

የደብረ ማርቆስ ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ የ2018 ዓ.ም የ3ኛው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ በድምቀት ተካሄደ
የደብረ ማርቆስ ከተማን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥና ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ የ3ኛው ሩብ ዓመት የቁልፍና አብይ ተግባራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ፣ የመምሪያው ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች በተገኙበት በመምሪያው መሰብሰቢያ አዳራሽ በድምቀት ተካሂዷል።
የዕቅድ አፈጻጸምና የተመዘገቡ ስኬቶች
የዕለቱን የአፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት የመምሪያው የዕቅድና ዝግጅት ቡድን መሪ አቶ ቢኒያም ገበየሁ እንደገለጹት፤ መምሪያው የከተማዋን ገጽታ በአዲስ መልክ ለመቅረጽና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አገራዊ ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን እንደ መመሪያ በመጠቀም በትጋት ሲንቀሳቀስ ቆይቷል።
በተለይም ባለፉት ዓመታት የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ለማሳደግና የተቀመጡ የልማት ግቦችን ለማሳካት በተደረገው የተቀናጀ ጥረት፣ አበረታችና ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውን በሪፖርታቸው አረጋግጠዋል። ተቋሙ ቀልጣፋ፣ ብቁና ተወዳዳሪ የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓትን በመዘርጋት የከተማዋን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ለማፋጠን በቆራጥነት መነሳቱም ተመላክቷል። በተጨማሪም የመልካም አስተዳደር እሴቶችን በተግባር ማስፈን የለውጥ እርምጃው ማዕከል መሆኑን በማመን፣ በዘርፉ የሚታዩ ማነቆዎችን በሳይንሳዊ መንገድ ለመፍታት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል።
የውይይቱ ፋይዳና መሠረታዊ መነሻዎች
ይህ የ3ኛው ሩብ ዓመት የአፈጻጸም ሪፖርት አገራዊና ክልላዊ የ5 ዓመት መሪ የልማት ዕቅዶችን መሠረት ያደረገ ነው። የውይይቱ ዋነኛ ዓላማም፦
• ያለፉት ዓመታት ጥንካሬዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ማድረግ፤
• ድክመቶች በዝርዝር ተለይተው እንዲታረሙ ማስቻል፤
• የነዋሪዎችን ንቁ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ባረጋገጠ መልኩ የዘርፉን ውስብስብ ችግሮች በዘላቂነት መፍታት ናቸው።
በመድረኩ የቀረቡ ተግባራት ላይ በጥልቀት ከተመከረ በኋላ፣ ተሳታፊዎች በታሪካዊ ኃላፊነት መንፈስ ለላቀ ውጤት እንደሚሰሩ የጋራ መግባባት ላይ ደርሰዋል።
የቀጣይ የሥራ አቅጣጫና ማጠቃለያ
የመመሪያው ኃላፊ አቶ አስምሮም ሞስነህ ከቤቱ የተነሱ ገንቢ ሃሳቦችን መነሻ በማድረግ የማጠቃለያ ንግግርና የቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል። ኃላፊው በንግግራቸው፦"በአፈጻጸም ሂደት ውስጥ ለአሠራራችን እንቅፋት የሆኑ በርካታ ሰው-ሰራሽና ተፈጥሯዊ ተግዳሮቶች ቢያጋጥሙንም፤ እነዚህን መሰናክሎች በጽናት ለመሻገር በአመራሩና በባለሙያው ዘንድ የታየው የዓላማ አንድነትና የሥራ ቁርጠኝነት ለስኬታችን ትልቁን ድርሻ ይይዛል" ሲሉ አፅንኦት ሰጥተዋል።
ወቅታዊና አካባቢያዊ ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ ካለፈው ዓመት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብና ዕቅዱን በድል ለማጠናቀቅ በቁልፍ ጉዳዮች ላይ የተቀናጀ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። ይህ የጋራ ጥረት በተቋሙ ውስጥ አዲስ የሥራ ተነሳሽነትና የድል መንፈስ እንዲነግስ ከማድረጉም በላይ፣ ለከተማዋ የወደፊት እድገትና ብልጽግና ጠንካራ መሠረት ጥሏል።
በመጨረሻም፣ በመድረኩ የተገኙ ግብዓቶችን እንደ መነሻ በመጠቀም፣ ቀሪውን የ4ኛው ሩብ ዓመት የልማት ጉዞ ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ መላው የመምሪያው አመራርና ባለሙያ በላቀ ቆራጥነት ለመሥራት ቃል በመግባት ውይይቱ ተጠናቋል።

የደብረ ማርቆስ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነዉ! በደብረ ማርቆስ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው አዲሱ የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ በቀንና...
14/03/2026

የደብረ ማርቆስ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነዉ!

በደብረ ማርቆስ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው አዲሱ የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ በቀንና በሌሊት ፈረቃ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

ፕሮጀክቱ በ153 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን ግንባታውን በሚመጣው ሚያዝያ ወር ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው።

ፕሮጀክቱ የህዝቡን የቆየ ጥያቄ ከመመለሱ ባለፈ፣ ለአካባቢው ከፍተኛ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ይኖረዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እያከናወናቸው ካሉ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች አንዱ የሆነው ይህ ማረፊያ፣ የከተማዋን የንግድና የቱሪዝም እንቅስቃሴ ያነቃቃል ተብሎ ይጠበቃል።

Address

Debre Markos
Debra Markos

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ደብረ ማርቆስ ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share