Debre Markos city administration health office

Debre Markos city administration health office በዚህ ገፅ ዓለም አቀፋዊ፣ አገራዊ፣ ክልላዊ፣ የከተማውንና የአካባቢውን ወቅታዊ የጤና ጉዳይ መረጃዎችን እናጋራለን።

05/09/2026
05/09/2026

Nyd de videoer og den musik, du holder af, upload originalt indhold, og del det hele med venner, familie og verden på YouTube.

    Opportunity : Pagume 3, 2018E.C
04/09/2026

Opportunity
: Pagume 3, 2018E.C

31/08/2026

ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከል በክረምት በጎ ፈቃድ ተግባራት እየተሰራ ነው።

ነሐሴ 25/2018ዓ.ም (ደብረ ማርቆስ ኮሙኒኬሽን): በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን የመከላከል ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለጸ።

የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ቡድን መሪ አቶ ታደሰ ተስፋ በሰጡት ማብራሪያ በክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ ግብር ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከልና የህብረተሰቡን ጤና ለማረጋገጥ ያለመ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫና የቅድመ መከላከል ሥራዎችን እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል ።

በክረምቱ ወቅት ለተላላፊ በሽታዎች ተጋላጭነት ለሆኑ ከ106ሺ በላይ የማህበረሰብ ክፍሎች የግንዛቤ የተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል።

​ቡድን መሪው እንደገለጹት የክረምት ወቅት ከዝናብና ከቅዝቃዜ ጋር ተያይዞ ለተላላፊ በሽታዎች መከሰት ምቹ ሁኔታ ስለሚፈጥር ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ የውኃና የምግብ ወለድ በሽታዎች መከላከል ስራ መሰራቱን ተናግረዋል።

በክረምት ጎርፍ ምክንያት የመጠጥ ውኃ የመበከል ዕድሉ ከፍተኛ በመሆኑ የውኃ ማጽጃ መድኃኒቶችን ማሰራጨትና የውኃ ምንጮችን የመንከባከብ ሥራ እየተሰራ መሆኑንም ገልፀዋል።

​ የሳንባ ምች (ኒሞኒያ)፣ የከባድ ጉንፋንና የቲቢ በሽታዎችን ለመከላከል በመኖሪያ ቤቶችና በሕዝብ መገልገያ ቦታዎች በቂ የአየር ዝውውር እንዲኖር የማስተማር ሥራ እየተከናወነ ስለመሆኑ አቶ ታደሰ አስገንዝበዋል።

​በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን በማስተባበር ከ11ሺ ሄክታር በላይ ውኀ ያቆሩ ቦታዎችን የማደፈን፣ የቦይ ማጽዳትና የትንኝ መራቢያ ቦታዎችን የማስወገድ ተግባራት ተከናውነዋል ብለዋል።

​ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች አጠቃላይ በህብረተሰቡ ላይ እያደረሱት ያለውን ጉዳት ለመቀነስ በበጎ ፈቃድ መርሃ ግብሩ የደም ግፊት፣ የደም ስኳር መጠን ፣ የክብደት መለኪያ ምርመራዎች መደረጋቸውን ገልፀዋል።

ጤናማ አኗኗር እንዲኖር ለማድረግ የልብ ህመም፣ የስኳር፣ የካንሰርና ደም ግፊት በሽታዎችን እንዴት መከላከል እንደሚቻል ጥራቱን የጠበቀ የምክር አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል ብለዋል።

​የአመጋገብ ጥንቃቄ ጨው፣ ስኳርና ቅባት ያላቸውን ምግቦች መቀነስ እንዲሁም የዘወትር ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን የማድረግ ባህል እንዲዳብር የማስገንዘብ ሥራ መከናወኑንም ቡድን መሪው ተናግረዋል።

​ ጤናን መጠበቅ የባለሙያ ወይም የጤና ተቋማት ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን የግለሰብና የህብረተሰቡ የዘወትር ተግባር መሆን እንዳለበት አሳስበዋል።

​ህብረተሰቡ በክረምት በጎ ፈቃድ የሚሰጡ የጤና አገልግሎቶችንና የግንዛቤ ፈጠራ መድረኮችን በአግባቡ እንዲሳተፉ፣ የመጠጥ ውኃውን አፍልቶ ወይም አክሞ እንዲጠጣ፣ ህመም ሲሰማውም በፍጥነት ወደ አቅራቢያው ጤና ተቋም በመሄድ ምርመራ እንዲያደርግ አቶ ታደሰ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከደብረ ማርቆስ ኮሚኒኬሽን ለማግኘት ሊንኩን በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
‎ቴሌግራም https://t.me/dmcomunicationoffice
‎ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php id=100064865823018
‎ቲክቶክ www.tiktok.com/
ዩቲብ:https://youtube.com/?si=h8-iiu60Df-Te3qJ

26/08/2026
የ76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ስብሰባ ተሳታፊዎች "Walk the Talk " በሚል መሪ መልዕክት  የእግር ጉዞ አደረጉ።________________________በመርሃ ግ...
24/08/2026

የ76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ስብሰባ ተሳታፊዎች "Walk the Talk " በሚል መሪ መልዕክት የእግር ጉዞ አደረጉ።
________________________

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ 76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ስብሰባ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ በመግለጽ ተሳታፊዎችም ዛሬ ያደረጉት የእግር ጉዞ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከልና የአኗኗር ዘይቤን ለማስፋፋት ዓላማ ያደረገ ነው ብለዋል።

የእግር ጉዞው የጤና ፖሊሲ ውሳኔዎችን ወደ ተጨባጭ ተግባር ለመቀየርና በአፍሪካ ሕዝቦች መካከል ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን ለማስፋፋት ያለመ ግንዛቤ ለመፍጠር መሆኑን በአለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጠናዊ ትስስር ዳይሬክተር የሆኑት ፕሮፌሰር መሀመድ ጃናቢ ናቸው፡፡

የአፍሪካ ሀገራት የጤና ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች፣ የዓለም ጤና ድርጅት አመራሮች፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር ስለሺ ስህን እንዲሁም ሌሎች ታዋቂ አትሌቶች ተሳትፈዋል።

የእግር ጉዞው ከአድዋ ድል መታሰቢያ ተነስቶ በከተማዋ የእግረኛ መንገድ በመከተል በጊዮን መናፈሻ ዳርቻዎች ተጠናቋል።

የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ 76ኛ ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ሲሆን በአፍሪካ የጤና አጀንዳዎች እና ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደያደርጋል።

መረጃው የጤና ሚኒስተር ነው።

19/08/2026
 ========================ተቋም:    #የመ/ደረጃ_ሆስፒታል የቅጥር ሁኔታ:  ሙያ:  #ፋርማሲስት፣  #ላቦራቶሪ እና  #ራዲዮሎጂስት (በዲግሪ) : ከነሃሴ 11-19, 2018ዓ....
18/08/2026


========================

ተቋም: #የመ/ደረጃ_ሆስፒታል
የቅጥር ሁኔታ:
ሙያ: #ፋርማሲስት፣ #ላቦራቶሪ እና #ራዲዮሎጂስት (በዲግሪ)
: ከነሃሴ 11-19, 2018ዓ.ም

16/08/2026

Address

Ethiopia, Amhara Region
Debra Markos

Telephone

+251587711940

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Debre Markos city administration health office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Debre Markos city administration health office:

Shortcuts

Share