ደብረ ማርቆስ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ክላስተር ማእከል

  • Home
  • Ethiopia
  • Debra Markos
  • ደብረ ማርቆስ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ክላስተር ማእከል

ደብረ ማርቆስ  የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ክላስተር ማእከል Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ደብረ ማርቆስ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ክላስተር ማእከል, Public & Government Service, Ambasel Building, Debre Markos, Debra Markos.

ዓላማችን ፡-ተገልጋዮቻችንን የወቅታዊ፣አካባቢያዊና ጠቃሚ መረጃዎቸ ባለቤት ማድረግ ነው !!!
‎ምዘና አገልግሎት = 058 178 1025
‎Facebook=https://www.facebook.com/www.dma.coc.gov
Telegram=https://t.me/ANRS_OCACA_DM_OCWhatsApp=https://whatsapp.com/channel/0029VbBjKCSF6smuRTq

ደብረ ማርቆስ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ክላስተር ማዕከል በዶሜስቲክ ወርክ ሙያ በተለያዩ ማዕከላት  ምዘና ሲሰጥ በከፊል
24/08/2026

ደብረ ማርቆስ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ክላስተር ማዕከል በዶሜስቲክ ወርክ ሙያ በተለያዩ ማዕከላት ምዘና ሲሰጥ በከፊል

ደብረ ማርቆስ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ክላስተር ማዕከል በነሃሴ ወር በተለያዩ ኮሌጆችና ሙያዎች   ምዘና ሲሰጥ በከፊል
24/08/2026

ደብረ ማርቆስ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ክላስተር ማዕከል በነሃሴ ወር በተለያዩ ኮሌጆችና ሙያዎች ምዘና ሲሰጥ በከፊል

ደብረ ማርቆስ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ክላስተር ማዕከል በፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ  ምዘና ሲሰጥ በከፊል
24/08/2026

ደብረ ማርቆስ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ክላስተር ማዕከል በፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ምዘና ሲሰጥ በከፊል

የደብረ ማርቆሥ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ክላሥተር ማዕከል   ከኮሌጆች ጋር በጋራ የሚሠራቸው ሥራዎች ላይ የመግባቢያ ሰነድ  ሥምምነት ተፈራረመ።==========================...
23/08/2026

የደብረ ማርቆሥ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ክላሥተር ማዕከል ከኮሌጆች ጋር በጋራ የሚሠራቸው ሥራዎች ላይ የመግባቢያ ሰነድ ሥምምነት ተፈራረመ።
======================================
የደብረ ማርቆስ ክላስተር ኮሌጆች 2018 በጀት አፈጻጸም እና 2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ አካሄዱ።

ደብረ ማርቆስ ክላስተር ኮሌጆች የደብረ ማርቆሥ ከተማ አስተዳደር እና የምሥራቅ ጎጃም ዞን ሥራና ክህሎት መምሪያ ሀላፊዎች በተገኙበት የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ በማስተዋወቅ የዉይይት መድረክ አካሂደዋል።

በመድረኩ በ2019 በጀት ዓመት በክላስተር ኮሌጆች የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፣ የደብረ ማርቆሥ ክላሥተር የሙያ ብቃት ምዘና ና ማረጋገጫ ማዕከል ከኮሌጆች ጋር በጋራ የሚሠራቸው ሥራዎች መግባቢያ ሰነድ ቀርቦ የውል ሥምምነት መፈራረም ፕሮግራም ተካሂዷል።

የዕቅድ ትውውቁ እና የውል ሥምምነቱ ዋና ዓላማ በክላስተሩ ውስጥ ያሉ ኮሌጆች በጋራ አቅጣጫ እንዲመሩ፣ የሚከናወኑ ተግባራትን በቅንጅት እንዲፈጽሙ እና የትብብር ስልጠና÷የሙያ ብቃት ምዘና÷ የኤግዚቢሽን፣ የጥነትና ምርምር፣ የቴክኖሎጂ ና ክህሎት ውድድር በተመለከተ በሰፊው ውይይት ተደርጎበታል።

በተለይም የሰልጣኞች ቅባለ ቁጥር መሻሻል፣ በተቋማዊ እና አገር አቀፋ የሙያ ብቃት ምዘና የስልጠና ጥራትን ማረጋገጥ፣የዉስጥ ገቢን ማሳደግ፣2019 ዓ.ም ቴክኖሎጅ ሽግግር ስራ፣ የኢንዱስትሪ ትስስርን ማጠናከር፣ የሰው ኃይልና የተቋም አቅምን ማሳደግ እንዲሁም የተቋማትን የስራ አፈጻጸም በተሻለ ደረጃ ማስመዝገብ በዕቅዶቹ ውስጥ የተካተቱ እና ዉይይት ከተደረገባቸዉ ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል ተጠቃሽ ናቸዉ።

ደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ነሐሴ 17/2018 ዓ.ም

ደብረ ማርቆስ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ክላስተር ማዕከል በደራሽ የስልጠናና የምዘና ማዕከል ምዘና ሲሰጥ በከፊል
23/08/2026

ደብረ ማርቆስ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ክላስተር ማዕከል በደራሽ የስልጠናና የምዘና ማዕከል ምዘና ሲሰጥ በከፊል

ደብረ  ማርቆስ  የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ክላስተር ማዕከል በፍኖተ ዳሞት  ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ምዘናን ሲያስመዝን በከፊል
22/08/2026

ደብረ ማርቆስ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ክላስተር ማዕከል በፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ምዘናን ሲያስመዝን በከፊል

ይነበብ  #ለሁሉም የምዘና ማዕከላት
20/08/2026

ይነበብ

#ለሁሉም የምዘና ማዕከላት

ደብረ ማርቆስ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ክላስተር ማዕከል ከምዘና ማዕከላት ጋር ውይይት አደረገ፡፡~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~...
15/08/2026

ደብረ ማርቆስ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ክላስተር ማዕከል ከምዘና ማዕከላት ጋር ውይይት አደረገ፡፡
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ነሃሴ 8፣2018 ዓ፣ም በአብክመ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ባለስልጣን ደብረ ማርቆስ ክላስተር ማዕከል በስሩ ከሚገኙ የግል የዶሜስቲክ ወርክ/የውጭ ሃገር ስራ ስምሪት ምዘና ማእከላት ባለቤቶችና አመራሮች ጋር ውይት አደረገ፡፡
ውይቱም ብልሹ አሰራርን በመቅረፍና የምዘና ጥራትን ማረጋገጥ፣ የምዘና ማዕከላትን አቅም ማሳደግና ወደ ተመሳሳይ ደረጃ ማምጣት፤ጥራት ያለው ተመዛኝ በምዘና ስርዓቱ እንዲያልፍ ማድረግ እና ብቁ ተመዛኞችን ማቅረብ እንዲሁም በምዘና ማዕከላት ውስጥ ያሉ የአሰራር ጎደሎዎችን ማረም በሚሉ ዓላማዎች ላይ ያጠነጠኑ የትኩረት ጉዳዮች ላይ የተመሰረተ እንደነበረ ታውቋል፡፡

የውይይት መነሻ እንዲሆን በክላስተር ማዕከሉ ሃላፊ በአቶ አስማማው አጥናፉ የመወያያ ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡በፅሁፉ ላይም የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ዓላማዎች በአዋጅ ቁጥር 104/90 በ1990፣ 632/2001 በ2001፣ በ928/ 2008 የወጣውና አሁን የሚተገበርበትን 1246/ 20013 አዋጅ ወጥቶለት በህግ እየተመራ መሆኑን ጠቅሰው መሰረታዊ ዓላማውም የዜጎችን መብት ለማስጠበቅ፣የወኪሎች ሃላፊነት ለመስጠት ፣የስልጠናና የምዘና ተቋማት በህግና ደንብ ተመርተው ዜጎችን እንዲያበቁ፣ ሀገሪቱ ከሌሎች ሀገራት ጋርም ህጋዊ የሁለትዮሽ ስምምነት እንዲኖራትና ህጋዊነቱን አስጠብቆ ዜጎች በሰላም በፈለጉት ሃገር ሄደው ሰርተው እንዲዲኖሩና እንዲመለሱ ለማስቻል እንዲያመች፣ዜጎች ከመሄዳቸው በፊትም በእውቀት፣በክህሎትና በአመለካከት ብቁ እንዲሆኑ የሚስችል ማዕቀፍም መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል፡፡
በመሆኑም መንግስት በዚህ ረገድ ከፍተኛና ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ከሚሰራባቸው ዘርፎች መካከል አንዱና ዋናው እንደሆነ በመጥቀስ የሃገር ውስጥ የስራ ስምሪት ጫናን በመቀነስ፣የውጭ ምንዛሬ ለሃገር በማስገኘት፣የዜጎችን የኑሮ ደረጃ በማሻሻል፣ከሌሎች ሃገራት የክህሎትና የቴክኖሎጂ ሽግግር በማምጣት፣ህገ-ወጥ የዜጎች ዝውውርን እንዲገታ ብሎም እንዲቆም በማድረግ፣ዜጎች በክብርና በደህነት ስራ ሰርተው እንዲመለሱ ቤተሰቦቻቸውንም እንዲጠቅሙ ብሎም የሀገር ገፅታ ግንባታም እንዲያደርጉ በማገዝ ደረጃ ከፍተኛ ጠቀሜታ በመኖሩ የውጭ ሃገር ስራ ስምሪቱ ፋይዳው የጎላ እንደሆነም አስረድተዋል ሃላፊው፡፡

ይሁን እንጅ ሥልጠናውን የሚሰጥ በሙያው የበቃና የሰለጠነ ባለሙያ ባለመኖሩ፣ሥልጠናውም በተቀመጠው ጊዜ መሰረት በልዩ ትኩረት ባለመሰጠቱ፤/21 ቀን/፣በተቀመጠው የስልጠና ርዕሶች/ የብቃት አሀድ/ ሥልጠና በደንብ ተለይቶ ባለመቅረቡ፤ስለ ሰልጣኞች ደህንነት፤መብት እና ግዴታ በትኩረት ባለመሰጠቱ፣በሚሄዱበት ሀገር መሰረታዊ የመግባቢያ ቋንቋ የሚባለውን /አረበኛ እና እንግሊዘኛ/ በትክክል እና በተቀመጠው ልክ ስልጠናው ባለመሰጠቱ፣መሰረታዊ ባህላዊ እሴቶችን እንዲያዉቁም እድል አለመሰጠቱ የሚሉት ሃሳቦች በስልጠናው ላይ የሚታዩ ክፍተቶች መሆናቸውም ተነስተዋል፡፡

ከዚህ ጋር በተያየዘም በምዝገባ ወቅትም የሚከሰቱ ችግሮች እንዳሉም በመጥቀስ በፍጥነት ከነዚህ ችግሮች በመውጣት ችግሮች እንዲታረሙ ተመላክቷል፡፡መረጃዎችንም በአግባቡና በተደራጀ መንገድ ሊያዙ እንደሚገባም መልዕክት ተላልፏል፡፡

በይበልጥም በምዘና ላይ ተሳታፊ የሆኑት ተዋናዮች ማለትም ተመዛኞች፣ መዛኞች፣ አስተባባሪዎችና የምዘና ማዕከሎች ምዘናው በአግባቡ ተጀምሮ እንዲፈፀም የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡም ጥሪው ተላልፏል፡፡ከብልሹ አሰራርም ራስን ፈፅሞ ንፁህ በማድረግ ትውልድንና ሃገርን መታደግ ይገባል ተብሏል፡፤
በመጨረሻም የመልካም አስተዳደር ችግር እንዳይኖር ከማድረግ አንፃር የስም ስህተት ችግርን በደንብ መቅረፍ በመቻል፣መረጃዎችን በአግባቡ አደራጅቶ በመያዝ፣ተመዛኞች ስማቻውን በካፒታል ፊደል ብቻ እንዲፅፉ በማድረግ፣የክላስተር ማእከሉን የአገልግሎት ክፍያንም በወቅቱና በትክክል በመክፈል እና የብቁ ተመዛኞችን ሰርተፊኬት በቶሎ ወስዶ ለተመዛኞች በማድረስ ችግሮች እንዳይኖሩ ማድረግ ይገባል ተብሏል፡፡

Facebook=https://www.facebook.com/www.dma.coc.gov

Telegram=https://t.me/ANRS_OCACA_DM_OCA_CCC

WhatsApp=https://whatsapp.com/channel/0029VbBjKCSF6smuRTqT1r1s

ነሃሴ 8፣2018
ደ/ማርቆስ

‎ምዘናውንናና የምዘና ስርዓቱን በአግባቡና በወጉ በመምራት የዜጎችን ብቃት እውን ልናደርግ  ይገባል ተባለ።‎===========================================‎ደብረ ማርቆስ...
13/08/2026

‎ምዘናውንናና የምዘና ስርዓቱን በአግባቡና በወጉ በመምራት የዜጎችን ብቃት እውን ልናደርግ ይገባል ተባለ።
‎===========================================
‎ደብረ ማርቆስ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ክላስተር ማዕከል የምዘና ስርዓታችንና ጥራት ብቃት ያለው ዜጋ ከመፍጠር አኳያ እንዴት እየተሰጠ መሆኑን ከውጭ ሃገር የስራ ስምሪት መዛኞች ጋር ነሃሴ 07/2018 ዓ፣ም ገመገመ ።

‎ብቁ ዜጋ ማፍራት ሃገሪቱ የምትፈልገው የሁሉም ባለድርሻ አካላት ተግባር በመሆኑ ሁሉም ድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተመላክቷል።

‎ምዘና ዜጎች በስልጠና ያገኙትን እውቀት ተመዝነው ብቁ መሆን አለመሆናቸውን የሚለኩበት ስልት መሆኑን የገለፁት የክላስተር ማዕከሉ ኃላፊ አቶ አስማማው አጥናፉ የምዘና ጥራቱ ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ ችግሮች እየተስተዋሉ መምጣታቸውን አንስተዋል ።

‎ ለምዘና ጥራቱ መጓደል በርካታ መንስኤዎችን ያነሱት ሃላፊው የአንበሳውን ድርሻ የሚወስደው ግን የመዛኞቹ በመሆኑ ለትውልድ ፣ለሃገርና ለራስም ህሊና እረፍት በትክክለኛው መንገድ ብቻና ብቻ በመመዘን ትውልድ ላይ ሊሰሩ እንደሚገባ በፅኑ አሳስበዋል ።

‎ሃላፊው አያይዘውም የምዘና ግብዓቶችን በአግባቡ ያለማረጋገጥ፣እቃዎችን በትክክል መስራት አለመስራታቸውን በደንብ ያለማረጋገጥ ችግር ፣ምዘናውንም በእውቀት ላይ ተመስርቶ የመመዘን ችግር መስተዋል፣ በምዘና ወቅት የተመዛኞች የስም ስህተት መኖርና አንገብጋቢ ችግር ሆኖ መቀጠል ፣የሙስናና የብልሹ አሰራር ስርዓቶችና አዝማሚያዎች እየተከሰቱ መምጣት እና ሌሎችም በፍጥነትና በትኩረት ሊታዩና ሊወገዱ የሚገባቸው አክሳሪና ትውልድ ገዳይ ተግባር መሆናቸውን አንስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል ።

‎መዛኞች በበኩላቸው ድርጊቱን አውግዘው ከችግሮች ፈጥነው በመውጣትና ትክክለኛ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ትውልድ በመፍጠር ለትውልድም ለሃገርም ባለውለታ እንደሚሆኑ ቃል በመግባት ተግባሩ ግን የብዙ ሰዎች ርብርብና መስተጋብርን የሚጠይቅ በመሆኑ ሁሉም ድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

‎በተጨማሪም የመዛኞችን የምዘና ክፍያ እንዲስተካከል ፣የትምህርትና ስልጠናውን ሁኔታ በትኩረት እንዲታይ ፣የምዘና ማዕከላት እና አስተባባሪዎች እንዲሁም ሁሉም የሚመለከተው ሁሉ በየዘርፉ በምዘና ጥራት ላይ በመስራት ትውልድ ማዳን ስራ ላይ ሊሰራ እንደሚገባም ጭምር መልዕክት ተላልፏል ።

‎ "ጥራት ያለው ምዘና በመስጠት ብቁ ዜጋ እናፍራ!"

‎ ነሃሴ 07/2018 ዓ፣ም
‎ ደ/ ማርቆስ

Address

Ambasel Building, Debre Markos
Debra Markos

Telephone

+2510581781025

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ደብረ ማርቆስ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ክላስተር ማእከል posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ደብረ ማርቆስ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ክላስተር ማእከል:

Shortcuts

Share