03/09/2026
የወረዳው መንገድ ትራንስፖርት ጽህፈት ቤት ተጨማሪ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
#ደብረብርሃን ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም (ባሶና ወራና ኮሙኒኬሽን)
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የባሶና ወራና ወረዳ መንገድ ትራንስፖርት ጽህፈት ቤት ለክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በድጋሚ ግምቱ 20 ሺ ብር የሆነ 20 ደርዘን ደብተርና 1 ፓኬት እስክሪቢቶ ድጋፍ አድርጓል።
የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ንጉሴ ፀጋዬ እንደገለፁት በጎ ፈቃድ "በጎነት ለራስ ነው"በሚል እሳቤ ከተሽከርካሪ ባለንብረቶችና ከአሽከርካሪዎች በተገኘ ገንዘብ የህዝብን አንድነትና መተባበርን የሚያጠናክር ትልቅ ተግባር መሆኑን የገለፁ ሲሆን በማህበረሰቡ ውስጥ የሚገኙ ችግረኛና ረዳት የሌላቸውን ወገኖች መደገፍ በክረምት በጎ ፍቃድ ብቻ የሚተገበር ሳይሆን ቀጣይነት ኖሮት በልዩ ትኩረት ሊተገበር እንደሚገባ ተናግረዋል።
የወረዳው ምክትል አስተዳደሪና የትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አፈወርቅ ዘውዴ በበኩላቸው የክረምት የበጎ ፈቃድ ተግባር ትልቅ ሚና ያለው መሆኑን ገልፀው ድጋፉ በችግር ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች በመማሪያ ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይፈናቀሉ ከማስቻሉም በላይ የእርስ በርስ መደጋገፍንና አንድነትን የሚያጠናክር ተግባር መሆኑን ገልፀው ጽ/ቤቱን አመስግነዋል።