በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት

በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ዘላቂ ሰላምና ልማትን በማስፈን ሁለንተናዊ ብልፅግናን እናረጋግጣለን!

የኢትዮጵያ_ማንሰራራት  ጳጉሜ_1 "የእምርታ_ቀን"በመንዝ ማማ ምድር ወረዳ የእመርታ ቀን በስንዴ ክላስተር ጉብኝትና በፓናል ውይይቶች እየተከበረ ይገኛል።በሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ማማ ምድር ወረ...
06/09/2026

የኢትዮጵያ_ማንሰራራት

ጳጉሜ_1 "የእምርታ_ቀን"

በመንዝ ማማ ምድር ወረዳ የእመርታ ቀን በስንዴ ክላስተር ጉብኝትና በፓናል ውይይቶች እየተከበረ ይገኛል።

በሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ማማ ምድር ወረዳ የመጀመሪያው የጳጉሜ ቀን "የእመርታ ቀን" በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል።

ከተረጅነት_ወደ_ምርታማነት እየተደረገ ያለውን ሂደት በወረዳው ዘራም ቀበሌ የተዘራውን የስንዴ ክላስተር በመጎብኘትና የፓናል ውይይት በማድረግ እየተከበረ ሲሆን በጉብኝቱ ላይ የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የፕላንና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማሙሸት የሺጥላ፣ የፓለቲክና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሀብተማርያም የሺጥላ፣ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወይዘሮ ብርቄ ደበበ እንዲሁም የግብርና ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የወረዳ ጠቅላላ አመራሮችና የቀበሌ አመራሮች ተገኝተው ምርታማነትን በማሳደግ ላይ እየተከናወነ ያለውን ተግባር ጎብኝተዋል።



"የእምርታ_ቀን"

የኢትዮጵያ_ማንሰራራት ጳጉሜን 1_"የዕመርታ_ቀን" ንን አስመልክቶ ለተረጂነት ቅነሳ የለማ ልዩ ልዩ የሰብል ምርት የመስክ ጉብኝት በማድረግ ተከበረ።በመሐል ሜዳ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሴ...
06/09/2026

የኢትዮጵያ_ማንሰራራት

ጳጉሜን 1_"የዕመርታ_ቀን" ንን አስመልክቶ ለተረጂነት ቅነሳ የለማ ልዩ ልዩ የሰብል ምርት የመስክ ጉብኝት በማድረግ ተከበረ።

በመሐል ሜዳ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሴክተር መስሪያ ቤቶች ኃላፊዎች ፣ የመንግስት ሰራተኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው ልዩ ልዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት ጳጉሜ1_"የዕመርታ_ቀን' በሚል መሪ ሀሳብ በከተማው ውስጥ በልዩ ልዩ ሰብሎች የለማውን 3.25 ሄክታር የሰብል ምርት የመስክ ጉብኝት በማድረግ ተከብሯል።

በሰብል መስክ ጉብኝቱ ላይ የመሐል ሜዳ ከተማ አስተዳደር የስራና ክህሎት ኃላፊና ምክትል ከንቲባ አቶ ደጀኔ መኮንን ፣ የመሐል ሜዳ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አሸነፍ ተስፋ እና የፓርቲው የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ብስራት ታደግ እና የከተማው የፅ/ቤት ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው አካላት በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተዋል።

በሰብል ምርት ጉብኝቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የከተማው ምክትል ከንቲባ አቶ ደጀኔ መኮንን እንደገለፁት ፣ "በከተማ ግብርናና በከተማ ኢንሼቲቭ ፕሮግራማችን ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ የኢትዮጵያን እምርታን እናረጋግጣለን!" በማለት ገልፀዋል።

በወረዳው ዱዋትና ቄውላ በክላስተር የለማ የስንዴ ሰብል የመስክ ጉብኝት በማድረግ የልምድ ልውውጥ ተደርጓል።

በመስክ ምልከታው የተሳተፉ አካላትም ተረጅነትን ለመቀነስ እና የኢትዮጵያን ማንሰራራት በሁሉም ዘርፍ ውጤታማ ለማድረግ እንደ ከተማ የተሰሩ የከተማ ግብርና ስራዎችና የተለያዩ ልማቶች ተስፋ ሰጪ መሆናቸው እና በቀጣይም የተሻለ ስራ እንሰራለን ብለዋል።

በቀጣዮቹ ቀናትም‎ አምስቱ የጳጉሜን ቀናት የተለያዩ ስያሜዎች ይዘው በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ይከበራሉ፦


#‎ጳጉሜን 1 ፦ "የዕመርታ ቀን"


የኢትዮጵያ ማንሰራራት ጳጉሜ 1  "የእመርታ ቀን”  በደብረ ብርሃን ከተማ በተለያዩ የልማት ሥራዎች ጉብኝት ተከበረ፤ደብረ ብርሃን፤ጳጉሜ 1/2018 ዓ.ም (ደብመኮ):-በደብረ ብርሃን ከተማ ጳ...
06/09/2026

የኢትዮጵያ ማንሰራራት

ጳጉሜ 1 "የእመርታ ቀን” በደብረ ብርሃን ከተማ በተለያዩ የልማት ሥራዎች ጉብኝት ተከበረ፤

ደብረ ብርሃን፤ጳጉሜ 1/2018 ዓ.ም (ደብመኮ):-በደብረ ብርሃን ከተማ ጳጉሜ 1 "የእመረታ ቀን " በሰብልና በኢንዱስትሪ ጉብኝት ተከበረ።

በመርሐ ግብሩ ላይ የደብረ ብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት፣የብልግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ጌታቸውን ጨምሮ አስተባባሪና የከተማ አመራሮች፣የጠባሴ ክፍለ ከተማ የሥራ ኃላፊዎች፣አርሶ አደሮች፣ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።(ደብኮ)



"የእመርታ ቀን

06/09/2026
06/09/2026
የኢትዮጵያ ማንሰራራት‎ጳጉሜ1 የእመርታ ቀን  'እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!"‎በሚል መሪ ቃል በደብረሲና ከተማ አስተዳደር የሌማት ቱርፋት የፓርቲ ኢንሼቲቭ ስራዎችን ጉብኝት በማድረግ ተከበረ።የደብ...
06/09/2026

የኢትዮጵያ ማንሰራራት

‎ጳጉሜ1 የእመርታ ቀን 'እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!"‎በሚል መሪ ቃል በደብረሲና ከተማ አስተዳደር የሌማት ቱርፋት የፓርቲ ኢንሼቲቭ ስራዎችን ጉብኝት በማድረግ ተከበረ።

የደብረሲና ከተማ አስተዳደር በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የስራ መስኮች ላይ በመሰማራት ውጤታማ የሆኑ ወጣቶችን የስራ እንቅስቃሴ በመስክ ምልከታ ጎበኘ።

በዕለቱ መርሃ-ግብር በከተማው ውስጥ ስራ እድል ከተፈጠረላቸው ኢንተርፕራይዞች ጋር የተሰሩ የፓርቲ ኢንሼቲቭ ስራዎች የከተማና የቀበሌ አመራሮች፣የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተጎብኝተዋል።

‎የደብረሲና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ላቀው ደበበ በመርሃ ግብሩ ላይ እንደተናገሩት ከተማ አስተዳደሩ ባለፈው ዓመት በፀጥታ ችግርና በፈተናዎች ውስጥ ሆኖ በርካታ አመርቂ ስራዎች የተከናወኑበት እና የወጣቱን ጥያቄ የተመለሰበት እንደነበር ገልጸዋል።

ከቲባው አክለው፦ከተማው የወጣቶችን ፍላጎት ለማርካት በሚደረገው ርብርብ ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት፣ በርካታ ስራ አጥ ወጣቶችን በማህበር በማደራጀት ወደ ተለያዩ የስራ መስኮች ለማሰማራት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በቀጣይም ሌሎች ስራ አጥ ወጣቶችን ለይቶ ወደ ተለያዩ ቋሚና ጊዜያዊ የስራ መስኮች ለማሰማራት ከተማው ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ከንቲባው አስታውቀዋል።

በዘርፉ የተገኙ ምርቶችም በቀጥታ ለተጠቃሚው መቅረብ መጀመራቸው በገበያው ላይ የሚታየውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት አግዟል ሲሉ የደብረሲና ከተማ ስራና ክህሎት ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ እዮሪካ ሞላ ተናግረዋል።

በመጨረሻም በአሁኑ ወቅት በእንቁላል ጣይ፣ በወተት ላሞች እና በጓሮ አትክልት የስራ ዘርፎች ተሰማርተው ውጤታማ መሆን በመቻላቸው፣ ራሳቸውን ችለው ቤተሰቦቻቸውን ማስተዳደር መጀመራቸውን ስራ እድል የተፈጠረላቸው ኢንተርፕራይዞች ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ማንሰራራት

የኢትዮጵያ መንሰራራትጳጉሜ 1 — የእመርታ ቀንየቀወት ወረዳ አስተዳደር ጳጉሜ 01 የእምርታ ቀንን በፓናል ውይይት አከበረ ። የሀገር ሉዓላዊነት ዛሬ በኢኮኖሚ ነፃነትና በጠንካራ የልማት ስራዎ...
06/09/2026

የኢትዮጵያ መንሰራራት

ጳጉሜ 1 — የእመርታ ቀን

የቀወት ወረዳ አስተዳደር ጳጉሜ 01 የእምርታ ቀንን በፓናል ውይይት አከበረ ።

የሀገር ሉዓላዊነት ዛሬ በኢኮኖሚ ነፃነትና በጠንካራ የልማት ስራዎቻችን ለማጠናከር ሀገራችን ከነበረችበት የውጭ እርዳታና ጥገኝነት ለመውጣት፣ በገበታችን ላይ የምናቀርበውን ምግብ በራሳችን አቅም ማምረትን ዋና አላማችን አድርገን ተነስተናል።

ወረዳውም እመርታን በዘላቂነት በሀገር በቀል የእርሻ ልማት የስንዴ ምርታማነትን ማሳደግ ፣ በሌማት ትሩፋትና በሀገር ውስጥ ምርት ማጠናከሪያ ንቅናቄዎች አማካኝነትም አመርቂ ውጤትና አዳዲስ የስራ እድሎች ተፈጥረዋል ።

የምግብ ዋስትናም ለማረጋገጥ ፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ፣ የግብርና መካናይዜሽን፣ በድህነት ቅነሳ የኢኮኖሚችንን መሰረት ዘላቂ ለማድረግ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ወሳኝ ስራዎች መከናወናቸው በውይይቱ ተነሰተዋል ።

የወረዳው ግብርና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ቅጣው ኃይሌ በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው እነዚህ መሰረታዊ ለውጦች ፈተናዎችን አልፈን ወደ ታላቅ ከፍታ መሸጋገር እንደምንችል ያሳዩን ሲሆን፣ ለአዲሱ ዓመትም የበለጠ ለመስራትና አዳዲስ የስኬት ምዕራፎችን ለመክፈት ትልቅ ብርታት አድርጎ መስራት ይጠበቃል ብለዋል ።

በፓናል ውይይቱ የወረዳው ፕላንና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ላውጋለት ማሞን ጨምሮ ሌሎች አመራሮችና ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን በቀጣይ 2019 የመኸር ምርት ውጤታማ እንዲሆን ለሚከሰቱ ወቅታዊ የአየር ንብረት ስጋቶች የመፍትሔ አቅጣጫ በማስቀመጥ አርሶ አደሩ የተሻለ ምርት እንዲያመርት ማድረግ ላይ በርብርብ መሰራት እንዳለበት የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል ።



#ጳጉሜ 1 — የእመርታ ቀን

የኢትዮጵያ ማንሰራራት “በተግባር የተደገፈ እመርታ ለዘላቂ ምግብ ዋስትና እና ኢኮኖሚያዊ እድገት!”በሰሜን ሸዋ ዞን የእነዋሪ ከተማ አስተዳደርበዛሬው ዕለት **የእመርታ ቀን” በሚል መሪ ሀሳብ...
06/09/2026

የኢትዮጵያ ማንሰራራት

“በተግባር የተደገፈ እመርታ ለዘላቂ ምግብ ዋስትና እና ኢኮኖሚያዊ እድገት!”

በሰሜን ሸዋ ዞን የእነዋሪ ከተማ አስተዳደር
በዛሬው ዕለት **የእመርታ ቀን” በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀውን ልዩ የመስክ ምልከታ ፕሮግራም በስኬት አከናውነናል። የምልከታው ዋና አላማ በከተማችን የሚገኙ የኢንቨስትመንት እና የማህበረሰብ ልማት እንቅስቃሴዎችን በቅርበት በመከታተል፣ ውጤታማነታቸውን ለማረጋገጥ እና ለቀጣይ ስራዎች አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ ነው።
በዕለቱ በዋናነት ሁለት ትልልቅ እና ስትራቴጂካዊ የልማት ፕሮጀክቶች ተጎብኝተዋል፡

የዱቄት ፋብሪካ መስክ ምልከታ፡
ፋብሪካው በአሁኑ ወቅት ያለበትን ሁኔታ ተመልክተናል።
የዶሮ እርባታ ልማት ምልከታ፡
በሁለተኛው ምልከታችን የዶሮ እርባታ ፕሮጀክቱን የጎበኘን ሲሆን፣ በዘመናዊ መንገድ የዶሮዎችን ጤና እና እንክብካቤ በመጠበቅ ከፍተኛ የእንቁላል እና የዶሮ ስጋ ምርት ለገበያ ለማቅረብ እየተሰራ ያለው ስራ ተጎብኝቷል። ፕሮጀክቱ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና የስጋና እንቁላል አቅርቦት እጥረትን ለመቅረፍ ትልቅ እመርታ ማሳየቱ ተረጋግጧል።

የቀጣይ አቅጣጫ እና የጋራ መግባባት፡

በመስክ ምልከታው ማጠቃለያ ላይ ከተሳታፊዎች እና ከባለሃብቶች ጋር በተደረገው ውይይት፣ ያሉትን ስኬቶች አጠናክሮ በመቀጠል የምርት ጥራት እና መጠንን የበለጠ ለማሳደግ፣ የሚገጥሙ ተደራሽነት እና የመሰረተ ልማት እጥረቶችን በጋራ ለመፍታት ስማምነት ላይ ተደርሷል።

እነዚህ መሰል የልማት እንቅስቃሴዎች የነገዋን ብሩህ የወደፊት ጊዜ የሚያመላክቱ በመሆናቸው፣ ድጋፋችን ተጠናክሮ ይቀጥላል!
#የእመርታቀን

Address

Debre Birhan Shewa
DEBERBRHAN

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share