06/01/2026
ለሁሉም የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳምን ወደ ቀደመ ቤቱ ሊመልስ፤ የተከፈተችውን ሲኦልን ወና አድርጎ የተዘጋችውን ገነት ሊከፍት ቃልኪዳን ነበረው።
ይህንንም ቃል ኪዳን ከድንግል ማርያም በመወለድ፤ ሰው ሆኖ የሰውን ልጅ ልያድን ወደዚህች ዓለም መጥቷል።
የሰማዩም የምድሩም ገዢ፤ የፍጥረት ሁሉ ጌታ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ በንግስናው ሳይሆን በትህትናው በከብቶች በረት ተወለደ። ይህ ብዙ ምስጢር ያለው ፤ እልፍ ትምህርት የምንቀስምበት ልዩ በዓል ነው።
ይህን ታላቅ በዓል ስናከብር ከተረፈን ላይ ሳይሆን ካለን ላይ ቀንሰን ለሌሎች በመትረፍ፣ በመደጋገፍ፣ በመተሳሰብ፣ ይበልጥ የምንቀራረብበት፤ ለሰው መሆንን የምንማርበት፤ በአብሮ የመኖር ኢትዮጵያዊ ትውፊቶቻችንን የበለጠ በማጥበቅ እንዲሁም የከተማችንን የልማት ስራዎች በተቀናጀ መልኩ በመከወን ሊሆን ይገባል።
ደብረ ብርሃን ከተማችን ከመቸውም በላይ የኢንቨስትመንት መዳረሻነቷን አጠናክራ እየቀጠለች ትገኛለች፤ ስለሆነም በሀሉም ዘርፎች ከተማችን አሁንም ቢሆን ለኢንቨስትመንት የሚሆን መሬቶችን በማዘጋጀት አልሚዎችን እየተጠባበቀች ትገኛለች።
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብና የአብሮነት በዓል እንዲሆንም ከልብ እየተመኘሁ፡በድጋሜ ለመላው የከተማችን ነዋሪዎች እና ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም ለክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ።
መልካም የገና በዓል ይሁንላችሁ !