Amhara North Shewa Zone Communication

Amhara North Shewa Zone  Communication ሰሜን ሸዋ ዞን በግምት 8 degree 38’ --- 10 degree 42’ ሰሜን ላቲቲዩድ 38 degree 40’ – 40 degree 43’ ሎጊትዩድ

ደብረብርሃን የተቆረቆረችውና የተሰየመችው ከ5ዐዐ ዓመት በፊት በ1446 ገደማ በአፄ ዘርዓያዕቆብ /1426 – 146ዐ/ ነበር፡፡
ከተማዋ ቀድሞ ደብረ ኢባ በመባል የምትታወቅ ሲሆን የንጉሱ የግራ በአልቲሐት ርስት ነበረች፡፡
በ144ዐ ዎቹ መጀመሪያ ንጉሱ ጐበኟትና ደስ ስለተሰኙባት የድንኳን ከተማቸውን ከተሙባት፡፡ አሁንም የስላሴ ቤ/ክርስቲያን በሚገኝበት ቦታ ላይ ሶስት አብያተ ክርስቲያናት ነበሩ፡፡
ከተማዋ ስያሜዋን ያገኘችው ለስዕልና ለመስቀል አንሰግድም የሚሉ የእስጢፋኖስ ተከታዮች በ1446 ከንጉሱና ከካህናቱ ጋር በጉባኤ ክርክር ላይ አቋማቸውን አንለውጥም በማለታቸው ምላሣቸው ተቆርጦ እንዲገደሉ ተፈረደባቸው ፍርዱ በተፈፀመ በ

38ኛው ቀን በስላሴ ቤ/ክርስቲያን “ ብርሃን “ ታዬ ይባላል፡፡ ንጉሱም በመዋዕለ ዜናቸው ይህንኑ ማየታቸውን ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡ እስጢፋኖሳውያኑ ላይ ለተፈረደው ቅጣት ለትክክለኛነቱ የታየው ብርሃን አምላካዊ ማረጋገጫ ነው በማለት ንጉሱ ከተማዋን ደብረብርሃን ብለው መሠየም ለ14 ዓመት በከተማዋ ኖረውባታል፡፡

‎በሰሜን ሸዋ ዞን የአረርቲ ከተማ አስተዳደር ጠቅላላ አመራሮች በወቅታዊ ስራዎችና የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት አድርገዋል።‎‎በውይይቱ ላይ የሰሜን ሸዋ ዞን ስራ እና ክህሎት መምሪያ ዋና ...
30/04/2026

‎በሰሜን ሸዋ ዞን የአረርቲ ከተማ አስተዳደር ጠቅላላ አመራሮች በወቅታዊ ስራዎችና የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት አድርገዋል።

‎በውይይቱ ላይ የሰሜን ሸዋ ዞን ስራ እና ክህሎት መምሪያ ዋና ሃላፊ አቶ ብርሃን ጨርቆስ የተገኙ ሲሆን በቀጣይ ቀናትና ሳምንታት የአመራሩን ሚና በሚሹ የምርጫ ፣የልማት እና የሰላም ስራዎች ዙሪያ ወይይት ተደርጎ በቀጣይ የሚከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዬች ላይ አቅጣጫ ተቀምጧል።

የሰሜን ሸዋ ዞን ገቢዎች መምሪያ የ9 ወር ዕቅድ አፈጻጸሙን ገመገመ። መምሪያው በ2018 በጀት ዓመት የ9 ወር ዕቅድ አፈጻጸሙን ከጠቅላላ ሠራተኞ እና ከወረዳና ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤ...
29/04/2026

የሰሜን ሸዋ ዞን ገቢዎች መምሪያ የ9 ወር ዕቅድ አፈጻጸሙን ገመገመ።

መምሪያው በ2018 በጀት ዓመት የ9 ወር ዕቅድ አፈጻጸሙን ከጠቅላላ ሠራተኞ እና ከወረዳና ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት ሃላፊዎች ጋር በቪዲዮ ሚቲንግ ገምግሟል፡፡

የመምሪያው ሃላፊ ወይዘሮ ቀለም ተስፋዬ በበጀት ዓመቱ ለመሰብሰብ ከታቀደው በ9 ወሩ ከመደበኛ ገቢ 3 ነጥብ 66 ቢሊየን ከከተማ አገልግሎት ገቢ 302 ነጥብ 2 ሚሊዬን በድምሩ 3 ነጥብ 96 ቢሊየን ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 73 ነጥብ 6 በመቶ መፈፀም ተችሏል ብለዋል፡፡

ገቢው ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በብልጫ የተሰበሰበ ሲሆን 45.6 በመቶ የገቢ እድገት ያሳየ መሆኑን ገልፀዋል ፡፡ ከክልሉ ካሉ ዞኖችም በ9ወሩ ሲወዳደር የተሻለ ገቢ በመሰብሰብ ቀዳሚነት ማግኘቱን ተናግረዋል::

እስከ መጋቢት 30/2018 ዓ.ም ድረስ በተደረገው ርብርብ በሁሉም የትኩረት መስኮች በጥንካሬና ትኩረት የሚደረግባቸውን በመገምገም ከወረዳና ከተሞች የተሻለ የፈፀሙ ተሞክሮ እንዲያርቡ እዲሁም የአፈጻጸም ችግር የታየባቸው ለምን እንደወደቁ ሪፖርት እንዲያቀረቡ በማደረግ ግምገማው ተካሂዷል፡፡

ሃላፊዋ በቀጣይ ቀሪ ወራቶች የሚሰሩ የትኩረት አቅጣጫዎች በተመለከተ በዝርዝር አቅርበዋል

የገቢ ተቋሙ አመራርና ሠራተኞች መደበኛ ሥራቸውን በወቅቱና በጊዜው እንዲፈፅሙ ድጋፍና ክትትል ሥራውን አጠናክሮ ማስቀጠል ይኖርብናል ሲሉም የቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

በመጨረሻም በጥቅል ስራዎች በ9 ወሩ የተሻለ አፈጻጸም ያላቸው ወረዳና ከተማ ገቢ ጽ/ቤቶች ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለወጡ ሽልማት ተሰጥቷል፡፡

በዚህም መሠረት ከወረዳ
1ኛ. ሞጃና ወደራ ወረዳ ኮምፒውተር፤
2ኛ .መንዝ ማማ ምድር፤ ኮምፒውተር፤
3ኛ. አንኮበር ወረዳ የዋንጫ የሰርተፍኬት ሽልማት ተሰጥቷል፤

ከከተማ አስተዳደር
1ኛ ቡልጋ ከተማ ኮምፒውተር፤
2ኛ አረርቲ ከተማ ኮምፒውተር፤
3ኛ መሀልሜዳ ከተማ የዋንጫ እና ሰርተፍኬት ሽልማት ተሰጥቶ ግምገማው ተጠናቋል፡፡

ቴክኖሎጂን ማሳደግ የክልሉ መንግሥት  የትኩረት አቅጣጫ ነው።  የአማራ ክልል ሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በመተባበር በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ያስለ...
29/04/2026

ቴክኖሎጂን ማሳደግ የክልሉ መንግሥት የትኩረት አቅጣጫ ነው።

የአማራ ክልል ሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በመተባበር በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ያስለማውን የኩነቶች ምዝገባ ሲስተም ተረክቧል።

የአማራ ክልል ሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ኀላፊ መዓዛ በዛብህ የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ዘመናዊ ዲጂታል ሥርዓትን እንዲከተል ለማድረግ በርካታ ሥራዎች ሢሠሩ መቆየታቸውን አንስተዋል። የለማው ቴክኖሎጂ ጥራት ያለውን መረጃ ለማደራጀት ያግዛልም ብለዋል።

የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት በክልሉ በ477 የምዝገባ ጣቢያዎች ተግባራዊ እየተደረገ መኾኑን ተናግረዋል። አሠራሮችን በማሻሻል ውጤታማ ሥራዎች መሥራታቸውንም አንሰተዋል።

በዚህም ከ11 ሚሊዮን በላይ ብር ማዳን እና ብልሹ አሠራርን የመቀነስ ሥራ መሠራቱን ተናግረዋል። የኩነቶች ምዝገባ ሲስተም በአጭር ጊዜ የጠራ መረጃ ለመሠነድ ያግዛል ነው ያሉት።

በጸጥታ ችግር ውስጥ ያሉ አካባቢዎችም ጭምር ምዝገባ እንዲካሄድ እየተደረገ ነው ብለዋል። ቴክኖሎጂው በቅንጅት መሠራቱንም አንስተዋል። የኩነቶች ምዝገባ ሲስተም ፈጣን እና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችልም ተናግረዋል።

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ኘሬዝዳንት መንገሻ አየነ (ዶ.ር) ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ባለፈ በቴክኖሎጂው ዘርፍ በርካታ ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል ብለዋል። ዩኒቨርሲቲው በቴክኖሎጂ ፈጠራ፣ በምርምር ሥራዎች እና በማኅበረሰብ አቀፍ አገልግሎት በርካታ ሥራዎችን እየሠራ መኾኑን አንስተዋል።

በተለይም መፍትሔ አመላካች የሲስተማ ማልማት እና ማበልጸግ ሥራዎች እየሠራ ነው ብለዋል። የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ሲሰተሙ የነበሩ ችግሮችን ሊፈታ የሚችል መኾኑን አንስተዋል። በክልሉ ለቀልጣፋ አገልግሎት የሚያገለግሉ ሲስተሞች በማልማት ለተቋማት ተደራሽ እያደረገ ይገኛል ነው ያሉት።

በቀጣይም ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የቴክኖሎጂ ማልማት ሥራዎች እንደሚሠሩም ገልጸዋል። የጠራ መረጃን ለመሰነድ ቴክኖሎጂን መጠቀም እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል።

የአማራ ክልል ኘላን እና ልማት ቢሮ ኀላፊ ደመቀ ቦሩ (ዶ.ር ) የክልሉ የ25 ዓመት አሻጋሪ የዕድገት እና ዘላቂ የልማት ዕቅድ ታቅዶ እየተሠራ መኾኑን ገልጸዋል።
ከዕቅዱ የትኩረት አቅጣጫ መካከል አንዱ ቴክኖሎጂ መኾኑንም ተናግረዋል።

የሲቪል ምዝገባ ዲጂታል መኾን የሕግ፣ የአሥተዳደር እና የስታትስቲክስ አገልግሎቶችን የማጠናከር ድርሻው ከፍተኛ ነው ብለዋል። ይህን ተግባር እስከ ቀበሌ ድረስ ተደራሽ በማድረግ በቴክኖሎጂ መሰነድ እንደሚገባም ተናግረዋል።

ቴክኖሎጂ ጥራት ያለው መረጃ በመሰነድ የነበሩ ችግሮችን ለመፍታት አይነተኛ መንገድ ነው ብለዋል።

የአሚኮ

ፅንፈኛው ቀብሮት የነበረ መሣሪያና ተተኳሽ በቁጥጥር ስር ውሏል። የሰሜን ምስራቅ ዕዝ አንድ ኮር በግዳጅ ቀጠናው በመንቀሳቀስ የህዝቡንና የአካባቢውን ሰላም ሲያውክ የነበረውን የፅንፈኛ ቡድን ...
29/04/2026

ፅንፈኛው ቀብሮት የነበረ መሣሪያና ተተኳሽ በቁጥጥር ስር ውሏል።

የሰሜን ምስራቅ ዕዝ አንድ ኮር በግዳጅ ቀጠናው በመንቀሳቀስ የህዝቡንና የአካባቢውን ሰላም ሲያውክ የነበረውን የፅንፈኛ ቡድን መቆጣጠር እንደቻለ የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ምክትል አዛዥ ለውጊያ ድጋፍ ሜጀር ጀነራል ሻምበል ፈረደ ገልፀዋል።

ኮሩ ሰሞኑን ባካሄደው ስምሪት በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ አካባቢ እየተሹሎከሎከ ሰላማዊ ሰዎችን ሲያግት እና የአካባቢውን ሰላም ሲያደፈርስ የነበረውን ፅንፈኛ ቡድን መውጫ እና መግቢያ እንዳያገኝ ማድረግ መቻሉን ምክትል አዛዡ አሥረድተዋል።

ፅንፈኛው ለእኩይ አላማው መፈፀሚያ ሊጠቀምባቸው የነበሩ በርካታ ተተኳሾችን እና የጦር መሳሪያዎችን ከቀበረበት ማውጣት ተችሏል ያሉት ሜጄር ጄኔራል ሻምበል ፈረደ ቡድኑ የጦር መሳሪያዎችን እና ተተኳሾችን በየጫካው መቅበሩ የሰራዊታችንን ፈጣን ተነቃናቂነት የሚያመላክት መሆኑንም ጠቁመዋል።

ኮሩ አስተማማኝ ወታደራዊ እና ስነ-ልቦናዊ ዝግጁነቱ የተረጋገጠ እንደሆነ ያወሱት ምክትል አዛዡ አካባቢውን ወደ ቀደመ ሰላሙ የመመለሱ ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። ሜጀር ጀነራል ሻምበል አያይዘውም ከፅንፈኛው ጎን ተሰልፈው የአካባቢውን ሰላም ሲያደፈርሱ የቆዩ 08 ታጣቂዎች እጃቸውን መስጠታቸውን ተናግረዋል።

ዘገባው የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ሚዲያ እና ህዝብ ግንኙነት ነው

በግሼ ወረዳ በቀጣይ  ወራት  በሚሰሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች  የምክክር መድረክ ተደረገበሰሜን ሸዋ ዞን የግሼ ወረዳ አመራሮችና ከዞን ደጋፊ አመራሮች ጋር በቀጣይ በወረዳዉ ላይ...
29/04/2026

በግሼ ወረዳ በቀጣይ ወራት በሚሰሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች የምክክር መድረክ ተደረገ

በሰሜን ሸዋ ዞን የግሼ ወረዳ አመራሮችና ከዞን ደጋፊ አመራሮች ጋር በቀጣይ በወረዳዉ ላይ በሚሰሩ የልማት:የሰላምና የመልካም አስተዳደር ስራዋች ዙሪያ ምክክር ተደርጎል

የወረዳዉ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ቢልልኝ ተድላ እንደተናገሩት የመንግስትና የፓርቲ አደረጃጀቶችን በማጠናከር የተሰሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዋች እንዲሁም 7ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ የቅድመ ዝግጅት ስራ በተመሳሳይ የሰላምና ፀጥታ ስራ እየተሰሩ መሆኑን ገልፅዋል ቀጣይ ባሉ ወራትም እነዚህ ስራዋች ተጠናክረዉ እንደሚሰሩ ሀሳብ አቅርበዋል

የወረዳዉ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከፍሌ አበራ እንደተናገሩት በወረዳዉ ላይ የተጀመሩ የሰላምና ፀጥታ ስራዋች እንዲሁም የልማትና የመልካም አስተዳር ስራዋች አመራሩና ማህበረሰቡ በቅንጅትና በትብብር እየሰራ በመሆኑ እና የወረዳችን ህዝብ ሰላምና ልማት ፈላጊ ስለሆነ ከመንግስ ጎን ሆኖ እያገዘ መሆኑንና የወረዳ አመራሩም የቻለዉን ሁሉ ስራ እየሰራ መሆኑንና ቀጣይ በቀሪ ወራት የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዋች እንዲሁም 7ኛዉ ሀገራዊ ምርጫና የሰላምና ፀጥታ ስራዋች ተጠናክረዉ እንደሚሰሩ ገልፅዋል ::

የሰሜን ሸዋ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ም/ሀላፊ እና የወረዳዉ ደጋፊ አመራር አቶ አባይ ድሌ እንደተናገሩት የግሼ ወረዳ ህዝብና አመራር በቅንጅትና በትብብር እየሰሩት ያለዉን የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዋችና በተመሳሳይ የሰላምና ፀጥታ ስራ እንዲሁም 7ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ ቅድመ ዝግጅት ስራ መልካም መሆኑን በማንሳት አመራሩንና ማህበረሰቡን አመስግነዋል :: በቀጣይ ወራት መሰራት የሚገባቸዉ የፓርቲና የመንግስት ስራዋች እንዲሁም የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዋች 7ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ የቅድመ ዝግጅት ስራ ተጠናክረዉ እንዲሰሩ ተናግረዋል :: በተጨማሪም 7ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የመንግስትና የፓርቲ አደራጀጀቶችን አጠናክረን በትብብር መስራት እንደሚገባ ገልፅዋል ::

የ105 አየር ወለድ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኒል አሰፋ አየለ እንዳሉት የወረዳዉ አጠቃላይ ማህበረሰብ ሰላም ወዳድና ልማት ፈላጊ እንዲሁም ከመንግስት ጎን ሆኖ አሁን የተገኘዉን አንፃራዊ ሰላም ወደ ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ የወረዳ አመራሩ እየሰራ ያለዉን ስራ አመስግነዉ በቀጣይ ወራት የወረዳዉን ሰላምና ፀጥታ ስራ እንዲሁም 7ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የወረዳዉ አመራርና ከማህበረሰቡ ጋር በጋራ ሀኖ እየሰራ ያለዉ ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዉ የ105 አየር ወለድ ከፍለ ጦር ከጎናቸዉ ሆኖ የተጀመረዉን ህግ የማስከበር ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፅዋል !!!!
#የግሼ ወረዳ ኮሙኒኬሽን

የትራንስፖርት ታሪፍ በተወሰነው መሰረት እንዲቀጥል ትዕዛዝ ተላለፈየትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የትራንስፖርት ታሪፍ በተወሰነው መሰረት ብቻ እንዲቀጥል ተዕዛዝ አስተላልፏል።ሚኒስቴሩ ...
29/04/2026

የትራንስፖርት ታሪፍ በተወሰነው መሰረት እንዲቀጥል ትዕዛዝ ተላለፈ

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የትራንስፖርት ታሪፍ በተወሰነው መሰረት ብቻ እንዲቀጥል ተዕዛዝ አስተላልፏል።

ሚኒስቴሩ የትራንስፖርት አገልግሎት ወደ መደበኛ ሁኔታ መመለሱን ለማሳወቅ ባወጣው መግለጫ÷ በመካከለኛው ምሥራቅ የተከሰተው ግጭት በዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አሳድሮ የነዳጅ ዋጋ ግሽበትና በአቅርቦት ላይ መስተጓጎል እንዲፈጠር አድርጓል ብሏል።

ይህም ሁኔታ በኢትዮጵያ የናፍታ ዕለታዊ አቅርቦትን ከ9 ሚሊየን ሊትር ወደ 4 ነጥብ 5 ሚሊየን ሊትር እንዲቀንስ አድርጎ በትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የሚታወቁ መስተጓጎሎችን አስከትሎ እንደነበር አስታውሷል።

መንግሥት ይህንን ችግር በፍጥነት ለመቆጣጠር የታሪፍ ማሻሻያ፣ የአቅርቦት አደረጃጀት ማሻሻል እና የሎጂስቲክስ ቅንጅት ማጠናከርን ጨምሮ በርካታ አስቸኳይ እና ዘላቂ ርምጃዎች መውሰዱን አመልክቷል።

ይህም የውጭ ጫናዎች ቢኖሩም የሀገር ውስጥ ኢኮኖሚ መረጋጋትን በመጠበቅ እና የሕዝብ አገልግሎቶች እንዳይቋረጡ በማድረግ በኩል መንግሥት የሕዝብ ጥቅምን በማስቀደም የሚከተለውን የፖሊሲ አቅጣጫ የሚያሳይ መሆኑን አስረድቷል።

ዛሬ የገንዘብ ሚኒስቴር በይፋ እንዳሳወቀው የነዳጅ አቅርቦት ወደ መደበኛ ሁኔታው ተመልሷል ያለው ሚኒስቴሩ÷ ይህ ሁኔታ በትራንስፖርት ዘርፍ የተፈጠሩ መስተጓጎሎች በፍጥነት እንዲፈቱ ያስችላልም ብሏል።

በመሆኑም ከዛሬ ጀምሮ ቀደም ሲል በነዳጅ እጥረት ምክንያት የተፈጠሩ የትራንስፖርት አገልግሎት መስተጓጎሎች ሙሉ በሙሉ እንዲቀረፉ፣ ከአዲስ አበባ እስከ ክልሎች የሚገኙ ሁሉም የዘርፉ አመራሮች እና ተዋናዮች ታሪፍ በተወሰነው መሰረት ብቻ እንዲቀጥል በጥብቅ እንድከታተሉና ትግበራውንም በጋራ ግብረ ኃይል እንዲያረጋግጡ አሳስቧል፡፡

መንግሥት የሕዝብ ኑሮ መረጋጋትን ማረጋገጥ፣ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ቀጣይነትን መጠበቅ እና የትራንስፖርት አገልግሎት በዘላቂ መልኩ እንዲጠናከር ያለውን ቁርጠኝነት ይቀጥላል ሲልም አስገንዝቧል።

ኤፍ ኤም ሲ

በሲያደብርና ዋዩ ወረዳ የ2018 በጀት ዓመት የ9 ወር የቁልፍና አበይት ተግባራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ። በመድረኩ ላይ የሰሜን ሸዋ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዘው...
29/04/2026

በሲያደብርና ዋዩ ወረዳ የ2018 በጀት ዓመት የ9 ወር የቁልፍና አበይት ተግባራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ።

በመድረኩ ላይ የሰሜን ሸዋ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዘውገ ንጉሴ፣ የወረዳው አመራሮች፣የተቋማት የማኔጅመንት አባላትና የሚመለከታቸው አካላት የተገኙ ሲሆን፣ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተከናወኑ ቁልፍና እና አባይት ተግባራት በዝርዝር ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

የሲያደብርና ዋዩ የሲቪል ሰርቪስ ጽ/ት ቤት መሥሪያ ቤቱ የሰው ኃይል ልማትን ለማሳለጥ፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻልና የመንግሥት ሠራተኛውን አቅም ለመገንባት በቁልፍ ተግባራት ረገድ ያከናወናቸው ተግባራት ቀርበዋል። የታዩ ጥንካሬዎችና የቀሩ ሥራዎች ተለይተዋል።

የሲያደብርና ዋዩ የፕላን ጽ/ት ቤት በወረዳው ውስጥ የልማትና የመልካም አስተዳደር ዕቅዶች ክትትልና ግምገማ በማድረግ አኳያ የተከናወኑ ተግባራት ቀርበዋል። የሀብት አጠቃቀምን ውጤታማ ለማድረግና ፕሮጀክቶች በተቀመጠላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ የተደረገው የቁጥጥር ሥራ በሪፖርቱ ተመላክቷል።

በመድረኩ የተገኙት አቶ ዘውገ ንጉሴ የወረዳው የልማት ጉዞ ስኬታማ እንዲሆን የሲቪል ሰርቪሱ ተቋማዊ አቅም መጠናከርና አባይት ተግባራትን አጠናክሮ ማስቀጠል እንዲሁም ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተመዘገቡ ስኬቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉና የታዩ ድክመቶች ደግሞ በቀሪው ወራት እንዲታረሙ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተገኝወርቅ ሸዋዬ አንድን ተቋሙ ውጤታማ ለማድረግ ግልፅ የሆነ እቅድና አላማ በመያዝ በፈጣን መግባባት በመያዝ አባይትና ቁልፍ ተግባራትን አጣጥሙ መምራት ያስፈልጋል ብለዋል።

የቀረቡትን ሪፖርቶች መነሻ በማድረግ የታዩ ጥንካሬዎች ወስዶ ያሉትን ክፍተቶች ሞልቶ መሄድ ያስፈልጋል ያሉት የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና መሬት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተፈሪ በሱፍቃድ ሲሆኑ በቀጣይ ለታቀዱ ተግባራት ስኬታማነት በቁርጠኝነት መሥራት እና የሀብት አጠቃቀማችንን በአግባቡ መያዝ ይጠበቃል ብለዋል።

ቁልፍ ተግባራትን በማጠናከር ለአባይት ተግባራት ማሳለጫ በማድረግ የተሻለ ስራ መስራትና ማህበረሰባችንን ተጠቃሚ ማድረግ ያስፈልገናል ያሉት የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ፕላን ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ወርቁሃ ምንዳሁን ብለዋል።

አያይዘውም በ9 ወራት የታዩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠልና የታዩ ክፍተቶችን በዝርዝር በመለየት በቀሪዎቹ ወራት ዕቅዱን በስኬት ለማጠናቀቅ ርብርብ መደረግ እንዳለበት አሳስበዋል።
ሲያደብርናዋዩ ወረዳ ኮሙኒኬሽን

‎የሚሊሻ  30ኛ አመት የምስረታ በዓል "በመስዋዕትነት የፀና በጀግንነት የታጀበ ህዝባዊ አገልጋይነት" በሚል መሪ ሀሳብ ተከበረ።‎‎በሰሜን ሸዋ ዞን አሳግርት ወረዳ የሚሊሻ 30ኛ ዓመት ምስረ...
29/04/2026

‎የሚሊሻ 30ኛ አመት የምስረታ በዓል "በመስዋዕትነት የፀና በጀግንነት የታጀበ ህዝባዊ አገልጋይነት" በሚል መሪ ሀሳብ ተከበረ።

‎በሰሜን ሸዋ ዞን አሳግርት ወረዳ የሚሊሻ 30ኛ ዓመት ምስረታ በዓል "በመስዋዕትነት የፀና በጀግንነት የታጀበ ህዝባዊ አገልግግሎት" በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ ፕሮግራሞች በዛሬው ዕለት በድምቀት ተከብሮ ውሏል።

‎በምስረታ በዓል አከባበሩ ላይ የሰሜን ሸዋ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ሀላፊ አበባው መሰለ፣112ኛ አየር ወለድ ክ/ጠር ተራራዉ 4ኛ ሻለቃ አዛዥ ሻምበል ወንድምነዉ በስፋት ፣የአሳግርት ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አላዩ ብሬ፣ የወረዳው የብልጽግና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ እሱባለው ሀይሌን ጨምሮ አመራሮችና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።

‎መስዋዕትነት እየከፈላችሁ ሰላም የምታፀኑ የሚሊሻ አባላት እንኳን ለ30ኛ አመት የምስረታ በዓል አደረሳችሁ በማለት ፕሮግራሙን ያስጀመሩት የአሳግርት ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አላዩ ብሬ ሚሊሻ ከሌሎች ከሰራዊቱ ጋር ተቀናጅቶ ሀገርን ከመፍረስ የታደገ ሃይል ነው ብለዋል።

‎ሚሊሻ በክልሉና በወረዳው ተፈጥሮ የነበረውን ወቅታዊ የፀጥታ ችግርን በመቀልበስ ሰላማን በማረጋገጥ አንፀባራቂ ድሎችን በማስመዝገብ የሚታይ የልማት ስራዎች እንዲቀጥሉና ኢኮኖሚው እንዲነቃቃ ማድረጉንም ገልጸዋል

‎አቶ አላዩ የፀጥታ ሃይሉ በገባው ቃልኪዳን ሀገርን ከመፍረስ የሚታደግ በመሆኑ ለተተኪ ትውልድ የተሻለች ሀገር ለማስተላለፍ አሁንም ሰላምን ማጽናት እንደሚገባው አሳስበዋል።

‎የወረዳው ሚሊሻ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ገድሉ እሸቴ እለቱን አስመልክተው የመወያያ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን የሚሊሻ ተቋም ከ1988ዓ/ም ጀምሮ በአዋጅ ህግ ተቋቁሞ በተሻለ የሰው ሀይል የተደራጀ ተልዕኮውን በማሳደግ ከደጀንነት ወደ መደበኛ ተዋጊነት እያደገ ያለ የሰላም አስከባሪ ሃይል መገንባት ተቸሏል ተብሏል።

ህዝባዊ ሚሊሻዎች ‎ጫካ የገቡ ሀይሎች የሰላም አማራጭ እንዲከተሉ፣ የመንግስት መዋቅሩ ተረጋግቶ ህዝብ የማገልገል ሚናውን እንዲወጣና 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ መንገድ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የማድረግ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ በምስረታ በአል አከባበሩ የተገኙ ተጋባዥ እንግዶች አስገንዝበዋል።

‎በመጨረሻም ከሰሜኑ ጦርነት ጀምሮ እስከ አሁኑ የክልላችን ቀውስ የሀገርና የህዝብን ክብር ከፍ ላደረጉ፣ ዋጋ ለከፈሉና ለቆሰሉ ሀገራቸውን በክብር አገልግለው ለተሰው ጀግና ሚሊሻዎችና ቤተሰቦቻቸው የዕውቅና እና የክብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በሲያደብርና ዋዩ ወረዳ የ2018 በጀት ዓመት የ9 ወር የቁልፍና አበይት ተግባራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ። በመድረኩ ላይ የሰሜን ሸዋ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዘው...
29/04/2026

በሲያደብርና ዋዩ ወረዳ የ2018 በጀት ዓመት የ9 ወር የቁልፍና አበይት ተግባራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ።

በመድረኩ ላይ የሰሜን ሸዋ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዘውገ ንጉሴ፣ የወረዳው አመራሮች፣የተቋማት የማኔጅመንት አባላትና የሚመለከታቸው አካላት የተገኙ ሲሆን፣ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተከናወኑ ቁልፍና እና አባይት ተግባራት በዝርዝር ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

የሲያደብርና ዋዩ የሲቪል ሰርቪስ ጽ/ት ቤት መሥሪያ ቤቱ የሰው ኃይል ልማትን ለማሳለጥ፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻልና የመንግሥት ሠራተኛውን አቅም ለመገንባት በቁልፍ ተግባራት ረገድ ያከናወናቸው ተግባራት ቀርበዋል። የታዩ ጥንካሬዎችና የቀሩ ሥራዎች ተለይተዋል።

የሲያደብርና ዋዩ የፕላን ጽ/ት ቤት በወረዳው ውስጥ የልማትና የመልካም አስተዳደር ዕቅዶች ክትትልና ግምገማ በማድረግ አኳያ የተከናወኑ ተግባራት ቀርበዋል። የሀብት አጠቃቀምን ውጤታማ ለማድረግና ፕሮጀክቶች በተቀመጠላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ የተደረገው የቁጥጥር ሥራ በሪፖርቱ ተመላክቷል።

በመድረኩ የተገኙት አቶ ዘውገ ንጉሴ የወረዳው የልማት ጉዞ ስኬታማ እንዲሆን የሲቪል ሰርቪሱ ተቋማዊ አቅም መጠናከርና አባይት ተግባራትን አጠናክሮ ማስቀጠል እንዲሁም ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተመዘገቡ ስኬቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉና የታዩ ድክመቶች ደግሞ በቀሪው ወራት እንዲታረሙ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተገኝወርቅ ሸዋዬ አንድን ተቋሙ ውጤታማ ለማድረግ ግልፅ የሆነ እቅድና አላማ በመያዝ በፈጣን መግባባት በመያዝ አባይትና ቁልፍ ተግባራትን አጣጥሙ መምራት ያስፈልጋል ብለዋል።

የቀረቡትን ሪፖርቶች መነሻ በማድረግ የታዩ ጥንካሬዎች ወስዶ ያሉትን ክፍተቶች ሞልቶ መሄድ ያስፈልጋል ያሉት የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና መሬት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተፈሪ በሱፍቃድ ሲሆኑ በቀጣይ ለታቀዱ ተግባራት ስኬታማነት በቁርጠኝነት መሥራት እና የሀብት አጠቃቀማችንን በአግባቡ መያዝ ይጠበቃል ብለዋል።

ቁልፍ ተግባራትን በማጠናከር ለአባይት ተግባራት ማሳለጫ በማድረግ የተሻለ ስራ መስራትና ማህበረሰባችንን ተጠቃሚ ማድረግ ያስፈልገናል ያሉት የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ፕላን ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ወርቁሃ ምንዳሁን ብለዋል። አያይዘውም በ9 ወራት የታዩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠልና የታዩ ክፍተቶችን በዝርዝር በመለየት በቀሪዎቹ ወራት ዕቅዱን በስኬት ለማጠናቀቅ ርብርብ መደረግ እንዳለበት አሳስበዋል።
#ሲያደብርናዋዩ ወረዳ ኮሙኒኬሽን

ከተለያዩ መደብሮች ጊዜያቸው ያለፈ መድሀኒቶችና ምግብ ነክ ምርቶች ተሰብስበው ተወገዱ።በአጣዬ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት የተደረገ ክትትልና ቁጥጥር ተከትሎ የማህበረሰቡን ጤ...
29/04/2026

ከተለያዩ መደብሮች ጊዜያቸው ያለፈ መድሀኒቶችና ምግብ ነክ ምርቶች ተሰብስበው ተወገዱ።

በአጣዬ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት የተደረገ ክትትልና ቁጥጥር ተከትሎ የማህበረሰቡን ጤና ሊጎዱ የሚችሉ ጊዜያቸው ያለፈ መድሀኒቶች፣ ምግብ ነክ ምርቶች እና ፈሳሽ ቅባቶች ከተለያዩ መደብሮች ተሰብስበው መወገዳቸው ተገለፀ።

የአጣዬ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እንድሪስ ከማል እንደገለፁት፣ በተደረገው የቁጥጥር ስራ ለህብረተሰቡ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ ዕቃዎች በወቅቱ ተለይተው ተሰብስበዋል።

በዕቃዎቹ የማስወገድ ሂደት የተገኙት የኮሚቴው አባል የአጣዬ ከተማ የንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እንድሪስ ከማል ፣ የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበባው ገረመው፣ የተቋሙ ቡድን መሪዎች ፣ከኤፍራታና ግድም ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት የጤና ጤናነክ ተቋማት ግብዓትና ቁጥጥር ኦፊሰር አቶ ሚኪያስ መንግስቱ ፣ከአጣዬ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት ም/ሳጅን ደምስ ሀይለ እየሱስ ፣ባለሙያ ተገኝተዋል።

የተቋሙ ጽ/ቤት የሸማች ጥበቃ ክትትል እና ድጋፍ ቡድን መሪ ወ/ሮ ፈትለ አደፍራሽ እና የንግድ ጽ/ቤት የውጪ ድህረ ፍቃድ እንስፔክሺን ቡድን መሪ አቶ ሻምበል ደስዬ በቁጥር እንደገለፁት 41 ኪሎ ግራም ጠጣር እና 23.143 ሊትር ፈሳሽ ምርቶች የተሰበሰቡ ሲሆን፣ በገንዘብ ሲተመኑ 30 ሺህ 636 ብር የሚያወጡ መሆናቸው እና በዛሬው እለት መወገዱን ታውቋል።

በመጨረሻም የጽ/ቤት ኃላፊው አቶ እንድሪስ በቀጣይ ባለድርሻ አካላት በየወሩ በመገናኘት ተመሳሳይ ችግር እንዳይከሰት የክትትልና ቁጥጥር ስራውን እንዲያጠናክሩ ጥሪ አቅርበዋል።

በመጨረሻም ጊዜያቸው ያለፉ ምርቶች በማቃጠልና በመቅበር ሥነ-ስርዓት ተወግደዋል።

አጣዬ ኮሙኒኬሽን

29/04/2026
29/04/2026

Address

Debre Birehan
Debre Birhan
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara North Shewa Zone Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Amhara North Shewa Zone Communication:

Share