ሰሜን ሸዋ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ

ሰሜን ሸዋ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ Government deparment

ሰሜን ሸዋ ዞን አንደኛ        👏👏👏👏👏👏እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ ያላችሁየአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማና...
02/09/2026

ሰሜን ሸዋ ዞን አንደኛ
👏👏👏👏👏👏
እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ ያላችሁ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ትውውቅ ስትራቴጂያዊ መድረክ ላይ በበጀት ዓመቱ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች እውቅናና ሽልማት ሰጥቷል።

#በዚህም መሰረት ​የከተማ አስተዳደሮች ደረጃ

1ኛ ደረጃ_ ጎንደር ከተማ አስተዳደር

2ኛ ደረጃ _ ደሴ ከተማ አስተዳደር

3ኛ ደረጃ _ ባህርዳር እና ደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር
ሲሆን ​
#የዞኖች ደረጃ ደግሞ

​1ኛ ደረጃ፡ ሰሜን ሽዋ ዞን

​2ኛ ደረጃ፡ ደቡብ ወሎ ዞን

​3ኛ ደረጃ፡ ደቡብ ጎንደር ዞን እና ሰሜን ጎጃም ዞን ናቸው።

ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ ለወጡ ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች የዴስክ ቶፕ ኮምፒውተርና ዋንጫ ተበርክቶላቸዋል።

02/09/2026
29/08/2026
የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ከሰሜን ሸዋ ዞን ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ!​በሰሜን ሸዋ ዞን ሀገረ ማርያም ከሰም ወረዳ የሚከበረውን የታላቋ ጻድቅ እምነ ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ዓመታዊ ...
29/08/2026

የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ከሰሜን ሸዋ ዞን ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ!
​በሰሜን ሸዋ ዞን ሀገረ ማርያም ከሰም ወረዳ የሚከበረውን የታላቋ ጻድቅ እምነ ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ዓመታዊ የእረፍት በዓል ለማክበር የሾላ ገበያ ከተማ ማህበረሰብ የበዓሉን ዋዜማ ዝግጅት በላቀ ሁኔታ በማካሄድ ላይ ይገኛል።
​በአሁኑ ወቅት የበዓሉ ተካፋይ ለመሆንና በረከትን ለመቀበል በርካታ ምዕመናን ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ወደ ወረዳው በመግባት ላይ ይገኛሉ።
​የሰሜን ሸዋ ዞን ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ወደ አካባቢያችን ለቀረባችሁ ምዕመናን፣ እንግዶችና የደብሩ ተበዳሪዎች በሙሉ "እንኳን ለታላቋ ጻድቅ እምነ ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ዓመታዊ የእረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ" እያለ በታላቅ ደስታ የመልካም በዓል መልእክቱን ያስተላልፋል።
​መልካም፣ የሰላምና የበረከት በዓል ይሁንልዎ!

28/08/2026

በሰሜን ሸዋ ዞን ሚዳ ወረሞ ወረዳ የልጆች ቁርባን ስርአት
ቱባ ባህላዊና ሀይማኖተዊ ኩነት

የመላው ሰሜን ሸዋ ዞን ወርልድ ቴኳንዶ ስፖርታዊ ውድድር በለሚ ከተማ ተጀመረ።ነሐሴ፣22/2018 ዓ.ም ለሚበሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ፣ የመላው ሰሜን ሸዋ ዞን ወርልድ ቴኳንዶ ስፖርታዊ ው...
28/08/2026

የመላው ሰሜን ሸዋ ዞን ወርልድ ቴኳንዶ ስፖርታዊ ውድድር በለሚ ከተማ ተጀመረ።

ነሐሴ፣22/2018 ዓ.ም ለሚ

በሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ፣ የመላው ሰሜን ሸዋ ዞን ወርልድ ቴኳንዶ ስፖርታዊ ውድድር በለሚ ከተማ በይፋ ተጀመረ።

በውድድሩ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ የአካባቢው የማህበረሰብ ክፍሎች፣ የስፖርት ቤተሰብ አባላት፣ የተለያዩ የቴኳንዶ ክለቦች ተወካዮችና ስፖርተኞች ተገኝተዋል።

የሰሜን ሸዋ ዞን ወርልድ ቴኳንዶ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ማስተር ናኾም ገድሉ በንግግራቸው፣ ውድድሩ የቴኳንዶ ስፖርትን በዞኑ ለማሳደግ፣ ወጣቶችን በስፖርት ለማሳተፍና የስፖርት ችሎታቸውን ለማውጣት ወሳኝ መድረክ መሆኑን ገልጸዋል።

ወጣቶች ጤናማ፣ ተግባራዊና ስርዓት ያለው አኗኗር እንዲከተሉ ከማድረጉም በላይ፣ የመተባበር፣ የመከባበርና የውድድር መንፈስን ለማጎልበት ያለውን ሚና ጠቅሰዋል። በመሆኑም የቴኳንዶ ስፖርት ልማትን ለማስቀጠል ተቋማትና ማህበረሰቡ በትብብር መስራት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

የእንሳሮ ወረዳ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማንደፍሮ ተካልኝ በበኩላቸው፣ ውድድሩ በለሚ ከተማ መካሄዱ የአካባቢውን የስፖርት እንቅስቃሴ ለማነቃቃት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል።

በተለይም ወጣቶች ከአላስፈላጊ ተግባራት ተጠብቀው በስፖርት እንዲሰማሩ፣ ችሎታቸውን እንዲያዳብሩና ወደ ተሻለ የስፖርት ደረጃ እንዲደርሱ በቀጣይም የስፖርት ልማት ሥራዎች ትኩረት እንደሚሰጣቸው አመልክተዋል።

በውድድሩ ላይ የተሳተፉ ስፖርተኞችና ተመልካቾችም፣ ውድድሩ የቴኳንዶ ስፖርትን ለማስፋፋትና ወጣቶች ችሎታቸውን በውድድር ለማሳየት ጥሩ እድል መፍጠሩን ገልጸዋል።

ተሳታፊዎቹ አያይዘውም፣ ወጣቶች በስፖርት ላይ በበለጠ እንዲሳተፉ የሚያደርጉ መድረኮች በተደጋጋሚ እንዲዘጋጁ፣ የስፖርት ቁሳቁስና የልምምድ አቅም እንዲሻሻል እንዲሁም ተስፈኛ ስፖርተኞች በተለየ ሁኔታ እንዲደገፉ ጠይቀዋል።

ውድድሩ በተለያዩ የቴኳንዶ ዘርፎችና የውድድር ምድቦች የሚካሄድ ሲሆን፣ ዓላማውም የስፖርተኞችን ችሎታ ማዳበር፣ የውድድር ልምድ ማስገኘትና በዞኑ የቴኳንዶ ስፖርትን በቀጣይነት ማሳደግ መሆኑ ተገልጿል። በዚህ ውድድር የዞኑ ሰባት ወረዳዎችና ሦስት ከተማ አስተዳደሮች ናቸው እየተሳተፉ የሚገኙት።

የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ምክር ቤት የ2018 አፈጻጸምና የ2019 ዕቅድ ግምገማ አከናወነ​የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ምክር ቤት የ2018 በጀት ...
26/08/2026

የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ምክር ቤት የ2018 አፈጻጸምና የ2019 ዕቅድ ግምገማ አከናወነ
​የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ምክር ቤት የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2019 በጀት ዓመት መነሻ ዕቅድ ላይ ተወያይቶ በስኬት አጠናቋል።
​ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች፦
​የማህበረሰብና ባህላዊ ስፖርት፦ "ስፖርት ለሁሉም" በሚል መርህ የበጋ ወጣቶችና የማህበረሰብ ስፖርትን ማስፋፋት እንዲሁም ባህላዊ ውድድሮችን ማጠናከር።
​መሰረተ ልማትና ታዳጊዎች፦ የስፖርት ማዕከላትን ደረጃ ማሻሻል እና ታዳጊ ስፖርተኞችን ለክልልና ብሔራዊ ውድድሮች ማዘጋጀት።
​የባለድርሻ አካላት ቅንጅት፦ ከባለሀብቶችና ማህበረሰብ ጋር በመቀናጀት የዘርፉን ገቢና ተሳትፎ ማሳደግ።
​ምክር ቤቱ በሁለቱም ነጥቦች ላይ ሙሉ ስምምነት ላይ በመድረስ የተዘጋጁትን የውሳኔ ሀሳቦች ለአጠቃላይ ጉባኤው ለማቅረብ ወስኗል።

26/08/2026

Address

Debre Birhan

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሰሜን ሸዋ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share