ANRS North Shoa Zone Administration የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር

ANRS North Shoa Zone Administration      የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር North Shoa Zone Administration የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር

05/09/2026
የሰሜን ሸዋ ዞን ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት በክልል ደረጃ የ2ኛ ደረጃ  በመሆን እውቅና ተሰጠው​የሰሜን ሸዋ ዞን ኮንስትራክሽን ተጠሪ ጽ/ቤት በ2018 በጀት አመት በክልሉ ኮንስትራክሽን ባለስልጣ...
04/09/2026

የሰሜን ሸዋ ዞን ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት በክልል ደረጃ የ2ኛ ደረጃ በመሆን እውቅና ተሰጠው

​የሰሜን ሸዋ ዞን ኮንስትራክሽን ተጠሪ ጽ/ቤት በ2018 በጀት አመት በክልሉ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ሥር ከሚገኙ ኮንስትራክሽን ተጠሪ ጽ/ቤቶች ጋር ተወዳድሮ 2ኛ ደረጃ በመውጣት የእውቅና ምስክር ወረቀት ተሸላሚ ሆኗል።

​የተገኘው ውጤት የሁሉም አመራሮችና ሰራተኞች የጋራ ጥረትና ትብብር ሲሆን እውቅናው በቀጣይም ለበለጠ የልማትና የፕሮጀክቶች ስኬት ትልቅ ብርታትና የሥራ ተነሳሽነትን የሚፈጥር ነው ሲሉ የፅ/ቤቱ ኃላፊ ወ/ሮ ነፃነት ንጉሴ የገለፁ ሲሆን ለመላው የሥራ ባልደረቦች እና በየደረጃው አስተዋፅኦ ላደረጉ ባለድርሻ አካላት በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

"የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት አስተማማኝ እና ዘላቂነት ያለው የስነ ሕዝብ መረጃ የሚመነጭበት ነው"
03/09/2026

"የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት አስተማማኝ እና ዘላቂነት ያለው የስነ ሕዝብ መረጃ የሚመነጭበት ነው"

የውጤት ዜና!🏆🏆🏆የአብክመ የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ባካሄደው የ2018 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ ላይ በሰሜን ሸዋ ዞን ፕላንና ልማት መምሪያ የሲቪል እና ቤተሰብ ም...
03/09/2026

የውጤት ዜና!🏆🏆🏆

የአብክመ የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ባካሄደው የ2018 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ ላይ በሰሜን ሸዋ ዞን ፕላንና ልማት መምሪያ የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን በክልሉ ከሚገኙ ዞኖች ጋር በመወዳደር የላቀ ውጤት በማስመዝገብ 2ኛ ደረጃን በመያዝ የዴስክ ቶፕ ኮምፒውተርና ፕሪንተር ሽልማት እንዲሁም የእውቅና እና የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል።

ይህ አንፀባራቂ ስኬት ከዞን እስከ ቀበሌ ድረስ ባለው መዋቅር የሚገኙ በየደረጃው ያሉ አመራሮች፣ የኮሚቴ አደረጃጀቶች፣ ሙያተኞች፣ የሌሎች ባለድርሻ አካላት እንዲሁም የመላው የዞኑ ህዝብ የተቀናጀ እና ያልተቋረጠ ጥረትና የጋራ እንቅስቃሴ ውጤት ነው። የሲቪልና የቤተሰብ ምዝገባ የእቅድ ግቦችን በማሳካት ረገድ የታየው ይህ ከፍተኛ የመፈጸም አቅምና የተቀናጀ ስራ፣ ከዞን እስከ ወረዳና ከተማ አስተዳደር ያለው የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን ህዝብን በቅንነት እና በጥራት ለማገልገል ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር ያረጋገጠ ነው።

ይህ የተበረከተው የሽልማትና የእውቅና ምስክር ወረቀት በ2018 በጀት ዓመት ለነበረው ጥረትና ውጤት የተሰጠ ከመሆኑም በላይ ዞኑ በቀጣይም አገልግሎቱን ይበልጥ በማዘመን እና አፈጻጸሙን በማሳደግ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ለሚደረገው ጉዞ ትልቅ የሞራል ስንቅ እና የብርታት ምንጭ ይሆናል።

ከዞን እስከ ቀበሌ በዘርፉ ተግባር ላይ ለተሳተፋችሁ አመራሮች፣ ባለሙያዎች፣ ባለድርሻ አካላት እና መላው የዞናችን ህዝቦች እንኳን ደስ አላችሁ!

የሰሜን ሸዋ ዞን ህብረት ስራ ተጠሪ ፅ/ቤት በክልል ደረጃ 2ኛ ወጣ!!የሰሜን ሸዋ ዞን ህብረት ስራ ተጠሪ ፅ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ያስመዘገበው የሥራ አፈጻጸም በመገምገም በአማራ ክልል ...
03/09/2026

የሰሜን ሸዋ ዞን ህብረት ስራ ተጠሪ ፅ/ቤት በክልል ደረጃ 2ኛ ወጣ!!

የሰሜን ሸዋ ዞን ህብረት ስራ ተጠሪ ፅ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ያስመዘገበው የሥራ አፈጻጸም በመገምገም በአማራ ክልል ዞኖች መካከል 2ኛ ደረጃ በመውጣት የእውቅናና ሽልማት ተቀበለ።

የአማራ ክልል ህብረት ስራ ኮሚሽን የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት የዕቅድ ትውውቅ መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩም በ2018 በጀት ዓመት ከፍተኛ የሥራ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች ዕውቅናና ሽልማት ተበርክቷል።

በዚህም የሰሜን የሰሜን ሸዋ ዞን ህብረት ስራ ተጠሪ ፅ/ቤት ከክልሉ ዞኖች መካከል 2ኛ ደረጃን በመያዝ ተሸላሚ ሆኗል።

የፅ/ቤቱ ሃላፊ አቶ ዘነበ ሃይሉ ለተገኘው ውጤት ለመላው ሠራተኞች፣ አመራሮች፣ ለአጋርና ባለድርሻ አካላት እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

የሰሜን ሸዋ ዞን መንገድ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ መምሪያ በክልል ደረጃ 2ኛ ወጣ!!የሰሜን ሸዋ ዞን መንገድ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ያስመዘገበው የሥራ አፈጻጸ...
03/09/2026

የሰሜን ሸዋ ዞን መንገድ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ መምሪያ በክልል ደረጃ 2ኛ ወጣ!!

የሰሜን ሸዋ ዞን መንገድ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ያስመዘገበው የሥራ አፈጻጸም በመገምገም በአማራ ክልል ዞኖች መካከል 2ኛ ደረጃ በመውጣት የእውቅናና ሽልማት ተቀበለ።

የአማራ ክልል መንገድ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት የዕቅድ ትውውቅ መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩም በ2018 በጀት ዓመት ከፍተኛ የሥራ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች ዕውቅናና ሽልማት ተበርክቷል።

በዚህም የሰሜን ሸዋ ዞን መንገድ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ መምሪያ ከክልሉ ዞኖች መካከል 2ኛ ደረጃን በመያዝ ተሸላሚ ሆኗል።

የመምሪያው ኃላፊ አቶ ደጀኔ በቀለ ለተገኘው ውጤት ለመምሪያው ሠራተኞች፣ ለአመራሮች፣ ለአጋርና ባለድርሻ አካላት እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

አቶ ደጀኔ በተለይም በየደረጃው የሚገኙ የዞን፣ የወረዳና የከተማ አመራሮች፣ የመምሪያው ማኔጅመንትና ሠራተኞች፣ የሕዝብ ትራንስፖርት ማኅበራት፣ አጋር ተቋማትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።

የተገኘው 2ኛ ደረጃ በመምሪያው የተመዘገበውን የሥራ አፈጻጸም የሚያሳይ ውጤት መሆኑን በመግለጽ፣ በቀጣይም የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ በትብብር መሥራት እንደሚገባ አመራሩ አመልክቷል።

ለሰሜን ሸዋ ዞን መንገድ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ መምሪያ፣ ለሠራተኞቹ፣ ለአጋርና ባለድርሻ አካላት እንኳን ደስ አላችሁ!

የአማራ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ታላቅ ኢግዚቢሽንና የፓናል ውይይት አካሄደ፡፡= = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = ባህርዳር ነሀሴ 2...
03/09/2026

የአማራ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ታላቅ ኢግዚቢሽንና የፓናል ውይይት አካሄደ፡፡
= = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = =
ባህርዳር ነሀሴ 28/2018 ዓ.ም (ኢቴቢ): የአማራ ክልል ርእሰ-መስተዳድር የተከበሩ አቶ አረጋ ከበደ፣ የኢፌዲሪ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ እና ሌሎች የፌደራልና የክልል አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተው ኢግዚቢሽኑን ጎብኝተዋል፤ በፓናል ውይይቱም ተሳትፈዋል፡፡

ክቡር አቶ አረጋ ከበደ ኢግዚቢሽኑን መርቀው የከፈቱ ሲሆን በፓናል ውይይቱም ንግግር በማድረግ ክልሉ ለቴክኖሎጂ ልዩ ትኩረት በመስጠት እስከ 2042 ዓ.ም የሚደርስ የ25 አመታት የስትራቴጂክ እቅድ ቀርፆ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ብለዋል፡፡

ቴክኖሎጂን ማዘመን በራሱ ግብ ሊሆን አይችልም፤ ይሁንና ዜጎች ጥራት ያለውና ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኙ በማስቻል እንዲሁም ሀብት በመፍጠር በኑሮ የተሻሻለ ማህበረሰብ መገንባት ግባችን ሊሆን ይገባል ሲሉ ርእሰ-መስተዳድሩ ተናግረዋል፡፡ ይህን አላማና ራዕይ ለመተግበርም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ስራወችን ሊመራ የሚችል የአማራ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ በአዲስ የተደራጀ መሆኑን በመግለፅ አስፈላጊውን ሀብት ለመመደብም ጥረት መደረጉን አስታውቀዋል፡፡

የአማራ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ የቻለ ይግዛው ‘’የኤሌክትሮኒክስ መንግስት የዲጅታል ኢትዮዽያ 2030 መሰረት’’ በሚል መሪ ቃል ወደተዘጋጀው የኢግዚቢሽንና ፓናል ውይይት እንኳን ደህና መጣቹህ በማለት በመክፈቻ ንግግራቸው መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
በፓናል ውይይቱ ቴክኖሎጂን ከፍ የሚያደርጉና ግንዛቤን የሚፈጥሩ ጥያቄወች የፓናሉ አወያይ በሆኑት በባህርዳር ዩንቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር መንገሻ አየን ቀርበው ተወያዮች አቶ ዳንኤል ጉታ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር፣ ዶክተር አብዮት ባዩ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና ዶክተር ደመቀ ቦሩ ከአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ለቀረበላቸው ጥያቄወች ምላሽ በመስጠት የፓናል ውይይቱ ተካሂዷል፡፡

በኢግዚቢሽኑ ቢሮው ያለማቸው እና ተግባራዊ እየተደረጉ የሚገኙ ከ30 በላይ የክልል ተቋማት ሲስተሞች ቀርበው ጉብኝት የተደረገባቸው ሲሆን ከነሃሴ 28 እስከ 30/2018 ዓ.ም ለክልል ተቋማት ሰራተኞችና ለህዝብ ለጉብኝት ክፍት ሆኖ ይቀጥላል፡፡

የሰሜን ሸዋ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በክልል ደረጃ 3ኛ ደረጃ ይዞ እውቅና አገኘደብረ ብርሃን፦ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም (ሰሸዞመኮ) የሰሜን ሸዋ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫ...
03/09/2026

የሰሜን ሸዋ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በክልል ደረጃ 3ኛ ደረጃ ይዞ እውቅና አገኘ

ደብረ ብርሃን፦ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም (ሰሸዞመኮ) የሰሜን ሸዋ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በ2018 በጀት ዓመት ያከናወናቸውን የፓርቲ ሥራዎች በተመለከተ በክልል ደረጃ በተካሄደ ጥቅል የአፈጻጸም ግምገማ ከሌሎች ዞኖች ጋር ተወዳድሮ 3ኛ ደረጃ በመያዝ እውቅና አግኝቷል።

የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በተለያዩ የፓርቲ ዘርፎች ባስመዘገበው የጥቅል አፈጻጸም ውጤት ይህንን ደረጃ ማግኘቱ ተገልጿል።

የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኤልያስ አበበ እንደገለጹት፣ የተገኘው እውቅና የተመዘገበውን ጥንካሬ ለማስቀጠልና ያሉ ድክመቶችን በመለየት ለቀጣይ ተልዕኮ በበለጠ ቁርጠኝነት ለመሥራት የሚያነሳሳ ነው።

አቶ ኤልያስ በተጨማሪም ለውጤቱ መገኘት ከዞን እስከ ወረዳና ቀበሌ ድረስ ያሉ አመራሮችና ባለሙያዎች፣ የፓርቲው አባላት፣ መላው የዞኑ ሕዝብ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።

የተገኘው 3ኛ ደረጃ በቀጣይ የፓርቲ ሥራዎችን በተሻለ አቅም ለማከናወን አዲስ መነሳሳት የሚፈጥር ሲሆን፣ የተገኙ ጥንካሬዎችን ማስቀጠልና የተለዩ ድክመቶችን ማረም የቀጣዩ የሥራ አቅጣጫ አካል መሆኑ ተጠቁሟል።

የዞኑ ግብርና መምሪያ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት አፈፃፀም 3ኛ በመውጣት ተሸላሚ ሆነየሰሜን ሸዋ ዞን ግብርና መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም ከዞኖች ጋር ተወዳድሮ 3ኛ ደረጃ በመውጣት ...
02/09/2026

የዞኑ ግብርና መምሪያ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት አፈፃፀም 3ኛ በመውጣት ተሸላሚ ሆነ

የሰሜን ሸዋ ዞን ግብርና መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም ከዞኖች ጋር ተወዳድሮ 3ኛ ደረጃ በመውጣት የዋንጫ፣ የምስክር ወረቀትና የላፕቶፕ ሽልማት ተቀብሏል።

ሽልማቱን የተቀበሉት የመምሪያው ኃላፊ አቶ ታደሰ ማሙሻ ለተገኘው የላቀ ውጤት በየደረጃው ያለው አመራርና ባለሙያ እንዲሁም አጋር አካላትን እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል።

የዞኑ ገቢዎች መምሪያ 1ኛ ደረጃ በውጣቱ እውቅናና ሽልማት ተበረከተለትየአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገቢዎች ቢሮ በዛሬው ዕለት የ2018 በጀት ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ በማካሔድ የሁ...
02/09/2026

የዞኑ ገቢዎች መምሪያ 1ኛ ደረጃ በውጣቱ እውቅናና ሽልማት ተበረከተለት

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገቢዎች ቢሮ በዛሬው ዕለት የ2018 በጀት ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ በማካሔድ የሁሉም ዞኖች በተገኙበት የተሻለ አፈፃፀም ለነበራቸው ዞኖችና ከተሞች እውቅናና ሽልማት ሰጠ።

በዚህም የሰሜን ሸዋ ዞን ገቢዎች መምሪያ ከዞኖች ተወዳድሮ 1ኛ ደረጃ በመውጣት ተሸላሚ ሆኗል።

ሽልማቱም ዋንጫ፣ ሰርተፊኬት፣ አንድ የኤሌትሪክ ባጃጅ እና ሁለት ዴስክቶፕ ከፒውተር ከሙሉ አክሰሰሪው መሆኑ ተገልጿል።

ለተገኘው ከፍተኛ ውጤት የገቢዎች ቢሮ ሀላፊዎች የዞናች ፣የዞኑ አስተባባሪ፣ በዞን በወረዳ ና ከተማ ያሉ ጠቅላላ አመራሮች፣ የሁልጊዜ የገቢ ተቋሙ ህይወትን በመለገስ ግብርና ታክስ በመሰብሰብ የዚህ የውጤት ባለቤቶች በዞን፣በወረዳና በከተማ ያላችሁ የማኔጅመንት አባላት ና ባለሙያዎች ፣ የሸዋ ጨዋው ግብር ከፋዮቻችን እና ባለድርሻ አካለት እንኳን ደስ አላችሁ ሲሉ የመምሪያው ኃላፊ ወ/ሮ ቀለም ተስፋዬ መልዕክት አስተላልፈዋል።

Address

Debre Birhan

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ANRS North Shoa Zone Administration የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share