26/08/2026
ለመንዝ ማማ እና መንዝ ላሎ ወረዳ በጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች፣ ለወረዳ ጤና ጽሕፈት ቤቶች፣ ሆስፒታል እና መላው አጋር አካላት፤
ደብረ ብርሃን ደም ባንክ ከሁለቱም ወረዳዎች ጋር በመተባበር ባካሄደው የደም ልገሳ መርሃ-ግብር/ንቅናቄ፣ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው በጎ ፈቃደኛ ወገኖች የወገንን ህይወት ለማዳን ደማቸውን በነፃነት ለግሰዋል።
❤ለክቡራን ደም ለጋሾች፦ የወገንን ህይወት ለመታደግ ደማችሁን በፈቃደኝነት በመለገስ የሰው ልጅ ህይወት እንዲቀጥል ላደረጋችሁት ታላቅ ሰብአዊነት ከልብ የመነጨ የከበረ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
❤ለወረዳ ጤና ጽሕፈት ቤቶች እና ሁሉም ባለድርሻ አካላት፦ ከደም ባንካችን ጋር በቅርበት በመተባበር፣ ህዝቡን በማንቀሳቀስ እና ንቅናቄው በከፍተኛ ድምቀትና ስኬት እንዲጠናቀቅ ላደረጋችሁት ያልተቆጠበ ጥረት እና አርአያነት ያለው አጋርነት ምስጋናችን የላቀ ነው።
የጀመራችሁት ይህ የተቀደሰ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ሙሉ እምነታችን ነው።
ለሰጣችሁት ህይወት ሰጪ ደም እና ለወገን አለኝታነታችሁ ሁልጊዜም እናመሰግናለን!
ከታላቅ አክብሮት ጋር፣
ደብረ ብርሃን ደም ባንክ