Debre Markos city communication

Debre Markos city  communication ዓላማው ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃን ለህዝብ ማድረስ ነው።

መቀነት የሴቶች ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር 4ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሂዷል።ጳጉሜ 1/2018ዓ.ም (ደብረ ማርቆስ ኮሙኒኬሽን): በደብረ ማርቆስ ከተማ የሚገኘው መቀነ...
06/09/2026

መቀነት የሴቶች ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር 4ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሂዷል።

ጳጉሜ 1/2018ዓ.ም (ደብረ ማርቆስ ኮሙኒኬሽን): በደብረ ማርቆስ ከተማ የሚገኘው መቀነት የሴቶች ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር 4ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን "በመቀነታችን እንቆጥባለን፤ ተባብረን እናድጋለን፤ባንካችንን እንገነባለን"! በሚል መሪ መለዕክት አባላቱ፣ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተካሂዷል።

በዕለቱም አጠቃላይ የኦዲት ሪፖርት እና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ቀርቦ ውይይት የተካሄደ ሲሆን በተጨማሪም ማህበሯን ለማሳደግ የሚያግዙ አዳዲስ ጉዳዮች ላይ ምክክር ተደርጓል።

የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የተቋቋመችው መቀነት የሴቶች ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር ከተመሰረተችበት ጊዜ ጀምሮ የሴቶችን ቁጠባ በማበረታታት፣ የብድር አገልግሎት በመስጠትና ሌሎች የአባላቷን በተለይም የሴቶችን የፋይናንስ አቅም የሚያሳድጉ በርካታ ውጤታማ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የማህበሩ ሰብሳቢ ወ/ሮ ስንታየሁ ከበደ ተናግረዋል።

ማህበሩ ከሶስት ዓመት በፊት በ 43 አባላት
በ 76ሺ ብር ተጀምሮ በአሁኑ ሰዓት የአባላቱን ቁጥር 143 በማድረስ የካፒታል መጠኑንም ከ2.4 ሚሊየን ብር በላይ ማሳደግ መቻሉን ተናግረዋል።

ከአባላቱ መካከልም 126ቱ ሴቶች መሆናቸውን ገልፀዋል።

2019 በጀት ዓመትም 200 አዳስ አባላትን በማፍራት ማፍራትየቁጠባ መጠንን ለማሳደግ ከአባላት 8ሚ ለመሰብሰብ መታቀዱን የገለፁት ሰብሳቢዋ ከተለያዩ የገንዘብ ማግኛ ምንጮች አጠቃላይ ካፒታሉን 13ሚሊየን500ሺ በማድረስና 11 ሚሊየን ብር በማበደር ከ1ሚሊየን ብር በላይ የተጣራ ትርፍ ለማግኘት እንደሚሰራ አስገንዝበዋል።

ለንግድ ማስፋፊያ፣ ለመኖሪያ ቤት፣ ለባጃጅ መግዣ፣ለቤት ቁሳቁስ መግዣ፣ ለአደጋ ጊዜና ለልዩ ብድር በአጭር ጊዜ ለማበደር መታቀዱንም ወ/ሮ ስንታየሁ ገልፀዋል።

አስተያይታቸውን የሰጡ የማህበሩ አባላት በኦዲት የታዩ ጥንካሬዎችን በማስቀጠልና የተሰጡትን ክፍተቶች በማረም ማህበሩን ለማሳደግ በትብብር መስራት ይኖርብናል ብለዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከደብረ ማርቆስ ኮሚኒኬሽን ለማግኘት ሊንኩን በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
‎ቴሌግራም https://t.me/dmcomunicationoffice
‎ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php id=100064865823018
‎ቲክቶክ www.tiktok.com/
ዩቲብ:https://youtube.com/?si=h8-iiu60Df-Te3qJ

የእምርታ ቀን (ጳጉሜ 1) ስናከብር የማህበረሰባችንን የላቀ ተጠቃሚነትና ስኬት የምናረጋግጥበት ዘመን እንዲሆን ለማድረግ ነው" ምክትል ከንቲባ ስለሽ ተመስገን*********ጳጉሜ 1/2018 ዓ...
06/09/2026

የእምርታ ቀን (ጳጉሜ 1) ስናከብር የማህበረሰባችንን የላቀ ተጠቃሚነትና ስኬት የምናረጋግጥበት ዘመን እንዲሆን ለማድረግ ነው" ምክትል ከንቲባ ስለሽ ተመስገን
*********
ጳጉሜ 1/2018 ዓ.ም (ደብረ ማርቆስ ኮሙኒኬሽን): በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የእመርታ ቀን (ጳጉሜን-1) "የኢትዮጵያ ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል በማምረት ላይ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎችን እና በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችን በመጎብኘት ተካሂዷል።

በጉብኝቱም የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ስለሽ ተመስገንን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ የስራ ሃላፊዎች፣ የከተማዋ የሀገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች ተሳትፈዋል።

የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲ ስለሽ ተመስገን "ጳጉሜ 1 "የእምርታ ቀንን" ስናከብር የማህበረሰባችንን የላቀ ተጠቃሚነትና ስኬት የምናረጋግጥበት ዘመን እንዲሆን ለማስቻል ነው ብለዋል።

የማንሰራራት ቀንን ስናስብ የባህልና ሀሳብ ሽግግር ማድረግ፣ሁሉን አቀፍ ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት ማምጣት አስፈላጊ ስለመሆኑ ምክትል ከንቲባው አስገንዝበዋል።

"የኢትዮጵያ መንሰራራት" በሚል መሪ ቃል እየተከበረሩ የሚገኙ የጳጉሜ ቀናቶችን ስናስብ ብዝሃነትን እንደ ፀጋ መጠቀም ያስፈልጋል ያሉት ምክትል ከንቲባ ስለሽ ተመስገን የኢኮኖሚ ዘርፉን በፊት ከነበረው መዋቅራዊ ሽግግር የሚያመጣ ስራ በትኩረት ለመፈፀም በከተማ አስተዳደሩ የተሰሩ ኢንዱስትሪና የግብርና ዘርፎች ጉብኝት ተካሂዷል ብለዋል።

​ሀገራዊውን የኢትዮጵያ ታመርት ንቅናቄ መሠረት በማድረግ በእምርታ ቀን በማምረት ላይ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ጉብኝት መካሄዱን የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ አቶ ተመስገን ተድላ ገልፀዋል።

​በእምርታ ቀን በከተማዋ የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎችና ኢንቨስተሮች በሙሉ አቅማቸው እንዳያመርቱ ያገዷቸውን የቴክኒክ፣ የፋይናንስና የመሠረተ ልማት ማነቆዎችን ለመፍታት ጉብኝት መካሄዱንና ማህበረሰቡም ልማቱን በማየት ደጋፊ እንዲሆን ነው ብለዋል።

ኃላፊው አምራቾችና ኢንቨስተሮች የቴክኖሎጂ ሽግግር በማድረግ የምርቶቻቸውን ጥራትና ብዛት እንዲያሳድጉ ጥሪ አቅርበው፣ መምሪያው ዘርፉ የሚጠይቀውን የሙያና የቴክኒክ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

በከተማዋ በአምራች ኢንዱስትሪዎችና በግብርና ዘርፉ የተመለከቷቸው ስራዎች የሚበረታቱ መሆናቸውን የገለፁት የጉብኝቱ ተሳታፊ የሀገር ሽማግሌ አቶ በቀለ መንግስት ሰላማችንን ጋረጋገጥን በርካታ ፕሮጀክቶችን መስራት ስለሚቻል ለሠላም ቅድሚያ ሰጠን ልንሰራ ይገባል ብለዋል።

ሌላኛዋ የጉብኝቱ ተሳታፊ ወጣት ድንቅነሽ መንግስት በጉብኝቷ መደሰቷን ገልፃ፤ የፍብሪካዎች ወደ ስራ መግባት ለወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ ላይ የሚኖራቸው ሚና ከፍተኛ ስለሆነ ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከደብረ ማርቆስ ኮሚኒኬሽን ለማግኘት ሊንኩን በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
‎ቴሌግራም https://t.me/dmcomunicationoffice
‎ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php id=100064865823018
‎ቲክቶክ www.tiktok.com/
ዩቲብ:https://youtube.com/?si=h8-iiu60Df-Te3qJ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብረ ማርቆስዲስትሪክት መጭውን አዲስ ዓመት በማስመልከት ለአቅመ ደካሞች የበዓል መዋያ ድጋፍ አደረገ።***************ጳጉሜ 1/2018ዓ.ም (ደብረ ማርቆስ ኮሙ...
06/09/2026

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብረ ማርቆስዲስትሪክት መጭውን አዲስ ዓመት በማስመልከት ለአቅመ ደካሞች የበዓል መዋያ ድጋፍ አደረገ።
***************
ጳጉሜ 1/2018ዓ.ም (ደብረ ማርቆስ ኮሙኒኬሽን): የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብረ ማርቆስ ዲስትሪክት የማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት 1ሚሊዮን 800 ሺህ ብር በላይ ወጭ በማድረግ የ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለተቸገሩ ወገኖች ማዕድ በማጋራት የመልካምነት እና የአብሮነት ተግባር አከናውኗል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብረ ማርቆስ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ አፈወርቅ ሰንደቁ ባንኩ ከዋና አገልግሎቱ ባሻገር ማኅበረሰቡን በሚጠቅሙ ተግባራት ላይ በቀጥታ በመሳተፍ ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን ለመደገፍ በትኩረት እየሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2018 ዓ.ም ዓመት180 ሚሊየን ብር በመመደብ ለ20ሺ ወገኖች የተለያዩ ድጋፎችን ለማድረግ አቅዶ እየሰራ መሆኑን የገለፁት አቶ ሰንደቁ ለዘመን መለዋጫ ባህልም ከ72 ሚሊየን ብር በላይ መድቦ በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።

የዘመን መለወጫ በዓልን ከቤተሰቦቻቸው ጋር በደስታ እንዲያሳልፉ ባንኩ በደብረ ማርቆስ ከተማ ከ1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ በማድረግ ለ200 ወገኖች 25 ኪሎ የጤፍ ዱቄት ፣ 5 ሊትር ዘይት እና ገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል ብለዋል፡፡

የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብሩ አረጋውያን እና አቅመ ደካሞች አዲሱን ዓመት በደስታ እንዲያሳልፉ ያግዛል ያሉት ዳይሬክተሩ በቀጣይም ባንኩ የማኅበራዊ ሃላፊነቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

​ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ተሾመ ዋለ የ2019 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለአቅመ ደካሞች ባዘጋጀው የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው መልዕክት አስተላፈዋል።

​ በዓላትን ስናከብር የተቸገሩትንና አቅም የሌላቸውን ወገኖች በማሰብ ሊሆን ይገባል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያደረገው ይህ ተግባር የወገን ደራሽነትንና የማህበራዊ ኃላፊነትን በተግባር ያሳየ ታላቅ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።

​ባንኩ የፋይናንስ አገልግሎት ከመስጠት ባለፈ በማህበረሰብ ልማትና በበጎ አድራጎት ስራዎች ለደብረ ማርቆስ ከተማ አቅመ ደካሞች ላደረገው ድጋፍ በከተማ አስተዳደሩ እና በህዝቡ ስም ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።

​ሌሎች ባለሀብቶች፣ የመንግስትና የሲቪል ማህበራትም የባንኩን አርአያነት በመከተል በአዲስ ዓመት ዋዜማ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች እጃቸውን እንዲዘረጉ ጥሪ አቅርበዋል።

በመርሃ ግብሩ የተገኙት የሃይማኖት አባት መላከ ስብሃትክብረ ኩሉ አለም በተሰማራንበትና በተሰጠን ፀጋ ተጠቅመን የሌላቸው ወገኖች ማሰብ የመልካምነት ስራ መገለጫ ስለሆነ ባንኩ ላደረገው ድጋፍ ሊመሰገን ይገባል ብለዋል።

በዕለቱም ድጋፉ የተደረገላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከደብረ ማርቆስ ኮሚኒኬሽን ለማግኘት ሊንኩን በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
‎ቴሌግራም https://t.me/dmcomunicationoffice
‎ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php id=100064865823018
‎ቲክቶክ www.tiktok.com/
ዩቲብ:https://youtube.com/?si=h8-iiu60Df-Te3qJ

የእመርታ ቀን (ጳጉሜን-1) በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር በማምረት ላይ የሚገኙ ፋብሪካዎች ጉብኝት እየተካሄደ ነው።***********ጳጉሜ 1/2018 ዓ.ም (ደብረ ማርቆስ ኮሙኒኬሽን): ...
06/09/2026

የእመርታ ቀን (ጳጉሜን-1) በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር በማምረት ላይ የሚገኙ ፋብሪካዎች ጉብኝት እየተካሄደ ነው።
***********
ጳጉሜ 1/2018 ዓ.ም (ደብረ ማርቆስ ኮሙኒኬሽን): በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የእመርታ ቀን (ጳጉሜን-1) "የኢትዮጵያ ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል በማምረት ላይ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎችን በመጎብኘት እየተከበረ ይገኛል።

በጉብኝቱ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ስለሽ ተመስገንን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ የስራ ሃላፊዎች፣ የከተማዋ የሀገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች እየተሳተፉ ነው።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከደብረ ማርቆስ ኮሚኒኬሽን ለማግኘት ሊንኩን በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
‎ቴሌግራም https://t.me/dmcomunicationoffice
‎ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php id=100064865823018
‎ቲክቶክ www.tiktok.com/
ዩቲብ:https://youtube.com/?si=h8-iiu60Df-Te3qJ

ጳጉሜን 1 — የእመርታ ቀን፤ ከተረጅነት ወደ አምራችነት!‎‎ በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ንጉስ ተክለ ኃይማኖት ክፍለ ከተማ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ያለመው የስንዴ ልማት የመስክ...
06/09/2026

ጳጉሜን 1 — የእመርታ ቀን፤ ከተረጅነት ወደ አምራችነት!

‎ በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ንጉስ ተክለ ኃይማኖት ክፍለ ከተማ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ያለመው የስንዴ ልማት የመስክ ምልከታ ተካሄደ።
‎ **********
ጳጉሜ1/13/2018 ዓ.ም(ደብረ ማርቆስ ኮሙኒኬሽን)‎"የኢትዮጵያ መንሰራራት" በሚል መሪ ቃል እንደ ሀገር እየተከበረ የሚገኘውን የጳጉሜን ቀናቶች የጳጉሜን 1 «የእመርታ ቀንን» ምክንያት በማድረግ በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ንጉስ ተክለ ኃይማኖት ክፍለ ከተማ ሀገራችን ከተረጂነት ወደ አምራችነት እያደረገች ያለችውን ታሪካዊ ሽግግር የሚያበስር የመስክ ጎበኝት ተደርጓል።

‎በምልከታው ለአደጋ ጊዜ መጠባበቂያ የሚውልና የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በትኩረት እየለማ የሚገኘው ከ5 ሄክታር በላይ የሚሸፍን የምርጥ ዘር ስንዴና ጤፍ ሰብል በቦታው በመገኘት የከተማ አስተዳደር፣የክፍለ ከተማና የቀበሌ አመራሮች እንዲሁም ልዩ ልዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጉብኝት አድርገዋል።

‎ #ጳጉሜን1 #የእመርታቀን #የኢትዮጵያመንሰራራት #ከተረጂነትወደአምራችነት #ሲያደብርናዋዩ #የስንዴልማት #ምግብሉዓላዊነት

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብረ ማርቆስ ዲስትሪክት መጭውን አዲስ ዓመት በማስመልከት ለ200 አቅመ ደካማዎች የማዕድ ማጋራት መርሃ -ግብር ድጋፍ አደረገ።************ጳጉሜ 1/2018ዓ.ም...
06/09/2026

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብረ ማርቆስ ዲስትሪክት መጭውን አዲስ ዓመት በማስመልከት ለ200 አቅመ ደካማዎች የማዕድ ማጋራት መርሃ -ግብር ድጋፍ አደረገ።
************
ጳጉሜ 1/2018ዓ.ም (ደብረ ማርቆስ ኮሙኒኬሽን): በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደብረ ማርቆስ ዲስትሪክት የአዲስ ዓመት መቀበያ የማእድ ማጋራት መርሃ ግብር" አዲስ ዓመት በአገልጋይነት እና በጎነት" በሚል መሪ ሃሳብ ተካሄደ።

በማዕድ ማጋራት መርሃ ግብሩ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ተሾመ ዋለ፣ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ መልካሙ ሽባበው፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብረ ማርቆስ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ አፈወርቅ ሰንደቁን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩና የባንኩ የስራ ሃላፊዎች፣ የከተማዋ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖች ተገኝተዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከደብረ ማርቆስ ኮሚኒኬሽን ለማግኘት ሊንኩን በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
‎ቴሌግራም https://t.me/dmcomunicationoffice
‎ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php id=100064865823018
‎ቲክቶክ www.tiktok.com/
ዩቲብ:https://youtube.com/?si=h8-iiu60Df-Te3qJ

እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!እንኳን ለእመርታ ቀን አደረሳችሁ! እመርታ ከአሉበት የከፍታ ደረጃ ወደ ላይኛዉ መስፈንጠር ነው፡፡ ከፍታን በአዝጋሚ ሂደትም ዘመናትን ወስዶ ማሻሻል ይቻላል፤ በዚያ አግባ...
06/09/2026

እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!

እንኳን ለእመርታ ቀን አደረሳችሁ! እመርታ ከአሉበት የከፍታ ደረጃ ወደ ላይኛዉ መስፈንጠር ነው፡፡ ከፍታን በአዝጋሚ ሂደትም ዘመናትን ወስዶ ማሻሻል ይቻላል፤ በዚያ አግባብ የሚመጣ መሻሻል ከታለመዉ ግብ ለመድረስ የትውልዶችን ጥረት የሚጠይቅ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ግን በቁጭት ለዘመናት ከቆየንበት ኋላ ቀርነት እና ድህነት በአዝጋሚ ጉዞ ለመላቀቅ ስለማይቻል እመርታዊ ለውጥ ማምጣትን ግብ አድርገን ሠርተን ስኬቶችን እያስመዘገብን ነው፡፡ ያለፉት ጥቂት ዓመታት ጥረቶቻችን ውጤቶች የሚያሳዩትም ይህንኑ ነው፡፡

የኢትዮጵያን ጀርባ ያጎበጡ የውጭ ዕዳዎችን ጫና በመቀነስ፣ ገቢ የመሰብሰብ ዐቅምን በማሳደግ፣ የኢንዱስትሪዎችን የማምረት ዐቅም በማሻሻል፣ የማዕድን ሀብቶች አጠቃቀምን በማላቅ እመርታዊ ለውጦች ተመዝግበዋል፡፡ የመንግሥት አጠቃላይ የማድረግ ዐቅም በእጅጉ ተለውጧል፡፡ ይህንን እመርታዊ ስኬት ማስመዝገብ የተቻለው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን በማድረግ፤ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል፤ የዜጎችን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት በማሳደግ፤ የቢዝነስ ሥርዐቱን ቀልጣፋና ግልጽ በማድረግ፤ የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ዐቅም ከዜጋ ተኮር እና ብሔራዊ ጥቅም አንጻር በመግራት የመደመር መንግሥት ባደረገዉ ሰፊ ጥረት ነው፡፡

ኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቶቿን በላቀ የኃላፊነት ስሜት በሕጋዊ አግባብ መጠቀም ጀምራለች፤ ታዳሽ ኃይልን በማምረት ከራስ አልፎ ለቀጠናዉ የኃይል ምንጭ ኾናለች፤ ብዝኃ ዘርፍ ኢኮኖሚን በመተግበር ኹለንተናዊ ዕድገቶችን እያስመዘገበች መጥታለች፤ የኢንዱስትሪ ምርቶችን በዓለም ገበያ ተወዳድራ የመሸጥ ዐቅም ፈጥራለች፡፡ የመንግሥት የልማት ዕቅድ ከቁጥ ቁጥ ወጥቶ ትውልድን ታሳቢ ያደረገ ግብ አስቀምጦ እየተተገበረ ነው፡፡ በ2018 ዓ/ም በሁሉም መስክ ከተስፋ ብርሃን ወደሚጨበጥ ለውጥ የመሸጋገር ሀገራዊ ራዕይን ማሳካት ተችሏል፡፡ ኢትዮጵያን በ2023 ዓ.ም አፍሪካዊት የብለጽግና ተምሳሌት የማድረግ ግብ ተቀምጦ ርብርብ እየተደረገ የስኬቱ ዋዜማ እየተቃረበ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በመደመር መንግሥት በተነደፉ የፖሊሲ ሐሳቦች ኹለንተናዊ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ጉዞን ጀምራለች፡፡ በገቢ አሰባሰብ ላይ የታየዉ እመርታ አንዱ አብነት ነው፡፡ የግብር እና ታክስ መሠረትን በማስፋት፣ ገቢ የመሰብሰብ ዐቅምን በማሳደግ፤ የግብር ከፋዩን የመንግሥት አገልግሎት እርካታ በመሶብ አንድ ማእከል እና በዲጂታል አገልግሎቶች ከፍ በማድረግ የላቀ አፈጻጸም ማሳየት ተችሏል፡፡ በዚህም የበጀት ጉድለትን በእጅጉ ማጥበብ ተችሏል፡፡

ባለፉት ጥቂት ዓመታት የመንግሥት ፕሮጀክቶችን የመፈጸም ዐቅም በእጅጉ አድጓል፡፡ ፕሮጀክቶች መቼ እንደሚጀመሩ እና በምን ያህል በጀት እንደሚፈጸሙ ብቻ ሳይኾን መቼ ተጠናቅቀው በትክክል አገልግሎት እንደሚሰጡ ጭምር በከፍተኛ የራስ መተማመን የመሠረት ድንጋይ ሲቀመጥ መናገር የሚቻልበት ቁመና ላይ ተደርሷል፡፡

እመርታዊ ስኬቶችን ዕውቅና ለመስጠት፣ በቀጣዮቹም ዓመታት የበለጠ እመርታዊ ስኬቶችን ለማስመዝገብ መዘጋጀት አስፈላጊ በመኾኑ ዛሬ ጳጒሜን 01 ቀንን “የኢትዮጵያ ማንሰራራት!” በሚል መሪ መልእክት እያከበርን ነው፡፡

እንኳን ለእመርታ ቀን አደረሳችሁ፣ አደረሰን!

ጳጒሜን 01 ቀን 2018 ዓ.ም
የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
አዲስ አበባ

የመንግሥትን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ ታጣቂዎች በሰላም ወደ ማህበረሰቡ ተቀላቀሉ፤በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ወረዳ ምስራቃዊ ቀጠና ከበለስ እስከ አጣምታና መረባ አካባቢዎች ታጥቀዉ  በጫካ ውስጥ...
06/09/2026

የመንግሥትን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ ታጣቂዎች በሰላም ወደ ማህበረሰቡ ተቀላቀሉ፤

በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ወረዳ ምስራቃዊ ቀጠና ከበለስ እስከ አጣምታና መረባ አካባቢዎች ታጥቀዉ በጫካ ውስጥ ሲንቀሳቀስ የቆየውና ራሱን የ208ኛ ኮር የራስ ገብሬ ብርጌድ ብሎ የሚጠራዉ ታጣቂ ቡድን የሰላም አማራጭን በመምረጥ በሰላም ገብተዋል።

በታጣቂዎች አጠራር በብርጌድ መሪው ዜናው ሃይለማርያም መሪነት የተደራጀው ይህ ኃይል፣ የሻለቃ አመራሮችንና የሻምበል መሪዎችን ጨምሮ አጠቃላይ 56 ታጣቂ አባላቱን ይዞ ወደ ሰላሙ ማህበረሰብ ተቀላቅሏል።

ቡድኑን ይዞት ከመጣው የጦር መሣሪያ ዝርዝር ውስጥ አንድ ስናይፐር፣ አንድ ብሬን እና የተለያዩ ነፍስ ወከፍ መሣሪያዎች ይገኙበታል።

ሀገር አቀፍ የሀገር ሽማግሌዎች የምክክር እና የልምድ ልውውጥ መድረክ  ላይ የተገኙ ተሳታፊዎች በደብረ ማርቆስ ከተማ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ሲጎበኙ ሰላም ለኢትዮጵያ! 🕊
06/09/2026

ሀገር አቀፍ የሀገር ሽማግሌዎች የምክክር እና የልምድ ልውውጥ መድረክ ላይ የተገኙ ተሳታፊዎች በደብረ ማርቆስ ከተማ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ሲጎበኙ

ሰላም ለኢትዮጵያ! 🕊

በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የጳጉሜ ቀናትን “የኢትዮጵያ መንሰራራት!” በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ ዝግጅቶች ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸው ተገለገፀ።**********ነሐሴ ...
05/09/2026

በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የጳጉሜ ቀናትን “የኢትዮጵያ መንሰራራት!” በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ ዝግጅቶች ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸው ተገለገፀ።
**********
ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም (ደብረ ማርቆስ ኮሙኒኬሽን): የጳጉሜ ቀናት በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ልዩ ቦታ ያላቸው ሲሆን ከአንድ ዓመት መጠናቀቅ እና ከአዲስ ዓመት መጀመር መካከል የሚገኙ የሽግግር ቀናት ናቸው።

የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ አቶ አበባው ግዛቸው በሰጡት ማብራሪያ የጳጉሜ ቀናት በሀገር አቀፍ ደረጃ በተሰጣቸው ስያሜ መሰረት በደብረ ማርቆስ ከተማ በተለያዩ መርሃ-ግብሮች ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን ገልፀዋል።

የጳጉሜ ቀናት ባሳለፍነው በጀት ዓመት የተሠሩ ሥራዎችን፣ የተገኙ ውጤቶችን፣ ያጋጠሙ ችግሮችንና የተገኙ ትምህርቶችን መሠረት ያደረገ የማህበራዊ ትስስርንና የአንድነት መንፈስን ለማጠናከር ልዩ ዕድል የሚፈጥሩ ስለመሆኑ አስገንዝበዋል።

የጳጉሜ ቀናት አከባበር ባህላዊ እሴቶቻችንን ለማስተዋወቅና ለትውልድ ለማስተላለፍም ጠቃሚ አጋጣሚ ነው ብለዋል።

የከተማዋን ማህበራዊ እሴቶች በተለያዩ መርሃ ግብሮች ለማሳየት እና ወጣቱ ትውልድ ስለሀገራዊ እሴቶቹ የበለጠ እንዲያውቅ ለማድረግ በሚያስችል መልኩ ዝግጅት ስለመደረጉ አቶ አበባው ገልፀዋል።

የእመርታ ቀን (ጳጉሜን-1) ፣የማንሠራራት ቀን (ጳጉሜን 2)፣ የጽናት ቀን (ጳጉሜን-3) ፣የኅብር ቀን (ጳጉሜን 4)፣ የነገ ቀን (ጳጉሜን 5) በሚል

የ2018 በጀት ዓመት የጳጉሜ ቀናቶችን በተቀናጀና በደመቀ መንገድ ለማክበር በቂ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተሠርተዋል ሲሉ አቶ አበባው ግዛቸው ተናግረዋል።

የጳጉሜ ቀናት የአሮጌው ዓመት ማጠቃለያ እና የአዲሱ ዓመት መሸጋገሪያ ድልድይ በመሆናቸው በከተማ ደረጃ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ይከበራሉ ብለዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከደብረ ማርቆስ ኮሚኒኬሽን ለማግኘት ሊንኩን በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
‎ቴሌግራም https://t.me/dmcomunicationoffice
‎ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php id=100064865823018
‎ቲክቶክ www.tiktok.com/
ዩቲብ:https://youtube.com/?si=h8-iiu60Df-Te3qJ

Address

Debre Mark'os
381

Telephone

+251587714141

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Debre Markos city communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share