የደቡብ ጎንደር ዞን ሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን

የደቡብ ጎንደር ዞን ሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን S/G VERA

04/02/2026
የደቡብ ጎንደር ዞን ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አስተባባሪ ኮሚቴ በደንብ ቁጥር 229/2011 እና በቴክኒክ ኮሚቴ አደረጃጀት ላይ ሁለቱ ኮሚቴዎች ማለትም የአስተባባሪ ኮሜቴዉና የቴክኒክ ኮሜቴዉ ...
04/02/2026

የደቡብ ጎንደር ዞን ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አስተባባሪ ኮሚቴ በደንብ ቁጥር 229/2011 እና በቴክኒክ ኮሚቴ አደረጃጀት ላይ ሁለቱ ኮሚቴዎች ማለትም የአስተባባሪ ኮሜቴዉና የቴክኒክ ኮሜቴዉ በጋራ ስልጠናዉን ከወሰዱ በኋላ ቡድኑ ያለበት ደረጃ መገምገሙ አስፈላጌ በመሆኑ የአስተባባሪ ከግንቦት 2017 እስከ ህዳር 30/2018 ዓ/ም ያለውን የምዝገባና ሌሎች የ6 ወራት አፈፃፀምን ሪፖርት በቡድን መሪዉ ቀርቦ በ22/5/2018 ዓ/ም በዞኑ የፍትህ መምሪያ ኃላፊ ሰብሰቢነት የሚመለከታቸውን ኮሚቴ አባላት መምሪያ ኃላፊዎችና ተወካዮች በተገኙበት ተገምግሟል፡፡
ስለሆነም ቡድኑ አሁን በአለበት ሁኔታ በሁሉም የምዝገባ አይነቶች የ7 ወራት አፈጻጸሙ ሲገመገም ከ2017 ዓ/ም አፈፃፀማችን ጋር ሲነጻጸር አሁን ላይ 107% መድረሱ እና ለሁሉም የምስክር ወረቀት መሰጠቱ የሚያበረታታ መሆኑን፣ ሌሎች ተግባራትም በተቀመጠላቸው እቅድ መሰረት እየተከናወኑ መሆኑን ገምግሞ እሰከ አሁን በአፈፃፀማቸው ከ 100 % በታች የሆኑትን ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ዝቅተኛ አፈጻጻም የታየባቸዉን ኩነቶች ፍች፣ጋብቻና ሞት የቤትዉስጥ የሚከሰት ልደትና ሞት ማሳወቂያ ፣የአንድ ማእከል ምዝገባንና የአድማጭ ቡድን ስራዎችን ትኩረት ሰጥተው በመስራት እስከ ሚያዝያ 30/2018 ዓ/ም የዞናችን የምዝገባ እቅድ መፈፀም እንዳለባቸው ኮሚቴው እየተከታተለ መደገፍና ማበረታታት እንደሚጠበቅበት ሰብሳቢው አቶ ጌታሰው መኳንንት አሳስበዋል ፡፡የኮሚቴ አባላት በቀጣይ ወራት እንደየመምሪያቸው የስራ ባህሪ መከናወን ያለባቸው የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ስራዎችን መደገፍ እንዳለባቸው ተግባብተዋል፡፡
እንዲሁም እቅዳቸውን እስከ አሁን 100 % ያልፈፀሙ ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች ተለይቶ አሁን በየወረዳው የአለው አመራር ድጋፍ እንዲያደርግ በኘላን መምሪያ ኃላፊው በኩል እንዲተላለፍ፣በተጨማሪም አዲሱን አደረጃጀት ምክንያት በማድረግ ስራ እንዳይዎድቅ በአስተዳደር ጽ/ቤት አማካኝነት ለሁሉም ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች የጽ/ቤት ሀላፊዎች፣የሲቭልና ቤተስብ ምዝገባ ቡድን መሪዎች የዙም ስብሰባ ተደርጎ ግንዛቤ እንዲፈጠርላቸዉ በሚል ተስማምተዋል ::

የሰዴ ሙጃ ወረዳ አሰ/ፅ/ቤትየሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባን በገጠርና በከተማ እንዴት መስራት እንዳለብን ከወረዳው አብይ ኮሚቴ ጋር የጋራ ውይይት ተደርኋል።በውይይቱም በወቅታዊ ችግሩ ምክንያት በማ...
04/12/2025

የሰዴ ሙጃ ወረዳ አሰ/ፅ/ቤት
የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባን በገጠርና በከተማ እንዴት መስራት እንዳለብን ከወረዳው አብይ ኮሚቴ ጋር የጋራ ውይይት ተደርኋል።በውይይቱም በወቅታዊ ችግሩ ምክንያት በማድረግ ምዝገባው የተዳከመበት ሁኔታ መኖሩን በመገምገም ጤና ኤክስቴንሽንና ስራ አስኪያጅ ተናበው በትኩረት በመስራት የላቀ ውጤት ማምጣት እንዳለብን ተወያይተናል

ኢየሱስ ከተማ አስተዳደር የሲብልና ቤተሰብ ቡድን ለቀበሌ አድማጭ ቡድኖችና ባለሙያዎች በወኩም ፅንሰ ሃሳብና ጠቀሜታ ዙሪያ ስልጠና ሰጠ።በደቡብ  ጎንደር  ዞን መካነ  ኢየሱስ ከተማ አስተዳደር...
04/12/2025

ኢየሱስ ከተማ አስተዳደር የሲብልና ቤተሰብ ቡድን ለቀበሌ አድማጭ ቡድኖችና ባለሙያዎች በወኩም ፅንሰ ሃሳብና ጠቀሜታ ዙሪያ ስልጠና ሰጠ።

በደቡብ ጎንደር ዞን መካነ ኢየሱስ ከተማ አስተዳደር የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን ለቀበሌ አድማጭ ቡድኖችና ባለሙያዎች በወኩም ፅንሰ ሃሳብና ጠቀሜታ ዙሪያ ስልጠና ሰጠ።

የስልጠናውን ሰነድ በመካነ ኢየሱስ ከተማ የሲቪልና ምዝገባ ቡድን መሪ በሆኑት በአቶ ገብሬ ወርቁ ቀርቦ ግንዛቤ ተፈጥሯል።

በተሠጠው ስልጠና ሰፊ ግንዛቤ ያገኙ መሆኑንና በስራ ላይ የሚገጥሙንን ክፍተቶችን ያረመላቸው መሆኑን የስልጠናው ተሳታፊዎች ገልፀዋል።

በስልጠናው የመካነ ኢየሱስ ከተማ አሰተዳደር ተወካይ ከንቲባና የከንቲባ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሞገስ አለነ እደገለፁት የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ሃገራዊ መረጃ በመሆኑ ስልጠነውን በትኩረት በመያዝ መረጃው በትክክልና ወቅቱን ጠብቆ መመዝገብ አለበት ሲሉ አሳስበዋል።

በስልጠናው የመካነ ኢየሱስከተማ አስተዳደር ተወካይ ከንቲባና ከንቲባ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሞገሰ አለነ መካነ ኢየሱስ የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን መሪ አቶ ገበሬ ወርቁና የኩነት ባለሙያዎች ፥ የቀበሌ ባለሙያዎችና አድማጭ ቡድኖችና አጋር አካላት ተገኝተዋል ።

"መረጃ ለሃገራዊ ፍይዳ"

ህዳር 23 2018 ዓ ም
መካነ ኢየሱስ ኮምንኬሽን

Address

Debre Tabor

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የደቡብ ጎንደር ዞን ሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share