Visit South Gondar

Visit South Gondar We are promoting south gondar zone especially tourist attractions .

ዳቃ ቂርቆስ ንጉስ ይትባረክ የተሸነፉበት(የሞቱበት) አፄ ይኩኖአምላክ ድል ያደረጉበት ቦታ ነው፡፡• በታች ጋይንት ወረዳ የሚገኝ የጦር አውድማ  ቦታወች ውስጥ አንዱ ሲሆን ከአርብ ገብያ አንሰ...
16/03/2026

ዳቃ ቂርቆስ ንጉስ ይትባረክ የተሸነፉበት(የሞቱበት) አፄ ይኩኖአምላክ ድል ያደረጉበት ቦታ ነው፡፡

• በታች ጋይንት ወረዳ የሚገኝ የጦር አውድማ ቦታወች ውስጥ አንዱ ሲሆን ከአርብ ገብያ አንሰታ ጊወርጊስ በሚያስሄደው መንገድ ከወረዳው ዋና ከተማ አርብ ገበያ በ13 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል ።በመኪና ከ20-30 ደቂቃ በእግር ለሚጓዙ ደግሞ ከ 1:30-2:00 ገደማ ይወስዳል። ብዙ ነገስታቶችን ያፈራረቀው ይህ ቦታ በክረምትም ሆነ በበጋ ለጎብኚዎች ምቹ ነው።

• ዳቃ ማላት በግዕዝ ወጋ ፤መታ፤ጎሰመ ማላት ነዉ፡፡

• ዳቃ ቂርቆስ በአፄ ኢዛና ዘመነ መንግስት እንደተመሠረተ የሚነገርለት ቤተክርስቲያን ፅላቱ ከእየሩሳሌም በንግስት ሳባ ልጅ በምንትልክ( በአፄ ሚኒሊክ አንደኛ ) አክሱም ፂወንን ሲያመጣ አብሮ የመጣ እንደሆነ ይነገርለታል ።

• በዚች ጥንታዊት ቤተክርስቲያን ከውጭ ወደ ቅጥር ጊቢው ሲገቡ በቀኝ በኩል ከተራራው ማዶ ላይ የፈራረሰ ጥንታዊ ከተማ ይታያል። ይህ ከተማ ዘበላ ከተማ በመባል ይጠራል ። ዘበላ ከተማ በንግስት ዘበላ በራሷ ስም የሚጠራ እንደሆን ታሪክ ያወሳል ።ይህ ከተማ ሰፊ ከተማ ሲሆን በአካባቢው የሚገኙ ገበሬዎች እርሻ በምናርስበት ሰአት አልፎ አልፎ የሰው ቅሪት አካል እናገኛለን ይላሉ።

• ዳቃ ቂርቆስ አበው እንደሚሉት ለ 2 ጊዜ ታድሷል። የመጀመርያው እድሳት በአፄ ይኩኖአምላክ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በ1964-65 ዓ.ም ነው።

• የዛጉዌ ፍፃሜ የመጣው የድል ናኦድ ዘር እና ትክክለኛ ወራሽ መሆኑን በቅዱስ ተክለ ሃይማኖትም ሆነ በቅዱስ ኢያሱ ሞአ መሪነት ራሱን ንጉስ ብሎ ያወጀው ይኩኖ አምላክ የመጨረሻውን የዛግዌ ንጉስን በማሳደድ ሲገድል ነበር ፡፡

• በዳቃ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ውስጥ የመጨረሻው የዛግዌ ስርዕዎ መንግስት እንደሆነ የሚነገርለት አፄ ይትባረክ የተፋለሙበት የተሸነፉበት(የሞቱበት) ከሰሎሞን ስርዎ መንግስት የሚመደበው አፄ ይኩኖአምላክ ድል ያደረጉበት ቦታ ነው። በዚህም የተነሳ አፄ ይኩኖአምላክ አፄ ይትባረክን በጦር "ደቃ" ሲል ዳቃ የሚለውን እንዳገኘ ይነገርለታል።

• በዚህ ድንቅ ቤተክርስቲያን ውስጥ የአፄ ይትባረክ፤ የርሳቸው ጳጳስ ክርስቶስ ደውሎ እና የኤዾስ ቆዾሱ ሀውልቶች ፊትና ኋላ ቁመው ይገኛሉ።

በስፍራው በወቅቱ አፄ ይኩኖ አምላክ ከጎጃም ጭነው እንዳመጡት የሚታመነው አፍር ይገኛል ።

የአበምኔቱ መካነ መቃብር ይገኛሉ። ሁሉንም መካነ መቃብሮች አሸናፊው ንጉስ አፄ ይኩኖአምላክ እንዳሰራቸው ይነገራል ።

ይምጡና ይጎብኙ፡፡

የደቡብ ጎንደር ዞን ባህልና ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ

‎ #ስለ ርብ_ወንዝ ውይዛ_ፏፏቴ_ምን_ያህል_ያውቃሉ?‎‎የርብ ወንዝ ውይዛ ፏፏቴ በደቡብ ጎንደር ዞን፣ ፋርጣ ወረዳ ውስጥ ከሚገኙ የተፈጥሮ ሀብቶች መካከል በልዩ ሁኔታ የሚጠቀስ እና የተስፋ ...
22/02/2026

‎ #ስለ ርብ_ወንዝ ውይዛ_ፏፏቴ_ምን_ያህል_ያውቃሉ?

‎የርብ ወንዝ ውይዛ ፏፏቴ በደቡብ ጎንደር ዞን፣ ፋርጣ ወረዳ ውስጥ ከሚገኙ የተፈጥሮ ሀብቶች መካከል በልዩ ሁኔታ የሚጠቀስ እና የተስፋ ምንጭ የሆነ ድንቅ ፏፏቴ ነው። ይህ ፏፏቴ በወረዳው ውስጥ በወዋ ማገራ ቀበሌና በደረሂና ቀበሌ መካከል በሚገኝ ተፈጥሯዊ ስፍራ ላይ ይገኛል።

‎ከፍታው፣ ውበቱና በዙሪያው ያለው አረንጓዴ ተፈጥሯዊ አካባቢ ፏፏቴውን ለመጎብኘት በጣም ማራኪ ያደርገዋል። የርብ ወንዝ ፏፏቴ ለኢኮ-ቱሪዝም እድገት፣ ለአካባቢው ህዝብ የገቢ ምንጭ ለመፍጠር እና የዞኑን ተፈጥሯዊ ሀብት ለሀገርና ለዓለም ማስተዋወቅ ታላቅ አቅም ያለው ነው።

‎በአጠቃላይ፣ የርብ ወንዝ ፏፏቴ በጥበቃና በልማት ተግባራት ተደግፎ ከተጠበቀ እና ከተሻሻለ፣ ለደቡብ ጎንደር ዞን እድገትና ለቱሪዝም መስፋፋት ዋና ድርሻ ይኖረዋል ፡፡

‎ አከባቢያችንን እንወቅ፡ እናስተዋውቅ!
‎ኑ ደቡብ ጎንደር ዞንን ጎብኙ

South gonder zone culture tourism and Sport office

 የምስቅና ምዕራብ ጎጃም ወረዳዎች የሚያዋስኑት የጮቄ ተራራ አካል የሆነው በደጋ ዳሞት ወረዳ በጣእመ ቀበሌ  የሚገኘው ሙሉ ኢኮሎጅ ፦በፈረንጆች አቆጣጥር 2023 ላይ አንድ የገጠር መንደር ክ...
08/02/2026



የምስቅና ምዕራብ ጎጃም ወረዳዎች የሚያዋስኑት የጮቄ ተራራ አካል የሆነው በደጋ ዳሞት ወረዳ በጣእመ ቀበሌ የሚገኘው ሙሉ ኢኮሎጅ ፦

በፈረንጆች አቆጣጥር 2023 ላይ አንድ የገጠር መንደር ክፍለ ሀገርና ሀገር አቋርጦ፤ ውቅያኖስ ከአሁጉራት ጋር ተሻግሮ ወደ አለም አደባባይ ብቅ አለ።

በዚህ መድረክ ከ150 በላይ ሀገራት ተሳተፉበት። 32 መንደሮች ታጭተው ቀረቡበት።

ሳውዲ አረቢያ በአልኡላ መንደር አስተናጋጅነት የ2023 የዓለም ምርጥ የቱሪዝም መንደር ሆኖ አንድ ደሳሳ መንደር አለም ፊት ተገለጠ።

ሲበዛ ገጠር ውስጥ ይገኛል። ነባረ ሀገረኛ ወግ ባህል ይዳሰስበታል። ተፈጥሯዊ ጸጋ ከአስደናቂ መልካምድር ጋርም ተቸሮታል።

ቅዝቃዜ ከጉም ጋር፤ ብርድ ከበረዶ ጋር ተፈራርቆ ይስተናገድበታል።

መንትያ ተራሮች እዚያ እና እዚህ ቆመው ያጅቡታል። ተፈጥሮን ከላይ ወደ ታች፤ ከቅርብ ወደ ሩቅ እያደነቁ ያጣጥሙበታል።
Visit Amhara
🎥

Ethiopia has a total of six UNESCO Biosphere Reserves, with designations occurring between 2010 and 2025. Each reserve w...
02/12/2025

Ethiopia has a total of six UNESCO Biosphere Reserves, with designations occurring
between 2010 and 2025. Each reserve was recorded in the UNESCO World Network of Biosphere Reserves under the Man and the Biosphere (MAB) Programme at different times.

Here are the UNESCO Biosphere Reserves in Ethiopia and their designation dates:

1. Kafa Biosphere Reserve: Designated in 2010.

2. Sheka Forest Biosphere Reserve: Designated in 2012.

3. Lake Tana Biosphere Reserve: Designated in June 2015.

4. Majang Forest Biosphere Reserve: Designated in June 2017.

5. Yayu Coffee Forest Biosphere Reserve: Designated around the same period as the others, prior to 2025.

6. Anywaa Biosphere Reserve: Officially registered on September 27, 2025.

These sites are established to promote and demonstrate a balanced relationship between people and nature, fostering biodiversity conservation and sustainable development.

√ You can find more information about these and other sites on the Ethiopian Biodiversity Institute website or the UNESCO MAB Programme pages.

South gonder zone culture and tourism office

የአማራ ክልል የባህል ቱሪዝምና ስፓርት ቢሮ
28/11/2025

የአማራ ክልል የባህል ቱሪዝምና ስፓርት ቢሮ

በደብረታቦር ከተማ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የኪነ ጥበብ ውድድር ተጠናቀቀ፡~የደቡብ ጎንደር ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ እና በደብረታቦር ከተማ ባህልና ቱሪዝም ተጠሪ ጽ/ቤት በጋራ በመሆ...
27/12/2024

በደብረታቦር ከተማ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የኪነ ጥበብ ውድድር ተጠናቀቀ፡
~

የደቡብ ጎንደር ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ እና በደብረታቦር ከተማ ባህልና ቱሪዝም ተጠሪ ጽ/ቤት በጋራ በመሆን ኪነ ጥበብ ለሰላም በሚል መሪ ቃል ለ2 ተከታታይ ቀናት ሲያካሂዱት የቆዮት የትያትር፣ባህላዊ ሙዚቃና ውዝዋዜ በዛሬው ዕለት ፍጻሜውን ሲያገኝ በመዝጊያው እለት በመገኘት ንግግር ያደረጉት የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጥላሁን ደጀኔ ኪነ ጥበብ ለሰላም ዋና መሳሪያ መሆኑንና ተሳታፊዎችም አሁን ላይ ያለውን ችግር ተቋቁማችሁ እዚህ በመገኜታችሁ ልትመሰገኑ ይገባል በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል ፡፡
አሽናፊዎች

በትያትር ዘርፍ
1. ወረታ ከተማ አስተዳደር የትያትር ቡድን
2.ፈርጥ የትያትር ቡድን/ፋርጣ ወረዳ
3.ሀገረ ቢዘን የትያትር ቡድን/ስማዳ ወረዳ/ አሸናፊ ናቸው

በባህላዊ ሙዚቃና ውዝዋዜ ዘርፍ
1.አዲስ ዘመን ከተማ የኪነት ቡድን/አዲስ ዘመን
2.ፊ/ገብርየ የባህል ቡድን/ላይ ጋይንት ወረዳ
3.ብሩህ ተስፋ የባህል ቡድን/እስቴ ወረዳ ናቸው፡፡
ሽልማት
~በሁለቱ ዘርፎች 1ኛ ለወጣ 10,000 ብር
~በሁለቱም ዘርፎች 2ኛ ለወጣ 5,000 ብር
~በሁለቱም ዘርፎች 3ኛ ለወጣ 3000 ብር ሲሆን በሁሉም ዘርፎች ኮከብ ለሆኑ የምስክር ወረቀት እና የ1000 ብር ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን የወረታ ከተማ የትያትር ቡድንና የአዲስ ዘመን ከተማ የኪነት ቡድን በጎንደር ከተማ በሚዘጋጀው 16ኛው ክልል አቀፍ የባህል ፌስቲቫል ላይ ደቡብ ጎንደርን ወክለው ተሳታፊ ይሆናሉ ፡፡

የደቡብ ጎንደር ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ከደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ተጠሪ ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን ታላቅ የኪነ ጥበብ ውድድር በደብረታቦር ከተማ በህብረት ሲኒማ አዳራ...
24/12/2024

የደቡብ ጎንደር ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ከደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ተጠሪ ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን ታላቅ የኪነ ጥበብ ውድድር በደብረታቦር ከተማ በህብረት ሲኒማ አዳራሽ ዛሬ 15/04/2017 ዓ.ም ተጀምሯል ፡፡ በእለቱም የደብረታቦር ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ሀይለእየሱስ ሰለሞን,አቶ ሀብታሙ ጌታሁን የደብረታቦር ከተማ ብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ሀለፊ, አቶ አለበል ደመላሽ የደብረታቦር ከተማ ባህልና ቱሪዝም ተጠሪ ጽ/ቤት ሀላፊ, አቶ ገደፋው ወርቁ የደቡብ ጎንደር ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ተወካይ ሀላፊ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ፕሮግራሙ በይፋ ተከፍቷል፡፡ በመክፈቻ ፕሮግራሙ ንግግር ያደረጉት አቶ ሀይለእየሱስ ሰለሞን ኪነ ጥበብ ለሰላም እና ለእድገት የለውን አበርክቶ እንዲሁም በኪነ ጥበብ ውስጥ በርካታ ችግሮች ሊገጥሙ እንደሚችሉና ተሰጥኦ ያላቸው ሁሉ ተስፋ ባለመቁረጥ ሙያቸውን እንዲያሳድጉ ሲሉ ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡

ቱሪዝም ለሰላም!
ኪነ ጥበብ ለሰላም!

የደቡብ ጎንደር ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ታህሳስ 15 ቀን 2017 ዓ/ም

14/12/2024
10/12/2024
 #ጎጣ ፏፏቴ # Gota Fall # ደቡብ ጎንደር ዞን   gonder Zone    woreda  Land Of origion
05/12/2024

#ጎጣ ፏፏቴ
# Gota Fall

# ደቡብ ጎንደር ዞን
gonder Zone

woreda

Land Of origion

Address

South Gondar Zone
Debre Tabor

Telephone

+251584410924

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Visit South Gondar posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Visit South Gondar:

Share