Mayor Office Of Debre Tabor City

Mayor Office Of Debre Tabor City This Is The Official Page Of Debre Tabor City Mayor Office

27/02/2026
27/02/2026

"የአድዋ ድል የመላ ኢትዮጵያውያን አንድነት ውጤት ነው"

የበለፀጉ የአውሮፓ ሃገራት ታዳጊ ሃገራትን በኃይል በመውረር በቅኝ ግዛት ስር ለማዋል የጠነሰሱት ሴራ በመላ ኢትዮጵያውያን አንድነት ከሽፏል።

የጣሊያን መንግስት ኢትዮጵያን ለመውረር አቋም ከወሰደና ከወሰነ በኋላ ወሰን ጥሶ፣ድንበር ተሻግሮ በወሎ ክፍለ ሀገር በወረኢሉ አውራጃ ቦሩ ሜዳ አካባቢ ውጫሌ በተባለ ልዩ ስፍራ ሚያዚያ 5/1881 በኢትዮጵያው ንጉስ ዳግማዊ አፄ ምኒልክና በኢጣሊያን መንግሥት ንጉስ አምቤርቶ መካከል ይሆናል ያሉትን የሠላምና የንግድ የውል ስምምነት አድርገው ነበር።

130ኛውን የአድዋ ድል በዓል አስመልክቶ የደቡብ ጎንደር ዞን ጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር የእንኳን አደረሳችሁ ምኞቱን ገልጿል።

የማህበሩ ሊቀመንበር አቶ አምባቸው ሞላ ባስተላለፉት መልዕክት ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሳይከፋፈሉ እንደቀደሞዎቹ አያት ቅድመ አያቶቹ የሀገርን ክብርና ሉዓላዊነት በአንድነት መጠበቅ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በወቅቱ ከነበሩት ግንባሮች መካከል ብርሃን ዘኢትዮጵያ እቴጌ ጣይቱ ብጡል የመሩት ጦር ከፍተኛ ጥበብ የተቸረው ነበረ ያሉት አቶ አምባቸው ሀገርን እንዴት መምራት እንደሚቻል ጭምር ከቀደምት ጀግኖች ኢትዮጵያውያን እንማራለን ብለዋል።

በመጨረሻም የእቴጌ ጣይቱ "እኔ ሴት ነኝ፣ጦርነት አልወድም፤ይህንን መሳይ ውል ከምንቀበል ይልቅ ጦርነት እመርጣለሁ" ከሚለው እንቁ ንግግር የምንማረው የሀገር ፍቅርን ነው ሲሉ አቶ አምባቸው አስታውሰዋል።

28/01/2026

Address

Debre Tabor

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mayor Office Of Debre Tabor City posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share