Save the Children and Mothers

Save the Children and Mothers Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Save the Children and Mothers, Evaton.

26/09/2025
ሰላም ቤተሰብ እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን።እጅባሮች በመተባበር ድንቅ ስራ በየአመቱ እንደሚሰሩት አሁንም ዝግጅታቸውን ለወገኖቻችን ለመርዳት አማሙቀውታል።አመራር ኮሚቴው እስካሁን ከወገኖቻችን ...
26/09/2025

ሰላም ቤተሰብ እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን።

እጅባሮች በመተባበር ድንቅ ስራ በየአመቱ እንደሚሰሩት አሁንም ዝግጅታቸውን ለወገኖቻችን ለመርዳት አማሙቀውታል።

አመራር ኮሚቴው እስካሁን ከወገኖቻችን በተላከው 227,061ብር ወገኖቻችን ለመርዳት ዝግጅት ላይ ናቸው ስለት የሰጡና ሌሌች ያስገቡ ወገኖቻችን ስም ዝርዝር ኮሚቴው እንዳስፈላጊነቱ ያሳውቀል። እጃችሁን የዘረጋችሁ በሙሉ እጅጉን እናመሰግናለን መልካም በዓል ይሁንልን ይሁንላችሁ።

የመስቀል ትዝታዎች በዲቲ ዘይገርም ነው

ትዝታዎችን በኮሜንት የረሳነውን አስታውሱን።

በዲቲ ሰፈሮች እንዴት በዓሉን እንደምታሳልፉ በውስጥ መስመር ላኩልን።

አጅባሮች  ከውጭ ከሚኖሩ ወንድምና እህቶቻቸው  እንዲሁም የእናቶችና ህፃናት አድን ድርጅት  - ኢትዬጵያ Save the children and mothers ጋር በመተባበር ወግኖቻችን ለመርዳት ለ...
18/09/2025

አጅባሮች ከውጭ ከሚኖሩ ወንድምና እህቶቻቸው እንዲሁም የእናቶችና ህፃናት አድን ድርጅት - ኢትዬጵያ Save the children and mothers ጋር በመተባበር ወግኖቻችን ለመርዳት ለመስቀል በዓል ዝግጅት ላይ ናቸው።

የልጆችና እናቶች አድን - ኢትዬጵያ Save the children and mothers ድርጅት በፈረንጆት ከ2007 ጀምሮ ለከተማችን እንዲሁም ለወገኖቻችን በመርዳት ላይ ይገኛል ወገኖቻችን በመርዳትና ከተማችን በማስተዋወቅ ይህ ድርጅት የመጀምሪያው ነው።

ሁላችሁም የቻላችሁትን በየሰፈራችሁ ጧሪ የለላቸውን እናትና አባቶች፣ ስራ አጥ ወንድም እና እህቶቻችን እንዲሁም ወቅታዊ የሆኑ ችግሮችን ለመፍታት እንሰባሰብ እንረዳዳ።

Account No= 1000705003967
Save the Children and Mothers-Ethiopia
የእናቶችና ህፃናት አድን ድርጅት-ኢትዮጵያ

በአሜሪካ የምትኖሩ በቴሌግራም ግሩፓችን Join በማድረግ በሪሁን መኲንን፣ እሱባለው መላኩን፣ ሰሎሞን ዘመነን እና ይበልጣል ፀሐይን ማነጋገር ትችላላችሁ።

https://t.me/savethechildrenandmothers

በርቱ ወገኖቻችን በያለንበት እንርዳ እንረዳዳ።

እናመሰግናለን።

የእናቶችና ህፃናት አድን ድርጅት - ኢትዬጽያ  ረዳት ለሌላቸው ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አንድ ደርዘን ለአንድ ተማሪ በሚል መሪ ሀሳብ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።        ...
06/09/2025

የእናቶችና ህፃናት አድን ድርጅት - ኢትዬጽያ ረዳት ለሌላቸው ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አንድ ደርዘን ለአንድ ተማሪ በሚል መሪ ሀሳብ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

የማህበራችን አስተባባሪ አቶ ሶሎሞን ዘመነ እንደተናገሩት በዛሬው ዕለት ከ35ሽህ ብር በላይ ወጭ የተደረገበት ደብተርና እስክርቢቶ ከመቶ በላይ ለሚሆኑ ረዳት ለሌላቸው ተማሪዎች ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልፀው ማህበሩ ከሀገር ውስጥ እስከ ሀገር ውጭ ድረስ የሚኖሩ አባላትን ያቀፈ በጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን ለአቅመ ደካማ እናቶች፣ አባቶችና ህፃናትን መደገፍ ነው ብለዋል።

የድጋፍ ፕሮግራሙ የዳግማዊ ቴዎድሮስ አጠቃላይ ፩ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን የነበሩ ዛሬ ላይ የዕድሜ ባለፀጋና ጡረተኞች በተገኙበት የተካሄደ ሲሆን ከእነዚህም መካከል መምህር ይግዛው ሰንደቄ ባስተላለፋት መልዕክት የድጋፉ ምንጮች በተለያዩ የውጭው ዓለማት የሚገኙ የትምህርት ቤቱ የቀደሞ ተማሪዎች ናቸው ብለዋል።

"ትውልድ ላይ መስራት ትርፋማ" እንደሚያደርግ የተገነዘቡት የማህበሩ አባላት ተምረው ካለፉበት ትምህርት ቤት የሚማሩ ደጋፊ የሌላቸውን ተማሪዎች በመርዳት ውጤታማና ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለመገንባት እየተጉ ይገኛሉም ብለዋል አቶ ይግዛው።

ጳጉሜ 1/2017 ዓ.ም
ፎቶ South Gonder communication

አንድ ደርዘን ደብተር ለአንድ ተማሪ በበጎ አድራጎት ተግባር መሳተፍ ለምትፈልጉ ይህ ይህን መጨረሻው የምንሰበስበት ሳምንት ይሄናል ያልተሳተፋችሁ  Account No= 1000705003967 (S...
23/08/2025

አንድ ደርዘን ደብተር ለአንድ ተማሪ በበጎ አድራጎት ተግባር መሳተፍ ለምትፈልጉ ይህ ይህን መጨረሻው የምንሰበስበት ሳምንት ይሄናል ያልተሳተፋችሁ
Account No= 1000705003967 (Save the Children and Mothers-Ethiopia ወይም የእናቶችና ህፃናት አድን ድርጅት-ኢትዮጵያ) ማስገባት ትችላላችሁ፡፡

በአካል መጥታችሁ ለመለገስ የምትፈልጉ፡-
1. ያሬድ ግሮሰሪ (አድራሻ፡- ከተባበሩት ማደያ ወደ መድሐኒያለም በሚወስደው መንገድ)
ስልክ= 0932192515
2. ጉና ካፍቴሪያ( አድራሻ፡- ዳግማዊ ቴወድሮስ አጠቃላይ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ፊት ለፊት)
ስልክ= 0904366243

3. በአሜሪካ የምትኖሩ በቴሌግራም ግሩፓችን Join በማድረግ በሪሁን መኲንን፣ እሱባለው መላኩን፣ ሰሎሞን ዘመነን እና ይበልጣል ፀሐይን ማነጋገር ትችላላችሁ፡ https://t.me/savethechildrenandmothers

የፋሲካን በዓል በማስመልከት አቅመ ደካሞችን እንዲሁም ለመደገፍ Save the children and mothers - Ethiopia እያሰባሰበ ይገኛል። ወገኖቻችን ለመርዳት በየአመቱ በተለያየ በ...
10/04/2025

የፋሲካን በዓል በማስመልከት አቅመ ደካሞችን እንዲሁም ለመደገፍ Save the children and mothers - Ethiopia እያሰባሰበ ይገኛል። ወገኖቻችን ለመርዳት በየአመቱ በተለያየ በዓላቶችና ወራቶች በመርዳት ይህ እርዳታ እግዚአብሔር ከረዳን በየቀኑ አቅመ ደካሞችን የምንደግፍበት ይሆናል ብለን አስበናል Save the Children and Mothers ከ2007G.C ጀምሮ ለተከታታይ አመታት በየአመቱ ወገኖቻችን የሚረዳ ድርጅት ሲሆን ዘንድሮም በተመሳሳይ ሁኔታ ገንዘብ እያሰባሰብን ሲሆን በተለይ በስሜን አሜሪካ የምትኖሩ በመላው አለም የምትኖሩ ወገኖቻችንና እና የደብረታቦር አካባቢ ተወላጆች በዚህ የበረከት ስራ እየተሳተፍ ሲሆን እስካሁን 32000 ብር ተሰብስቧል። የደብረታቦር ተወላጆች እንዲሁም ኢትዬጵያውያን ኤርትራውያን የዚህ በረከት ተሳታፊ እንድትሆኑ በእግዚአብሔር ስም እጠይቃለሁ።

ቴሌግራም ግሩፕ ሊንኩን ከፍተው Join ያድርጉ።

https://t.me/savethechildrenandmothers

አመሰግናለሁ።

እንኳን አደረሳችሁ!!በቅድሚያ እንኳን ለ2017 ዓ.ም. የጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሰኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!! እያልን፡- እኛ ስንደክም የብርታታችን ምንጮች፣እኛ ስንዝ...
07/04/2025

እንኳን አደረሳችሁ!!
በቅድሚያ እንኳን ለ2017 ዓ.ም. የጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሰኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!! እያልን፡-
እኛ ስንደክም የብርታታችን ምንጮች፣
እኛ ስንዝል ጥንካሬወቻችን፣
እኛ ስንረሳ አስታዋሾቻችን፣
እኛ ስንጨነቅ አረጋጊወቻችን፣
እኛ ስንጎድል ሙላቶቻችን፣…
የሆኑት ሁሌም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በደብረ ታቦር ከተማ የሚገኙ አቅመ ደካሞችን በመርዳትና በመደገፍ የሚታወቁት በውጭ የሚገኙ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ዘንድሮም እንደተለመደው አለሁላችሁ ብለውናል፡፡ እስካሁን በዋናነት በመስቀል፣ በገና፣ በትንሳኤና በዘመን መለወጫ በዓላት እንዲሁም በክረምት ወቅት ብርድ ልብስ፣ ለህፃናት መማሪያ ደብተር በተለያዩ አደረጃጀቶች በመለገስ ወገኖቻችን ሲረዱ እና ሲደግፉ የቆዩ ሲሆን ወደፊት እነዚሁን የማህበረሰባችን አካላት በቋሚነት ለመደገፍ እና ከውጭ ግብረሰናይ ድርጅቶች ጋር አብሮ ለመስራት በማሰብ በከተማችን የበጎ አድራጎት ተምሳሌት በሆነው በወንድማችን በሪሁን መኮንን አነሳሽነት አ.ኤ.አ ከ 2006 ዓ.ም. ጀምሮ በደቡብ አፈሪካ ተቋቁሞ በደቡብ አፍሪካ እንዲሁም በኢትዮጵያና በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ግልጋሎት ሲሰጥ የነበረውን እስከ አሁን ድረስም አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘውን እድሜ ጠገብ የበጎ አድራጎት ድርጅት በከተማችን ደብረታቦር Save the Children and Mothers-Ethiopia (የእናቶችና ህፃናት አድን ድርጅት-ኢትዮጵያ) በሚል ስም አዲስ የበጎ አድራጎት ድርጅት ያቋቋምን ሲሆን አስፈላጊ የሆኑት ዶክመንቶችን በሙሉ አሟልተን በመገኘታችን ከደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን ፍትህ መምሪያ የሰነዶች፣ ሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶችና ጠበቆች ቡድን በቀን 13/06/2017 የምዝገባ ሰርቲፊኬት እና የበጎ አድርጎት ድርጅት መመስረታችን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ተቀብለናል፡፡ ይህንን ምክንያት በማድረግ ከወዲሁ በህፃናት፣ እናቶችና አረጋውያን ላይ የሚሰሩ አንዳንድ የውጭ ድርጅቶች አብረውን ለመስራት ቃል ገብተውልናል፡፡
የማህበሩን መመስረት ምክንያት በማድረግም ሁሌም ከጎናችን የሆኑት የአካባቢያችን ልጆች፣ ኢትዮጵያዉያን እና ኤርትራውያን ከወዲሁ የ2017 ዓ.ም. የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድግ አዲስ በተቋቋው ድርጅታችን ስም ለአቅመ ደካሞች በዓል መዋያ ይሆን ዘንድ በበሪሁን መኮንን አስተባባሪነት ገንዘብ አዋጥተው ልከውልናል፡፡ በዚህም መሰረት፡-
• በሪሁን መኮንን ከአትላንታ=$100
• ሰላም ፎቶ ከአትላንታ= $100
• መቅደስ ከዱባይ= 4160 Birr አስገብተውልናል፡፡ እኛም ስለተደረገልን መልካም ድጋፍ እያመሰገንን እነዚህን የአካባቢያችን ድምቀት የሆኑ እህቶቻችን እና ወንድሞቻችን ድንግል ማሪያም ትከተልልን፣ እግዚአብሔር አምላክ ያክብርልን፣ ጨምሮ ጨማምሮ ይስጥልን፣ በሔዱበት ሀገር ሁሉ ይጠብቅልን፣ ያሰቡትን ያስፈጽምልን፣ ከትንሳኤ እረዴት በረከት ያካፍልልን፣ በወጣው ይተካ እንላለን! አሜን!!!
ማስታወሻ፡- ውድ የአካባቢያችን ልጆች፣ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ አቅመ ደካማ እናቶቻችን እና አባቶቻችንን መደገፍ የምትፈልጉ በሙሉ፡- በውጭ የምትኖሩ ወንድማችን በሪሁን መኮነንን እንዲሁም በሀገር ውስጥ የምትኖሩ ደግሞ እሱባለው መላኩን፣ ሰሎሞን ዘመነን እና ይበልጣል ጸሐይን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ የእናቶቻችን እና አባቶቻችን ምርቃት አይለየን! አሜን! ይቆየን!!!

ሸር በማድረግና የድርጅቱ አባል ደጋፊ በመሆን ይሳተፉ።
ቴሌግራም ግሩፕ: https://t.me/+_nCqFEBkgZthYmUx

Save the Children and Mothers South Africa team.
For more information please visit http://www.savethechildrenandmothers.org/about.html and https://www.facebook.com/savethechildrenandmothers/info.

Celebrating my 13th year on Facebook. Thank you for your continuing support. I could never have made it without you. 🙏🤗🎉
23/09/2024

Celebrating my 13th year on Facebook. Thank you for your continuing support. I could never have made it without you. 🙏🤗🎉

17/04/2015
31/01/2015
Save the Children and Mothers in Ethiopia 2015-01-08.
22/01/2015

Save the Children and Mothers in Ethiopia 2015-01-08.

Address

Evaton

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Save the Children and Mothers posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Save the Children and Mothers:

Share