26/12/2019
┄┉✽̶😎ምስጢራዊ ሌባ😎̶̥✽̶┉┄
▬▬▬❁ ክፍል አንድ ❁▬▬▬
ከጠዋቱ አራት ሰአት አካባቢ ነበረ የግቢ በር ከወትሮው በተለየ መልኩ በኃይል መንኳኳት የተጀመረው...
ቁርስ በልታን ተነስተን ነበረ ቀኑ ቅዳሜ ስለነበረ ት/ቤት አልሄድኩም እቃውን በመጠብ ላይ ቢዝ ሆኜ ነበረ፣
ኧረ መጣሁ መጣሁ ብልም በሩን ከመንኳኳት አልተቆጠቡም እንደውም በፍጥነት መንኳኳት ጀመሩ...
እኔም በፍጥነት ሄጄ በሩን ከፈትኩት በእናትሽ ውስጥ አስገብኝ አለኝ
እኮ ለምን አልኩት
በእናትሽ አሁኑኑ ተመልሼ እወጣለሁ አስገብኝ አለኝ
እሺ ግን ማነህ?
ለምን እኛ ቤት መግባት ፈለክ አልኩት
ኧረ በፈጣሪ ምኗ ደረቅ ነት በቃ ሁሉንም ነገር እናግርሻለሁ ግን አሁን ሊገሉኝ ነው አስገብኝ አለኝ
እሺ ብዬ እንዲገባ ፍቀድኩለት
እሱም ፈጥኖ ግቢ ውስጥ ገባ፣
ልክ እሱ ግቢ ውስጥ እንደገባ የሆነ ልጆች ዱላ ድንጋይ ምናምን ይዘው መጡ...
የግቢው በር አልተዘገም ነበረ እነሱ ግን እዚህ ግቢ ይገባል ብሎ ምንም አልተጠረጠሩም ከልጆቹ መሃል አንዱ ልጅ የሆነ ቀይ ረዥም በእጁ ፕላስቲክ የያዛ ልጅ በዚህ አልፏል ወይ ብሎ ጠየቀኝ
አዎ አሁን ወደዛ አልፏል ግን ምን አድርገው ነው አልኩት
ሌባ ነው ሰርቆ ነው አለኝ
ልጅ እኛ ግቢ ውስጥ ነው በዛ ላይ ሌባ አልወድም ግን ልጁ ይገሉኛል ብሎ ስለነበረ አዘንኩላት ልጆቹም እየሮጡ ሄዱ።
ልጆቹ አልፎ ከሄዱ በኋላ አንተ ሌባ ሌባ መሆንህን ብያውቅ እኛ ግቢ አትገባትም ነበረ ምን ይመስላል አንተ ገና ወጣት ነህ አይደል ለምን ሰርታ አትበላም አልኩት
እሱ ግን እህቴ በጣም አመሰግናለሁ ዛሬ አልቆልኝ ነበረ ብሎ ልሄድ ሲል...
እሺ እናግርሻለሁ ያልከኝን ንገረኝ አልኩት
እሱ ግን ዝም ብሎ በፍጥነት እየሮጣ ሄደ።
ለምን እንደሆነ ደስ አላለኝም ቲሽሽሽሽ ለምን ሌባ አልኩት ብዬ ትንሽ ፀፀት ውስጥ ገባሁኝ
እነሱ ሌባ አሉኝ እንጂ መሆን አላመሆኑን እኔ በምን አውቃለሁ ትክክል አልነበርኩም ብዬ እራሴን ወቀስኩ..
በር ላይ ቆሜ ከራሴ ጋር ክርክር ውስጥ እያለሁ ልጁ ተመልሶ እየሮጣ መጣ...
ምርጥ የፍቅር ታሪኮችን
LIKE እና SHARE ማድረግ እንዳይረሱ አስተያየት ካላችሁ ላይ ቻናላችሁን ማስተዋወቅ የምትፈልጉ ላይ ይፃፉልን !!! በfacebook ላይ በ Instagram ላይም ጀምረናል
➪💟በፌስቡክ https://www.facebook.com/kezim_kezam
➪💟በኢስታግራም https://www.Instagram.com/kezim_kezam
➪💟በቴሌግራም https://t.me/kezim_kezam
Subscribers telegram channel , page and Instagram page