Dejen Ketema Communication Office

Dejen Ketema Communication Office Serving communication service to the public

በክረምት ወራት ሲያስተምራቸው የቆዬ ተማሪዎችን አስመረቀ ።**************************ደጀንከተማ ኮምዬኒኬሽን ነሀሴ 23/2018 ዓ/ም ላይፍ ላይን አካዳሚ በክረምት ወራት በተለ...
29/08/2026

በክረምት ወራት ሲያስተምራቸው የቆዬ ተማሪዎችን አስመረቀ ።
**************************
ደጀንከተማ ኮምዬኒኬሽን ነሀሴ 23/2018 ዓ/ም
ላይፍ ላይን አካዳሚ በክረምት ወራት በተለያዬ የትምህርት ዘርፎች ሲያስተምራቸው የቆዬ ተማሪዎችን በዛሬው እለት አስመርቋል ።
የፕሮግራሙን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደጀን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ፍቅረሰብ አለሙ ሲሆኑ የዚችን ሀገር ተረካቢ ህፃናትን የሚገባቸውን እንክብካቤና ፍቅር ከመስጠት ባሻገር በእውቀትና በስነ ምግባር ኮትኩቶ የማሳደግ ሀላፎነትም ያስፈልጋል ይህ ደግሞ እሚጀምረው ከህፃናት ነው አንድን ዛፍ መጣመም ሲጀምር ከቡቃያው ጀምረን ካላቃናነው እና ካላስተካከልነው ካደገ በኋላ ለማስተካከል ብንሞክር እንደማይቻል ሁሉ ህፃናትንም በዚህ እድሚያቸው ትክክለኛውን መንገድ እያሳየንና በስነ ምግባር እየኮተኮትን ግብረ ገብነትን እያሳየን ካላሳደግናቸው ካደጉ በኋላ ለማስተካከል ይከብደናል ከዚህ ረገድ ላይፍ ላይን አካዳሚ እያደረገ ያለው ትውልድን የመቅረፅ ሂደት የሚያስመሰግን በመሆኑ በዚሁ አጋጣሚ አክብሮቴን ለመግለጽ እወዳለሁ ያሉት ሀላፊው ይህን መልካም ተግባራችሁንም ወደ ፊት አጠናክራቸሁ እንደምትቀጥሉ አልጠራጠርም በማለት ተናግረዋል ።
ይህን ት/ቤት እዚህ ለማድረስ ብዙ ውጣ ውረዶች እንዳሳለፍና አሁንም ብዙ ችግሮች ቢኖሩም ትውልድን በማነጽ ረገድ ተግባሮችን ለማስቀጥል ወደ ኋላ እንደማይሉ የተናገሩት የት/ቤቱ መስራችና ር/መምህር አቶ ደሳለኝ ሙሉጌታ ሲሆኑ በክረምት ወራት ህፃናት ጊዜያቸው በከንቱ እንዳያሳልፍና ለቀጣይ መደበኛ ትምህርት ማጠናከሪያ እንዲሆናቸው በተጨማሪም የቋንቋ ንግግር ክህሎታቸውን ለማዳበር እና ከዛም በላይ የስነ ምግባርና የግብረ ገብ ትምህርቶች የሀይማኖት እኩልነትን ባሰፈነ መልኩ ሀይማኖታዊ ትምህርቶችን ልምድ ባላቸው መምህራን ሲሰጡ መቆየታቸውን ገልፀዋል ። አቶ ደሳለኝ አያይዘውም በ2019 ዓ/ም የትምህርት ዓመት በአዲስ ት/ቤት በአዲስ መልኩ ምዝገባ የጀመርን በመሆኑ ወላጆች አዲሱ ት/ቤታችን መብራት ሀይል ይሰራበት የነበረ ግቢ ውስጥ ስለሆነ ያለን ክፍት ቦታ አነስተኛ በመሆኑ ልጆቻችሁን እየመጣችሁ እንድታስመዘግቡ በማለት ጥሪያቸውን አስተላልፈው ተመራቂ ተማሪዎችንም የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል ።
በእለቱም በተመራቂ ተማሪዎች የተለያዬ የብሄር ብሄረሰብ ውዝዋዜዎች የአብነትና ቁርዓን ትምህርቶች እንዲሁም የእንግሊዘኛ ክህሎትን የሚያዳብሩ ንግግሮች ቀርበዋል።
በመጨረሻም ካርድና የተሻለ ተሳትፎ ለነበራቸው ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማትና ሰርተፍኬት በመስጠት ፕሮግራሙ ተጠናቋል ።

‎በደጀን ከተማ የከሴ አጨዳና የእንግጫ ነቀላ  ዓመታዊ ክብረ በዓል ተከበረ‎‎በደጀን ከተማ አስተዳደር የእንግጫ ነቀላና የከሴ አጨዳ ትውፊታዊ በዓል በተለያዬ ፕሮግራሞች በደማቅ ሁኔታ ተከበረ...
27/08/2026

‎በደጀን ከተማ የከሴ አጨዳና የእንግጫ ነቀላ ዓመታዊ ክብረ በዓል ተከበረ

‎በደጀን ከተማ አስተዳደር የእንግጫ ነቀላና የከሴ አጨዳ ትውፊታዊ በዓል በተለያዬ ፕሮግራሞች በደማቅ ሁኔታ ተከበረ፡፡
ደጀን ከተማ ኮሙዬኒኬሽን ነሀሴ 21/2018 ዓ/ም

‎በምስራቅ ጎጃም ዞን፣ በደጀን ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ስነ-ጥበብ፣ ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት አስተባባሪነት የከሴ አጨዳና የእንግጫ ነቀላ ዓመታዊ ክብረ በዓል በድምቀት ተከብሮ ውሏል፡፡ በበዓሉ የበዓል ቡድን ዓባላት፣የከተማ አመራሮች፣ ወጣቶች እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፈዋል፡፡

‎በክብረ በዓሉ የደጀን ከተማ ከንቲባን ወክለው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደጀን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅረሰብ አለሙ ሲሆኑ በመክፈቻ ንግግራቸው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በማስተላለፍ በዓሉ ታሪካዊ እሴትና ትውፊት የሚገልጽ ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፊ የመጣ መሆኑን በመልዕክታቸው አስተላልፈዋል።
የከሴ አጨዳና የእንግጫ ነቀላ ታሪካዊ ዳራ፣ ባህላዊ እሴትና ትውፊታዊ አመጣጥ የሚያስረዳ አጭር ሰነድ በደጀን ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ስነ-ጥበብ፣ ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ በአቶ ዳምጤ ብሬ ቀርቧል፡፡
‎ባህላችንን እንጠብቅ፤ ትውፊታችንን እናስተላልፍ፤ አንድነታችንን እናጠናክር!

በምስራቅ ጎጃም ዞን በደጀን ከተማ አስተዳደር ውጫዊ የወረራ ስጋትና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማትን እናረጋግጣለን በሚል መሪ ቃል ከባጃጅ አሽከርካሪዎች ጋር በመ...
27/08/2026

በምስራቅ ጎጃም ዞን በደጀን ከተማ አስተዳደር ውጫዊ የወረራ ስጋትና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማትን እናረጋግጣለን በሚል መሪ ቃል ከባጃጅ አሽከርካሪዎች ጋር በመወያየት ላይ ይገኛል ።
ደጀን ከተማ ኮሙዬኒኬሽን ነሀሴ 21/2018 ዓ/ም

በደጀን ከተማ አስተዳደር የእንግጫ ነቀላና ከሴ አጨዳ ትውፊታዊ በአል በተለያዬ ፕሮግራሞች በደማቅ ሁኔታ በመከበር ላይ ይገኛል ።ደጀን ከተማ ኮሙዬኒኬሽን ነሀሴ 21/2018 ዓ/ም
27/08/2026

በደጀን ከተማ አስተዳደር የእንግጫ ነቀላና ከሴ አጨዳ ትውፊታዊ በአል በተለያዬ ፕሮግራሞች በደማቅ ሁኔታ በመከበር ላይ ይገኛል ።
ደጀን ከተማ ኮሙዬኒኬሽን ነሀሴ 21/2018 ዓ/ም

‎የሃገርና የክልል ሰላም  ከሚፈታተኑ ውጫዊና ውስጣዊ ስጋቶች በመጠበቅ ዘላቂ ልማትን ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለጸ።‎ደጀን ከተማ ፦ነሐሴ18/2018 ዓ.ም(ደጀን ከተማ ኮሙኒኬሽን) "ውጫዊ የወ...
25/08/2026

‎የሃገርና የክልል ሰላም ከሚፈታተኑ ውጫዊና ውስጣዊ ስጋቶች በመጠበቅ ዘላቂ ልማትን ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለጸ።

‎ደጀን ከተማ ፦ነሐሴ18/2018 ዓ.ም(ደጀን ከተማ ኮሙኒኬሽን) "ውጫዊ የወረራ ስጋት እና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማት እናረጋግጣለን!” በሚል መሪ ሀሳብ ከደጀን ከተማ ጠቅላላ የመንግስት ሠራተኞች ጋር የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

‎በመድረኩ የሃገርና የክልል ሰላምን ከሚፈታተኑ ውጫዊና ውስጣዊ ስጋቶች አንፃር የሰላምን ዋጋ ማስጠበቅ፣ የሕዝብን አንድነት ማጠናከር፣ ሕገ-ወጥ ተግባራትን መከላከልና ሰላምን መሠረት ያደረገ ዘላቂ ልማትን ማረጋገጥ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል።

‎በውይይቱ የከተማዋ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸዉ ሸጌ ሰላም ለከተማዋ የልማትና የመልካም አስተዳደር መሠረት መሆኑን ባቀረቡት ሰነድ ጠቁመው፣ የተረጋጋ ሰላም ሳይኖር የልማትን ፍላጎት ማሳካት እንደማይቻል ገልፀዋል። ስለሆነም ሰላምን ማስጠበቅ፣ ሕግን ማስከበር፣ የሕዝብን አንድነት ማጠናከርና የልማት ሥራዎችን በተጠያቂነት ማስፈጸም ወሳኝ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል።

‎በመሆኑም የከተማዋ የመንግስት ሠራተኞ የሕዝብን አገልግሎት ከመስጠት ባለፈ የሃገርና የክልል ሰላም ከሚፈታተኑ ውጫዊና ውስጣዊ ስጋቶች ለመጠበቅ በሰላም ግንባታ፣ በሕግ ማስከበርና በሕዝብ አንድነት ጉዳዮች ላይ የራሱን ሚና በመወጣት ዘላቂ ልማትን ማረጋገጥ እንዳለበት አቶ ጌታቸዉ አብራርተዋል። በዉይይቱ ከመንግስት ሰራተኞች ሀሳብና አስተያየት የተሰጡ ሲሆን ለተሰጡ ሃሳቦች የደጀንከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ጤናዉ ደረስ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ሀሳቦች ሀሳብና አስተያት በመስጠት ሁሉም የመንግስት ሰራተኞች ለሰላም በሀሳብ ፣በጉልበትእንዲሁም በገንዘብ ለሚደረጉ ድጋፎች የሰነለቦና ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ በመጠቆም መድረኩ ተጠናቋል፡፡

የደጀን ከተማ አስተዳደር በደጀን ከተማ ከሚገኙ የንግዱ ማህበረሰብ ጋር የ2018 ቁርጥ ገብርና በሀገራዊ ጉዳዬች ዙሪያ ውይይት በማካሄድ ላይ ይገኛል ።ደጀን ከተማ ኮምዬኒኬሽን ነሀሴ 18/20...
24/08/2026

የደጀን ከተማ አስተዳደር በደጀን ከተማ ከሚገኙ የንግዱ ማህበረሰብ ጋር የ2018 ቁርጥ ገብርና በሀገራዊ ጉዳዬች ዙሪያ ውይይት በማካሄድ ላይ ይገኛል ።
ደጀን ከተማ ኮምዬኒኬሽን ነሀሴ 18/2018 ዓ/ም

ከበጎ ፈቃድ ተሳትፎ ባሻገር፤ የወጣቶች ልምድና ተሞክሮ ልውውጥ‎‎በደጀን ከተማ አስተዳደር ከደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የመጡ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በተለያዩ የበጎ ፈቃድ ሥራዎች ላይ ተሳት...
19/08/2026

ከበጎ ፈቃድ ተሳትፎ ባሻገር፤ የወጣቶች ልምድና ተሞክሮ ልውውጥ

‎በደጀን ከተማ አስተዳደር ከደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የመጡ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በተለያዩ የበጎ ፈቃድ ሥራዎች ላይ ተሳትፎ አደረጉ።

‎በምስራቅ ጎጃም ዞን ደጀን ከተማ አስተዳደር፣ ከደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የመጡ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ከደጀን ከተማ ወጣቶች ጋር በተለያዩ የበጎ ፈቃድ ተግባራት ተሳትፈዋል።

‎ወጣቶቹ በአረንጓዴ አሻራ እና በከተማ ጽዳት ሥራ በጋራ በመሳተፍ ለከተማዋ ውበትና አረንጓዴነት የሚያበረክት በጎ ተግባር አከናውነዋል።

‎የወጣቶቹ የጋራ ተሳትፎ የበጎ ፈቃድ ሥራን ከማጠናከር ባለፈ፣ በወጣቶች መካከል ልምድና ተሞክሮ ለመለዋወጥ፣ የጋራ ትስስርን ለማጠናከር እና የበጎ ፈቃድ ባህልን ለማስፋት የሚያግዝ መድረክ ፈጥሯል።

‎ወጣቶች በጋራ ሲሰሩ፣ ለማህበረሰብ የሚጠቅም ትልቅ ለውጥ ይመጣል!
ከደጀን ከተማ pp ማህበራዊ ገጽ የተወሰደ

‎በምስራቅ ጎጃም ዞን በደጀን ከተማ አስተዳደር “በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ሐሳብ እየተከናወነ የሚገኘው የዜጎች የክረምት በጎ አድራጎት ሥራ በቤት ግንባታና ጥገና ዘርፍ ተጠናክሮ ...
19/08/2026

‎በምስራቅ ጎጃም ዞን በደጀን ከተማ አስተዳደር “በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ሐሳብ እየተከናወነ የሚገኘው የዜጎች የክረምት በጎ አድራጎት ሥራ በቤት ግንባታና ጥገና ዘርፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ከደጀን ከተማ pp ማህበራዊ ገጽ የተወሰደ

የደጀን ከተማ አስተዳደር ከደብረ ማርቆስ ከተማ ለመጡ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች አቀባበል አደረገ ።******************************ደጀን ከተማ ኮሙዬኒኬሽን ነሀሴ 12/2018 ዓ/ም...
18/08/2026

የደጀን ከተማ አስተዳደር ከደብረ ማርቆስ ከተማ ለመጡ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች አቀባበል አደረገ ።
******************************
ደጀን ከተማ ኮሙዬኒኬሽን ነሀሴ 12/2018 ዓ/ም
የደጀን ከተማ አስተዳደር ከደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ወሰን ተሻጋሪ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶችን እንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል አደረገ ።
በኘሮግራሙም የደጀን ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ መንግስቴ አያሌው ፣ ወ/ሮ ራዲ ኡመር የደጀን ከተማ አስተዳደር ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ሀላፊን ጨምሮ የከተማና የቀበሌ አመራሮች ፣የደጀን ከተማ አስተዳደር በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች እና የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል ።
ይህን መልካም ተግባር ሰንቃችሁ ለሌሎች አርአያ ልትሆኑና የከተማችሁን የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ልምድ ልታካፍሉን ወደ ከተማችን የመጣችሁ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች እንኳን ወደ ከተማችን በደህና መጣችሁ በማለት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን ያስተላለፍት የደጀን ከተማ አስተዳደር ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ራዲ ኡመር ናቸው።
የደጀን ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ቅ/ጽ/ቤት ፓለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ መንግስቴ አያሌው እንደተናገሩት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ህሊናን ከማስደሰቱም ባሻገር የሁሉም እምነት የሚጠይቀው መልካም ተግባር በመሆኑ በዚህ ተግባር በመሠማራታችሁ ልትኮሩ ይገባል ። ያሉት አቶ መንግስቴ በከተማችን በሚኖራችሁ ቆይታ የተሻለ የሚያስመሰግንና አርአያ የሆነ ስራ እንደምትሰሩ ተስፍ እየጣልኩባችሁ ወደ ውቧና የደረቅ ወደብ ወደ ሆነችው ደጀን ከተማ እንኳን በደህና መጣችሁ በማለት ለወጣቶቹ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸው አስተላልፈዋል ።
ወጣቶችም በከተማዋ በሚኖራቸው ቆይታ በተለያዬ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተግባራት ላይ ተሠማርተው የተለያዬ ስራዎችን እንደሚሰሩ ተጠቁሟል ።

ከተረጂነት ለመላቀቅ ያለንን ፀጋ በመለየት መስራት እንደሚገባ ተገለፀ ።******************************ደጀን ከተማ ኮምዬኒኬሽን ነሀሴ 04/2018 ዓ/ም በም/ጎ/ዞን በደጀን ...
10/08/2026

ከተረጂነት ለመላቀቅ ያለንን ፀጋ በመለየት መስራት እንደሚገባ ተገለፀ ።
******************************
ደጀን ከተማ ኮምዬኒኬሽን ነሀሴ 04/2018 ዓ/ም
በም/ጎ/ዞን በደጀን ከተማ አስተዳደር "ከተረጅነት ወደ ምርታማነት " በሚል መርህ በከተማዋ በተለያዬ ቀበሌዎች ከዚህ በፊት ለእርሻ ስራ ይውሉ ያልነበሩ መሬቶችን በመለየት ወደ እርሻ ስራ በማስገባት እና በዘር በመሸፈን ምርትና ምርታማነትን በመጨመር በምግብ እራስን በመቻል ከተረጅነት ለመላቀቅ ተግባራት በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ በመከናወን ላይ ይገኛሉ።
በመሆኑም በዛሬው እለት በተለያዬ በተመረጡ ለሰብል ምርት በተዘጋጅ ቦታዎች ዘር የመዝራትና መሠል ተግባራት ሲከናወኑ ውለዋል ።

Address

Dejen Town
Dejen

Telephone

+251587760079

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dejen Ketema Communication Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share