Dembecha Zuria Woreda Revenue Office/ደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት.

  • Home
  • Ethiopia
  • Dembech'a
  • Dembecha Zuria Woreda Revenue Office/ደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት.

Dembecha Zuria Woreda Revenue Office/ደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት. Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dembecha Zuria Woreda Revenue Office/ደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት., Government Organization, dembecha, Dembech'a.

የእርሻ ግብር አሠባሠብ በደምበጫ ዙሪያ                           የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት የእርሻ ግብር እየሠበሠበ ነው። የግብር አሠባሠብ ሂደቱ የሚከናወነው ለሠ...
28/04/2026

የእርሻ ግብር አሠባሠብ በደምበጫ ዙሪያ የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት የእርሻ ግብር እየሠበሠበ ነው። የግብር አሠባሠብ ሂደቱ የሚከናወነው ለሠራተኞች ስምሪት በመስጠት ሲሆን ሠራተኞች በተሠጣቸው ስምሪት መሠረት በትብብር እየሠሩ ይገኛሉ። በግብር አሠባሠብ ሂደቱ በየቀኑ ለሚመጡ አርሶ አደሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ እየተሠራ ሲሆን የ2018 በጀት ዓመት የእርሻ ግብር አሰባሠብ ካለፉት አመታት በተሻለ የካዳስተር መረጃውን በመጠቀም ገቢን አሟጦ ለመሠብሠብ በቅንጅት እየተሠራ ነው።

28/04/2026

የእርሻ ግብር አሠባሠብ በደምበጫ ዙሪያ የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት የእርሻ ግብር እየሠበሠበ ነው። የግብር አሠባሠብ ሂደቱ የሚከናወነው ለሠራተኞች ስምሪት በመስጠት ሲሆን ሠራተኞች በተሠጣቸው ስምሪት መሠረት በትብብር እየሠሩ ይገኛሉ። በግብር አሠባሠብ ሂደቱ በየቀኑ ለሚመጡ አርሶ አደሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ እየተሠራ ሲሆን የ2018 በጀት ዓመት የእርሻ ግብር አሰባሠብ ካለፉት አመታት በተሻለ የካዳስተር መረጃውን በመጠቀም ገቢን አሟጦ ለመሠብሠብ በቅንጅት እየተሠራ ነው።

የእርሻ ግብር አሠባሠብ በደምበጫ ዙሪያ                           የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት የእርሻ ግብር እየሠበሠበ ነው። የግብር አሠባብ ሂደቱ የሚከናወነው ለሠራ...
28/04/2026

የእርሻ ግብር አሠባሠብ በደምበጫ ዙሪያ የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት የእርሻ ግብር እየሠበሠበ ነው። የግብር አሠባብ ሂደቱ የሚከናወነው ለሠራተኞች ስምሪት በመስጠት ሲሆን ሠራተኞች በተሠጣቸው ስምሪት መሠረት በትብብር እየሠሩ ይገኛሉ። በግብር አሠባሠብ ሂደቱ በየቀኑ ለሚመጡ አርሶ አደሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ እየተሠራ ሲሆን የ2018 በጀት ዓመት የእርሻ ግብር አሰባሠብ ካለፉት አመታት በተሻለ የካዳስተር መረጃውን በመጠቀም ገቢን አሟጦ ለመሠብሠብ በቅንጅት እየተሠራ ነው።

https://www.facebook.com/100068667050208/posts/1268893655409524/?app=fbl
18/04/2026

https://www.facebook.com/100068667050208/posts/1268893655409524/?app=fbl

‎ከ111 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ገለፀ።

‎በበጀት አመቱ ባለፉት 9ወራት 111 ሚሊዮን 513 ሺህ 254 ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤ ሃላፊ አቶ ባለው ስንሻው ተናግረዋል።

‎በ2018 በጀት አመት 211 ሚሊየን 465 ሺህ 4 መቶ 63 ብር ገቢ ለመሰብስብ ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን የገለፁት ሃላፊው እስካሁን 111 ሚሊዮን 513 ሺህ 254 ብር መሰብሰባቸውን ተናግረዋል። ይህም የዕቅዳቸውን 52 ከመቶ በላይ ማሳካት መሆኑን ተናግረዋል።

‎ሀላፊው አክለውም ገቢ አሰባሰቡ ከአምናዉ ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጸተር ከፍተኛ መሻሻል አሳይቷል ብለዋል።

‎አቶ ባለው አክለውም ግብር ከፋዩ ግብሩን በወቅቱ በመክፈል የተጀመሩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማቶች እንዲቀጥሉ የድርሻውን መወጣት እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡

‎በመጨረሻም ሃላፊው የሰሩበትን ግብር በወቅቱ የከፈሉ ነጋዴዎችን አመስግነው በወቅቱ ግብር ያልከፈሉ ነጋዴዎች ላልተፈለገ ቅጣት ከመዳረጋቸው በፊት የሰሩበትን ግብር እንዲከፍሉ አሳስበዋል።

በአዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ ለመንግስት ሠራተኞች ስልጠና ተሠጠ                                የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ለወረዳ መንግስት ሠራተኞች  በአዲሱ የገቢ...
14/03/2026

በአዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ ለመንግስት ሠራተኞች ስልጠና ተሠጠ የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ለወረዳ መንግስት ሠራተኞች በአዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ 1395/2017 ዓ.ም ላይ ስልጠና ተሠጠ። በስልጠናውም በአዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ የነጋዴ ደረጃዎች ፣የመክፈያ ጊዜያት ፣VAT የሚመለከታቸው እነማን ናቸው፣ ደረሰኝ የሚጠቀሙ ነጋዴዎች የትኞቹ ናቸው እና ከመንግስት ሠራተኞች ምን ይጠበቃል በሚሉ ርዕሰ ጉዳዪች ላይ ስልጠና ተሠቷል።

05/02/2026

2053665 ብር ተሠበሠበ በደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት በቀን 28/05/2018 ዓ.ም 2053665 ብር ተሠበሠበ ። ይህንን ገቢ ለመሠብሠብ ሠፊ ጥረት የተደረገ ሲሆን እስከዚህ ወር ድረስ 67 610 085 ብር መሠብሠብ ተችሏል። ይህን ገቢ ለመሠብሠብ በተደረገው ጥረት ገቢውን ለመሠብሠብ በተሠራ ስራ እና ለነጋዴው ግንዛቤ በመፍጠር በኩል ርብርብ ተደርጓል በዚህ ተግባር የተሳተፍ ባለሙያዎችን እና አጋር አካለትን እንዲሁም በወቅቱ የከፈሉ ግብር ከፋዬችን እያመሰገንን ግብር ያልከፈላችሁ ግብር ከፋዬች ግብራችሁን መጣችሁ እንድትከፍሉ ያሳስባል። ጽ/ቤቱ

10/01/2026


ጥር 1 ቀን 2018 ዓ/ም
ፍ/ሠላም፣
በዞናችን የሚገኙ ነጋዴዎች የንግድ ፈቃድ እድሳት ያለ ቅጣት የሚታደስበት ጊዜ ከሀምሌ 1 እስከ ታህሳስ 30 ብቻ መሆኑ ይታወቃል። ሆኖም ግን በነጋዴው ቸልተኝነት እና ከሲስተም ችግር ጋር ተያይዞ ነጋዴው የንግድ ፈቃዱን ሳያድስ በመቅረቱ ለቅጣት እንዳይዳረግ ታሳቢ በማድረግ ለ15 ቀን ብቻ የተራዘመ መሆኑን የምዕ/ጎጃም ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አስታውቋል።
የምዕ/ጎጃም ዞን ንግድና ገበየ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አለልኝ አሠፋ በዞናችን የምትገኙ ነጋዴዎች ፈቃድ አውጥታችሁ በመዘናጋት ያላሳደሳችሁ ነጋዴዎች በክልሉ አማካኝነት የተራዘመውን ጊዜ በመጠቀም ከሰኞ እስከ አርብ ዘወትር በስራ ሰአት እና ቅዳሜ እስከ ቀኑ 6:00 ሰዓት ድረስ በወረዳ ደረጃ ወደ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ፈጥነው በመሄድ በማደስ ካላስፈላጊ ወጭና ቅጣት ራሳችሁን እንድትጠብቁ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አክለዉም በዞናችን ውስጥ የምትገኙ ነጋዴዎች የንግድ ፈቃድ ማደሻ ጊዜ ካሳለፋችሁ የንግድ ምዝገባ አዋጅ 980/2008 መሰረት በህግ ያስቀጣል፣ የንግድ ፍቃድ ያሰርዛል በማለት ጥብቅ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የቅጣቱን የገንዘብ መጠን እንደቆይታው ደረጃ በመጠን የተቀመጠውን የህግ ድንጋጌ ዝርዝር አመላክተዋል።
#1ኛ, ከጥር 1 እስከ 30 = 2,500 ብር
#2ኛ, ከየካቲት 1 እስከ 30 = 4,000 ብር
#3ኛ, ከመጋቢት 1 እስከ 30 = 5,500 ብር
#4ኛ, ከሚያዚያ 1 እስከ 30 = 7,000 ብር
#5ኛ, ከግንቦት 1 እስከ 30 = 8,500 ብር
#6ኛ, ከሰኔ 1 እስከ 30 = 10, 000 ብር እያለ ፈቃድ እስከ መሰረዝ ድረስ ስለሚያስቀጣ ፈቃደዎን በተሰጠው ጊዜ ብቻ በመጠቀም ፈጥነው ማሳደስ እንዳለባቸው የምዕ/ጎጃም ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አለልኝ አሠፋ በድጋሜ ጥብቅ ማሳሠቢያ ሠጥተዋል ።

05/01/2026

228825 ብር ተሠበሠበ የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት በቀን 27/04/2018 ዓ.ም 228825 ብር መሠብሠቡን ገለጸ። እስከ ታህሳስ 27/2018 ዓ.ም ድረስ 52 045 758 ብር የተሠበሠበ ሲሆን ይህን ገቢ ለመሠብሠብ ስምሪት በመስራት የስልክ ቅስቀሳ እና በመስክ የመቀስቀስ ስራዎች ተሠርተዋል።

16/12/2025

50097396 ብር ተሠበሠበ የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት እስከ ህዳር 30/2018 ዓ.ም ድረስ 50097396 ብር የሠበሠበ ሲሆን የእቅዱን 23.69% መፈጸም መቻሉ ተገልጿል:: ገቢው የተሠበሠበው ከልዩ ልዩ 46768788 ከንግድ 3328608 ብር የተሠበሠበ ነው። ይህን ገቢ ለመሠብሠብ የግል ድርጅቶችን ነገዴዎችን በስልክ የመቀስቀስ እንዲሁም ኬላ በመዘርጋት ነጋዴዎችን ግብር እንዲከፍሉ የመቀስቀስ ስራ እና እንዲ ከፍሉ የማድረግ ተሠርቷል::

Address

Dembecha
Dembech'a

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dembecha Zuria Woreda Revenue Office/ደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት. posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share