Borena Sayint worehimeno national park

Borena Sayint worehimeno national park BSWNP is located in ANRS, South Wollo Administrative Zone, which is far from Dessie town by 184kms and from Bahirdar 280kms.

03/08/2026

አዲስ የተለቀቀው የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ሬንጀሮች መዝሙር

31/07/2026

ጋራው፣ ሸንተረሩ፣ ብርዱና ቁሩ ሳይበግራችሁ ለዱር አንስሳት ዘብ የቆማችሁ ሬንጀሮቻችን እንኳን ለአለም የሬንጀሮች ቀን አደረሳችሁ።

31/07/2026
31/07/2026

On World Ranger Day, we pay tribute to the guardians of nature – those who stand on the frontlines to protect wildlife, forests, and natural treasures!

Because of you, countless species continue to thrive.

Happy World Ranger Day!

31/07/2026

ሬንጀሮች፡- ተለዋዋጭ ለሆነችው ፕላኔት ጠባቂዎች (RANGERS: GUARDIANS OF A CHANGING PLANET)

ውድ የኢትዮጵያ ሬንጀሮች

እንኳን ለዓለም አቀፍ የሬንጀሮች ቀን በሰላም አደረሳችሁ!

የዘንድሮው የዓለም አቀፍ የሬንጀሮች ቀን ሬንጀሮች፡- ተለዋዋጭ ለሆነችው ፕላኔት ጠባቂዎች (RANGERS: GUARDIANS OF A CHANGING PLANET) በሚል መሪ ቃል ይከበራል።

ይህ መሪ ቃል የተመረጠው ዓለማችን በአየር ንብረት ለውጥ፣ በአካባቢ ብክለት፣ በብዝሃ ሕይወት መመናመንና መጥፋት፣ እንዲሁም በተለያዩ አዳዲስ የጤና ስጋቶች እየተፈተነች በመሆኗ ነው። እነዚህ ተግዳሮቶች የምድራችንን ሥነ-ምህዳራዊ ሚዛን እና የሰው ልጅን የወደፊት ሕልውና በእጅጉ እየፈተኑ ይገኛሉ።

በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሬንጀሮች የተፈጥሮ ሀብትን እና የዱር ሕይወትን በመጠበቅ ለፕላኔታችን ሕልውና የማይተካ አስተዋፅኦ ያበረክታሉ።

ለዚህ ክቡር ተልዕኮ የሚያበረክቱት አስተዋፅኦ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና እያገኘ በመምጣቱ ይህ ዕለት በየዓመቱ በልዩ ክብር ይከበራል።
የኢትዮጵያ ሬንጀሮችም የሀገራችንን የተፈጥሮ ሀብትና የዱር ሕይወት በመጠበቅ ንፁህ ውሃ፣ ለም አፈር፣ የተረጋጋ ሥነ-ምህዳር፣ የዱር እንስሳትና ዕፅዋት ለአሁኑና ለሚቀጥለው ትውልድ እንዲጠበቁ በፅናት እየሰሩ ይገኛሉ።

በተለይም በጥበቃ ቦታዎች ውጤታማ ጥበቃ እንዲኖር በየዕለቱ ከባድ ፈተናዎችን በመቋቋም፣ ሕይወታችሁን ለአደጋ በማጋለጥ ለምትከፍሉት መስዋዕትነት ከፍተኛ ክብርና እውቅና ይገባዋል።

በመሆኑም የምታበረክቱት አስተዋፅኦ ለሰው ልጅ ሕልውናና ለዘላቂ ልማት መሠረታዊ ነው። እናንተ የሀገራችንን የተፈጥሮ ሀብት ለትውልድ የምታስተላልፉ እውነተኛ ጀግኖች ናችሁ።

የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ሁልጊዜም ለምታበረክቱት የከበረ አገልግሎት ከልብ ያመሰግናችኋል፤ ያከብራችኋልም።

ባለስልጣኑ የሬንጀሮችን የሙያ አቅም ለማጠናከር፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ የጥበቃ ሥርዓት ለማስፋፋት፣ የሬንጀሮችን ክህሎትና ዕውቀት ለማሳደግ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሬንጀሮች ማህበር ይበልጥ እንዲጠናከር በቀጣይነት ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል።

በዚህ አጋጣሚ በተፈጥሮ ጥበቃ ተልዕኳችሁ በፅናት እንድትቀጥሉ በመግለጽ፣ ለሀገራችንና ለፕላኔታችን የምታደርጉትን የከበረ አገልግሎት በድጋሚ እናመሰግናለን።

ዘላለማዊ ክብር ለዱር ሕይወት ሕልውና ሲሉ ውድ ሕይወታቸውን ለሠዉ ፤ አካላቸውን ለገበሩ ሬንጀሮች እና ለዘርፉ ባለሙያዎች።

የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን

አቶ ኩመራ ዋቅጅራ
የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር

21/07/2026
09/07/2026
18/04/2026

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት፤

‎ክቡራን በየደረጃው የምትገኙ የአካባቢ፣ የደንና የብዝሃ ህይወት ጠበቃ ለሆናችሁ የባለስልጣኑ የስራ ባልደረቦቻችንና በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት የምትገኙ አጋሮቻችን እንዲሁም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ሁሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሳዔው በሰላም አደረሳችሁ።

‎በዓሉ የሠላምና የጤና በዓል ይሁን እያልን፤ መጪው ጊዜ ሁሉም ማህበረሰብ የአካባቢና ደን ጥበቃ ቤተሰብ በመሆን የአካባቢ፣ የደን፣ የዱር እንስሳትና የብዝሃ ህይወት ሀብቶች ልማትና ጥበቃ ስራዎችን በተሻለ ውጤት ለትውልድ ለማስረከብ የምንፀናበትና የምንተጋበት በዓል እንዲሆን እንመኛለን።

‎አካባቢን መጠበቅ የአሁኑንና የቀጣዩን ትውልድ ሁለንተናዊ ልማትና ህልውናን ማረጋገጥ ብሎም የነገ ትውልድን አደራ መወጣት ነው።

‎ መልካም የትንሣኤ በዓል!!

‎የአማራ ክልል የአካባቢ ጥበቃ ባለሰልጣን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች

Address

Dembi Dolo
49

Telephone

+251332201023

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Borena Sayint worehimeno national park posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share