ደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ

ደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ, Government Organization, Dessi.

በቃሉ ወረዳ የገርባ ጤና ጣቢያ የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል፣ መሰረተ ልማቶችን ለማሟላት እና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የሰራቸውን አበራች ስራዎች የሚያመላክት የመስክ ምልከታ ተካሄደ። ...
24/08/2026

በቃሉ ወረዳ የገርባ ጤና ጣቢያ የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል፣ መሰረተ ልማቶችን ለማሟላት እና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የሰራቸውን አበራች ስራዎች የሚያመላክት የመስክ ምልከታ ተካሄደ።

ነሀሴ 18/2018 ዓ/ም (ቃሉ ኮሙኒኬሽን)

በዚሁ መድረክ የደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ ም/ሀላፊ አቶ አብዱ መሀመድ፣ የቃሉ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሙህዲን አህመድ፣ የወረዳው ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤና የጤና ጣቢያው ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አረጋ ታደሰ፣ የጤና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ዳንኤል ጋሻው፣ የጤና አመራሮችና ባለሙያዎች፣ የቀበሌ አሴተዳዳሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

​የገርባ ጤና ጣቢያ ሀላፊ አቶ ጀማል አህመድ የጤና ጣቢያውን ንጽህና፣ የጎርፍና የመንገድ ችግሮች በማህበረሰብ ተሳትፎ መፍትሔ ማግኘታቸውን፣ ተጨማሪ ክፍሎችን በመገንባት፣ የCBC ማሽን ስራ ላይ በማዋል እና ከትውልደ-ኢትዮጵያዊያን ባለሀብቶች እስከ 250,000 ብር የሚደርስ የገንዘብና የጄኔሬተር ድጋፍ ቃል ማስገባት መቻሉን ተናግረዋል። በተጨማሪም የ022 እና 023 ጤና ኬላዎች መታደሳቸውን፣ የደንበኞች ምክር ቤት መቋቋሙንና ለተማሪዎች ነፃ የህክምና እና የንጽህና ቁሳቁስ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ጨምረው በገርባ ጤና ጣቢያና በ023 ጀርጀሮ ቀበሌ ስራ የጀመረውን የኮንምፕረንሲቭ ጤና ኬላ አገልግሎትና የተጀመረውን ግንባታ አስመልክተው ገለፃ አዶርገዋል።

በመድረኩም ​የወረዳው ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤና የጤና ጣቢያው የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አረጋ ታደሰ የጤና ጣቢያው ባለሙያዎች በተለየ ተነሳሽነት በመስራታቸው ተቋሙን ማራኪ ገፅታን በማላበስ ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት መቻሉን እና የእናቶችና ህፃናት ክፍል ከፍተኛ መሻሻል ማሳየቱን ገልጸዋል። በጤና ተቋሙጰግቢውን በማስፋፋትና የቀዶ ሕክምና ክፍል (OR) ከተገነባ የሕክምና ቁሳቁሶችን ሙሉ በሙሉ ለማሟላት ቃል የገባ ባለሀብት በመኖሩ የህብረተሰቡ ርብርብ እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል።

​የቃሉ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙህዲን አህመድ እንደገለፁት ከአንድ ዓመት በፊት የነበረውን የቅሬታ ምንጭ በመቀየር፣ በተደረገ ጤናማ ፉክክር የጤና ጣቢያው የውስጥና የውጭ ገጽታ፣ ጽዳትና ማራኪነት በከፍተኛ ደረጃ መሻሻሉን ተናግረዋል። በሆስፒታል ደረጃ የሚገኙ መሳሪያዎች እንደ CBC እና አልትራሳውንድ በማህበረሰብና በድጋፍ የተሟሉ ሲሆን፣ የመድኃኒት አቅርቦት 99% ማድረስ ተችሏል። ከ56 የላቦራቶሪ መመርመሪያ ዓይነቶች 48ቱ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ ብለዋል።
​የጤና ጣቢያው ዋናው ፈተና የቦታ ማስፋፊያ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ሙህዲን፣ ግቢውን የማስፋት ስራ ከተሰራ ለግንባታው ወረዳው በጀት በመመደብ ግንባታ ማካሄድ እንደሚችልና ግብአቶችንም ለማሟላት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል። ለተሰራው ስኬታማ ስራ ሚና ለነበራቸው አካላት ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

​የደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ ም/ሀላፊ አቶ አብዱ መሃመድ በበኩላቸው ​ቃሉ ወረዳ በዞኑ ካሉ ወረዳዎች ጋር ተወዳድሮ በክልሉ ጤና ቢሮ አንደኛ በመውጣት ያስመዘገበው ውጤት የሚደነቅ ሲሆን፣ የጤና ተቋማትን ቀረብ ብሎ በመምራትና በጤናማ ውድድር የተገኘው ተሞክሮ ወደ ሙሉ ዞኑ ሊሰፋ እንደሚገባ ገልጸዋል።

በተከለሰው የጤና ኤክስቴንሽን ፖሊሲ መሰረት ባለፈው ዓመት 34 አጠቃላይ ጤና ኬላዎች ደረጃቸው የተሻሻለ ሲሆን፣ በ2019 ዓ.ም ደግሞ 40 አዳዲስ አጠቃላይ ጤና ኬላዎችን በ20 ወረዳዎች ለማስፋፋት መታቀዱን ጠቁመዋል። ​የላቦራቶሪ፣ የክትባትና የወሊድ ክፍሎች መዘመናቸውንና የመድኃኒት አቅርቦት እስከ 100% መሸፈኑን አበክረው የገለፁት አቶ አብዱ፤ የዞኑ ጤና መምሪያና የክልሉ ጤና ቢሮ በግብአት፣ በስልጠናና በቴክኖሎጂ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል። አሁን ያለው የገርባ ጤና ጣቢያ ቦታ ጠባብ በመሆኑም ህብረተሰቡና አመራሩ ተባብረው ግቢውን በአስቸኳይ እንዲያስፋፉ አደራ ብለዋል።

በመጨረሻም ለውጤቱ መመዝገብ ወሳኝ ሚና ለነበራቸው የተለያዩ የጤና ባለድርሻ አካላትና ተቋማት የእውቅናና ምስጋና መርሃግብር ተካሂዷል።

ምቹ፣ ፅዱና ማራኪ የጤና ተቋም ለላቀ የአገልግሎት ጥራት!በደቡብ ወሎ ዞን ሀገራዊውን "ፅዱ ኢትዮጵያ" ኢኒሼቲቭ መሠረት በማድረግ ምቹ፣ ፅዱና ማራኪ የጤና ተቋማትን የመፍጠርና አገልግሎታቸውን...
24/08/2026

ምቹ፣ ፅዱና ማራኪ የጤና ተቋም ለላቀ የአገልግሎት ጥራት!

በደቡብ ወሎ ዞን ሀገራዊውን "ፅዱ ኢትዮጵያ" ኢኒሼቲቭ መሠረት በማድረግ ምቹ፣ ፅዱና ማራኪ የጤና ተቋማትን የመፍጠርና አገልግሎታቸውን የማሻሻል እንቅስቃሴ በከፍተኛ ትኩረት ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የዚህ በጎ እቅድ ማሳያ የሆነው በቃሉ ወረዳ የሚገኘው ገርባ ጤና ጣቢያ፤ ግቢውንና የህክምና መስጫ ክፍሎቹን ምቹ፣ ፅዱና ማራኪ በማድረግ ለአገልግሎት ፈላጊዎች የሚሰጠውን የእንክብካቤ ጥራት አዲስ ደረጃ ላይ አድርሶታል:: የጤና ጣቢያው አሁናዊ አየር በአይን የሚስብና ለህክምና የመጡ ወገኖችን መንፈስ የሚያድስ ገጽታ ተላብሷል።( ከደቡብ ወሎ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን )
ነሀሴ 18/2018ዓ.ም

የተንታ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም የስራ አፈፃፀም እና የ2019 ዓ.ም የፊዚካል ስራዎች የእቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄደ።******አጅባር፣ ነሃሴ 17/2018(ተንታ ኮሙኒኬሽን) የተን...
23/08/2026

የተንታ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም የስራ አፈፃፀም እና የ2019 ዓ.ም የፊዚካል ስራዎች የእቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄደ።
******
አጅባር፣ ነሃሴ 17/2018(ተንታ ኮሙኒኬሽን)

የተንታ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም የስራ አፈፃፀም እና የ2019 ዓ.ም የፊዚካል ስራዎች የእቅድ ትውውቅ መድረክ ያካሄደ ሲሆን የተንታ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሠይድ መኮዬ የተቋሙን የዕቅድ አፈፃፀፀምና በቀጣይ የትኩረት ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የመነሻ ፅሁፍ አቅርበዋል።

በውይይቱ ወቅት የጤና ጣቢያ ኃላፊዎች ሀሳባቸውን እንደገለፁት የጤና ተቋማት ለህሙማን ምቹ ፣ሳቢና ማራኪ እንድሆኑ በትኩረት መስራት ይገባል ያሉ ሲሆን ጤና ጣቢያዎች የተሻለ ህክምና እንዲሠጡ የተሻለ የበጀት ድልድልና የሠው ሀይል ማሟላት ላይ በትኩረት መሠራት አለበት ብለዋል።

አቶ አበበ አለባቸው የተንታ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ በዕለቱ እንደተናገሩት የጤና ተቋሙ እየሠራቸው ያሉ ስራዎች የሚበረታቱ ሲሆን በቀጣይ ማህበረሠብ አቀፍ የጤና መድህን ተግባር ላይ በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።

የተንታ ወረዳ ግብርና ፅ/ቤት ኃላፊና የተንታ ወረዳ ም/አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ አለባቸው በበኩላቸው ጤና ተቋሙን በቁርጠኝነት በመደገፍ የእናቶችና ህፃናት ብሎም ማህበረሠቡ የተሻለ የጤና አገልግሎት እንዲያገኝ ይደረጋል ብለዋል።

በዕለቱ በዓመቱ የተሻለ ለፈፀሙ ጤና ጣቢያዎች እንድሁም ለባለ ድርሻ አካላት የዕውቅና እና የምስጋና መርሃ ግብር ተከናውኗል።

በደቡብ ወሎ ዞን ለአጠቃላይ የጤና ስርዓቱ ዘመናዊነትና ጥራት ከ6.5 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ድጋፍ ተደረገደሴ፣ ነሐሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም (ደቡብ ወሎ ኮሙዩኒኬሽን) በአሜሪካ መን...
17/08/2026

በደቡብ ወሎ ዞን ለአጠቃላይ የጤና ስርዓቱ ዘመናዊነትና ጥራት ከ6.5 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ድጋፍ ተደረገ
ደሴ፣ ነሐሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም (ደቡብ ወሎ ኮሙዩኒኬሽን)

በአሜሪካ መንግስት የገንዘብ እገዛ የሚደገፈው እና ከጄ.ኤስ.አይ (JSI) እንዲሁም ከጤና ልማትና ፀረ-ወባ ማህበር ጋር በጋራ የሚተገበረው "ሞመንተም ኢንተግሬትድ ሄልዝ ሬዚሊያንስ (MIHR)" የተሰኘው የግብረሰናይ ድርጅት፣ በደቡብ ወሎ ዞን የጤና አገልግሎትን ዲጂታላይዝ ለማድረግና የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል ያለመ አዲስ የኮምፒውተር ድጋፍ አደረገ።

ድርጅቱ በዛሬው ዕለት ያደረገው ድጋፍ የጤና ተቋማትን የመድኃኒትና የህክምና መሳሪያዎች አስተዳደርና ስርጭት ለማዘመን የሚያግዙ 2.9 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ 9 ዘመናዊ የዳጉ ኮምፒውተሮችን እና 171 የመዝገብ ድጋፎችን ያካተተ ነው።

የደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ አብዱ መሐመድ እንደተናገሩት፣ ድርጅቱ ከዚህ ቀደም ካደረገው 3.5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ 52 ዓይነት የህክምና ቁሳቁሶች (ራዲያንት ዋርመር እና ሲፓፕ ማሽኖችን ጨምሮ) ድጋፍ ጋር ተደምሮ እስካሁን ለአካባቢው የጤና ስርዓት ማጠናከሪያ ያበረከተው አጠቃላይ የግብአት ድጋፍ ከ6.5 ሚሊዮን ብር በላይ ማድረሱን ገልጸዋል።

በአምባሰል፣ ተሁለደሬ፣ ቃሉ፣ ከላላ እና ሳይንት ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ 16 ጤና ጣቢያዎች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራው ይህ ፕሮጀክት ከተጀመረበት ከባለፉት 6 ወራት ወዲህ በርካታ አመርቂ ተግባራትን አከናውኗል ብለዋል አቶ አበዱ፡፡

የአቅም ግንባታና ስልጠና፡ በእናቶችና ህፃናት ጤና፣ በአገልግሎት ጥራት፣ በክትባትና በጤና ተቋማት ፅዳት ዙሪያ ለ400 በላይ ባለሙያዎች ስልጠናና የተቀናጀ የሜንተርሽፕ ስራ ተሰጥቷል።

ተንቀሳቃሽ የህክምና አገልግሎት (Mobile Health Team)፡ ለመድረስ አስቸጋሪ በሆኑ 17 ቀበሌዎች ለሶስት ተከታታይ ዙሮች የተቀናጀ የህክምና አገልግሎት በመስጠት የስነ-ምግብ ችግር ያለባቸውን ህፃናት የመለየትና ህክምና የመስጠት ስራ ተከናውኗል ሲሉም ምክትል መምሪያ ኃላፊው አስረድተዋል።

የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች መከላከል፡ የወረርሽኝና የጤና አደጋዎችን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ የፈጣን ምላሽና የወረቀት አልባ ሪፖርት አቀራረብ ስልጠናዎች ለባለሙያዎችና ለህብረተሰብ መሪዎች ተሰጥተዋል።
ድጋፋዊ ጉብኝት፡ በቼክሊስት የተደገፈ ተከታታይ ክትትል በማድረግ በስልጠና የተገኙ እውቀቶች በተግባር መተርጎማቸውን የማረጋገጥ ስራ ተሰርቷል።

ምክትል ኃላፊው አቶ አብዱ አክለውም ድርጅቱ "እንደ ስሙ ከጎን ሆኖ ከአንገት ሳይሆን ከአንጀት እያገዘን ያለ ድርጅት ነው" ሲሉ አድናቆታቸውን ገልጸው፤ የተደረገው ድጋፍ ማህበረሰቡን በጤናው ዘርፍ ተጠቃሚ ለማድረግ ትልቅ አበርክቶ እንደሚኖረው ተናግረዋል።

"በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ!!"በደቡብ ወሎ ዞን በሀርቡ  ከተማ የክረምት የዜጎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ምክንያት በማድረግ የደም ልገሳ መረሃ ግብር እየተካሄደ ነው።
17/08/2026

"በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ!!"

በደቡብ ወሎ ዞን በሀርቡ ከተማ የክረምት የዜጎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ምክንያት በማድረግ የደም ልገሳ መረሃ ግብር እየተካሄደ ነው።

የደቡብ ወሎ ዞን ጤና ምሪያ የ2019 ዓ.ም ወረዳን መሰረት ያደረገ  ዕቅድ እና የ3 ዓመት 2ኛው የጤና ሴክተር እድገትና ኢንቬሰትመንት ስትራቴጅክ እቅድ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
17/06/2026

የደቡብ ወሎ ዞን ጤና ምሪያ የ2019 ዓ.ም ወረዳን መሰረት ያደረገ ዕቅድ እና የ3 ዓመት 2ኛው የጤና ሴክተር እድገትና ኢንቬሰትመንት ስትራቴጅክ እቅድ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

አምሪፍ ሄልዝ አፍሪካ በደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ የቃሉ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ትኩረት የሚሹ ሀሩራማ በሽታወችን ከመደበኛ የጤና ስርዓት ጋር የማቀናጀት የሙከራ ፕሮጄክት (Integrating N...
13/06/2026

አምሪፍ ሄልዝ አፍሪካ በደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ የቃሉ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ትኩረት የሚሹ ሀሩራማ በሽታወችን ከመደበኛ የጤና ስርዓት ጋር የማቀናጀት የሙከራ ፕሮጄክት (Integrating NTDs to Health System pilot project) የተግባር ማስጀመሪያ ወርክሾፕ በደሴ ከተማ ተከሄደ።

ደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ
ሰኔ 6 /2018 ዓ.ም
ደሴ

በወርክሾፑ ላይ የቃሉ ወረዳ ዋና አስተዳደሪን ጨምሮ የጤና ፣ የት/ት ፣ የውሃ እና ኢነርጂ፣ የፋይናንስ እንድሁም የሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ሀላፊዎች እና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለሞያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

መድረኩን በእንኳን ደህና መጣችሁ መልክት የከፈቱት የደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ ም/ሃላፊ አቶ አብዱ መሀመድ እንደገለፁት አምሪፍ ሄልዝ አፍሪካ የጤና ዲጂታላይዜሽን ተግባር ላይ ጉልህ አስተዋፅኦ እያደረገ ያለ አጋር ድርጅት መሆኑን ገልፀው አሁን ላይ ትኩረት የሚሹ ሀሩራማ በሽታዎች ላይ መስራቱ እነዚህን በሽታዎች የአለም ጤና ድርጅት (WHO) ባስቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ለማስወገድ በሚደረገው ጥረት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ተናግረዋል።

የቃሉ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙህዲን አህመድ በበኩላቸው ፕሮጄክቱ የታለመለትን ግብ እንድያሳካ የወረዳው አስተዳደር ተገቢውን ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ጠቁመው ፕሮጄክቱ የተሳካ እንደሚሆን ያላቸውን እምነነት ገልፀዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የፕሮጄክቱ አስተባባሪ የሆኑት አቶ በለጠ መንግስቱ በበኩላቸው አምሪፍ ሄልዝ አፍሪካ ይህን ፕሮጄክት ጨምሮ በተለያዩ የጤና ፕሮግራሞች ላይ እየሰራ የሚገኝ አጋር ድርጅት መሆኑን በመግለፅ ይህ የሙከራ ፕሮጄክት በስኬት የሚጠናቀቅ ከሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለማስፋት የታቀደ ፕሮግራም በመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለስኬታማነቱ የድርሻቸውን እንድወጡ አሳስበዋል።

ፕሮጄክቱ በሀገር ደረጃ በተመረጡ ሶስት ክልሎች ማለትም በአማራ ክልል ቃሉ ወረዳ በሲዳማ ክልል አለታ ወንዶ ወረዳ እንድሁም ኦሮሚያ ክልል ሾቤ ሶቦ ወረዳዎች በሙከራ ደረጃ የሚተገበር ፕሮጄክት ሲሆን ለቀጣይ 2 ዓመታት ቆይታ እንደሚኖረው ተገልፇል::

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ! በዓሉ የሰላምና የጤና በዓል እንድሆን እንመኛለንደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ
26/05/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

በዓሉ የሰላምና የጤና በዓል እንድሆን እንመኛለን

ደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ

18/05/2026
14/05/2026

Address

Dessi

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share