South Wollo Zone High Court

South Wollo Zone High Court ይህ ገጽ የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ህዝብ ግንኙነት ገጽ ነው
(1)

24/08/2026
20/08/2026

ባሕርዳር፣ ነሐሴ 14/2018 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት

ማስታወቂያ

በአይ.ሲ.ቲ የሥራ መደቦች ፈተና ለመውሰድ ተመርጣችሁ የፈተና ቦታ እንዲቀየርላችሁ ላመለከታችሁ፤

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ27/04/2018 ዓ.ም በተለያዩ ቦታዎች የአይ.ሲ.ቲ የስራ መደቦች ላወጣው የስራ ማስታወቂያ ነሐሴ 08/2018 ዓ.ም ወደ ቀጣይ የፈተና ሂደት ያለፉ ተወዳዳሪዎችን ዝርዝር አስታውቋል፡፡

በየዘርፎቹ የተዘረዘሩ መስፈርቶችን አሟልተው ያልተካተቱ ተወዳዳሪዎች ቅሬታቸውን እስከ ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም እንዲያስገቡ በተቀመጠው መሰረት፣ ቅሬታ ያላቸው አመልካቾች ቅሬታቸውን አስገብተው በመታየት ላይ ሲሆን፣ ለፈተና አልፋችሁ በተለያየ ምክንያት ከአመለከታችሁበት አካባቢ ውጭ የሆናችሁ ተወዳዳሪዎች የፈተና ቦታ ይቀየርልን ብላችሁ በጠየቃችሁት መሰረት የፈተና ቦታ ቅያሬ የተደረገላችሁ መሆኑን እያስታወቅን፣ ከስር በተቀመጠው አግባብ በእለቱ ለፈተና እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ፤ የሌሎች ቅሬታ አቅራቢዎች ማመልከቻ በመታየት ላይ ሲሆን፤ በቅርቡ የምናስታውቅ ይሆናል።

የተሁለደሬ ወረዳ ፍ/ቤት በወረዳው ስር በሚገኙ ቀበሌዎች ለተቋቋሙ የባህል ፍርድ ቤት ዳኞች እና ባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ​🗓 ነሃሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም | ደሴ​ከU...
17/08/2026

የተሁለደሬ ወረዳ ፍ/ቤት በወረዳው ስር በሚገኙ ቀበሌዎች ለተቋቋሙ የባህል ፍርድ ቤት ዳኞች እና ባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ

​🗓 ነሃሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም | ደሴ

​ከUNDP Peace Support Facility በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ፣ በተሁለደሬ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች ለተቋቋሙ የባህል ፍርድ ቤት ዳኞች፣ ለቀበሌ አስተዳዳሪዎች እና ለተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በዛሬው እለት ተሰጥቷል።

​የስልጠና መድረኩን በንግግር የከፈቱት የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ ትእግስት ዳኛቸው እንደገለጹት፤ አባት አደር ከሆኑት የማህበረሰብ ጥበቦች አንዱ የሆነው የሽምግልና ስርአት ለዘመናት በግለሰቦች፣ በቡድኖች እና በማህበረሰብ መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በመፍታት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሲያደርግ መቆየቱን አውስተዋል። አሁን ላይ እየተዘነጋ የመጣውን ይህን መልካም እሴት ስርአት እና ደንብ ይዞ እንዲቀጥል ለማስቻል ህጋዊ እውቅና አግኝቶ፣ ማስተግበሪያ መመሪያ ተዘጋጅቶለት ከመደበኛ ፍርድ ቤቶች ጎን ለጎን አማራጭ የሙግት መፍቻ ስርአት ተደርጎ ወደ ተግባር መገባቱን ገልጸው፤ የባህል ፍርድ ቤቶች መቋቋም አላማ እና የሚጠበቁ ውጤቶችን አብራርተዋል።

​የተሁለደሬ ወረዳ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት የተከበሩ አቶ ደረጀ ደምሴ በበኩላቸው፤ ፍርድ ቤቱ በሀይቅ ከተማ አስተዳደር እና ተሁለደሬ ወረዳ በሚገኙ 20 ቀበሌዎች የባህል ፍርድ ቤቶችን በማቋቋም ወደ ስራ ማስገባት መቻሉን ጠቁመዋል። አክለውም የባህል ፍርድ ቤቶች ከጊዜ፣ ከወጪ እና ከተደራሽነት አንጻር ለማህበረሰቡ ያላቸውን ከፍተኛ ጠቀሜታ አብራርተዋል።

​ፕሬዚዳንቱ አያይዘውም የስልጠናው ዋና አላማ የባህል ፍርድ ቤት ዳኞችን ግንዛቤ ከማሳደግ ባለፈ፣ ተሳታፊ ባለድርሻ አካላት እና የቀበሌ አስተዳዳሪዎች የማቋቋሚያ አዋጁን እና መመሪያውን በበቂ ሁኔታ ተረድተው ለህብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲፈጥሩና አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ማስቻል መሆኑን አስገንዝበዋል። ለዝግጅቱ አስፈላጊውን ድጋፍ ላደረጉት UNDP Peace Support Facility እና ለወረዳው አስተዳደርም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

​ስልጠናው በደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት በተከበሩ አቶ ምትኬ ወርቁ አሳታፊ በሆነ መልኩ የተሰጠ ሲሆን፤ ትኩረቱም በአብክመ የባህል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 298/2017 እና ይህን አዋጅ ለማስፈፀም በወጣው ደንብ ቁጥር 23/2018 ላይ ያተኮረ ነበር።

የተሁለደሬ ወረዳ ፍ/ቤት በወረዳ አስተዳደሩ ስር በሚገኙ ቀበሌዎች ለተቋቋሙ የባህል ፍርድ ቤት ዳኞች እና ለባህል ፍርድ ቤት አማካሪ ምክር ቤት አባላት ስልጠና ሰጠ።ነሀሴ 08/2018ዓ.ም ሀ...
14/08/2026

የተሁለደሬ ወረዳ ፍ/ቤት በወረዳ አስተዳደሩ ስር በሚገኙ ቀበሌዎች ለተቋቋሙ የባህል ፍርድ ቤት ዳኞች እና ለባህል ፍርድ ቤት አማካሪ ምክር ቤት አባላት ስልጠና ሰጠ።
ነሀሴ 08/2018ዓ.ም ሀይቅ
===================
የዛሬው የስልጠና መድረክ በንግግር የከፈቱት የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ኘሬዝደንት ወ/ሮ ትዕግስት ዳኛቸው ሲሆኑ በንግግራቸውም የባህል ፍርድ ቤቶች መጠናከር ማህበረሰቡ በአካባቢው ፣በባህሉ እና በወጉ ፣በአነስተኛ ወጭ ፣ዘላቂ የእርስ በእርስ ግንኙነትን በማይጎዳ መልኩ እና በአጠረ ጊዜ ፍትህ እንዲያገኝ የሚያስችል በመሆኑ ከስልጠናው የሚገኘውን ግብዓት በአግባቡ በመጠቀም ማህበረሰቡን በቅንነነት እንዲያገለግሉ ያሳሰቡ ሲሆን ይህንን ስልጠና ከUNDP Peace Support Facility ጋር በመተባበር በሎጎ ሀይቅ ሪዞርት ላዘጋጁት ለተሁለደሬ ወረዳ ፍርድ ቤት ኘሬዝደንት አቶ ደረጀ ደምሴ ምስጋና አቅርበዋል።
====================
ስልጠናውን የሰጡት የደብብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ም/ኘሬዝደንት የሆኑት አቶ ምትኬ ወርቁ ሲሆኑ ስልጠናው ትኩረቱን ያደረገው በአብክመ የባህል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 298/2017እና ይህን አዋጅ ለማስፈፀም በወጣው ደንብ ቁጥር 23/2018ነው።
=================
የስልጠናው ተሳታፊዎች በተግባር ካጋጠማቸው ችግሮች በመነሳት ጥያቄዎችን ያቀረቡ ሲሆን በአሰልጣኙ በቂ ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጧል።
=================
የተሁለደሬ ወረዳ ፍ/ቤት ኘሬዝደንት ስልጠና በጥሩ ሁኔታ እንዲሳካ በገንዘብ እና በአይነት ድጋፍ ለደረጉት ለUNDP PSF እና ሎጎ ሀይቅ ሪዞርት ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፤
======================
በመጨረሻም የስልጠናው ተሳታፊዎች የሎጓ ሀይቅ ሪዞርትን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
===================

የተቋማዊ መግባባትና አብሮነት አስፈላጊነት፡ ከደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የ2018 ዓ.ም ተሞክሮ​አንድ ተቋም ውጤታማ፣ ስኬታማ እና ግልጽ አገልግሎት ሰጭ እንዲሆን የቴክኖሎጂ አቅርቦት...
14/08/2026

የተቋማዊ መግባባትና አብሮነት አስፈላጊነት፡ ከደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የ2018 ዓ.ም ተሞክሮ

​አንድ ተቋም ውጤታማ፣ ስኬታማ እና ግልጽ አገልግሎት ሰጭ እንዲሆን የቴክኖሎጂ አቅርቦት ወይም የቁሳቁስ መሟላት ብቻውን በቂ አይደለም። ከተቋሙ ግቦች በስተጀርባ የሚሰሩ የአመራሮች፣ የዳኞች እና የሰራተኞች የአእምሮና የልብ መገናኘት (ተቋማዊ መግባባት) ወሳኝ ድርሻ አለው።
የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንት ሀሳብ አመንጭነት በ2018 ዓ.ም ያካሄዳቸው ሁለት ስኬታማ "የአብሮነት ቀናት" ይህንን ተቋማዊ መግባባት በተግባር ያረጋገጡ እና ለሌሎችም አርአያ የሚሆኑ ተግባራት ናቸው።

​1. ተቋማዊ መግባባት (Institutional Unity & Consensus) ማለት ምን ማለት ነው?
​ተቋማዊ መግባባት ማለት በአንድ ተቋም ውስጥ የሚገኙ አመራሮች፣ ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች የጋራ ህልም፣ እሴት እና ግብ እንዲኖራቸው የማድረግ ሂደት ነው። ይህ መግባባት የሚፈጠረው የዕለት ተዕለት የሥራ ግንኙነት ብቻ ሳይሆን፣ ሰብአዊ መቀራረብ፣ እርስ በእርስ መከባበር እና ግልጽ የመረጃ ልውውጥ ሲኖር ነው።
​በተለይም እንደ ፍርድ ቤት ባሉ ከፍተኛ የህግና የፍትህ ተቋማት ውስጥ የሙያና የስልጣን እርከኖች በመኖራቸው ምክንያት የሚፈጥረውን የስራ ጫና እና ማህበራዊ ርቀት (Social Distance) ለማጥበብ እንዲህ ያሉ የጋራ መድረኮች ያላቸው ሚና ከፍተኛ ነው።

​2. የተቋማዊ መግባባት ጠቀሜታዎች
​ተቋማዊ መግባባት በደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንደታየው የሚከተሉትን ዘለቄታዊ ጠቀሜታዎች ይሰጣል፡
​የስራ አካባቢን ምቹ እና ሳቢ ማድረግ፡ ሰራተኞችና ዳኞች በስራ ቦታቸው ዘና ብለው፣ ፍቅራቸውንና ክብራቸውን ገልጸው ሲሰሩ የስራ ጭንቀት (Work Stress) ይቀንሳል።
​የቡድን መንፈስን (Team Spirit) ማጠናከር፡ የስልጣንና የሙያ ልዩነት ሳይኖር በጋራ ማለፍ፣ "እኔ" ከሚለው ስሜት ይልቅ "እኛ" የሚለውን የተቋማዊ ባለቤትነት ስሜት ያጎለብታል።
​የአገልግሎት ጥራትንና ምርታማነትን ማሳደግ፡ በሰራተኞች መካከል መልካም ግንኙነትና መግባባት ሲኖር የስራ ቅንጅት ይጨምራል፤ ይህም ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ቀልጣፋና ፍትሃዊ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል።
​ልምድና እውቀትን ማሸጋገር፡ በስራ ላይ ያሉ ሰራተኞች ከቀድሞ ባለሙያዎችና ባለአደራዎች ተሞክሮ የሚወስዱበት አጋጣሚ ይፈጥራል።

​3. የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የ2018 ዓ.ም የአብሮነት ቀናት
​ፍርድ ቤቱ በዓመቱ መጀመሪያ እና መጨረሻ ያከናወናቸው ሁለት የአብሮነት ቀናት ተቋማዊ መግባባትን እውን ለማድረግ የታለሙና ግባቸውን በብቃት የመቱ ነበሩ፡
​ሀ/ የመጀመሪያው የአብሮነት ቀን ህዳር 7 ቀን 2018 ዓ.ም (በተቋሙ ግቢ)
​በዓመቱ መጀመሪያ በተቋሙ ግቢ ውስጥ በተደረገው መርሃ-ግብር ሁሉም ዳኞች፣ የጉባኤ ተሿሚዎች እና የአስተዳደር ሰራተኞች በአንድነት ተሳትፈዋል። ፕሮግራሙ አብሮ ከመብላትና መጠጣት ባለፈ፡

​የቀድሞ ሰራተኞችን ማክበር፡ ተቋሙን ለረጅም ዘመን አገልግለው በጡረታ የተሰናበቱ ሰዎችን በመጋበዝ እውቅና የመስጠት እና የህይወትና የስራ ተሞክሯቸውን እንዲያካፍሉ ተደርጓል። ይህም አዲሱን ትውልድ ለስራ የሚያነሳሳና የቆየውን ባለሙያ የሚዘክር ታላቅ እሴት ነው።
​መልካም አፈጻጸምን ማበረታታት፡ በ2017 ዓ.ም የተሻለ አፈጻጸም ላሳዩ ሰራተኞች የምስክር ወረቀት በማበርከት የሰራተኛውን የውድድርና የስራ ተነሳሽነት ማሳደግ ተችሏል።
​ለ/ ሁለተኛው የአብሮነት ቀን ሀምሌ 25/2018 ዓ.ም (ከደሴ ከተማ ወጣ ብሎ በሀይቅ እሪኩም ሎጅ እና ሎጎ ሀይቅ ሪዘርት)
​በዓመቱ መጨረሻ የተካሄደው ፕሮግራም ደግሞ ሰራተኛው ከተለመደው የስራ አካባቢ ወጣ ብሎ ዘና እንዲልና ተፈጥሮን እየተንከባከበ የታደሰ መንፈስ እንዲያገኝ ያስቻለ ነበር፡
​እኩልነትና ወንድማማችነት፡ በሀይቅ እሪኩም ሎጅ በተደረገው የምሳ ግብዣና የባህል ሙዚቃ መርሃ-ግብር የሙያም ሆነ የስልጣን ልዩነት ሳይደረግ አመራሩ፣ ዳኛውና ሰራተኛው አብሮ በመጨፈርና በመጫወት እውነተኛ መቀራረብን አሳይተዋል።

​አዳዲስ ቦታዎችን መጎብኘት፡ አዲስ የተከፈተውን የሎጎ ሀይቅ ሪዘርት በመጎብኘት ያማረና በደስታ የተሞላ ጊዜን ማሳለፍ ተችሏል።

​ማጠቃለያ
​እነዚህ መርሃ ግብሮች ከተጠናቀቁ በኋላ የፍርድ ቤቱ ሰራተኞችና ዳኞች በቋሚ የቴሌግራም ግሩፓቸው ላይ የገለጹት ከፍተኛ ደስታና አወንታዊ አስተያየት፣ የፕሮግራሞቹን አስፈላጊነትና ስኬታማነት በግልጽ ያሳያል።
​በፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንት ሀሳብ አመንጭነት የተጀመረው ይህ የመቀራረብና የአብሮነት ባህል፣ በተቋሙ አመራር፣ ዳኞችና ሰራተኞች መካከል የጠበቀ ወንድማማችነትን በመፍጠር ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል። ይህ ተቋማዊ መግባባት ወደፊትም ተጠናክሮ በመቀጠል ለዞኑ ህብረተሰብ የሚሰጠውን የፍትህ አገልግሎት ጥራትና ቅልጥፍና ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው እምነት አለን

Address

Dessi
251

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when South Wollo Zone High Court posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to South Wollo Zone High Court:

Shortcuts

Share