05/09/2026
የደሴ ከተማ የክረምት በጎፈቃድ ቴክኒክ ኮሚቴ በሁሉም ክፍለ ከተማ በክረምት ወራት የተሠሩ ተግባራትን ክትትልና ድጋፍ አካሄዱ።
የቴክኒክ ኮሚቴውም በ5ቱም ክፍለ ከተማው ውስጥ በሚገኙ የ17ቱን ቀበሌዎች በክረምት በጎፈቃድ የተሠሩ ተግባራት በመስክ ምልከታ የአዲስ ቤት ግንባታ እና ጥገና በተመለከተ፣ የተሠበሰቡ የትምህርት ቁሳቁስና አልባሳት፣ የትምህርት ቤት ጥገና ተግባራትን እና በቢሮ አጠቃላይ የተከናወኑ ተግባራትን የዶክመንት መረጃዎችን በማየት የክትትልና ድጋፍ ስራን አካሂደዋል።
በክትትልና ድጋፋ የታዩ ተግባራትን ቴክኒክ ኮሚቴው ለክፍለ ከተማው ስትሪክት ኮሚቴ በጥንካሬና በድክመት አንስተው ተወያይተዋል።
በየቀበሌው የተሠበሰቡ፣ ቃል የተገቡ የትምህርት ቁሳቁስን ወደ አንድ በማሠባሠብ በተደራጀ መንገድ ከተማ አስተዳደሩ በሚያስቀምጠው አቅጣጫ ለማሠራጨት እንዲዘጋጁ መልእክት አስተላልፈዋ።
ክፍለከተማውም የተሠጡትን አስተያየት በመቀበል በቀሪ ወራቶች የተጀመሩትን በመጨረስ እና የተሻለ ተግባራትን በመፈጸም የዜጎች በጎፈቃድ ተግባርን ለማሳካት እንደሚሠሩ ገልጸዋል።