Kutaber Woreda Prosperity Party Office/ኩታበር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Dessie
  • Kutaber Woreda Prosperity Party Office/ኩታበር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት

Kutaber Woreda Prosperity Party Office/ኩታበር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት The page is dedicate to promote developmental & democratic line of KWPP/kutaber woreda Prosperity Pa

በደቡብ ወሎ ዞን ኩታበር ወረዳ ❝ዉጫዊ የወራሪ ስጋትና ዉስጣዊ የጽንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማትን እናረጋግጣለን❞  በሚል መሪ ቃል ከመንግስት ሰራተኞች ጋር ዉይይት እየተካ...
21/08/2026

በደቡብ ወሎ ዞን ኩታበር ወረዳ ❝ዉጫዊ የወራሪ ስጋትና ዉስጣዊ የጽንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማትን እናረጋግጣለን❞ በሚል መሪ ቃል ከመንግስት ሰራተኞች ጋር ዉይይት እየተካሄደ ነዉ።

‎❝በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ❞‎‎በደቡብ ወሎ ዞን ኩታበር  ወረዳ የክረምት የዜጎች በጎ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካሞች ቤት ግንባታ ተጠናክሮ ቀጥሏል።‎በዛሬዉ እለት በ01 ከተማ የአቅመ ደካ...
20/08/2026

‎❝በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ❞

‎በደቡብ ወሎ ዞን ኩታበር ወረዳ የክረምት የዜጎች በጎ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካሞች ቤት ግንባታ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በዛሬዉ እለት በ01 ከተማ የአቅመ ደካማ ቤት ግንባታ ስራ እና የቤት ጥገና ሲካሄድ ዉሏል።

‎❝በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ❞‎‎በደቡብ ወሎ ዞን ኩታበር  ወረዳ የክረምት የዜጎች በጎ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካሞች ቤት ግንባታ ተጠናክሮ ቀጥሏል።‎‎የኩታበር ወረዳ 03 አላንሻ ማዶ ቀበ...
20/08/2026

‎❝በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ❞

‎በደቡብ ወሎ ዞን ኩታበር ወረዳ የክረምት የዜጎች በጎ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካሞች ቤት ግንባታ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

‎የኩታበር ወረዳ 03 አላንሻ ማዶ ቀበሌ በዛሬዉ እለት የአቅመ ደካማ ቤት ግንባታ ስራ ሲሰራ ዉሏል።

በዚህ ፕሮግራም ላይ የኩታበር ወረዳ ብልጽግና ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ሀሰን፣የኩታበር ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ እሸቱ ይመር የአካባቢዉ ህብረተሰብና በጎ ፈቃድ ሰጭ ወጣቶች ተገኝተዋል።

በኩታበር ወረዳ ለሰማዕታት ቤተሰቦች ከካሳ  ነጻ የሆነ የቦታ እርክክብ   ተደረገ።በደቡብ ወሎ ዞን ኩታበር ወረዳ ለሀገር ሰላምና ደህንነት ሲሉ ህይወታቸውን መስዕዋት ላደረጉ የሰላም አስከባሪ...
17/08/2026

በኩታበር ወረዳ ለሰማዕታት ቤተሰቦች ከካሳ ነጻ የሆነ የቦታ እርክክብ ተደረገ።

በደቡብ ወሎ ዞን ኩታበር ወረዳ ለሀገር ሰላምና ደህንነት ሲሉ ህይወታቸውን መስዕዋት ላደረጉ የሰላም አስከባሪ፣ የፖሊስና የሚሊሻ አባላት ቤተሰቦች ከካሳ ነጻ የሆነ የቤት መስሪያ ቦታ እርክክብ ተደረገላቸው።

የእርክክብ መርሃ ግብሩን የከፈቱት የኩታበር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጀማል ይመር፣ ለሀገር ሰላም ሲሉ ህይወታቸውን የሰጡ የጸጥታ አካላት ያበረከቱት መስዋትነት ታላቅ ክብር የሚገባው መሆኑን ገልጸዋል።

በመርሃ ግብሩ የደቡብ ወሎ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ሀላፊ ኮሚሽነር ዘለቀ አለባቸው፣ የደቡብ ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ ሀላፊ ኮማንደር አሳምን፣ የኩታበር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጀማል ይመር፣ የኩታበር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ እብራሂም ሀሰን፣ የኩታበር ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ሀላፊ ኮሎኔል ክፍሌ መኮንን፣ የኩታበር ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት ሀላፊ ኢንስፔክተር ሀብታሙ መርጊያው፣ የኩታበር ወረዳ ሚሊሻ ፅ/ቤት ሀላፊ መቶ አለቃ ጌታቸው ከበደ እንዲሁም ሌሎች የወረዳና የዞን አመራሮች፣ የጸጥታ አካላትና የተለያዩ እንግዶች ተገኝተዋል።

በመድረኩ ላይ ተሳታፊዎች ለሀገር ሰላም የተከፈለውን መስዋትነት በማስታወስ የ03 እና 05 ቀበሌ ነዋሪዎች ከካሳ ውጭ ቦታ መበርከቱ ለሰማዕታት ቤተሰቦች የሚደረገው ድጋፍ ለሌሎች ወረዳዎች ተምሳሌት የሚሆንና መጠናከር እንዳለበት ገልጸዋል።

የሠማዕት ቤተሠቦች የተደረገላቸው ድጋፍ የሰማዕታቱን መስዋትነት የሚያከብርና በችግር ጊዜ ከጎናቸው መቆምን የሚያሳይ በመሆኑ በደስታ መቀበላቸውን ገልጸዋል።

በተለይም የቦታ ድጋፉ ለእነርሱና ለቤተሰቦቻቸው ትልቅ እፎይታ የሚሰጥ መሆኑን በመግለጽ፣ ለወረዳው አመራርና ለድጋፉ ምክንያት ለሆኑ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በደቡብ ወሎ ዞን ኩታበር ወረዳ ❝የፀረ-ጽንፈኝነት ትግልን ከተበታተነ  ጥረት ወደ ህዝባዊ ማዕበል በመለወጥ የጠላትን የቆይታ ጊዜ እናሳጥር❞ በሚል ሀሳብ ከጠቅላላ የመንግስት ሰራተኞች ጋር የ...
14/08/2026

በደቡብ ወሎ ዞን ኩታበር ወረዳ ❝የፀረ-ጽንፈኝነት ትግልን ከተበታተነ ጥረት ወደ ህዝባዊ ማዕበል በመለወጥ የጠላትን የቆይታ ጊዜ እናሳጥር❞ በሚል ሀሳብ ከጠቅላላ የመንግስት ሰራተኞች ጋር የዉይይት መድረክ እየተካሄደ ነዉ።

" ካልተግባባን በንግግር እንጨቃጨቅ ፣ጊዜው እንዳያልፍብን ግን እንጠንቀቅ"ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አዲሱን የባህርዳር መንገደኞች ተርሚናል በመረቁበት ወቅት የተናገሩት።ጊዜው የሥራ ነው...
06/08/2026

" ካልተግባባን በንግግር እንጨቃጨቅ ፣ጊዜው እንዳያልፍብን ግን እንጠንቀቅ"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አዲሱን የባህርዳር መንገደኞች ተርሚናል በመረቁበት ወቅት የተናገሩት።

ጊዜው የሥራ ነው፤የጠመንጃ እሽቅድምድም አይደለም። ጠመንጃ ሕዝብ አደኸየ፣ህይወት ቀጠፈ ፣ንብረት አወደመ፣ተማሪ እንዳይማር፣ነጋዴው እንዳይነግድ አደረገ እንጂ የፈየደው ነገር የለም።

ሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎች በልማት እየሮጡ ነው ፣ የአማራ ክልል ህዝብም የልማት ጊዜ እንዳያልፍበትና ከዚህ በላይ እንዲጠቀም ቆም ብለን ማሰብ እንዳለብን አሳስበዋል።

“ጫና መቋቋም አቅቷቸው ሸብረክ የሚሉ ሰዎች ጥጃው ሳይወለድ በረቱን እንደሚዘጋ ሰው ዓይነት ናቸው። ለጊዜያዊ ችግር ሲሉ ሸብረክ የሚሉ ሰዎችም፣ ጥጃው ሳይወለድ በረቱን የዘጋውም ሒደቱ በአጭር...
31/07/2026

“ጫና መቋቋም አቅቷቸው ሸብረክ የሚሉ ሰዎች ጥጃው ሳይወለድ በረቱን እንደሚዘጋ ሰው ዓይነት ናቸው። ለጊዜያዊ ችግር ሲሉ ሸብረክ የሚሉ ሰዎችም፣ ጥጃው ሳይወለድ በረቱን የዘጋውም ሒደቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚፈጸም ስላልሆነ፣ ለርካሽ ዓላማ ሲባል ከቁም ነገር መጉደል አይሁንባችሁ።” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

"የአማራ እና ኦሮሞ ሕዝቦች ለዘመናት በጥብቅ መስተጋብር የተሣሠሩ የሀገር ግንባታ ዋልታዎች ናቸው" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)  በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የአማራ እና የኦሮሞ ...
31/07/2026

"የአማራ እና ኦሮሞ ሕዝቦች ለዘመናት በጥብቅ መስተጋብር የተሣሠሩ የሀገር ግንባታ ዋልታዎች ናቸው" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የአማራ እና የኦሮሞ ሕዝቦች በጋብቻ፣ በፖለቲካዊ ትሥሥር እና በባህላዊ መስተጋብር የተሣሠሩ የሀገር ግንባታ ዋልታዎች መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር በነበራቸው ቆይታ የሁለቱን ሕዝቦች የዘመናት አብሮነት እና አኩሪ ታሪክ በስፋት አብራርተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው የኢትዮጵያ ሕዝብ በዘመናት መካከል አብሮ የኖረ፣ የተጋመደ እና የተዋለደ መሆኑንም አስታውሰዋል።

በተለይም በአቀማመጥ እና በቁጥር ሰፊ ድርሻ ያላቸው የአማራ እና ኦሮሞ ሕዝቦች በባህላዊ ጋብቻ እና በፖለቲካ ጋብቻ እንዲሁም በባህላዊ የጉዲፈቻ ሥርዓት ለዘመናት በጥብቅ መስተጋብር ውስጥ ማለፋቸውን አብራርተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሸዋ እና የይፋት ሡልጣኔቶችን እንዲሁም የጎንደር፣ የየጁ እና የወረ ሂመኑ ሥርወ መንግሥታትን በታሪክ ማሳያነት አንሥተዋል።

በእነዚህ ረጅም ዘመናት በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የተፈጠሩት ሰፊ ውህደቶች ሕዝቦቹ አብረው ሲዘምቱ፣ ሲያለሙ እና አብረው ሲዋጉ መኖራቸውን በግልጽ እንደሚያሳይ አስረድተዋል።

የዘመናዊት ኢትዮጵያ ታሪክ ከእነዚህ ሕዝቦች ውህደት ውጤት እንሆነ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያብራሩት።

አፄ ምኒልክን ያለ ራስ ጎበና፣ ራስ ጎበናንም ያለ አፄ ምኒልክ ማሰብ አይቻልም፤ ዘመናዊት ኢትዮጵያ የተፈጠረችው በእነዚህ ታላላቅ ሰዎች ውህደት ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያውያን በጋራ የሚኮሩበት የዓድዋ ድልም የዚሁ ውህደት ትልቁ ማሳያ መሆኑ ጠቅሰዋል። አፄ ምኒልክ፣ ፊታውራሪ ገበየሁ እና ደጃዝማች ባልቻን የመሳሰሉ ጀግኖች ለአንዲት የከበረች ሀገር የጋራ ሕልውና በጋራ ዘምተው ያመጡት ድል መሆኑንም አብራርተዋል።

በሕዝቦች ደረጃም በፊውዳሉ ሥርዓት ላይ የተነሡት የጎጃም እና የባሌ ገበሬዎች አመፆች የሕዝቦቹን ተመሳሳይ የትግል ታሪክ የሚያንፀባርቁ መሆናቸውንም አስታውሰዋል።

31/07/2026

Address

Dessie

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kutaber Woreda Prosperity Party Office/ኩታበር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share