Mekaneselam womans legue offeice

Mekaneselam womans legue offeice Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Mekaneselam womans legue offeice, Political organisation, Dessie.

12/09/2025
28/11/2022
28/11/2022

የዜጎችን ሰላምና ደህንነት በማስጠበቅ ማህበራዊ ብልጽግናን እናረጋግጣለን!

ሁለንተናዊ ማኅበራዊ ብልጽግናን የማረጋገጥ ጉዳይ የፓርቲያችን የማኅበራዊ ፕሮግራም አንድ ዋና የትኩረት ማዕከል ነው። በመሆኑም ለብልጽግና ፓርቲ የማኅበራዊ ልማት ሥራዎቻችን የዕድገትና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት መንትያ ግቦችን የማሳካት ጉዳይ ነው።

የማኅበራዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት ተደራሽነትና አካታችነት ባለው መልኩ የማኅበረሰብን ጤና፣ ሰላምና ደህንነት የሚያስጠብቅ እንዲሆን ፓርቲያችን ተግቶ እየሰራ ይገኛል። ማኅበራዊ ፕሮግራማችን ዜጎችን የሚያስተሣስር፣ ከችግርና ከመከራ የሚታደጋቸው እና የሀገርን አለኝታነት የሚያሠርጽ ፕሮግራም ነው።

የማህበረሰባችን ግማሽ አካል የሆኑት ሴቶች በሚደርስባቸው ሁለንተናዊ ጭቆና ምክንያት ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳትፏቸው እና ተጠቃሚነታቸው አሁንም በሚፈለገው ልክ አለመሆኑን ፓርቲያችን የሚያምንና ይህንኑ ችግር ለመቅረፍ እየሰራ የሚገኝ ፓርቲ ነው፡፡

የሴቶችን እኩል ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም መብትና ደህንነት ለማስጠቅ እየተሰራ ቢሆንም አሁንም ያልተሻገርናቸው ዘርፈ ብዙ ችግሮች አሉ፡፡

በሴቶች እና ልጃ ገረዶች ላይ የሚደርሱ ፆታዊ ጥቃቶች ዓለም አቀፋዊ ችግሮች ናቸው። በዓለም ጤና ድርጅት ትንታኔ መሠረት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሦስት ሴቶች መካከል አንዷ በሕይወቷ ውስጥ አካላዊ ወይም ወሲባዊ ጥቃት ይደርስባታል።

እንደ በጎርጎሮሳዊያኑ አቆጣጠር በ2016 የተደረገው የሥነ-ህዝብና ጤና የዳሰሳ ጥናት መረጃ መሰረት በሀገራችን ከ15 እስከ 49 የዕድሜ ክልል የሚገኙ ሴቶች መካከል 23 በመቶ አካላዊ፣ 10 በመቶ ደግሞ ወሲባዊ ጥቃት በሕይወት ዘመናቸው አንድ ጊዜ እንደሚደርስባቸው ያመለክታል፡፡

እንዲህ ዓይነቱን በተደጋጋሚ የሚፈጸሙ ጾታዊ ጥቃቶችን መከላከል ላይ የሚያተኩር የፀረ ጾታዊ ጥቃት (የነጭ ሪቫን) ቀን በሚካሄድ ዘመቻ ታስቦ እየተከበረ ይገኛል።

በአለም አቀፍ ደረጃ ለ31ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ17ኛ ጊዜ የሚከበረው የፀረ ጾታዊ ጥቃት (የነጭ ሪቫን) ቀን "ሴቶችን አከብራለሁ፤ ጥቃታቸውንም እከላከላለሁ!" በሚል መሪ ቃል ከህዳር 16 እስከ ታህሳስ 1/2015 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ 16 ቀናት እንደሚከበር ከአማራ ክልል ሴቶች፣ ህፃትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በሴቶች ላይ የሚፈጸም ጾታዊ ጥቃት የሚስከትለው ስነ ልቦናዊና አካላዊ ጉዳት ከፍተኛ ነው፡፡ የፀረ ጾታዊ ጥቃት (የነጭ ሪቫን) ቀን ሲከበር በፆታዊ ጥቃት ምክንያት የሚከሰቱ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ላይ ግንዛቤ በመፍጠር፣ በፅኑ በማውገዝና አመለካከቱንም ሆነ ድርጊቱን በዘላቂነት መታገል የሚቻልበት ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ይከበራል፡፡

በሴቶችና ልጃገረዶች ላይ የሚፈጸም ጾታዊ ጥቃት ዘላቂ መፍትሔ እንዲገኝም ሁሉም ባለድርሻ አካል ጥቃት የሚፈፀምባቸው ሴቶች ፍትህ እንዲያገኙ በቅንጅት መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡

•~•~•
"ለሀገር ክብር በትግል እናብር -ቃላችንን ፈፅመን ከፍታው ላይ እንገናኝ"
~~~
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- https://twitter.com/AppAmhara?s=09
ዩቲዩብ :- https://youtube.com/channel/UCxQ5MOnm-YH514Qdta0Kysg
ቴሌግራም ፡-https://t.me/appamhara01.

13/11/2022
13/11/2022
12/11/2022

የሌማት ትሩፋት የልማት ዘመቻችን ግቦች

★ ስጋ ፣እንቁላል፣ማር እና ወተት የቅንጦት ሳይሆን በቀላሉ የሚገኙ አማራጮች እንዲሆኑ ማድረግ።

በሀገራችን እነኚህ ምርቶች በቅንጦት ደረጃ የሚፈረጁ ምርቶች እንጂ እለት በእለት በምግብ አማራጮቻችን ውስጥ የሚገኙ ግብአቶች አይደሉም።ይህም ሊሆን የቻለው ለዘርፉ የተሰጠው ትኩረት እምብዛም አመርቂ ባለመሆኑ የተነሳ ነው።በመሆኑም ይህን ችግር በተረባረበ አቅም እና በቴክኖሎጂ በታገዘ አካሄድ በመፍታት ዘርፈ ብዙ አማራጮችን መፍጠር እንችላለን።በቀላሉም ወተት፣ማር፣ስጋ እና እንቁላል በገበያው እንዲገኙ ማድረግ እንችላለን።

★ ሀገራችን በእንስሳት ተዋእፆ ያላትን እምርታ ማሳደግ::

በእንሰሳት ተዋእፆ ምርቶች ላይ የተወሰነ ስራ ቢሰራ ፍሬ ሊያፈራ የሚችል ሀብት በሀገራችን ውስጥ አለ።ለከብቶች የሚስማማ አየር፣ለንቦች አመቺ የሆነ ስነ ምህዳር፣ስጋ እና እንቁላል ሊያትረፈርፍ የሚችል ተፈጥሮ አለን።ይህን በከፍተኛ ንቅናቄ አውጥተን በመጠቀም እንደ ሀገር ያለንን እምርታ ማሳደግ እንችላለን።

★ ተመጣጣኝ ምግብ በብዛት እና በጥራት በገበያው እንዲኖር ማስቻል።

ምርት ሲበዛ በግብአቶች ላይ የሚኖረው የዋጋ ግሽበት በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ ይመጣል።በመሆኑም ስጋ፣እንቁላል ማር እና ወተት በብዛት በማምረት ወደ ገበያው የሚቀርበውን የምግብ አማራጭ በማስፋት በምግቦች ላይ የዋጋ ግሽበት እንዳይፈጠር እንዲሁም የተመጣጠነ የምግብ ስርአት የዳበረ የአመጋገብ ዘይቤ መገንባት እንችላለን!!

★ የምግብ አማራጮቻችንን ሰፊ በማድረግ የአመጋገብ ባህላችንን ማሻሻል።

ምግብ ራሱን የቻለ ሳይንስ ነው!!የምግብ አማራጮቻችን በሰፉ ቁጥር የአመጋገብ ባህላችንም እንደሚሻሻልም እውን ነው።በተለይም እሴት ጨምሮ ለገበያ ማቅረብ ላይ እና ለውስጥ ፍላጎታችን መጠቀም ላይ ትኩረት አድርገን በመስራት የአመጋገብ ባህላችንን ማሻሻል የሌማት ትሩፋት ዘመቻችን ሌላኛው ግብ ነው።

★ ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ የምግብ ስርአት መዘርጋት።

እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ወተት፣ማር፣እንቁላል እና ስጋ በቀላሉ ሊያገኘው የሚገባ የምግብ አማራጭ መሆን እንዳለበት ፓርቲያችን በፅኑ ያምናል።ሌሎች የምግብ አማራጮች ተደራሽ በሆኑበት ልክ እነኚህም ምርቶች በቀላሉ ሊገኙ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።ለዚህም እልፍ አእላፍ የሆነውን በሀገራችን ውስጥ ያለውን ሀብት በቴክኖሎጂ በማዳበር ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ የሆነ የምግብ ስርአት መዘርጋት ይኖርብናል።

Address

Dessie

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mekaneselam womans legue offeice posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share