ኑሩ አሊ /Nuru Ali

ኑሩ አሊ /Nuru Ali Ethiopia Wollo

14/05/2026

የባሕር በራችን፦ የተቀማው ትርታችን እና የትውልዱ ትንሣኤ
***********************

ኢትዮጵያ የቀይ ባሕር ሥልጣኔ ባለቤትና ታላቅ የባሕር ኃይል እንደነበረች ያውቃሉ? የአክሱም ግዛት በዓለም ካሉ አራት ታላላቅ ኃይሎች አንዱ ሊሆን የቻለው የባሕር ንግድ መስመሮችን በበላይነት በመቆጣጠሩና የአዱሊስ ወደብ የዓለም የንግድ ትርታ በመሆኗ ነበር። ሆኖም ይህ ታሪካዊ ጸጋችን በቅኝ ገዥዎች ሴራና በታሪካዊ ስህተቶች ምክንያት ተነጥቆ፣ ዛሬ አገራችን በዓለማችን ትልቋ የየብስ ተከል አገር እንድትሆን ተፈርዶባታል።

ይህ የባሕር በር አልባነት በኢኮኖሚያችን ላይ እያደረሰ ያለው ኪሳራስ ምን ያህል ዘግናኝ እንደሆነ ያውቃሉ? ጥናቶች እንደሚያሳዩት ኢትዮጵያ በየዓመቱ እስከ 31 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ታጣለች። ይህ ማለት ለወደብ ኪራይና ለሎጂስቲክስ ወጪ ብቻ የምንገብረው ሀብት ለትምህርት፣ ለጤና እና ለልማት መዋል የነበረበትን ግዙፍ አቅም ገደል እየከተተው ይገኛል።

የባሕር በር ጥያቄያችን የፖለቲካ ፍላጎት ሳይሆን የ130 ሚሊዮን ሕዝብ የህልውና እና የክብር ጥያቄ ነው! አዲሱ ትውልድ ይህንን ታሪካዊ ኢ-ፍትሃዊነት ለመቀየርና የአባቶቹን የባሕር ኃይል ክብር ለመመለስ ቆርጦ ተነስቷል።

ከአክሱም ሥልጣኔ እስከ ዛሬው የኢኮኖሚ እስራት፣ ከታሪካዊ ሴራዎች እስከ ትውልዱ ትንሣኤ ድረስ ያለውን ጥልቅ ትንተና እና አስደንጋጭ አሃዞችን የያዘውን ሙሉ ጽሑፍ ከታች ባለው ሊንክ ገብተው ያንብቡ።

14/05/2026
29/03/2026

ከመገለል ወደ ማዕከልነት፡ የመጋቢት ለውጥ እና የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ አካታችነት አዲስ ምዕራፍ
*****************************

የመጋቢት 2010 ዓ.ም ለውጥ በኢትዮጵያ ዘመናዊ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ቀደም ሲል የነበረውን የተገደበ እና የተወሰኑ ቡድኖች ብቻ የበላይ የሆኑበትን ሥርዓት በመቀየር ረገድ ትልቅ የታሪክ ምዕራፍ ሆኖ ይመዘገባል።

ይህ ለውጥ በተለይ ላለፉት ሦስት አሥርተ ዓመታት "አጋር" በሚል መጠሪያ ከማዕከላዊ የውሳኔ ሰጪነት ሚና ተገልለው የነበሩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ወደ መሐል ያመጣበት ሂደት ዋና መገለጫው ነው።

ቀደም ሲል በነበረው የኢሕአዴግ አወቃቀር ውስጥ አራቱ አባል ድርጅቶች ብቻ የሀገራችንን ዕጣ ፈንታ የሚወስኑበት ሲሆን ፤ እንደ ሶማሌ፣ አፋር፣ ቤንሻንጉል-ጉሙዝ፣ ጋምቤላ እና ሐረሪ ያሉ ክልሎች በሞግዚትነት የሚመሩበት ሥርዓት ሰፍኖ ቆይቷል።

ይህ አሠራር በክልሎቹ ሕዝቦች ዘንድ የሁለተኛ ዜግነት ስሜት በመፍጠር ለሀገራዊ አንድነት መላላት ምክንያት ሆኖ የቆየ ቢሆንም፣ ከለውጡ ማግስት ይህ ታሪካዊ አድልዎ በውህደት ተቀይሯል።

የቀድሞ "አጋር" ክልል ተወካዮች በከፍተኛ የሥልጣን እርከን ማለትም በሥራ አስፈፃሚ እና በማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ እኩል ውክልና እንዲኖራቸው በማድረግ የክልሎችን እኩልነት በተግባር ተረጋግጧል።

ከዚህም ጎን ለጎን በስደት የነበሩ የፖለቲካ ኃይሎች ወደ ሀገር ቤት ገብተው በሰላማዊ መንገድ እንዲታገሉ መደረጉ ለአንድ ፓርቲ የበላይነት ስርዓት ማብቃት ትልቅ መሠረት ጥሏል።

ምንም እንኳ የፖለቲካ ባህላችንን ከእልህ ወደ ውይይት የመቀየር ጉዞ አሁንም ፈተናዎች ቢገጥሙትም፣ የመጋቢት ለውጥ ያስገኘው ፖለቲካዊ አካታችነት ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ታሪካዊ መነሻ ነው።

ይህንን ዕድል ለዘላቂ ሰላም ማዋል የሁሉም ፖለቲካዊ ተዋናዮች የጋራ ኃላፊነት መሆኑን መገንዘብ ይገባል።

በለሚ ታደሰ

ሙሉ መረጃውን በአስተያየት መስጫው ያገኙታል! 🔗

በደቡብ ወሎ ዞን አልብኮ ወረዳ የማገኘው የደጋጋ የመጀመሪያ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል።ግንባታው መማሪያ ክፍሎች፣የአስተዳደርና የመጸዳጃ ቤትን ያካትታል።
29/03/2026

በደቡብ ወሎ ዞን አልብኮ ወረዳ የማገኘው የደጋጋ የመጀመሪያ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል።ግንባታው መማሪያ ክፍሎች፣የአስተዳደርና የመጸዳጃ ቤትን ያካትታል።

10/03/2026
👉አድዋ የጥቁር ህዝቦች ኩራት👉አድዋ የአንድነት ምልክት👉አድዋ የይቻላል መንፈስ ነፀብራቅ
01/03/2026

👉አድዋ የጥቁር ህዝቦች ኩራት
👉አድዋ የአንድነት ምልክት
👉አድዋ የይቻላል መንፈስ ነፀብራቅ

"ይህ 2026 እንጂ 1946 አይደለም፤ አፍሪካ በጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ ሊኖራት ይገባል" - አንቶኒዮ ጉቴሬዝ*******************የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ዋና...
14/02/2026

"ይህ 2026 እንጂ 1946 አይደለም፤ አፍሪካ በጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ ሊኖራት ይገባል" - አንቶኒዮ ጉቴሬዝ
*******************

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በ39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ አፍሪካ በተመድ ውስጥ በሁሉም እንቅስቃሴዎች ቀዳሚ ተሳታፊ እንደምትሆን ገለጹ።

ዋና ጸሐፊው በ39ኛው የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ "እስከ ሥልጣን ዘመኔ መጨረሻ ድረስ አፍሪካ በተመድ ውስጥ ያላት ሚና ከቀዳሚዎቹ ተርታ እንዲሰለፍና በሁለቱ ተቋማት መካከል ያለው አጋርነት ከምንጊዜውም በላይ እንዲጠነክር ለመስራት ቃል እገባለሁ" ብለዋል።

የአፍሪካ ኅብረት የቅኝ ግዛት ትግሎችን በጋራ ከመምራት ጀምሮ "ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ" በሚል መርህ እስከ ዛሬ የዘለቀ ተቋም መሆኑን ዋና ጸሐፊው አውስተዋል።

ይሁን እንጂ በሱዳን፣ በዲሞክራቲክ ኮንጎ እና በአንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት የሚታየውን አለመረጋጋት ለመፍታት ኅብረቱ በትኩረት እንዲሰራ አሳስበዋል።

የአየር ንብረት ለውጥን ተጽዕኖ ለመቋቋም ሀገራት የታዳሽ ኃይል አማራጮችን እንዲጠቀሙ ኅብረቱ ማበረታታት እንዳለበትም ጠቁመዋል፡፡

"ይህ 2026 እንጂ 1946 አይደለም፤ በመሆኑም አፍሪካ በተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ ሊኖራት ይገባል" ሲሉም አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ንግግራቸውን አጠቃለዋል።

በሀብተሚካኤል ክፍሉ

Address

Dessie

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኑሩ አሊ /Nuru Ali posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category