Dessie Bunbua wuha subcity communication/ደሴ ቧንቧውሀ ክፍለከተማ ኮሙኒኬሽን

  • Home
  • Ethiopia
  • Dessie
  • Dessie Bunbua wuha subcity communication/ደሴ ቧንቧውሀ ክፍለከተማ ኮሙኒኬሽን

Dessie Bunbua wuha subcity communication/ደሴ ቧንቧውሀ ክፍለከተማ ኮሙኒኬሽን bast info

03/09/2026
01/09/2026
በደሴ ከተማ የቧንቧ ውሃ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት፣ «ውጫዊ የወረራ ስጋትንና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማት እናረጋግጣለን» በሚል መሪ ...
24/08/2026

በደሴ ከተማ የቧንቧ ውሃ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት፣ «ውጫዊ የወረራ ስጋትንና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማት እናረጋግጣለን» በሚል መሪ ሀሳብ ጠቅላላ የመንግስት ሰራተኞች የውይይት መድረክ ተካሄደ።

ቧንቧ ውሃ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን
ነሐሴ 18/12/2018 ዓ.ም

በመድረኩ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር በማድረግ መድረኩን ያስጀመሩት የቧንቧ ውሃ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ኑሩ ይማም ሲሆኑ በንግግራቸው የዛሬው የውይይት መድረክ በሀገራችን ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤያችንን የምናሳድግበት፣ የጋራ ኃላፊነታችንን የምናጠናክርበትና ለሰላምና ለልማት ያለንን ቁርጠኝነት የምናረጋግጥበት እና ሀገራችን በልማትና በእድገት ጉዞዋ ውስጥ እያለች ከውጭ ሊመጡ የሚችሉ የወረራ ስጋቶችንም ሆነ ከውስጥ በፅንፈኝነት ሊነሱ የሚችሉ አደጋዎችን በጥንቃቄ መመልከትና በአንድነት መመከት ይገባናል ብለዋል።

በመድረኩም የሀገራችንን ሰላም፣ ሉዓላዊነትና የልማት ጉዞ ሊፈታተኑ የሚችሉ ውጫዊ የወረራ ስጋቶችንና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋዎችን በመመከት፣ የሰላምና የልማት መስፈርቶችን በማጠናከር ዙሪያ ሰፊና ገንቢ ውይይት ተካሂዷል።
በውይይቱ ሀገራዊ ሰላምንና ሉዓላዊነትን ማስጠበቅ የሁሉም ዜጋ የጋራ ኃላፊነት መሆኑ በመገንዘብ፣ ከፅንፈኝነትና ከሌሎች የሰላም ጠንቆች በመራቅ ለዘላቂ ሰላም፣ ልማትና ብልፅግና በትብብር መስራት እንደሚገባ ትኩረት ተሰጥቷል።
የውይይት መድረኩም ሰራተኞች በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ግንዛቤ በማሳደግ፣ ለሀገር ሰላምና ልማት ያላቸውን የጋራ ኃላፊነት ለማጠናከር ጠቃሚ መድረክ ሆኗል።

በመድረኩ ላይ የክፍለ ከተማው የከተማ ደጋፊ አመራሮች፤የክፍለ ከተማው ጠቅላላ አመራሮች ፤የቀበሌ አመራሮች እና ጠቅላላ የመንግስት ሰራተኞች ተገኝተውበታል።

የቧንቧ ውሃ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የጠቅላላ አመራርና መንግስት ሰራተኞች ከ90ቀናት ዕቅድ የአንድ ወር አፈጻጸም ግምገማ መድረክ አካሄደ።ቧንቧ ውሃ ክፍለ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ነሐሴ 08/12/...
14/08/2026

የቧንቧ ውሃ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የጠቅላላ አመራርና መንግስት ሰራተኞች ከ90ቀናት ዕቅድ የአንድ ወር አፈጻጸም ግምገማ መድረክ አካሄደ።

ቧንቧ ውሃ ክፍለ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን
ነሐሴ 08/12/2018 ዓ.ም

የቧንቧ ውሃ ክፍለ ከተማ አጠቃላይ ጽ/ቤቶች የአንድ ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በክፍለ ከተማው ፕላንና ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አብዱከሪም የሱፍ ቀርቧል። በቀረበው ሪፖርት ላይ ሰፊ ውይይት የተካሄደ ሲሆን ከሪፖርቱ በመነሳት የተሰሩ ስራዎች በጥልቀት ተገምግመዋል።
በአንድ ወር ውስጥ የተሰሩ መልካም ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ቀሪ ያልተፈፀሙ ተግባራት ላይም በትኩረት እንዲሰሩ እና በተለይ በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ሁሉም ሴክተር ቁልፍ ተግባር በማድረግ በመስራት ለቀጣይ የተሻለ አፈጻጸም መምጣት እንዳለበት መድረኩን የመሩት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ኑሩ ይማም እና የክፍለ ከተማው ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አይተነው መከተ አሳስበዋል።

የቧንቧ ውሃ ክፍለ ከተማ ሚሊሻ ጽ/ቤት በክረምት በጎ ፈቃድ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።ቧንቧ ውሃ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ነሐሴ 08/12/2018 ዓ.ምየክፍለ ከተማው ማሊሻ ጽ/ቤት ለደ...
14/08/2026

የቧንቧ ውሃ ክፍለ ከተማ ሚሊሻ ጽ/ቤት በክረምት በጎ ፈቃድ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

ቧንቧ ውሃ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን
ነሐሴ 08/12/2018 ዓ.ም

የክፍለ ከተማው ማሊሻ ጽ/ቤት ለደጀን ሀይል ለተሰማራው ሰላም አስከባሪ ቤተሰቦች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።ድጋፉ ከአስተዳደር ጽ/ቤት እና ከሁሉም ቀበሌዎች የተገኘ ሲሆን የክፍለ ከተማው አስተዳደር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ማርቆስ መልኬ እና የክፍለ ከተማው ሚሊሻ ጸ/ቤት ሀላፊ አቶ ሀይሉ አስማረ በጋራ ለቤተሰቦች አስረክበዋል።

የቧንቧ ውሃ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት በክረምት በጎ ፈቃድ የአልባሳት ድጋፍ አደረገ።      ድጋፉን ያስረከቡት የክፍለ ከተማው ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አይተነው መ...
09/08/2026

የቧንቧ ውሃ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት በክረምት በጎ ፈቃድ የአልባሳት ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉን ያስረከቡት የክፍለ ከተማው ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አይተነው መከተ ፣ የማህበራዊ ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሰይድ እንድሪስ ፣የአስተዳደር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ማርቆስ መልኬ እና የጽ/ቤቱ ሰራተኞች በተገኙበት ነው።

ቧንቧ ውሃ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን
ነሐሴ 03/12/018 ዓ.ም

Address

Dessie
Dessie

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dessie Bunbua wuha subcity communication/ደሴ ቧንቧውሀ ክፍለከተማ ኮሙኒኬሽን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share