Dessie PP Youth Wing

Dessie PP Youth Wing የደሴ ከተማ ብልፅግና ፖርቲ ወጣቶች ክንፍ የወጣቶች ፓለቲካዊ:ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንሰራለን!

02/09/2026
ውጫዊ የወረራ ስጋት እና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማትን እናረጋግጣለን! »​በደሴ ከተማ በሁሉም ቀበሌዎች «ውጫዊ የወረራ ስጋትን እና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋ...
02/09/2026

ውጫዊ የወረራ ስጋት እና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማትን እናረጋግጣለን! »

​በደሴ ከተማ በሁሉም ቀበሌዎች «ውጫዊ የወረራ ስጋትን እና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማትን እናረጋግጣለን!» በሚል መሪ ቃል ከወጣቶችና ከሴቶች ጋር የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

​ ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት በማጠናከር የውጭና የውስጥ ወራሪዎችን እንዲሁም የፅንፈኛ ቡድኖችን እኩይ አላማና እንቅስቅሴ በፅናት ለመታገል የወጣቶችና የሴቶች ሚና የጎላ መሆኑ ተመላክቷል።

የደሴ ከተማንና የክልሉን ዘላቂ ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ የሚደረጉ ጥረቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል አስፈላጊ መሆኑም በመድረኮቹ ተገልጿል።

ተሳታፊ ወጣቶችና ሴቶች በበኩላቸው የከተማዋንና የሀገራቸውን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ የፅንፈኝነት አደጋዎችን ለማክሸፍና የህዝቡን አንድነት ለማጠናከር የበኩላቸውን ሀገራዊ ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

31/08/2026
በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ!» በሚል መሪ ቃል የደሴ ከተማ ወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቀደኛ ወጣቶች በሀይቅ ከተማ በመገኘት ዘርፈ ብዙ የበጎ አድራጎት ተግባራት አከናውነዋል።​በመርሀ ግብሩ ከተከናወኑ...
20/08/2026

በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ!» በሚል መሪ ቃል የደሴ ከተማ ወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቀደኛ ወጣቶች በሀይቅ ከተማ በመገኘት ዘርፈ ብዙ የበጎ አድራጎት ተግባራት አከናውነዋል።

​በመርሀ ግብሩ ከተከናወኑት አበይት ተግባራት መካከል ​የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር፣ የጽዳት ዘመቻና ​ የአዲሱን የትምህርት ዘመን ምክንያት በማድረግ አቅም ደካማ ለሆኑ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁሶችን በማስረከብ ለነገ ሀገር ተረካቢዎችን ወገንተኝነት አሳይተዋል።

​ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በወሰን ወይም በአካባቢ የማይወሰን የጋራ እሴታችን መሆኑ ተገልጿል።

ይህ ተግባር በወጣቶች መካከል የመረዳዳት፣ የትብብር እና የእህትማማችነት/ወንድማማችነት ባህልን በፅኑ የሚያጎለብት መሆኑም ተመላክቷል።

​ይህ የደሴ ከተማ ወጣቶች በጎ አድራጎት ከአንድ ከተማ አልፎ በዙሪያው ባሉ አካባቢዎች ሁሉ ፍቅርንና አንድነትን መዝራት እንደሚቻል ማሳያ ሲሆን፣ የመደጋገፍና አብሮ የመስራት አገራዊ እሴትን በተግባር ያሳየ ሞዴል ተግባር እንደሆነ ተገልጿል።

የደሴ ከተማ ሴቶች፣ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ የሀይቅ ከተማ አስተዳደር ላደረገለት ደማቅ አቀባበል ምስጋና አቅርቧል

በደሴ ከተማ በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከተያዘው ዕቅድ እስከአሁን  ውጤታማ ሥራ መከናወኑን የክልሉ ሱፐርቪዥን ቡድን ገለጸ​በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የክረምት የበጎ ፈቃድ አገል...
07/08/2026

በደሴ ከተማ በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከተያዘው ዕቅድ እስከአሁን ውጤታማ ሥራ መከናወኑን የክልሉ ሱፐርቪዥን ቡድን ገለጸ

​በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሱፐርቪዥን ቡድን በደሴ ከተማ አስተዳደር ያደረገውን የመስክ ምልከታ በማጠናቀቅ ከከተማው አስተባባሪ ስቲሪንግ ኮሚቴ ጋር የማጠቃለያ መድረክ አካሂዷል።

​ቡድኑ እስከ ሃምሌ 29/2018 ዓ.ም ድረስ የተከናወኑ የበጎ ፈቃድ ሥራዎችን አፈጻጸም በዝርዝር የገመገመ ሲሆን፣ በበጀት ዓመቱ በተለዩት 17ቱም የክረምት የተግባር መስኮች ከተጠበቀው በላይ የተሻለና አበረታች ሥራ መከናወኑን አረጋግጧል።

​በዘንድሮው የክረምት ወራት የዜጎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎች ማሳተፍ ተችሏል።

ይህም የበጎ ፈቃድ ባህልን በማህበረሰቡ ዘንድ የበለጠ ለማስረጽና የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል።

​የሱፐርቪዥን ቡድኑ በምልከታው ያረጋገጣቸውን ዋና ዋና ስኬቶችና የትኩረት አቅጣጫዎች ​የ17ቱ ተግባራት አፈጻጸም፡ ከአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ እስከ አቅመ-ደካሞች ቤት እድሳት፣ የደም ልገሳ፣ ማህበራዊ ድጋፍና የትምህርት ቁሳቁስ ማሰባሰብ ባሉት ሙሉ 17ቱ የተግባር መስኮች የተቀናጀና ውጤታማ እንቅስቃሴ ተደርጓል።

​የህዝብ ተሳትፎና ባለቤትነት ህብረተሰቡ በገንዘብ፣ በጉልበትና በእውቀቱ ያደረገው ንቁ ተሳትፎ ለስራው ስኬታማነት ዋና ምክንያት መሆኑ ተጠቅሷል።

​በየደረጃው ያሉ የአመራር አካላትና የስትሪንግ ኮሚቴው ያደረጉት ቅርብ ክትትልና ድጋፍ በስራው ላይ ግልጽ ለውጥ ማምጣቱ ተመላክቷል።

​በመድረኩ ማጠቃለያ የደሴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሸናፊ ዓለማየሁ እንደገለፁት ያሉት ጥንካሬዎችን በማስቀጠል ከተሰጡት ግብረ-መልሶች በመነሳት የቀሩትን የክረምት ወራት ተግባራት በተመሳሳይ ትጋትና ጥራት በማጠናቀቅ የታቀዱትን ግቦች ሙሉ በሙሉ ለማሳካት ከተማ አስተዳደሩ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።

ተስፋን እንትከል !🌴በደሴ ከተማ አስተዳደር "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ መልዕክት የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ የንቅናቄ መርሀ ግብር በመንበረ ፀሐይ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ተ...
03/08/2026

ተስፋን እንትከል !🌴

በደሴ ከተማ አስተዳደር "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ መልዕክት የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ የንቅናቄ መርሀ ግብር በመንበረ ፀሐይ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ተጀምሯል።

በአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላው በከተማው ባሉ ቀበሌዎች በሙሉ በ92 ሄክታር መሬት ላይ 359 ሺህ ችግኞች ይተከላል ተብሏል።


የደሴ ከተማ በጎፈቃድ ወጣቶች በመናፈሻ ክፍለ ከተማ የተለያዩ የተፈጥሮ ሀብት ስራውችን አከናወኑ። በደሴ ከተማ አስተዳር የሚገኙ በጎፈቃድ ሰጭ ወጣቶችም በመናፈሻ ክፍለከተማ በተዘጋጀው የችግኝ...
01/08/2026

የደሴ ከተማ በጎፈቃድ ወጣቶች በመናፈሻ ክፍለ ከተማ የተለያዩ የተፈጥሮ ሀብት ስራውችን አከናወኑ።

በደሴ ከተማ አስተዳር የሚገኙ በጎፈቃድ ሰጭ ወጣቶችም በመናፈሻ ክፍለከተማ በተዘጋጀው የችግኝ መትከያ ቦታ ላይ የችግኝ ጉድጓድ ቁፋሮ እና የአፈር እቀባ ስራ በስፋት ተከናውኗል።

የሰላም ሚኒስቴር በደሴ ከተማ ለበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ስልጠና ሰጠ።የሰላም ሚኒስቴር ከደሴ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር የክረምት የሰላም በጎ ፈቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራምን በስልጠ...
29/07/2026

የሰላም ሚኒስቴር በደሴ ከተማ ለበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ስልጠና ሰጠ።

የሰላም ሚኒስቴር ከደሴ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር የክረምት የሰላም በጎ ፈቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራምን በስልጠና መርሃ ግብር ጀምሯል።

ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የደሴ ከተማ ሴቶች፣ ወጣቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሪት ትእግስት አበበ ሲሆኑ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የበጎ ፈቃድ ስራ በሀገራችን ዘላቂ ባህል ሆኖ ሲተገበር እንደቆየ አስታውሰዋል።

ወ/ሪት ትእግስት አክለው፣ የተዘጋጀው የበጎ ፈቃድ የስልጠና መድረክ በርካታ ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመርዳት በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ተግባሩን በባለቤትነት እንዲይዙ በቂ ግንዛቤ ለማስጨበጥ እንደሆነ ገልጸዋል።

ስልጠናውን የሰጡት የሰላም ሚኒስተር የክረምት በጎ ፈቃድ አስተባባሪ አቶ ገዛኸኝ ጨናሶ የስልጠናው አላማ ወጣቶችን በማሳተፍ የማህበረሰብ ተሳትፎ በጎላ መልኩ በማስተሳሰር ሀገራዊ እድገት ላይ አሻራ ለማስቀመጥና ሰላም እንዲረጋገጥ ለማድረግ መሆኑን ጠቁመዋል።

በሰጡት ስልጠናም የበጎ ፈቃድ ጽንሰ ሃሳብ፣ ታሪካዊ ዳራው፣ መርሆዎች፣ የበጎ ፈቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት አይነቶች፣ የሚያስፈልጉ ክህሎቶች፣ ጠቀሜታና ተያያዥ ርእሶችን ዳሰዋል።

ሰልጣኝ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በሰጡት አስተያየት የበጎ ፈቃድ ስራ ለህሊናም ከፍተኛ እርካታ የሚሰጥ በመሆኑ ያላቸውን አቅም አሟጠው ግቡን ለማሳካት እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል።

መርሃ ግብሩ ወጣቶችን ለማበረታታት እና የማህበረሰብ አገልግሎትን ወደ ተግባራዊ እርምጃዎች ለመቀየር ያለመ ውጤታማ ጅምር ነው።

በስልጠና መድረኩ የከተማና የክፍለ ከተማ የሴትና ወጣት ክንፍ አመራሮች ተሳትፈዋል።

"በሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ የተቀመጡ መንትያ ግቦች እንዲሳኩ የወጣቶችና ሴቶች ሚና የአንባሳውን ድርሻ ይወስዳል"- አዝመራ ማስረሻየደሴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶችና የሴቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤ...
02/07/2026

"በሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ የተቀመጡ መንትያ ግቦች እንዲሳኩ የወጣቶችና ሴቶች ሚና የአንባሳውን ድርሻ ይወስዳል"- አዝመራ ማስረሻ

የደሴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶችና የሴቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማና በ7ኛው ምርጫ አስታዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የምስጋናና የእውቅና መርሀ-ግብር አካሂዷል።

በመድረኩ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የደሴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አዝመራ ማስረሻ በ2018 በጀት ዓመት ወጣቶችና ሴቶችን በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና በፖለቲካዊ ተሳትፎ ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልፀዋል።

የከተማችን ወጣቶችና ሴቶች የሰባተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ጉልህ አሻራቸውን በማሳረፍ ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሂደቱ የድርሻቸውን መወጣታቸውን የጠቆሙት ወ/ሮ አዝመራ በቅድመ ምርጫው የተቀመጡ መንታ ግቦች እንዲሳኩ የአንባሳውን ድርሻ ይወስዳሉ ብለዋል ።

የደሴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ወጣት አክሊሉ ሰለሞን በምርጫው ሂደት ወጣቶች ለሰላም፣ ለልማትና ለዴሞክራሲ እሴቶች መጎልበት ያሳዩት አንፀባራቂ ተሳትፎ ለቀጣይ የፖለቲካ ተሳትፎአቸው ትልቅ መነሳሳት መፍጠሩን ገልፀዋል።

ወጣቶችና ሴቶች በሰባተኛው ምርጫ ሀገር እንድትቀጥል የሚያስችል አኩሪ ተግባር ማከናወናቸውንም ገልፀዋል።

የደሴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ ቅ/ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ አብዮት ጋሻው የሴቶች ክንፍ አባላት ለላቀ ውጤት በትብብርና በአንድነት መስራታቸውን ሊያጠናክሩ እንደሚገባ አሳስበው የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተቀመጡ ዕቅዶችን በአዲሱ በጀት ዓመትም አልቆ መተግበር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በበጀት ዓመቱ የሴቶችን ሁለንተናዊ አቅም ለማጠናከር የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት መከናወናቸውንም አስረድተዋል፡

የደሴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ ቅ/ ጽ/ቤት ም/ኃላፊ ወ/ሮ ዙፋን ወልዴ የ2018 በጀት ዓመት እቅድና ሰባተኛውን ሀገራዊ ምርጫ አፈፃፀም አቅርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

በመጨረሻም በሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ስኬት ጉልህ አስተዋጽዖ ላበረከቱ ወጣቶችና ለሴቶች አደረጃጀቶች የምስጋናና የእውቅና መርሀ-ግብር ተካሂዷል።

በመድረኩ የደሴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አዝመራ ማስረሻ፣ የደሴ ከተማ ሴቶች፣ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሪት ትዕግስት አበበ ፣የክፍለ ከተማ የሴትና የወጣት ክንፍ ኃላፊዎች፣ የክፍለ ከተማ የወጣትና የሴት ክንፍ ስራ አስፈፃሚዎች፣የወጣትና የሴት ማህበር፣ፌደሬሽኖችና ልዩ ልዩ አደረጃጀቶች ተሳትፈዋል።

27/06/2026

Address

Dessie

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dessie PP Youth Wing posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share