Amhara Sayint woreda Communication Affairs/አምሐራ ሳይንት ወረዳ ኮሙኒኬሽን

  • Home
  • Ethiopia
  • Dessie
  • Amhara Sayint woreda Communication Affairs/አምሐራ ሳይንት ወረዳ ኮሙኒኬሽን

Amhara Sayint woreda Communication Affairs/አምሐራ ሳይንት ወረዳ ኮሙኒኬሽን ወረዳው ከባህር ወለል በላይ ከ596 እስከ 4247 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝ ሲሆን በአባዛኛው ወጣ ገባና በፕላቶ መሬት የተከበበ ነው፡፡

በሚቀጥሉት አስር ቀናት ለዝናብ መፈጠር ምቹ የአየር ሁኔታ እንደሚኖር ይጠበቃል።ከምስራቅ አማራ ሜትሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በሚቀጥሉት አስር ቀናት ለዝናብ መ...
01/09/2026

በሚቀጥሉት አስር ቀናት ለዝናብ መፈጠር ምቹ የአየር ሁኔታ እንደሚኖር ይጠበቃል።

ከምስራቅ አማራ ሜትሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በሚቀጥሉት አስር ቀናት ለዝናብ መፈጠር ምቹ የአየር ሁኔታ ይኖራል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአብዛሀኛው የምስራቅ አማራ አካባቢዎች አልፎ አልፎ ባሉት ቀናት ቀላል መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ ይጠበቃል።

በተወሰኑ የምስራቅ አማራ አካባቢዎች ደግሞ እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ በተመሳሳይ የትንበያ መረጃዎች ያመለክታሉ።

በእድገት ላይ ለሚገኙ ሰብሎች ለረዥም ጊዜ ቋሚ ሰብሎች ፣ ለእስሳት የግጦሽ ሳር ልምላሜ፣ ለከርሰ ምድር እና ገፀ ምድር ውሀ የራሱ የሆነ አስተዋጽኦም አለው።

አርሶአደሩ እና በግብርናው ዘርፍ የሚሰሩ አካላት እርጥበት አጠር በሆኑ አካባቢዎች ውሀን ለማከማቸት የሚጠቀሙበት ጊዜ በመሆኑ አስቀድመው የወትሮው ዝግጁነት እንዲኖራቸው ተጠቁሟል።

መረጃው ደሴ ፋና ኤፍ ኤም 96.0 የተወሰደ ነው።

የሕዝብን የላቀ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ባደረጉት የማይናወጥ ትጋትና የላቀ የሕዝብ ወገንተኝነት፣ የደቡብ ወሎ ዞን እንቁ ከፍተኛ መሪዎች እንዲህ በደስታና በሐሴት ደምቀዋል።በየደረጃው የሚገኘውን...
01/09/2026

የሕዝብን የላቀ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ባደረጉት የማይናወጥ ትጋትና የላቀ የሕዝብ ወገንተኝነት፣ የደቡብ ወሎ ዞን እንቁ ከፍተኛ መሪዎች እንዲህ በደስታና በሐሴት ደምቀዋል።

በየደረጃው የሚገኘውን የፖለቲካና የፀጥታ አመራር፣ ባለሙያዎችንና መላውን ሕዝብ በቅንጅትና በከፍተኛ ንቅናቄ በማስተባበር የተመዘገበው ይህ የላቀ ውጤት፣ ዞኑን በወጥ አፈጻጸም ላለፉት ሁለት ተከታታይ ዓመታት በአማራ ክልል ግንባር ቀደም ተሸላሚ አድርጎታል።

ይህ በደስታ ድምቀት የታጀበው ታሪካዊ ስኬት፣ የጋራ ጥረትና የሕዝብ ቁርጠኝነት ያመጣው የድል ፍሬ ነው።

ደቡብ ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን

01/09/2026
የድል ሐሴት ለነገው ከፍታ፡ ለደቡብ ወሎ ህዝብና አጠቃላይ አመራር የተላለፈ የምስጋና መልዕክት​​በ2018 በጀት ዓመት የፓርቲና የመንግሥት ሥራዎች አፈጻጸም ከመላው የአማራ ክልል ዞኖች በመጀ...
01/09/2026

የድል ሐሴት ለነገው ከፍታ፡ ለደቡብ ወሎ ህዝብና አጠቃላይ አመራር የተላለፈ የምስጋና መልዕክት

​በ2018 በጀት ዓመት የፓርቲና የመንግሥት ሥራዎች አፈጻጸም ከመላው የአማራ ክልል ዞኖች በመጀመሪያ ደረጃ ማጠናቀቃችንን ስገልጽ በታላቅ ኩራትና በልዩ ስሜት ነው። ይህ ድል በአጋጣሚ የተገኘ አይደለም፤ የጋራ ትጋታችን፣ የጸና ርምጃችን እና የህዝባችንን አደራ በታማኝነት የመወጣታችን ፍሬ ነው።

ታሪክን በሥራ የሚቀይረው ህዝባችን፤ ለተከበራችሁ የዞናችን አርሶ አደሮች፣ ሴቶች፣ወጣቶች እና ባለሀብቶች እና አጠቃላይ የህብረተሰብ ክፍሎች፤ በፈተናዎች መሀል ጸንታችሁ ከጎናችን በመቆማችሁ ዛሬ ይህንን ታሪክ መጻፍ ችለናል። ስኬቱ የሁላችንም የድካም ውጤት ነው።

የህዝብ አደራን በብቃት የተወጣችሁ አገልጋዮች፤ ቀንና ማታ ሳይበገሩ ለህዝብ ማገልገል የመረጣችሁ የፓርቲ እና የመንግስት አመራሮች፣የጸጥታ መዋቅር፣ ባለሙያዎችና ሠራተኞች፤ የሰራችሁት አርዓያነት ያለው ተግባር የሚመሰገን ነው።
​ይህ ያመጣነው አንደኛ ደረጃ የጉዞ ማጠናቀቂያ ሳይሆን፣ ለቀጣዩ በጀት ዓመት የላቀ ከፍታ መነሻ መሰረታችን ነው።

ድሉ የመጨረሻው መስመር አይደለም፤ ይልቁንም ለሚቀጥለው ዓመት የላቀ ስኬት ማሻገርያ ደረጃችን ነው። የታሪክ ባለቤቶች እንደ መሆናችን መጠን፣ በቀጣዩ በጀት ዓመትም የላቀ ቁርጠኝነትን ይዘን በመነሳት፣ የዞኑን ታላቅነት በሁሉንም መስክ አሁንም እናስቀጥላለን።

​በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ!

​አቶ አሊ መኮንን
የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ

 #የቅጥር ማስታወቂያ  #አወጣጥከደቡብ ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን የተወሰደ
01/09/2026

#የቅጥር ማስታወቂያ #አወጣጥ

ከደቡብ ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን የተወሰደ

30/08/2026

ማስታወቂያ
በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመማር ለተመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ።

ትምህርት ሚኒስቴር ለ2019 የትምህርት ዘመን ትምህርት በሚሰጥባቸው ነባርና አዲስ የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች በ9ኛ እና 10ኛ ክፍል ተማሪዎችን አወዳድሮ ለመቀበል ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት ተመዝግባችሁ በመጠባበቅ ላይ ያላችሁና ለፈተና የተመረጣችሁ ተማሪዎች በተመዘገባችሁበት ሊንክ መለያ ኮዳችሁን ( Reference Number) በማስገባት ማየት የምትችሉ መሆኑ እንገልጻለን።

በተጨማሪም ለፈተና የተመረጣችሁ ተማሪዎች ፈተና የሚሰጠው በበየነ መረብ (online) ስለሆነ የሚቀርባችሁን የፈተና መስጫ ማዕከል በዛው ሊንክ በመግባት መምረጥ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የሙከራ ፈተና እሮብ ነሃሴ 27/2018 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን ዋና ፈተናው ነሃሴ 28/2018 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑ አውቃችሁ ዝግጅት እንድታደርጉ ለማሳሰብ እንወዳለን።

የወባ በሽታን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት  ማህበረሰቡ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ የአማራ ሳይንት ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት ጥሪ አቀረበ።    ነሐሴ  24 ቀን 2018 ዓ.ም (የአማራ ሳይንት...
30/08/2026

የወባ በሽታን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ማህበረሰቡ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ የአማራ ሳይንት ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት ጥሪ አቀረበ።

ነሐሴ 24 ቀን 2018 ዓ.ም (የአማራ ሳይንት ወረዳ ኮሙኒኬሽን)

በአማራ ሳይንት ወረዳ የወባ በሽታን ለመከላከል በሁሉም አካባቢዎች የአከባቢ ቁጥጥርና የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎች በሥፋት እየተሰሩ እንደሚገኙ ተገልጿል።

ከወረዳው ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የወባ በሽታ ስርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ሲሆነ በሽታውን ለመከላከል ከምንጊዜውም በላይ የአካባቢ ቁጥጥርና ክትትል ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ።

ከክረምት ወቅት ጋር ተያይዞ ለወባ መራቢያ ምቹ የሆኑ አካባቢዎችና የኩሬ ውሃዎችን የማፋሰስ፣የማዳፈን፣የመረበሽና የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎች በስፋት እየተሰሩ ይገኛሉ።

ይሁን እንጂ እነዚህን ተግባራት ውጤታማ ለማድረግና የበሽታውን ስርጭት ለመቀነስ የማህበረሰቡ ተሳትፎ አስፈላጊ እነደሆነ ነው ጽ/ቤቱ የገለፀው።

እናም አሁን ላይ ያለንበት ወቅት ለወባ ወረርሽኝ መከሰትና መስፋፋት ምቹ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን በሚከናወኑ የቅድመ መከላከል ስራዎች ላይ ህብረተሰቡ እንዲሳተፍ ጥሪ ቀርቧል።

በቀጣይ የጤና ባለሙያዎችን ምክርና የመከላከያ መንገዶችን በመተግበር አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራስን ከወባ በሽታ መጠበቅ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

‎በወረዳው ያሉ ሁሉም ጤና ተቋማት የወባ በሽታ መከላከልን ጨምሮ የወባ በሽታ ምልክት የታየባቸውን የማህበረሰብ ክፍሎች የተሻለ ህክምና ለመስጠትና የበሽታውን ስርጭት ለመቀነስ በትኩረት እንዲሰሩ አቅጣጫ የተቀመጠ ስለመሆኑም የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ያደረሰን መረጃ ያመለክታል ።

በአማራ  ሳይንት ወረዳ  04  #ሸንጎደፈር ቀበሌ የስንዴ ሰብል አሁናዊ ቁመና በምስል
30/08/2026

በአማራ ሳይንት ወረዳ 04 #ሸንጎደፈር ቀበሌ የስንዴ ሰብል አሁናዊ ቁመና በምስል

29/08/2026
በአማራ ሳይንት ወረዳ 51 ተማሪዎች 300 እና ከዚያ በላይ ውጤት አምጥተዋል።አጅባር፦ ነሐሴ 22 ቀን 2018 ዓ.ም (የአማራ ሳይንት ወረዳ ኮሙኒኬሽን)በ2018 የትምህርት ዘመን  353 ተማ...
28/08/2026

በአማራ ሳይንት ወረዳ 51 ተማሪዎች 300 እና ከዚያ በላይ ውጤት አምጥተዋል።

አጅባር፦ ነሐሴ 22 ቀን 2018 ዓ.ም (የአማራ ሳይንት ወረዳ ኮሙኒኬሽን)

በ2018 የትምህርት ዘመን 353 ተማሪዎች የ12ኛን ሀገር አቀፍ ፈተና የተፈኑ ሲሆን 51 ተማሪዎች (14 ነጥብ 44 በመቶ) 300 እና ከዚያ በላይ ውጤት አምጥተዋል።

ከነዚህ መካከል በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪ ዮናስ ደምሴ እሸቱ 521 ነጥብ 08 (አማካይ ውጤት 86 ነጥብ 85) በማምጣት ከፍተኛውን ውጤት አስመዝግቧል።

በተመሳሳይ በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪ ፂዮን ጋረድ መለሰና ተማሪ ትግስት ደረበ ዘለለው እኩል 493 ነጥብ 33 ነጥብ (አማካይ 82 ነጥብ 22) በማምጣት ከታዩን ደረጃ ይዘዋል።

በወረዳው ሶስት 2ኛና መሰናዶ ት/ቤቶች የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን ያስፈተኑ ሲሆን ሳይንት ከፍተኛ 2ኛና መሰናዶ ት/ቤት ካስፈተናቸው 265 ተማሪዎቾ መካከል 44 ተማሪዎች (16 ነጥብ 6 በመቶ) 300 እና ከዚያ በላይ አምጥተዋል።

#እዋ 2ኛና መሰናዶ ት/ቤት 46 ተማሪዎችን አስፈትኖ 4 ተማሪዎች (8 ነጥብ 69 በመቶ) እንድሁም

#ጓሜዳ 2ኛና መሰናዶ ት/ቤት 43 ተማሪዎችን አስፈትኖ 3 ተማሪዎች (6 ነጥብ 97 በመቶ) 300 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጡ መሆኑን ከወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በዚህ ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ውጤት በወረዳ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበ ሲሆን በባለፈው ዓመት ከፍተኛው ውጤት 510 እንደነበር ይታወሳል።

Address

Dessie

Telephone

+251914057840

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Sayint woreda Communication Affairs/አምሐራ ሳይንት ወረዳ ኮሙኒኬሽን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Amhara Sayint woreda Communication Affairs/አምሐራ ሳይንት ወረዳ ኮሙኒኬሽን:

Shortcuts

Share