South Wollo Zone Gov. Communication Dept.

South Wollo Zone Gov. Communication Dept. የደቡብ ወሎ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ
ደሴ

የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የብልፅግና ፓርቲን የለውጥ ሥራ አደነቀ። በብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ የውጭ ግንኙነት ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ ነብዩ ስሑል የተመ...
01/09/2026

የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የብልፅግና ፓርቲን የለውጥ ሥራ አደነቀ።

በብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ የውጭ ግንኙነት ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ ነብዩ ስሑል የተመራ የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ልዑክ በቻይና ጉብኝት እያደረገ ይገኛል።

ልዑኩ በቤጂንግ ከቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የአፍሪካ ጉዳዮች ኮሚቴ ጋር የፓርቲ ለፓርቲ ግንኙነትን በተመለከተ ውይይት አካሂዷል።

በውይይቱ ላይ አቶ ነብዩ ስሑል፣ ብልፅግና ፓርቲ የሚመራበት የመደመር እሳቤና የፓርቲው ፕሮግራሞች በኢትዮጵያ ለሚታዩት ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ለውጦች ዋነኛ መሠረት መሆናቸውን ገልጸዋል።

የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ፖሊሲው ውጤታማነት፣ የከተማና የገጠር ልማትን በተቀናጀ መልኩ ማከናወን፣ ሕዝብን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚከናወኑ የልማት ሥራዎች እና የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ የፓርቲውን የእሳቤ ጥራትና የማስፈጸም አቅም የሚያሳዩ ዋነኛ ተግባራት መሆናቸውንም አቶ ነብዩ ጠቁመዋል።

የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ ከሀገር ውስጥ የልማት ሥራ ባሻገር፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ አቅም እያጠናከረ ያለ ተግባር መሆኑንም ገልጸዋል።

በፖለቲካው መስክ እየተመዘገቡ ያሉ አበረታች ለውጦችን በመጥቀስ፣ ኢትዮጵያ በ2026 የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤን በአዲስ አበባ ለማስተናገድ መመረጧንና ለጉባኤው ዝግጅት እያደረገች መሆኗን አስረድተዋል።

በሌላ በኩል፣ ልዑኩን የተቀበሉት የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል ወ/ሮ ሪኦ ዩሃ ብልፅግና ፓርቲ “ጠንካራ ፓርቲ ለጠንካራ መንግሥት፤ ጠንካራ መንግሥት ለጠንካራ ሀገር” በሚል እሳቤ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እያስመዘገበ ያለውን ለውጥ ፓርቲያቸውና መንግሥታቸው በከፍተኛ አድናቆት እንደሚከታተሉ ገልጸዋል።

ወ/ሮ ሪኦ ዩሃ አክለውም፣ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲና ብልፅግና ፓርቲ በፓርቲ ለፓርቲ ግንኙነት የሚያደርጉትን ትብብር እና የጋራ ጥቅሞችን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ቅንጅት በቀጣይ ለማጠናከር ፓርቲያቸው ጠንካራ አቋም እንዳለው አረጋግጠዋል።

የብልፅግና ፓርቲ ልዑክ በቤጂንግ በነበረው የመጀመሪያ ቀን ውሎ፣ ከሁለትዮሽ ውይይቱ በተጨማሪ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲን ታሪክ፣ ልምድ፣ ድሎችና ተግዳሮቶች የሚያሳየውን የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ሙዚየም ጎብኝቷል።

ጉብኝቱ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ካለፈው ታሪኩ በመማር የአሁኑን ስኬቶች እንዴት እያጠናከረ እንደሚገኝና የወደፊት ራዕዩን ለማሳካት እያከናወነ የሚገኘውን እንቅስቃሴዎች ለመመልከት ጠቃሚ የመማማሪያ ልምድ ሆኗል።

በቀጣዮቹ ቀናት የሁለቱ ፓርቲዎች አመራሮች የጋራ ልምድ የሚጋሩበትና እርስ በእርስ የሚማማሩበት መርሃ ግብር ይከናወናል።

*****
የደቡብ ወሎ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ
ተደራሽ የሚያደርግባቸው አማራጮች ቀጣዮቹ አድራሻዎች ናቸው። ሊንኮቹን በመጫንና በመወዳጀት ፈጣንና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት ቤተሰባችን ይሁኑ!
ፌስ ቡክ፡ https://www.facebook.com/Southwollozonecommunicationaffairoffice
ኤክስ ገጽ፡ https://twitter.com/WolloNews?t=Lrv74tG3nMkhl51mvR4_QA&s=09
ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/p/Cb1bEhbK0hw/?utm_medium=copy_link
ዩቱዩብ፡https://youtube.com/channel/UC5WAkOJxv-uE3HxyTQepVrA
ቴሌግራም፡https://t.me/Southwollocommunicationdeptgov
ዌብ ሳይት፡ https://www.southwollocommunication.gov.et

የሕዝብን የላቀ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ባደረጉት የማይናወጥ ትጋትና የላቀ የሕዝብ ወገንተኝነት፣ የደቡብ ወሎ ዞን እንቁ ከፍተኛ መሪዎች እንዲህ በደስታና በሐሴት ደምቀዋል።በየደረጃው የሚገኘውን...
01/09/2026

የሕዝብን የላቀ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ባደረጉት የማይናወጥ ትጋትና የላቀ የሕዝብ ወገንተኝነት፣ የደቡብ ወሎ ዞን እንቁ ከፍተኛ መሪዎች እንዲህ በደስታና በሐሴት ደምቀዋል።

በየደረጃው የሚገኘውን የፖለቲካና የፀጥታ አመራር፣ ባለሙያዎችንና መላውን ሕዝብ በቅንጅትና በከፍተኛ ንቅናቄ በማስተባበር የተመዘገበው ይህ የላቀ ውጤት፣ ዞኑን በወጥ አፈጻጸም ላለፉት ሁለት ተከታታይ ዓመታት በአማራ ክልል ግንባር ቀደም ተሸላሚ አድርጎታል።

ይህ በደስታ ድምቀት የታጀበው ታሪካዊ ስኬት፣ የጋራ ጥረትና የሕዝብ ቁርጠኝነት ያመጣው የድል ፍሬ ነው።

"የክልሉ ዕቅድ እንዲሳካ በየደረጃው የሚገኙ መሪዎች በቁርጠኝነት መሥራት ይጠበቅባቸዋል" ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የአማራ ክልል ከፍተኛ  እና መከካለኛ መሪዎች የ2018 በጀት ዓመት የፓ...
01/09/2026

"የክልሉ ዕቅድ እንዲሳካ በየደረጃው የሚገኙ መሪዎች በቁርጠኝነት መሥራት ይጠበቅባቸዋል" ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ

የአማራ ክልል ከፍተኛ እና መከካለኛ መሪዎች የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲ እና የመንግሥት ሥራዎች አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት የዕቅድ ትውውቅ መድረክ ተካሂዷል።

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የክልሉን የጸጥታ ችግር በዘላቂነት ለማረጋገጥ በቅንጅት መሥራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ዞኖች በቅንጅት ሲሠሩ የጽንፈኛውን እንቅስቃሴ እና ጥፋት ማስቆም እንደሚችሉም ገልጸዋል። ሕዝቡ ጽንፈኛውን አምርሮ ጠልቶታል፤ ይሄን የሕዝብ አቅም በአግባቡ መጠቀም ያስፈልጋል ነው ያሉት።

የልማት ሥራዎችን ማፋጠን እና የሕዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚቻለው የጸጥታ ችግሮችን መፍታት ሲቻል እንደኾነም አንስተዋል።

የክልሉ መንግሥት የልማት ሥራዎች እንዲፋጠኑ እና የተጀመሩት እንዲጠናቀቁ በትኩረት እንደሚሠራም ገልጸዋል። በፌዴራል እና በክልሉ መንግሥት የተጀመሩ ፕሮጀክቶች በውጤታማነት እንዲፈጸሙ ሰላምን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ብለዋል።

የበርካታ ፕሮጀክቶች ፈተና የጸጥታ ችግር እንደኾነ ያነሱት ርእሰ መሥተዳድሩ የጸጥታ ችግሩን በመፍታት ፕሮጀክቶቹ እንዲጠናቀቁ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

በየደረጃው የሚገኙ መሪዎች ክልሉ ያቀደው ዕቅድ በአግባቡ እንዲፈጸም መሥራት እንደሚገባቸውም አስገንዝበዋል። ሕዝቡ በባለቤትነት እንዲሳተፍበት እና ሚናውን እንዲወጣ ለማድረግም ከሕዝብ ጋር መወያየት እንደሚገባም ገልጸዋል።

የአማራ ክልል ሕዝብ ለሀገረ መንግሥት ግንባታ የራሱን አስተዋጽኦ ያደረገ እና ለሕግ ተገዢ የኾነ ነው ብለዋል። የአማራ ክልል ሕዝብ ማኅበራዊ ትስስሩ ሕግ እንደኾነም አንስተዋል። ይህን መልካም እና የቆዬ እሴት ማጠናከር እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

አንድነትን እና ማኅበራዊ ትስስርን አሁንም ማጠናከር ያስፈልጋል ነው ያሉት። ከአንድነት እና ከጠንካራ ማኅበራዊ ትስስር ውጭ ያለው አካሄድ እንደማይጠቅምም ተናግረዋል።

መሪዎች የአካባቢያቸውን ጸጋ ታሳቢ ያደረገ ሥራ በመሥራት ኢኮኖሚን ማረጋገጥ እንደሚጠበቅባቸውም አስገንዝበዋል። የመልካም አሥተዳደር ጥያቄዎችን መፍታት እንደሚገባቸውም አሳስበዋል።

የነገን እድገት እና ተወዳዳሪነት ታሳቢ ያደረገ ሥራ መሥራት ያስፈልጋልም ብለዋል። መንግሥት የሕዝብ ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ እንደሚፈታም አንስተዋል።

የታቀደው ዕቅድ እንዲሳካ፣ ውጤታማ ሥራዎችም እንዲሠሩ መሪዎች ዕቅዱን በአግባቡ መረዳት፣ መተግበር እና ማስተግበር እንደሚገባቸውም አሳስበዋል።
አሚኮ

የድል ሐሴት ለነገው ከፍታ፡ ለደቡብ ወሎ ህዝብና አጠቃላይ አመራር የተላለፈ የምስጋና መልዕክት​​በ2018 በጀት ዓመት የፓርቲና የመንግሥት ሥራዎች አፈጻጸም ከመላው የአማራ ክልል ዞኖች በመጀ...
01/09/2026

የድል ሐሴት ለነገው ከፍታ፡ ለደቡብ ወሎ ህዝብና አጠቃላይ አመራር የተላለፈ የምስጋና መልዕክት

​በ2018 በጀት ዓመት የፓርቲና የመንግሥት ሥራዎች አፈጻጸም ከመላው የአማራ ክልል ዞኖች በመጀመሪያ ደረጃ ማጠናቀቃችንን ስገልጽ በታላቅ ኩራትና በልዩ ስሜት ነው። ይህ ድል በአጋጣሚ የተገኘ አይደለም፤ የጋራ ትጋታችን፣ የጸና ርምጃችን እና የህዝባችንን አደራ በታማኝነት የመወጣታችን ፍሬ ነው።

ታሪክን በሥራ የሚቀይረው ህዝባችን፤ ለተከበራችሁ የዞናችን አርሶ አደሮች፣ ሴቶች፣ወጣቶች እና ባለሀብቶች እና አጠቃላይ የህብረተሰብ ክፍሎች፤ በፈተናዎች መሀል ጸንታችሁ ከጎናችን በመቆማችሁ ዛሬ ይህንን ታሪክ መጻፍ ችለናል። ስኬቱ የሁላችንም የድካም ውጤት ነው።

የህዝብ አደራን በብቃት የተወጣችሁ አገልጋዮች፤ ቀንና ማታ ሳይበገሩ ለህዝብ ማገልገል የመረጣችሁ የፓርቲ እና የመንግስት አመራሮች፣የጸጥታ መዋቅር፣ ባለሙያዎችና ሠራተኞች፤ የሰራችሁት አርዓያነት ያለው ተግባር የሚመሰገን ነው።
​ይህ ያመጣነው አንደኛ ደረጃ የጉዞ ማጠናቀቂያ ሳይሆን፣ ለቀጣዩ በጀት ዓመት የላቀ ከፍታ መነሻ መሰረታችን ነው።

ድሉ የመጨረሻው መስመር አይደለም፤ ይልቁንም ለሚቀጥለው ዓመት የላቀ ስኬት ማሻገርያ ደረጃችን ነው። የታሪክ ባለቤቶች እንደ መሆናችን መጠን፣ በቀጣዩ በጀት ዓመትም የላቀ ቁርጠኝነትን ይዘን በመነሳት፣ የዞኑን ታላቅነት በሁሉንም መስክ አሁንም እናስቀጥላለን።

​በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ!

​አቶ አሊ መኮንን
የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ

የአማራ ክልል መንግስት ባካሄደው የግምገማና የስትራቴጂክ ዕቅድ መድረክ ላይ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ዞኖችና ከተሞች እውቅና ተሰጠ​የአማራ ክልል ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የ2018 በጀት...
01/09/2026

የአማራ ክልል መንግስት ባካሄደው የግምገማና የስትራቴጂክ ዕቅድ መድረክ ላይ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ዞኖችና ከተሞች እውቅና ተሰጠ

​የአማራ ክልል ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲና የመንግሥት ሥራዎች ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ኦሬንቴሽን መድረክ ከነሐሴ 23 እስከ 27/2018 ዓ.ም ሲካሄድ ቆይቶ በስኬት ተጠናቋል።

​በበጀት ዓመቱ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ አካላት የእውቅናና የሽልማት መርሃ ግብር ተካሂዷል።

በዚህም መሰረት ​የከተማ አስተዳደሮች ደረጃ

1ኛ ደረጃ_ ጎንደር ከተማ አስተዳደር

2ኛ ደረጃ _ ባህዳር ከተማ አስተዳደር

3ኛ ደረጃ _ ደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር

ሲሆን ​የዞኖች ደረጃ ደግሞ

​1ኛ ደረጃ፡ ደቡብ ወሎ ዞን

​2ኛ ደረጃ፡ ሰሜን ሸዋ ዞን

​3ኛ ደረጃ፡ ምስራቅ ጎጃም ዞን

​በመርሃ ግብሩ ላይ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የልዩ ተሸላሚነት እውቅና ተበርክቶለታል።

*****
የደቡብ ወሎ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ
ተደራሽ የሚያደርግባቸው አማራጮች ቀጣዮቹ አድራሻዎች ናቸው። ሊንኮቹን በመጫንና በመወዳጀት ፈጣንና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት ቤተሰባችን ይሁኑ!
ፌስ ቡክ፡ https://www.facebook.com/Southwollozonecommunicationaffairoffice
ኤክስ ገጽ፡ https://twitter.com/WolloNews?t=Lrv74tG3nMkhl51mvR4_QA&s=09
ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/p/Cb1bEhbK0hw/?utm_medium=copy_link
ዩቱዩብ፡https://youtube.com/channel/UC5WAkOJxv-uE3HxyTQepVrA
ቴሌግራም፡https://t.me/Southwollocommunicationdeptgov
ዌብ ሳይት፡ https://www.southwollocommunication.gov.et

መልካም ዜና!የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር እንደ ባለፈው ዓመት ሁሉ ዘንድሮም ታላቅ ድል ተቀዳጅቷል!የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር በ2018 በጀት ዓመት በፓርቲና በመንግሥት በተከናወኑ ሁለንተናዊ...
01/09/2026

መልካም ዜና!

የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር እንደ ባለፈው ዓመት ሁሉ ዘንድሮም ታላቅ ድል ተቀዳጅቷል!

የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር በ2018 በጀት ዓመት በፓርቲና በመንግሥት በተከናወኑ ሁለንተናዊ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የላቀና አርአያነት ያለው ከፍተኛ አፈጻጸም በማስመዝገቡ የ1ኛ ደረጃ አሸናፊ በመሆን የመኪና እና የዋንጫ ባለታሪክና ተሻላሚ ሆኗል።

ይህ የተገኘው የላቀ ውጤት የህዝቡ ተሳትፎ፣ የክትትልና አመራር ጥንካሬ እንዲሁም የመላው አመራርና ሠራተኞች የጋራ ድካም ውጤት ነው!

እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን!
ስኬቱና ልማቱ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

*****
የደቡብ ወሎ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ
ተደራሽ የሚያደርግባቸው አማራጮች ቀጣዮቹ አድራሻዎች ናቸው። ሊንኮቹን በመጫንና በመወዳጀት ፈጣንና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት ቤተሰባችን ይሁኑ!
ፌስ ቡክ፡ https://www.facebook.com/Southwollozonecommunicationaffairoffice
ኤክስ ገጽ፡ https://twitter.com/WolloNews?t=Lrv74tG3nMkhl51mvR4_QA&s=09
ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/p/Cb1bEhbK0hw/?utm_medium=copy_link
ዩቱዩብ፡https://youtube.com/channel/UC5WAkOJxv-uE3HxyTQepVrA
ቴሌግራም፡https://t.me/Southwollocommunicationdeptgov
ዌብ ሳይት፡ https://www.southwollocommunication.gov.et

01/09/2026

Education for Sustainable Development (ESD) and ADRA Ethiopia                                        አዲስ የዲጂታል እና ግሪን ስኪ...
01/09/2026

Education for Sustainable Development (ESD) and ADRA Ethiopia አዲስ የዲጂታል እና ግሪን ስኪል ፕሮጀክት በደሴ ከተማ ተበሰረ

ደሴ፣ ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም (ደቡብ ወሎ ኮሙዩኒኬሽን)

በደሴ ከተማ Education for Sustainable Development (ESD) and ADRA Ethiopia ድርጅት አዲስ የወጣቶች ስልጠና እና ስራ ፈጠራ ፕሮጀክት ማስተዋወቂያ መርሃ ግብር አካሄደ።

በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደሴ ከተማ ገንዘብ መምሪያ ተወካይ አቶ አክሊሉ አለማየሁ እንደገለጹት፤ ሀገሪቱ ዲጂታል ኢኮኖሚን እውን ለማድረግ የያዘችውን ግብ ለማሳካት የመንግስት ጥረት እንዳለ ሆኖ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ሚና ከፍተኛ ነው።

አሁን ይፋ የሆነው አዲስ ፕሮጀክት ይህን ሀገራዊ ኢኒሼቲቭ ለማሳካት ትልቅ እገዛ የሚያደርግ በመሆኑ፣ ለስኬታማነቱ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የESD ዋና ቢሮ የፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ዳንኤል ኃይለገብርኤል እንደገለጹት ድርጅቱ ከተቋቋመ 19 ዓመታት ያስቆጠረ ሲሆን፣ በ2000 ዓ.ም በደብረ ብርሃን አካባቢ በ4 ወረዳዎች በህፃናት ቅድመ-መደበኛ ትምህርት እና እናቶችን በማበቃት ስራውን መጀመሩን አስታውሰዋል። በአሁኑ ወቅት ድርጅቱ አቅሙን በማሳደግ በ4 ክልሎች (አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ሲዳማ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ) ትኩረቱን አድርጎ እየሰራ ይገኛል።

አቶ ዳንኤል አክለውም ድርጅቱ የመጀመሪያ ዓመታዊ በጀቱ ከነበረበት 10 ሚሊዮን ብር በአሁኑ ወቅት ወደ 256 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር ማደጉን ጠቁመው፤ ከትምህርት ጥራት፣ ከሴቶች እና ወጣቶች ማበቃት በተጨማሪ ከ2021 (እ.አ.አ) ጀምሮ በሰብአዊ እርዳታ እና በካምፕ ውስጥ በሚገኙ ተፈናቃይ (IDP) ህፃናት ትምህርት ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት ከስዊዘርላንድ ፋውንዴሽኖች በሚገኝ ድጋፍ የድርጅቱ ከ60% በላይ በጀት በወጣቶች ስራ ፈጠራ እና ክህሎት ማሳደግ ላይ የዋለ ሲሆን፤ አዲሱ ፕሮጀክትBMZ እና ከadra Germany' በተገኘ ድጋፍ ከadra Ethiopia' ጋር በመተባበር የሚተገበር ነው።

በሚቀጥሉት 3 ዓመት ከግማሽ ውስጥ ወይዘሮ ሲኂን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሚተገበረው ፕሮጀክት ከ31 ሚሊዮን በር በላይ በሚሆን በጀት 200 ወጣቶችን በ'Green Skills' (በሶላር ቴክኖሎጂ) እና በ'Digital Skills' ለማሰልጠን አቅዷል።

ይህም ቀደም ሲል ላለፉት 7 ዓመታት በ8 የTVET ኮሌጆች ሲሰጥ የነበረውን የሶላር ቴክኖሎጂ ስልጠና (747 ሰልጣኞች ተጠቃሚ የሆኑበትን) በዲጂታል ክህሎት የበለጠ ለማጠናከር እና ወጣቶችን በገበያው ተወዳዳሪ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ ነው ሲሉ አቶ ዳንኤል አክለዋል።

የወይዘሮ ሲኂን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ሰለሞን ይመር በበኩላቸው፤ ኮሌጁ ከደረጃ 1 እስከ 5 ከሚሰጣቸው የረጅም ጊዜ ስልጠናዎች ባሻገር ለስራ ፈላጊ ወጣቶች አጫጭር ስልጠናዎችን በመስጠት ወደ ስራ የማሰማራት ተልእኮ እንዳለው ገልጸዋል። አዲሱ የESD ፕሮጀክት በጀት ይዞ የመጣ በመሆኑ የኮሌጁን አቅም እንደሚያጎለብት፣ የመምህራንን አቅም እንደሚገነባ እና አስፈላጊ የዲጂታል እና የግሪን ስኪል መሳሪያዎችን (ኢክዊፕመንቶች) እንደሚያሟላ ተናግረዋል።

ዲኑ አክለውም፣ አሁን ያለው ዘመን የዲጂታል ዘመን በመሆኑ ተቋማት ራሳቸውን ዲጂታላይዝ ማድረግ እንዳለባቸው ጠቁመው፤ መንግስት ያስቀመጣቸውን እንደ "5 ሚሊዮን ኮደርስ" እና የክልሉን "ዲጂታል አማራ" ያሉ ኢኒሼቲቮችን ስኬታማ ለማድረግ እና የሀገሪቱን የዲጂታል ኢኮኖሚ ግብ ለማሳካት ኮሌጁ ከኤንጂኦዎች ጋር በቅንጅት ለመሰራት ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።

በፕሮጀክቱ ትውውቅ መርሃ ግብር ላይ ከኮሌጁ በተጨማሪ ፣ የሰራና ክህሎት እንዲሁም የፋይናንስ ሴክተር መስሪያ ቤቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን፤ እነዚህ አካላት ሰልጣኝ ወጣቶች ስልጠናቸውን ሲጨርሱ የኢንዱስትሪ ልምምድ እንዲያደርጉ፣ የመነሻ ካፒታል እና የብድር አገልግሎት ከአበዳሪ ተቋማት ጋር በመጨረስ ወደ ስራ እንዲገቡ የማመቻቸት እና የመከታተል ድርሻ ይኖራቸዋል።

በደቡብ ወሎ ዞን .በቃሉ ወረዳ በከፍተኛ የህብረተሰብ ተሳትፎ ተገንብቶ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው የደጋን አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትም/ቤት G+2 ህንፃ ግንባታ አሁናዊ ገፅታ
01/09/2026

በደቡብ ወሎ ዞን .በቃሉ ወረዳ በከፍተኛ የህብረተሰብ ተሳትፎ ተገንብቶ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው የደጋን አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትም/ቤት G+2 ህንፃ ግንባታ አሁናዊ ገፅታ

በደቡብ ወሎ ዞን ወረኢሉ ወረዳ 03 ቀበሌ  መተገሬ  ክላስተር እየለማ የሚገኝ የስንዴ ሰብል አሁናዊ ገጽታ በምስል
01/09/2026

በደቡብ ወሎ ዞን ወረኢሉ ወረዳ 03 ቀበሌ መተገሬ ክላስተር እየለማ የሚገኝ የስንዴ ሰብል አሁናዊ ገጽታ በምስል

Address

Dessie

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when South Wollo Zone Gov. Communication Dept. posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to South Wollo Zone Gov. Communication Dept.:

Shortcuts

Share