Dehana Woreda Communication Affairs office የደሀና ወረዳ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Dessie
  • Dehana Woreda Communication Affairs office የደሀና ወረዳ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

Dehana Woreda Communication Affairs office የደሀና ወረዳ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ በማድረስ ለህብረተሰብ ለዉጥ እንተጋለን ።

04/09/2026

#ዘወትር #አርብ #ከቀኑ 11:00 ⌚ ☝️በቀጣይ ሳምንት በሌላ ልዩ መርሐግብር ይጠብቁን!
29/2018ዓ.ም #ስለ ።
ሙሉውን ለመመልከት
👇👇👇
https://youtu.be/NmYrEEwf5J4?si=LbZZuSzKmnFXyCdR

ተጨማሪ መረጃዎችን እንድናደርስዎት የደሃና ወረዳመንግስት ኮሙኒኬሽንን ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጫኑ።

Facebook
https://www.facebook.com/profile.100066304790042
👉YouTube ፤
https://youtube.com/channel/UCBbTi4Tq6iNrrxwMyg22FtQ
👉Telegram
https://t.me/amd1512
👉TikTokሀ
tiktok.com/
👉
https://x.com/wereda169222/status/2000868480283730223?

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ልማታዊ እና ክርስቲያናዊ  ተራድኦ ኮሚሽን  ከስደተኞችና ከሰደት ተመላሾች መምሪያ ተጋላጭ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉ ተገለ...
04/09/2026

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ልማታዊ እና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ከስደተኞችና ከሰደት ተመላሾች መምሪያ ተጋላጭ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉ ተገለጸ ።

ደሃና፣አምደወርቅ:ንሃሴ 29 /2018ዓ.ም (Dehana woreda communcation) የዋግ ኽምራ ብ/ሰብ አስ/ር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ልማታዊ እና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ከስደተኞችና ከሰደት ተመላሾች መምሪያ ተጋላጭ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉ ተገለጸ።

ድጋፍ የተደረገላቸው አካላትም አካላዊ ጉዳት በደረሰባቸው ፣በስነ-ልቦና ፣ በኢኮኖሚያዊ፣ በማህበራዊ ፣ ተጋላጭ በሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ አጥቢና ነብሰጡር እናቶች እንዲሁም በአካል ጉዳተኛ በተጨማሪም በሌሎች ተግባራት እየሰሩ መሆኑን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ልማታዊ እና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ከስደተኞችና ከሰደት ተመላሾች መምሪያ የማህበረሰብ አገልግሎት በአለሞያ የሆኑት አቶ አዲስ ዓለም ሰጥቶኝ አመላክተዋል ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ልማታዊ እና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ከስደተኞችና ከሰደት ተመላሾች መምሪያ የፕሮቴክሽን ኦፊሰር የሆኑት ወ/ሮ ቤዛዊት አለማየሁ በበኩላቸው ኮሚሽኑ በወረዳው ለባለ ድርሻ አካላት ስልጠና በመስጠት እና በአምደወርቅ ጤና ጣቢያ በየደረጃው ላሉ የሴቶች ማበልጸጊያ ማዕከል በመገንባት በላይፍ እስኪል ስራ ሴቶችን በማሰማራት የተሻለ ስራ እየሰሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

የደሃና ወረዳ ሴ/ወ/ማ/ጉ/ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ መሰረት አባቸው ኮምሽኑ ተጋላጭ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ለ277 ማህበረሰቦች ለያንዳዳቸው 30 ሸህ ብር የገንዘብ ድጋፍ እና ከ2 ሽህ በላይ ለሚሆኑ ሴቶች ለንጽህና መጠበቂያ የሚሆን ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ እንደተደረገላቸው ጠቁመዋል።

በዛሬው እለትም ለ10 አካል ጉዳተኞች ዊርቸር ፣ክራንች፣ አቅጣጫ ጠቋሚ/ምርኩዝ/ እንዲሁም ለ40 ሴቶች ምንጣፍ ፣ አነስተኛ ብርድልብስ ሌሎች የቤት ቂሳቁሶችንም እና ለ50 ሴቶች የንጽህና መጠበቂያ ደጋፍ እንደተደረገ አብራርተዋል።

አክለውም በአካል ጉዳተኞች ፣የስራድል ፈጠራ፣ ጥቃት በደረሳባቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ፣በእደ ጥበባት ስራ እና በሰላምና ግጭት ተግባራት ከመንግስት ጉን በመሆን ኮምሽኑ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በመጨረሻም ከልማት በተጨማሪ ሰባዊ የርዳታ ድጋፍ ላደረገላቸው የዋግ ኽምራ ብ/ሰብ አስ/ር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ልማታዊ እና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ከስደተኞችና ከሰደት ተመላሾች መምሪያን ወ/ሮ መሰረት አምባቸው መስጋና አቅርበዋል።

🕊🕊🕊 በአምጣቸው አዳነ

ተጨማሪ መረጃዎችን እንድናደርስዎት የደሃና ወረዳመንግስት ኮሙኒኬሽንን ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጫኑ።

Facebook
https://www.facebook.com/profile.100066304790042
👉YouTube ፤
https://youtube.com/channel/UCBbTi4Tq6iNrrxwMyg22FtQ
👉Telegram
https://t.me/amd1512
👉TikTokሀ
tiktok.com/
👉
https://x.com/wereda169222/status/2000868480283730223?t=YDjfJGEF09wzCqZE6z-TCw&s=19
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን

   👉ጥንታዊቷ ደብረ ሎዛ ዉቅር ማርያም ቤተክርስቲያን። 👉አርብ  ነሐሴ 29/2018ዓ.ም 👉ከቀኑ 11:00 ⌚ ይጠብቁንተጨማሪ መረጃዎችን እንድናደርስዎት የደሃና ወረዳመንግስት ኮሙኒኬሽንን ለ...
03/09/2026



👉ጥንታዊቷ ደብረ ሎዛ ዉቅር ማርያም ቤተክርስቲያን።
👉አርብ ነሐሴ 29/2018ዓ.ም
👉ከቀኑ 11:00 ⌚ ይጠብቁን

ተጨማሪ መረጃዎችን እንድናደርስዎት የደሃና ወረዳመንግስት ኮሙኒኬሽንን ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጫኑ።

Facebook
https://www.facebook.com/profile.100066304790042
👉YouTube ፤
https://youtube.com/channel/UCBbTi4Tq6iNrrxwMyg22FtQ
👉Telegram
https://t.me/amd1512
👉TikTokሀ
tiktok.com/
👉
https://x.com/wereda169222/status/2000868480283730223?

03/09/2026
"ከተረጅነት ወደ ምርታማነት" ደሃና፣  ጉራንባ ፣ ንሃሴ 28/2018 ዓ.ም ( Dehana Woreda Communication) በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በደሃና ወረዳ   በ014 ጉራንባ...
03/09/2026

"ከተረጅነት ወደ ምርታማነት"

ደሃና፣ ጉራንባ ፣ ንሃሴ 28/2018 ዓ.ም ( Dehana Woreda Communication) በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በደሃና ወረዳ በ014 ጉራንባ ቀበሌ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና አገራዊውን "ከተረጅነት ወደ ምርታማነት" ራዕይ ዕውን ለማድረግ የተጀመረው የግብርና እንቅስቃሴ በስኬት እየቀጠለ ይገኛል።

በደሃና ወረዳ በአገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን "ከተረጅነት ወደ ምርታማነት" በመሸጋገር ሰባዊ ድጋፍን በራስ አቅም የመሸፈን ኢንሸቲቭን እውን ለማድረግ በ014 ቀበሌ 3.5 ሄክታር መሬት የጤፍ አረም መርሃ -ግብር በህብረተሰብ ተሳትፎ እየተከናወነ ነው።

በተለይም በወረዳው 014 ቀበሌ ጉራንባ በ2018/2019 የመኸር የምርት ዘመን የታቀደውን "ከተረጅነት ወደ ምርታማነት"ለማሳካት በተደረገው የተቀናጀ ጥረት በዛሬው እለት 3.5 ሄክታር መሬት የጠፍ አረም እንቅስቃሴ በንቅናቄ እየተከናወነ መሆኑን የደሃና ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ጸጋነው ወዳጅ ገልጸዋል።

ይህ በጤፍ ክላስተር የተከናወነው የአረም ሥራ እንቅስቃሴ ፣ የአካባቢውን አርሶአደር ምርታማነት ከማሳደጉም በላይ የምግብን ራስ-ችሎታን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጉዞ ውስጥ ትልቅ እቅስቃሴና ተስፋ ሰጪ ውጤት መሆኑን አቶ ጸጋነው ወዳጅ አመላክተዋል ።

"ከተረጅነት ወደ ምርታማነት"

በአምጣቸው አዳነ

ተጨማሪ መረጃዎችን እንድናደርስዎት የደሃና ወረዳመንግስት ኮሙኒኬሽንን ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጫኑ።

Facebook
https://www.facebook.com/profile.100066304790042
👉YouTube ፤
https://youtube.com/channel/UCBbTi4Tq6iNrrxwMyg22FtQ
👉Telegram
https://t.me/amd1512
👉TikTokሀ
tiktok.com/
👉
https://x.com/wereda169222/status/2000868480283730223?

"የ2018 በጀት ዓመት ስኬቶችን ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር ለ2019 በጀት ዓመት ዝግጁ ነን" በግምገማ መድረኩ የተሳተፉ አመራሮችየአማራ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ባካሄደው የ2018 በ...
03/09/2026

"የ2018 በጀት ዓመት ስኬቶችን ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር ለ2019 በጀት ዓመት ዝግጁ ነን" በግምገማ መድረኩ የተሳተፉ አመራሮች

የአማራ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ባካሄደው የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ መድረክ የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች እና የዞን/ከተማ አስተዳደር የኮሙኒኬሽን ኃላፊዎች በመድረኩ በቀጣይ ዓመት የተሻለ ስራ ለመስራት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።

​የአማራ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አባይ መንግስቴ፤ በ2018 በጀት ዓመት ቢሮው ህዝብና መንግስትን የሚያገናኝ ድልድይ ሆኖ በመስራት የመረጃ ሰጭነት ሚናውን በሚገባ መወጣቱን ገልጸዋል።

ክልሉ ከነበረበት አንጻራዊ የጸጥታ ችግር ወደ ተሻለ ሰላም እንዲሸጋገር በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ የህዝብ ግንዛቤ በመፍጠር፣ ሰላም ነሺና ግጭት ቀስቃሽ ሀይሎችን እኩይ ተግባር ለማክሸፍ አበክሮ መሰራቱንም አብራርተዋል።

​ኃላፊው አክለውም በኢኮኖሚው፣ በግብርናውና በኢንዱስትሪው ዘርፍ መነቃቃት እንዲፈጠር፣ የሀገራዊ ምርጫ ሂደት ውጤታማ እንዲሆን እንዲሁም ዲጂታል ሚዲያን ጨምሮ ሁሉንም የመገናኛ ዘዴዎችና ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር የተደረጉ ቅንጅታዊ አሰራሮችን በመጠቀም ፈጣን የመረጃ ቅብብሎሽ ማካሄድ መቻሉን ገልጸዋል።

የዋግህምራ ብሔረሰብ ዞን መምሪያ ኃላፊ አቶ ከፍያለው ደባሽ በበኩላቸው፤ ዓመቱ ፈተናዎች የበዙበት ቢሆንም ፈተናዎችን ወደ መልካም አጋጣሚ በመቀየር በሁሉም የወረዳ መዋቅሮች የተቀራረበና ውጤታማ ስራ መከናወኑን ገልጸው፤ በቀጣይም ህዝብና መንግስትን የሚያቀራርብ ስራ ለመስራት መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል።

የጎንደር ከተማ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ አቶ ተመስገን ተስፋዬ፤ በተቀናጀና በተናበበ አሰራር ህብረተሰቡ ዘንድ የተሳሳቱ መረጃዎች እንዳይሰራጩ ግልጽ መረጃ በመስጠት በከተማዋ ተጨባጭ ሰላም እንዲሰፍንና የአካባቢ ማስተማሪያ ሚዲያዎች በውጤታማነት እንዲጠቀሙ መደረጉን ጠቁመዋል።

​የደቡብ ወሎ ዞን መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ መዝገብ ስጦታ በበኩላቸው፤ ከእቅድ ዝግጅት ጀምሮ ሁሉንም የሚዲያ ፕላትፎርሞችን አሟጦ በመጠቀም፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን በማጉላት እና ከሌሎች ሚዲያዎች ጋር በቅንጅት በመስራት ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን አስረድተዋል።

በመጨረሻም ​አቶ አባይ መንግስቴ በቀጣይ ዓመት በሚከተሉት ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ በትኩረት እንደሚሰራ አመላክተዋል።

ይህም የክልሉ ሰላም እንዲጸና እና የህግ ማስከበር ስራዎች እንዲሳኩ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ የመሪነት ሚናውን ይጫወታል።

በግብርና፣ በጤና እና በትምህርት ዘርፎች የታቀዱ ግቦችን ለማሳካት ህብረተሰቡን የማነቃቃት ስራ በትኩረት ይሰራል።

የሚዲያ ስራዎች በክልል ደረጃ ብቻ ሳይወሰኑ ሀገራዊ ገዥ ትረካዎችንና አጀንዳዎችን መሰረት ያደረጉ ይሆናሉ፤ የሚዲያ የበላይነትን በመጨበጥ የክልሉን በጎ ገጽታ የመገንባት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል።

የህዝብ ግንኙነት ፎረም ክትትልና ድጋፍ ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን ህዝቡ ከመንግስት የሚፈልገውን ትክክለኛ መረጃ በወቅቱ እንዲያገኝ አሰራሮች ይዘረጋሉ።

​የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ለክልሉ ሰላም፣ ልማትና መልካም አስተዳደር መረጋገጥ በግንባር ቀደምትነት እንዲሰሩና የመረጃ ቅብብሎሽ መዋቅሩን በአግባቡ እንዲጠቀሙ የቢሮ ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል።

ውጫዊ የወረራ ስጋት እና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማትን እናረጋግጣለን!” በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በደሃና ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስተ...
03/09/2026

ውጫዊ የወረራ ስጋት እና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማትን እናረጋግጣለን!”

በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በደሃና ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስተባባሪነት “ውጫዊ የወረራ ስጋት እና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማትን እናረጋግጣለን!” በሚል መሪ ሃሳብ ከፓርቲው አባላቱ ጋር የውይይት መድረክ ተካሄዷል ።

🕊 ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም! 🕊
👉

ውጫዊ የወረራ ስጋት እና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማትን እናረጋግጣለን!” በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በደሃና ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስተ...
02/09/2026

ውጫዊ የወረራ ስጋት እና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማትን እናረጋግጣለን!”

በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በደሃና ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስተባባሪነት “ውጫዊ የወረራ ስጋት እና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማትን እናረጋግጣለን!” በሚል መሪ ሃሳብ በ026 ቀበሌ ሽመላ ከወጣቶች ጋር የውይይት መድረክ ተካሄዷል ።

🕊 ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም! 🕊
👉

የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር መንገድ፣ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ መምሪያ በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት በገጠር ትስስር ለምግብ ዋስትና ፕሮግራም በክልሉ ካሉት ዞኖች 2ኛ ደረጃ በመሆኑ የ...
02/09/2026

የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር መንገድ፣ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ መምሪያ በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት በገጠር ትስስር ለምግብ ዋስትና ፕሮግራም በክልሉ ካሉት ዞኖች 2ኛ ደረጃ በመሆኑ የምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል።

የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 ዕቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄደ፤​የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ከዞን፣ ብሔረሰብ እ...
02/09/2026

የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 ዕቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄደ፤

​የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ከዞን፣ ብሔረሰብ እና ከተማ አስተዳደር የኮሙኒኬሽን መምሪያ ኃላፊዎች ጋር ሲያካሂድ የቆየውን የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት የዕቅድ ትውውቅ መድረክ በስኬት አጠናቋል።

​በመድረኩ የተገኙት የቢሮው ኃላፊ አቶ አባይ መንግሥቴ እንደገለጹት፤ በበጀት ዓመቱ የኮሙኒኬሽን አመራሮች እና ባለሙያዎች ሀገራዊ አንድነትን የሚያጠናክሩ፣ ሰላምና ልማትን የሚያፋጥኑ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተግባራትን በጥንካሬ በመፈጸማቸው የጽንፈኛ ኃይሎችን አፍራሽ ዓላማ ማክሸፍ ተችሏል።

​ኃላፊው አክለውም በቀጣይ የሚዲያና የመረጃ የበላይነትን በመያዝ የጠላትን ሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳ ማክሸፍ እና የሕዝቡን የጋራ መግባባት ማጎልበት ተችሏል።

​የጋራ መግባባትን የሚያጠናክሩ እንዲሁም የክልሉን የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች በሁሉም የሚዲያ አማራጮች አጉልተው የሚያሳዩ ይዘቶችን ማቅረብ ተችሏል። ለሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች መረጃ ተዳራሽ ለማድረግ የሕትመት ውጤቶችን፣ የቲቪ ፓርኮችን፣ የማስታወቂያ ሰሌዳዎችን እና የአካባቢ ሚኒ-ሚዲያዎችን በአግባቡ መጠቀም ይገባል ብለዋል።

​ የዲጂታል ሚዲያ አጠቃቀምን ማሳደግና የይዘት ጥራትን በጥንቃቄ መጠበቅ እንዲሁም በገጠር አካባቢዎች የዲጂታል አሰራርን ማስፋት ያስፈልጋል ሲሉም ቢሮ ሃላፊዉ አክለዋል።

​የቢሮዉ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ ሙሉነህ ዘበነ በበኩላቸዉ የክልሉን ገጽታ የሚያበላሹና ሕዝብን የሚያደናግሩ አካላት ከድርጊታቸዙ እንዲቆጠቡና መረጃ የማጣራት ሥራን በማጠናከር ትክክለኛውን መረጃ ለሕዝብ ማድረስ ይገባል። ዘመኑ የዲጅታል ዘመን በመሆኑ ሁሉም ባለሙያ ራሱን ማዘጋጀት አለበት ብለዋል።

​በሌላ በኩል የቢሮው ምክትል ወ/ሮ ትብለጥ መንገሻ በበኩላቸው፤ የ2018 በጀት ዓመት የተናበበና የተቀናጀ የመረጃ ቅብብሎሽ የተከናወነበት፣ ተቋሙ ከቀዳሚ አጀንዳ ተቀባይነት ወደ አጀንዳ ሰጪነት የተሸጋገረበት እና አብዛኞቹ ዕቅዶች ከመቶ ፐርሰንት በላይ የተፈጸሙበት የስኬት ዓመት እንደነበር ገልጸዋል።

​በመጨረሻም ቢሮው በ2018 በጀት ዓመት ከፍተኛ የሥራ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የዞንና የከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን መምሪያዎች የእውቅናና የሽልማት ሥነ-ሥርዓት አከናውኗል።

በዚህም ​በከተማ አስተዳደሮች ደረጃ፦

​ጎንደር ከተማ አስተዳደር (1ኛ ደረጃ)
​ደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር (2ኛ ደረጃ)
​ደሴ ከተማ አስተዳደር (3ኛ ደረጃ)

​በዞኖች ደረጃ፦

​ደቡብ ወሎ ዞን (1ኛ ደረጃ)
​አዊ ብሔረሰብ ዞን (2ኛ ደረጃ)
​ሰሜን ሸዋ እና ማዕከላዊ ጎንደር ዞን (3ኛ ደረጃ) በመሆን ተሸላሚ ሆነዋል።

Address

Amdewerqe
Dessie

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dehana Woreda Communication Affairs office የደሀና ወረዳ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share