Beyeda Communications

Beyeda Communications የስሜንን፣ በተለይም የበየዳ ወረዳን ሁለንተናዊ ገፅታ እናስ?

በሰሜን ጎንደር ዞን በደባርቅ ወረዳ ታጥቀው በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀበሉ።ደባርቅ፡ ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም (የሰሜን ጎንደር ኮሙኒኬሽን)በሰሜን ጎንደር ዞን በ...
05/09/2026

በሰሜን ጎንደር ዞን በደባርቅ ወረዳ ታጥቀው በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀበሉ።

ደባርቅ፡ ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም (የሰሜን ጎንደር ኮሙኒኬሽን)

በሰሜን ጎንደር ዞን በደባርቅ ወረዳ በምስራቁ ቀጠና ታጥቀው በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በርካታ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለዋል።

የሃገር መከላከያ ሰራዊት የ10ኛ ዕዝ ዘመቻ አመራሮችና አባላት፣ የሰሜን ጎንደር ዞን እና የደባርቅ ወረዳ አመራሮች፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ አስተባባሪ ኮሚቴዎች፣ በየደረጃው ያሉ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎች አካላት ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

መረጃዉ የደባርቅ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ነዉ።

የ2018 ዓ.ም የጳጉሜን ቀናት ስያሜ #ጳጉሜን
03/09/2026

የ2018 ዓ.ም የጳጉሜን ቀናት ስያሜ

#ጳጉሜን

በሰሜን ጎንደር ዞን በደባርቅ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች ዛሬም የሰላም አማራጭን እየተቀበሉ ነው።ነሐሴ 28/ 2018 ዓ/ም በየዳ ኮሙኒኬሽን(ድልይብዛ)በሰሜን ጎንደር ዞን በደባ...
03/09/2026

በሰሜን ጎንደር ዞን በደባርቅ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች ዛሬም የሰላም አማራጭን እየተቀበሉ ነው።

ነሐሴ 28/ 2018 ዓ/ም በየዳ ኮሙኒኬሽን(ድልይብዛ)

በሰሜን ጎንደር ዞን በደባርቅ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች ከዚህ በፊት የሰላም አማራጭን መቀበላቸው ይታወሳል።

በወረዳው በምዕራቡ ቀጠና ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች ዛሬም የሰላም አማራጭን ተቀብለው ወደ ህብረተሰቡ ተቀላቅለዋል።

የሰላም አማራጭ የተቀበሉትን ታጣቂዎች የደባርቅ ወረዳ አመራሮች እና አስተባባሪ ኮሚቴዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የሰላም አማራጭን የተቀበሉት ታጣቂዎች ሲጓዙበት የነበረው መንገድ የተሳሳተ መኾኑን መገንዘባቸውን ገልጸዋል።

የነበሩበትን የጥፋት መንገድ በመተው ወደ ኅብረተሰቡ እና ሰላማዊ ሕይወት ለመመለስ መወሰናቸውንም አስታውቀዋል።

የደባርቅ ወረዳ ኮሙኒኬሽን

ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ለአንድ ሀገር እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገለፀ።ነሀሴ 28/2018 ዓ/ም በየዳ ኮሚዩኒኬሽን (ድልይብዛ)ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ለአንድ ሀገር እድገት ከፍተኛ አስተ...
03/09/2026

ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ለአንድ ሀገር እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገለፀ።

ነሀሴ 28/2018 ዓ/ም በየዳ ኮሚዩኒኬሽን (ድልይብዛ)

ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ለአንድ ሀገር እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገለፀ።

የበየዳ ወረዳ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አስተዳደር ግቢ ከሚገኙ የህዝብ ግንኙነት (ፎካሎች) ጋር ስለሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ሚና እና ቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ውይይት አካሂዷል።

የበየዳ ወረዳ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ አሰፉ ግዛው እንደገለጹት ኮሙዩኒኬሽን ህዝብንና መንግስትን የሚያገናኝ ድልድይ መሆኑን በመግለጽ በሀገራችን ባለፋት የለውጥ ዓመታት በፖለቲካው፣በኢኮኖሚና በማህበራዊ ዘርፎች የተመዘገቡ ስኬቶች በማስተዋወቅ ህብረተሰቡን ለላቀ ልማት ከማነሳሳት አኳያ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ሚና የላቀ እንደነበረ ገልጸዋል።

እንደ ወ/ሮ አሰፉ ግዛው ገለጻ ኮሙዩኒኬሽን በሁሉም ሴክተር መስሪያ ቤቶች የሚሰሩ ተግባራት የሚሰራ የሁሉም እስትንፋስ ስለሆነ በጋራ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

የሚዲያ ይዘትን በመረዳት ስራቸውን በኮሙዩኒኬሽን በማጀብ የሚያሰሩ ሴክተር መስሪያቤቶች እንዳሉ ገልጸው ከእነዚህ ሊማሩ የሚገባቸው ጽ/ቤቶችም እንዳሉ በመግለጽ ሚዲያ የቅንጅት ስራ የሚጠይቅ መሆኑን አብራርተዋል።

ኮሙዩኒኬሽን የወረዳው የመረጃ ቋት መሆኑን በመረዳት መረጃ ህይወት መሆኑን በመገንዘብ ማንኛውንም መረጃ በሃርድም ሆነ በሶፍት መስጠት መቻል አለባችው ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ለሃገር ገጽታ ግንባታና ለኢኮኖሚ ዕድገት ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን የማይተካ ሚና ያለው በመሆኑ የጋራ መግባባት በመፍጠር በዘርፉ የሚከናወኑ ተግባራትን ውጤታማ ለማድረግ የህዝብ ግንኙነት ከፍተኛ የሆነ ሚና እንዳለው አብራርተዋል።

ባለፉት የለውጥ ዓመታት የመንግስት ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን ለህዝቡ ከማስተዋወቅ አኳያ በርካታ ሥራዎችን መስራት መቻሉን ገልጸው የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች የጠራ ግንዛቤ በመያዝ እውነተኛና ሚዛናዊ መረጃ በወቅቱ ለወረዳው ኮሙዩኒኬሽን የተጠናከረ መረጃ በመስጠት ስራችውን የማስተዋወቅና የመሸጥ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል መቻል አለበት ብለዋል።

ሚዲያ ገዥ ትርክት በማስረጽ የሀገረ መንግስት ግንባታ በማሳለጥ እና የለውጡ ጉዞ በማጽናት ሁለንተናዊ ለውጥን ለማረጋገጥ ጉልህ ሚና እንዳለው በውይይቱ ተገልጿል።

የተሰሩ መልካም ሥራዎችን ለማስቀጠልና የታዩ ደካማ ጎኖችን ለማረም እና በጋራ ለመስራት የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ከወረዳው የመንግስት ሚዲያዎች ጋር በመገናኘት አስፈላጊ የመረጃ ልውውጥ በማድረግ በቅንጅት መስራት መቻል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

በሰሜን ጎንደር ዞን በበየዳ ወረዳ ለቀበሌ ሚሊሻ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ።ነሀሴ 27/2018 ዓ/ም በየዳ ኮሙዩኒኬሽን (ድልይብዛ)በበየዳ ወረዳ ሚሊሻ ጽ/ቤት የሠላም አስከባሪ አመራርና ...
02/09/2026

በሰሜን ጎንደር ዞን በበየዳ ወረዳ ለቀበሌ ሚሊሻ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ።
ነሀሴ 27/2018 ዓ/ም በየዳ ኮሙዩኒኬሽን (ድልይብዛ)

በበየዳ ወረዳ ሚሊሻ ጽ/ቤት የሠላም አስከባሪ አመራርና አባላት ለቀበሌ ሚሊሻ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ።

በጀግንነት መጠበቅ በሰብአዊነት ማገልገል በሚል ርዕሰ ጉዳይ የሠላም አስከባሪ አመራርና አባላት የተለያዩ ስልጠናዎችን ሲሰጥ ቆይቷል።

በዛሬው ዕለት ከስልጠናው ጎን በጎን ጥቅማጥቅማችን መንግስት ሊያስከብርልን ይገባል ሲሉ የተለያዩ ጥያቄዎችን ለሚመለከተው አካላት የጠየቁ ሲሆን ከጥያቄዎቹ መካከል:-ጦሬታችን ይከበር፣በሲቪል ሰርቩስ መታቀፍ አለበት፤በግብርና ምርት ስራ በጉልበት ልንታገዝ ይገባል ፤አልባሳት ጊዜውን ጠብቆ አየተሰጠን አይደለም ፤ሬሽን እያጠረን ነው፤ግዳጅ ስንሄድ የጤና ባለሙያ መመደብ አለበት፤ካፕ ላይ ውሃ ሊገባልን ይገባል፤የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ሊሰጠን ይገባል፤እጀባ ስንሄድ አስፈላጊውን አበል እየተከፈለን አይደለም፤የደሞወዝ ጭማሪ ያስፈልገናል በወቅቱ ሊገባልን ይገባል፤ሎጅስቲክ ኦዲት መሆን አለበት ፤የአባላት ብዛት ሳይሆን ጥራት ላይ መስራት አለበት የሚሉት ሲሆኑ በተጠየቁ ጥያቄዎች ላይ የሚመለከታቸው የጽ/ቤት ኃላፊዎች ተገንተው ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተውበታል።

የውይይት መድረኩን የመሩት የወረዳው ም/አስተዳዳሪና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሴ አለበል የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ምስጋናው ሞላ እንዲሁም አቶ አስፋው ጌጡ የወረዳው ሠላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ በተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተውበታል።

"የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ በክልሉ ሰላምና ልማት እንዲረጋገጥ የድርሻውን እየተወጣ ነው" -አቶ አባይ መንግሥቴ​የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት አጠቃላ...
02/09/2026

"የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ በክልሉ ሰላምና ልማት እንዲረጋገጥ የድርሻውን እየተወጣ ነው" -አቶ አባይ መንግሥቴ

​የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸም፣ የተመዘገቡ ስኬቶችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን የሚገመግም መድረክ እያካሄደ ነው።

​በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግርና የሥራ መመሪያ ያስተላለፉት የቢሮው ሃላፊ አቶ አባይ መንግሥቴ፤ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን መረጃ ለሕዝብ ከማድረስ ባሻገር በክልሉ ሰላም፣ መረጋጋትና ልማት እንዲሰፍን ታሪካዊ ሚና እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል። አክለውም በክልሉ ለተገኘው የሰላም አየርና ለሕዝቡ አብሮነት መጎልበት ዘርፉ ከፍተኛ ድርሻ ማበርከቱን አብራርተዋል።

​በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተግባራት የዘርፉን ኃያልነት በተግባር ያረጋገጡ እንደነበሩ የጠቆሙት ሃላፊው፤ እነዚህ ሥራዎች የሕዝቡን የልማት እንቅስቃሴ የሚያፋጥኑ፣ እውነትን የሚያጎሉና የክልሉን መልካም ገጽታ በመገንባት ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል።

​በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ የተካሄደው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዲሞክራሲያዊ፣ ፍትሐዊና ተዓማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ የተወጣው ሚና በታሪክ የሚዘከር መሆኑን ጠቅሰዋል።

​ዘርፉ የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ የልማት ፍላጎት በማንጸባረቅ ረገድ የተጫወተው ሚና ለልማት ሥራዎች መፋጠን ትልቅ አቅም መሆኑንም አቶ አባይ አብራርተዋል።

​በመድረኩ ያለፉትን ስኬቶችና ያጋጠሙ ማነቆዎችን በመፈተሽ፤ በቀጣይ የበጀት ዓመት የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ ለክልሉ ዘላቂ ሰላም፣ ወንድማማችነትና ሁለንተናዊ እድገት በላቀ ኃላፊነት እንዲሠራ መንገድ የሚጠርግ መሆኑ ተመላክቷል።

#አማራ ኮሙኒኬሽን

"ውጫዊ የወረራ ስጋትና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማትን እናረጋግጣለን"በሚል መሪ ቃል ውይይት ተካሄደ።ነሀሴ 26/2018 ዓ/ም በየዳ ኮሙዩኒኬሽንድልይብዛበሰሜን ...
01/09/2026

"ውጫዊ የወረራ ስጋትና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማትን እናረጋግጣለን"በሚል መሪ ቃል ውይይት ተካሄደ።

ነሀሴ 26/2018 ዓ/ም በየዳ ኮሙዩኒኬሽንድልይብዛ

በሰሜን ጎንደር ዞን በበየዳ ወረዳ "ውጫዊ የወረራ ስጋትና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማትን እናረጋግጣለን" በሚል መሪ ቃል ከወረዳው ሠላም አስከባሪ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ።

የመወያያ ሰነዱን ያቀረቡት የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ምስጋናው ሞላ ሲሆኑ"ውጫዊ የወረራ ስጋትና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማትን እናረጋግጣለን" እንደ ሀገር የተቃጣውን የውጭና የውስጥ አደጋ ለመመከት በቅንጅት መስራት የጠላትን የወረራ ስልት በመቀልበስ ሰላም ወዳዱ የወረዳችን ህዝብ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ከጸጥታ መዋቅሩ ጎን መሠለፍ እንደለበት ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

እንደ አቶ ምስጋናው ሞላ ገለጻ ሠላም ለሁሉም ሁሉም ለሠላም ዘብ በመቆም ውጫዊ የወረራ ስጋትን እና ውስጣዊ የጽንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ አበክረን መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

በተጨማሪም ሰላምና ልማት ተነጣጥለው የሚታዩ ጉዳዮች እንዳልሆኑ በመግለጽ የተረጋጋ ሰላም ለወረዳችን የልማት እንቅስቃሴና ለህዝቡ ብልፅግና ወሳኝ መሆኑን አብራርተዋል።

የወረዳው ሠላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አስፋው ጌጡ እንደገለጹት የሰላም አስከባሪ በጀግንነት መጠበቅ በሰባዊነት ማገልገል የውጭ ወረራን በመመከት የውስጥ ጽፈኝነትን አደጋ በመረዳት የውስጣችን ሰላም በማጽናት ዘላቂ ልማትን ማረጋገጥ በሚሉ ሀሳቦች የፖለቲካ ስልጠና በስነምግባርና አደረጃጀት ዙርያ አቅም ግንባታ ስራ እንዲሁም አዲሱን እና ነባሩንሰላም አስከባሪ ማዋሀድ ወታደራዊ ስልጠናን ያካተተ ስልጠናም እንደሚካሄድ አብራርተዋል።

‎‎መድረኩን የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ምስጋናው ሞላ እና የወረዳው ሠላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አስፋው ጌጡ የመሩት ሲሆን ለተጠየቁ ጥያቄዎችና አስተያየቶች መልስና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ሠላም ለሁሉም ሁሉም ለሠላም!!!

01/09/2026
"ወልቃይት የኢትዮጵያ የብሔራዊ ህልውና እና የስትራቴጂ መተንፈሻ ቁልፍ ነው" ቹቹ አለባቸው (ዶ.ር) "የተከዜ ፖለቲካ"ሲሉ ባሳተሙት መጽሐፋቸው "ወልቃይት የኢትዮጵያ የብሔራዊ ህልውና እና የ...
30/08/2026

"ወልቃይት የኢትዮጵያ የብሔራዊ ህልውና እና የስትራቴጂ መተንፈሻ ቁልፍ ነው"

ቹቹ አለባቸው (ዶ.ር) "የተከዜ ፖለቲካ"ሲሉ ባሳተሙት መጽሐፋቸው "ወልቃይት የኢትዮጵያ የብሔራዊ ህልውና እና የስትራቴጂ መተንፈሻ ቁልፍ ነው" ይሉታል።

የወልቃይት እና አካባቢው ጂኦ ፖለቲካ ከ19ኛው ክፍለ ዘመን የወቅቱ ኀያላን (እንግሊዝ) ጀምሮ እስከ አሁኖቹ ድረስ በቀላል አይመለከቱትም።

አካባቢው የቀጥታ ድንበር ተዋሳኞችን ጨምሮ፣ የቅርብ ጎረቤቶች (መካከለኛው ምሥራቅ) እና የሩቅ የጂኦ ፖለቲካ ፍላጎት አራማጆች ትኩረት የሚብላላበት ነው። አካባቢውንም አልፋሽጋ ብለው ይጠሩታል።

ዓለም አቀፍ የምድረ ገጽ ፖለቲካ (ጂኦ_ፖለቲካ) ጥናት ውስጥ የተወሰኑ መልክዓ ምድራዊ ይዞታዎች ከአካባቢያዊ ስፋታቸው በላይ የዓለምን የምጣኔ ሃብት እና የኀይል ሚዛን የመወሰን ብርቱ መዋቅራዊ አቅም አላቸው፤ ለዚህም ማሳያ የሚኾነው የሆርሙዝ ሰርጥ ነው ይላሉ።

"ሆርሙዝ በተዘጋ ጊዜ ዓለምን እንደሚያናጋ ሁሉ በምሥራቅ አፍሪካ ደግሞ የወልቃይት ጠገዴ -ሑመራ ቀጣና ለኢትዮጵያ ሀገረ መንግሥት ኅልውና "የራሷ የሆርሙዝ ሰርጥ ነው"

በዶክተር ቹቹ አለባቸው የተጻፈው "የተከዜ ፖለቲካ" መጽሐፍ በዋናነት የቀጣናውን የጂኦፖለቲካ፣ የብሔራዊ ደኅንነት፣ የኀይል እና ማንነትን ምሰሶ አድርጎ በታሪክ ሽፋን ተሸሽገው የቆዩ እና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚፈታተኑ የፖለቲካ ሴራዎችን ምሁራዊ በኾኑ መከራከሪያዎች ለመንግሥት እና ለፖሊሲ ቀራጮች ምክንያታዊ ሀሳብ እና ማስረጃ ያቀርባል።

መጽሐፉ የኢትዮጵያ ሰሜናዊ እና ሰሜን ምዕራብ አካባቢ ውሥብሥብ የጂኦ ፖለቲካ ተለዋዋጭነት ከብሔራዊ ደኅንነት ቀለበት አንፃር በተከዜ ወንዝ መነጽር ይመለከታቸዋል። ይህ መጽሐፍ ተከዜን ተራ የውኃማ አካል አድርጎ አይመለከተውም ይልቅ "የሀገሪቱ የደኅንነት አጥር እና የሉዓላዊነት አምድ ነው" ሲል ያስረዳል።

የተከዜ ፖለቲካ መጽሐፍ ወልቃይት እና አካባቢውን ከማንነት መጠያየቂያ ባለፈ የሀገር ስልታዊ ምሽግነት፣ የምጣኔ ሀብታዊ ጋሻነት፣ ሦሥትዮሻዊ የፍላጎት መገናኛነት፣ ስትራቴጂካዊ ጉሮሮነት፣ የውኃ ፖለቲካ ትስስር፣ የሩቅ ኀይላት ፍላጎትን ከታሪክ እና ከወቅቱ ፍላጎት፣ በሀገር ውስጥ መንግሥታዊ ዕይታ ደግሞ ከአክሱም እስከ አሁኑ ድረስ ያለውን የአሥተዳደራዊ ቅርጽ ይዳስሳል።

ይህ የወልቃይት ፖለቲካ የተሰኘ መጽሐፍ በአራት ክፍሎች እና በ20 ምዕራፍ በ223 ገጾች ተሰናድቶ ለአንባቢያን የቀረበ ነው።

"የተከዜ ፖለቲካ መጽሐፍ" የምረቃ ሥነ ሥርዓትም በአዲስ አበባ ሚኒስትሮች፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላት፣ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች፣ ምሁራን እና ሌሎች እንግዶች በተገኙበት እየተመረቀ ነው።

አሚኮ

  🎉🎉ዮናስ ሰውነት በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን በየዳ ወረዳ በድልይብዛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ሲኾን ከ600 ጥያቄ 561 በመመለስ ከፍተኛ ...
29/08/2026

🎉🎉

ዮናስ ሰውነት በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን በየዳ ወረዳ በድልይብዛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ሲኾን ከ600 ጥያቄ 561 በመመለስ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ ችሏል።

✅ የተማሪ ዮናስ ፈተናዎች እና የዓመታት ጥረት

ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ ለዓመታት 1ኛ ደረጃን በመያዝ በስኬት መጓዙን ያነሳል። "የመብራት አገልግሎት ባለመኖሩ ለዓመታት በባትሪ አንብቤ ውጤታማ ሁኛለሁ" ነው ያለው።

በድልይብዛ ከተማ የመብራት አገልግሎት አለመኖሩ በሌሊት ተነስቶ ይበልጥ ለማንበብ ከፍተኛ ችግር ይፈጥርበት እንደነበር ተናግሯል።

💪 የንባብ መንገድህ ምን ይመስል ነበር?

ቀን ከተማሪዎች ጋር በኅብረት በማንበብ፤ ቤተ መጽሐፍትን አዘውትሮ በመጠቀም፤ ሌሊት ላይ የመብራት ችግርን በመቋቋም በእጅ ባትሪ በማንበብ ውጤታማ ኾኛለሁ ነው ያለው።

በተለይም ቀድሞ በመዘጋጀት እና ፈተና በሚደርስበት ወቅት ንባብ አጠናቆ በቂ እረፍት በማድረግ ራሱን ለፈተና እንደሚያዘጋጅም ነው ያስታወሰው።

✅የመምህራን እና የወላጆች ድጋፍ

የታላቅ ወንድሙ እና ቤተሰቦቹ ክትትል እና ድጋፍ እንዳልተለየው ያነሳው ተማሪ ዮናስ 12ኛ ክፍልን ብቻ በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት መማሩም ደግሞ ይበልጥ እንዳገዘው ተናግሯል።

ከታች ክፍል ጀምሮ መምህራን የተለያዩ ጥያቄዎችን በማዘጋጀት፤ የማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠት፤ የሕይወት ተሞክሯቸውን በማካፈል እገዛ ያደርጉላቸው እንደነበርም አስታውሷል።

✅ የተማሪ ዮናስ ራዕይ እና ለተማሪዎች ያስተላለፈው መልዕክት

ውጤታማ በመኾኑ ደስተኛ መኾኑን ያነሳው ተማሪ ዮናስ በቀጣይ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ባለሙያ ለመኾን ጥረት እንደሚያደርግ ተናግሯል። ተማሪዎች ማንኛውም ፈተና ቢያጋጥማቸው ለዓላማቸው በጽናት በመታገል ዓላማን ማስቀደም አለባቸው ነው ያለው።

አሚኮ

Address

Dil Yibza

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Beyeda Communications posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Beyeda Communications:

Shortcuts

Share