28/07/2026
የጊዶሌ ከተማ አስተደደር ትምህርት ጽ/ቤት "ትምህርት ያለ ስስት "በሚል መሪ ቃል የትምህርት ንቅናቄ መድረክ አካሄዴ ፡፡
ሐምሌ 21/2018ዓ/ም (ጊዶሌ ከተማ አስተዳደር መ/ኮ) መድረኩ በጊዶሌ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ ት/ቤቶች ርዕሳኔ መምህራን ፣ሱፔር ቫይዘሮች ፣የት/ቤቶች ወመህ አባላት የ3ቱ ቀበሌ ሊቃነመናብርት ፣ ሥራ አስኪያጆችና ለሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል ፡፡
የጊዶሌ ከተማ አስተዳደር ም/ከኒቲባና የት/ት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ዲማ በመክፈቻ ንግግራቸው ለትምህርት ቤቶች የክረምት ወራት ተግባራት በተሰካ ሁነታ ማከናወን ቀጣዩን የትምህርት ጊዜ ምቹ እንዲሆን ከማስቻል ባለፈ ተማሪዎች የሚገባቸውን ዕውቀት ማግኘት እንዲችሉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው በዚህም በመድረኩ የተሳተፉ አካላት በተግባር ስራው ላይ ግንባር ቀደም ሆነው ለሎችን በማስተባበር በቅንጂት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል ፡፡
የ2018ዓ/ም ክረምት ወራት ተግባር ዕቅድ አፈጻጸም ሰነድ በጊዶሌ ከተማ አስተዳደር ት/ጽ/ቤት ት/ቤት/መሻ/ፕ/ቪዥን ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ በሆኑት በአቶ ተካልኝ መሰለ በዝርዝር ቀርቧል፡፡
የክረምት ተግባራት ማህበረሰቡን በማስተባበርና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ሃብት በማሰባሰብ የትምህርት ተቋማት ዝግጁነት በማረጋገጥ ትምህርት ለትውልድ መርህ እንዲሳካ የትምህርት ግብአቶችን በሟሟላት ከዚህ ቀደም ያልተሳኩ የትምህርት ግቦች በላቀ ደረጃ ለመፈፀም በ2019 ውጤታማ የመማር ማስተማር ተግባራትን ለማከናወን የክረምት ተግባራት በትኩረት ማከናወን ውጤታማ ለመሆን እንደሚረዳ ተገልጿል ፡፡
በንቅናቄ መድረኩ በቀረበው ዕቅድ አተገባበር በቀጣይ ሊያጋጥሙ በሚችሉ ጉዳዮች ከተሳታፊዎች ሃሳብ አስተያየት ተሰጥቶባቸዋል ፡፡
የጊዶሌ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ መኩርያ ሞላ ትምህርት ቤቶቻችን ካለባቸው በርካታ ጉድለቶች አሁን ላይ ላለው የትምህርት ስርዓት ጋር አብሮ ለመሄድ ፈታኝ የሆኑ ጉዳዮች እንዳሉ በመግለፅ ይህን ሁነታ ለመቀየር ሁሉም በየዘርፉ በባለቤትነት ሊረባረብ እንደሚገባ ገልፀዋል ፡፡
በመጨረሻም በተነሱ ሃሳብ አስተያየቶች ላይ ምላሽና ማብራርያ በመስጠት የትምህርት ስርዓቱ ውጤታማ ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ የትኩረት አቅጣጫ በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል ፡፡
#የጊዶሌ ከተማ አስተዳደር መ/ኮ